Remember What God Has Overcome!
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 81-82 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 81-82 በጣም የተለያዩ ናቸው ፡፡ እርስ በእርሳቸዉ የተለያዩ ናቸዉ ነገር ግን ሁለቱም መዝሙሮች ከአሳፍ ናቸው ፡፡ እነዚህ መዝሙሮች ለመነሳት የተጮኹ እንደሆኑ አምናለሁ ፡፡ ሁላችንም ለመነቃቃት እየጮህን እንደ ሆነ አስባለሁ ፤ ወደ እግዚአብሄር ሰዎች፣ ሕዝቦች ማየት እወዳለሁ ! ማሰብ ያልቻልናቸዉን ነገሮች እግዚአብሄር መጫወት/ማመቻቸት ቢችልም ኃይለኛ ጠብ እየሆነ ያለበትን ጊዜ እየለመድነዉ/እየደረስንበት ነው ፡፡ 1ዜና (16፡ 1-5) ስለ አሳፍ እንደ ማጣሪያ እና እንደ መነሻ አንብቡት ፡፡
በመፅሀፍ ላይ ተጠቅሶ የምናየዉ አንድ ነገር በሆነ ነገር ስጦታ የተሰጣቸዉ የተወሰኑ ሰዎች መኖራቸዉን ነው ፡፡ የአምልኮ መሪዉን አሳፍን እጠራለሁ - ስጦታ እንዳለዉ ይታወቅ የነበረዉ አስደናቂዉ የአምልኮ መሪ ፣ በአሁኑ ጊዜም ተመሳሳይ የአምልኮ መሪነት ስጦታ የተሰጣቸዉ ሰዎች አሉ ፡፡ አምልኮን በነፍስ እርካታነት እመለከተዋለሁ ፤ በአምልኮ ስጦታ የተሰጣቸዉ ሰዎች የነፍስን ችግር ለመረዳት ያዘነበሉ የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ ፡፡ አሳፍ ችግር እንደ ነበር አስተዋለ ለመነሳትም/እንደ ገና ለመታደስም በለቅስ አዘነ ፡፡ በምዕራፍ 81 ከሀዘን እግዚአብሄር ታላቅ ነገር እንደሚያደርግ ተስፈኛ ወደ መሆን ወደ ምዕራፍ 82 ሄደ ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ከእግዚአብሄር መለየታችን አይኖቻችንን በሌሎች ነገሮች ላይ አድርገኝ በምናገኘዉ ጊዜ በጠላት የነፍስ መጎበጥ ነው ፡፡ በተስፋ ወደ እግዚአብሄር ነገሮች ስንመለከት ነፍሳችንን እንዴት ወደ ስፍራዋ እንደሚመልሳት እግዚአብሄር መልሶ መስራቱን ያውቃል ፡፡ አምልኮ ለተስፋ መቁረጥና ለኃዘን መልሶ መሰራት ሊሆን ይችላል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (80፡ 1-7)፡ በዚህ መዝሙር ዉስጥ አሳፍ እግዚአብሄር ጥንካሬአቸው፣ ተቤዢአቸዉ እና አንሺአቸዉ እንደ ነበር አስታውሳለሁ አዉቃለሁም ይላል ፡፡ ቁጥር 6 “ ጫንቃዉን ከሸክም አስወገድሁ “ ከባርነት የእስራኤልን ነፃ መዉጣት ያመለክታል ፡፡ ብዙዎች ነፃ ወጥተዉበት የነበረው በግብፅ አስቀምጠዉት ከነበረዉ ማሰሮዉች እንደሆነ ያምናሉ ፤ ከዚያም አሳፍ “ የመከራን/ማዕበል ስፍራ ድብቅ ሚስጥር “ አመለከተ/ጠቀሰ ፡፡ ብዙ ጊዜ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ስለ ማዕበልና ስለ መብረቅ በምታነቡ ጊዜ በእግዚአብሄር ድምፅ የተከተለ ነው ፡፡
የመሪባ ዉሃ ሙሴ አለቱን ሲመታው ከአለቱ ዉስጥ የፈሰሰዉ ነበር ፡፡ ከባርነታችን ነፃ አዉጥቶን ስለ ሁኔታዉ ቅሬታ በምናቀርብ ጊዜ እግዚአብሄር ቅር ይሰኛል ፡፡ አሳፍ እስራኤላዊያንንእግዚአብሄር በምን ከምን አድኗቸዉ እንደ ነበርና እግዚአብሄር እንዴት መግቧቸዉ እንደ ነበር አስታወሳቸው ፡፡ አሳፍ “ አስታዉሱ ! “ እያለ ነው ፡፡
እግዚአብሄርን ስናስታዉስ እንባችን ይደርቃል ምክንያቱም ፀሎታችንን በመመለስ ህይወትን እንደሚያመጣልን ስለ ምናውቅ ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች መጨረሻ ላይ “ ፈተንሁህ “ የሚል ቃል እናያለን ፤ ይህን ቃል በማይ ጊዜ ሁልጊዜ በመቆም ምን እንዳነበብሁ አስባለሁ ፡፡ ይህ የማንፀባረቂያ/ምላሽ የሚሰጥበት ጊዜ ፈዉስ የሚጀምርበትና እግዚአብሄር መልሶ ለአምልኮ የሚጠራብን ስፍራ ነው ፡፡
መዝሙር (81፡ 8-16)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ኃዘንን መስማት ትችላላች ፤ ቁልፉ ጥቅስ ቁጥር 13 እንደ ሆነ አምናለሁ፣ አሳፍ “ ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን እስራኤልም በመንገዴ ሄደዉ ቢሆን ! “ ብሎ ሲፅፍ እስራኤላዊያን እንደ ሰጪአቸዉና እንደ ጥንካሬአቸዉ በእግዚአብሄር ላይ ከመደገፍ ይልቅ በህይወታቸዉ ደስታ እየመጣ እንደ ነበር ምቾትን አሰቡ ፡፡
አብዛኛዉን ጊዜ የመዝሙር መፅሀፍ ባነበብነዉ ንግግሮች የተለመዱ የምቾት ፅሁፎች ይሆናሉ፣ ነገር ግን በማቆም እግዚአብሄር እንዴት አሸንፎት እንደ ነበር ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፤ ይህ ተስፋ በሚያስቆርጥ ተስፋ ቢሶች በሆንን ጊዜ እንዴት እግዚአብሄር እንደታደገን እንድናስታዉስ ያበረታናል ፡፡ በመቆም በሕይወቴ እግዚአብሄር ያሸነፈልኝን በማስብ ጊዜ ሁኔታዬን ላይቀይረዉ ይችላል ነገር ግን እንባዬን በማድረቅ ተስፋን ይሰጠኛል ፡፡ በህይወቴ እግዚአብሄር ያደረገልኝን ማስታወስ ስጀምር ነፍሴ በመፅናናት መነሳሳትን ይጀምራልም ስለ ወደፊቱም እደሰታለሁ ፤ ከህመም በኋላ እንደ ተመለሰ ጥንካሬ እንዲሰማ ያደርጋል ፡፡
በቁጥር 14 ሕዝቡ ከእግዚአብሄር ተመልሰዉ ስለ ነበር እግዚአብሄር ራሱን የገለፀ ባለመሆኑ በእዉነት ኃዘኑን ማየት ትችላላችሁ ፡፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን ንቀዉታል ብዬ አላስብም ፤ አድርጎላቸዉ የነበረዉን እንደረሱት አስባለሁ ፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን ታላቅ እቅድ ስለ ነበረዉ ቁጥር 16 እወደዋለሁ ፡፡ ዛሬ አለታችን ማነው ? አለታችን ክርስቶስ ነው ፡፡ አሳፍ ያረካቸዉ አለቱ እንዳልሆነ ነገር ግን ከአለቱ የሆነዉ እንደ ሆነ አመለከተ ! እዚህ ጋር ላለዉ እንቅስቃሴ ትኩረት እንድንሰጥ እፈልጋለሁ ፤ የአምልኮ መሪዉን “ የት እንዳለን አዉቃለሁ ግን በመከት እግዚአብሄርን ለማምለክ አዲስ መዝሙር ማበጀት ፤ ከየት እንደ መጣን እናስታውስ “ እንዲል ወሰደው ፡፡ የአምልኮ መሪዎች ማድረግ የሚችሉትን እወደዋለሁ ፡፡ ወደ ነበርንበት ስፍራ መዉሰድ በመቻል እግዚአብሄር ምን አድርጎልን እንደ ነበር በማስታወስ ወደ ምስጋና ይመራናል ፡፡
መዝሙር (82፡ 1-2)፡ ይህ መዝሙር ከቀደመዉ ጋር የተገናኜ አይደለም ፡፡ ከሌላ ሁኔታ የመጣ ነው - ከተለዬ ሁኔታ የመጣ የአሳፍ አንዲ መዝሙር ነው ፡፡ እግዚአብሄር በሁሉም ነገሮች ላይ የሚያስተዳድሩትን ኃያላን ሰዎችን ይፈርድባቸዋል (ኢዮ 12፡ 16-23) ፡፡
እግዚአብሄር በእዉነት አለም ላይ ይሰራል ፡፡ እግዚአብሄር በኑሮአችን ላይ ጣልቃ አይገባም ፤ አለመታዘዛችን አንዱ እግዚአብሄር ካዘጋጀው በላይ በተለያዩ መንገዶች ላይ ያስቀምጠናል ፡፡ በምቾታችን በምንጓዝ ጊዜ ከፅድቅ መንገድ ያወጣናል ፡፡ እዉነትን የሚበልጥ የሚያደርገዉ ተፈጥሮ ለእግዚአብሄር አለ ፤ ተፈላጊነትን አይጫወትም፣ እዉነቱን የሚወዱትን ይጠብቃቸዋል የማይወዱትን ደግሞ ይቀጣቸዋል ፡፡
መዝሙር (82፡ 3-8)፡ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ በመነሳት በአለም ላይ የሚሆነዉን እንደሚጠብቅ አላምንም ፤ እግዚአብሄር አለምን በመቀጠል አዲስ ነገር እስክታገኝ ድርስ ትዕዛዙን እንድትከተል አዝዟታል ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ታዘን ነበር ነገር ግን እግዚአብሄር እንድናደርገዉ የሚፈልገዉን ወደ ምናይበት ስፍራ የሚወስደን የሚለይ አይምሮ አለን ፡፡ እግዚአብሄር ትልቅ መልክ አላማና ማስተዋል አለው ፤ እግዚአብሄር ችግሩ ነገሮች ከትዕዛዝ ዉጪ መሆናቸዉ ነዉ እያለ ነበር - ድሀ፣ ችግረኛ፣ የተጨነቀ እና ምስኪን ሰዎች እንዲኖሩ የእግዚአብሄር እቅድ አልነበረም፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታዮች እኛ መጀመሪያዉኑ ነገሮችን እግዚአብሄር አቅዷቸዉ ወደ ነበረዉ ሀሳብ መልሰን ወደ ብርሃን እንድናመጣቸዉ ደግሞን ለመታዘዝ ተሰይመናል ፡፡ አሳፍ እግዚአብሄር እንዳለዉ የአምልኮን ሂደት ጀመረው፡፡
መደምደሚያ
በመጨረሻዉ ቁጥር አሳፍ “ እግዚአብሄር ዉድቀታችሁን በመለየት የራሳችሁ ዉድቀት እንዲሆን አይፈቅድም ፤ ታላቅ ነገሮችን እንደምታደርጉ አዉቃለሁ ፤ እግዚአብሄር ስራችሁን ይሰራል ፤ የምንደናቀፍ እንድንሆን አይፈቅድም “ አለ ፡፡ ስናመልክ እግዚአብሄር ኃዘናችንን ወደ ዝላይ/ወደ ደስታ መቀየር ይችላል ፤ ለቅሷችን እንደ ቁጥር 8 ተመሳሳይ እንደሆነ አምናለሁ ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ሲመጣ ማየት እንፈልጋለን ነገር ግን በሕይወቴ ይጀምር ፡፡
ጥያቄዎች
-
መዝ (81፡ 7) “ በመከራም/በመሪባ ዉሃ ፈተነሁህ “ ይላል ፤ በእግዚአብሄር የተፈተኑ ሆኑ ማለት ምን ማለት ነው ? በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ የተጠቀሰ ነው በምንስ አገላለፅ ? (ዘጸ 17፡ 7)
-
መዝ (81፡ 11-12) የዘመናዊ/የወቅቴ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሁኔታ መልክ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
-
በራሳችሁ ቃል በመዝ (82፡ 5) “ የምድር መሰረቶች ሁሉ ተናወጡ “ ማለት ምን ማለት ነው ? ለዛሬስ ይህ እዉነት ነው ?
-
በመዝሙር (81-82) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 81:10
“I am Yahweh your God, who brought you up from the land of Egypt. Open your mouth wide, and I will fill it.”
እግዚአብሔር ለህዝቡ እንደሚያግዛቸው ተናግሯል ፡፡ “ እኔ ያህዌ ነኝ “ ብሏል ፡፡ እርሱ እግዚአብሔር አምላክ ነው ፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ኢየሱስን ከመቀበልህ በፊት ከነበርክበት ከየትኛውም ቦታ አስመልጦሃል ፡፡ እስራኤላውያን በግብጽ በባርነት ውስጥ ነበሩ እግዚአብሔርም ወደ አስራኤል መልሶ አመጣቸው ፡፡ “ እኔ አምላክህ ነኝ አድኜሃላሁም ደግሞም እግዝሃለሁ ፡፡ አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም ። “ እግዚአብሔር የዚህን አይነት ድነትን እና እገዛን ለአንተም እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል ፡፡
አይኖችህን በኢየሱስ ላይ ለማድረግ ፣ እርሱን ማግኘት አለብህ ፡፡ ይህን ስታደርግ አፍህ ዝም ብሎ እርሱን ይጠራል ፡፡ አፍህን ክፈት ፡፡ ራስህን አሳልፈህ ስጥ ፡፡ ዳካማነትህን እመንና ያበረታህ ዘንድ እርሱን ጠብቀው ፡፡ እንደሚሞላህ ተናግሯል ፡፡ ለአንተ እንደሚሰጥ እንደሚረዳ ተናግሯል ፡፡ የሚረዳህ እርሱ ግድ ስለሚለው ፣ ስለሚያውቅና ያንን የማድረግ ኃይል ስላለው ነው ፡፡ ዛሬ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ ፣ መጀመሪያ እርሱን እሻው ፡፡ በትህትና አፍህን ክፈት ፡፡ እናም ይህን ስታደርግ ከምታስበው ከየትኛውም ነገር በላይ ፣ ለህይወትህ እርሱ በሰጠው ተስፋ ውስጥ ትመላለሳለህ ፡፡
“ ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም ። “
- መዝሙር 81፡10
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 81:11–13 — “ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም ። እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥ በልባቸውም አሳብ ሄዱ ። ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን “
ማቴዎስ 6:31–33 — “ እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና ። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ። “
2ኛ የጴጥሮስ 1:3 — “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።