Wisdom Books Psalms

Revival With the God of Israel

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 79-80 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 428 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 30 ሌላ የኃዘን መዝሙር ነው ፡፡ ኃይማኖታቸዉን በመተዋቸዉ ምክንያት ሕዝቡ ተወግደዉ ነበር - ከእግዚአብሄር ፊታቸዉን አዞረዉ የኃሰት ጣዖቶችን ተመለከቱ ፤ ስለዚህም ይህ መዝሙር እንዲያድሳቸዉ ወደ እግዚአብሄር የተደረገ ፀሎት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ መዝሙር በ722 ከክርስቶስ ልደት በፊት በአስር የሰሜን ነገዶች ምርኮኝነት ላይ ከኢየሩሳሌም በአድናቆት የተፃፈ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ይህ በአሳፍ የተፃፈዉ ሌለኛዉ መዝሙርና የተዘመረዉ ነበር ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (80፡ 1-3)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ መንጋህን አድን “ በማለት ያስቀምጣቸዋል ፡፡ አሳፍ የእስራኤል እረኛ መንጋዉን ለማዳን እንዲነሳ እግዚአብሄርን ተጣራ (ቁጥር 1) ፤ አሳፍ እግዚአብሄርን በቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ በኪሩቤል ላይ እንደ ተቀመጠ ገለፀው ፤ ይህ የመነቃቃት መዝሙር ነው ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት በዚያ ስለ ነበር አሳፍ መገኘቱ በኤፍሬም፣ በቢኒያም እና በምናሴ ነገዶች ፊት የታወቀ እንዲሆን ፈለገው (ቁጥር 2) ፤ አሳፍ እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ በሞገስ በመመልከት እንዲያድናቸውጥያቄዉን ደገመው (ቁጥር 3) ፡፡ “ በሞገስ ተመልከታቸው “ የሚለዉ “ ፊትን አብራ “ በማለት ሊተረጎም የሚችል ሲሆን ጥያቄዉ በሚገባ ተቀባይ እንደሚሆንለት ልመናን የሚያስይ በእርሱ ፊት በጥያቄ ለመጣዉ የንጉሱን ፈገግታም ያመለክታል ፡፡ እግዚአብሄር እረኛ ነው፣ ይጠብቀናል ምንም ነገርም አያሳጣንም (መዝሙር 23)፣ እግዚአብሄር በጎቹን ሲሰበስብ ይጠራቸዋል ይመልሱለታልም (ዮሐንስ 10) ፡፡

መዝሙር (80፡ 4-7)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮችን “ ሕዝብህን እዘንለት “ በማለት ያስቀምጣቸዋል ፡፡ በቁጥር 4 አሳፍ ፀሎታቸዉ እንዳልተመለሰ ስለተሰማቸዉ እግዚአብሄር እስከመቼ እንደተቆጣ እንደሚቆይ ጠየቀ ፤ ይልቁንም ለመብላት የእምባ መናን እና ለመጠጣት የእምባ ዉሃን ብቻ ተቀብለዉ ነበር (ቁጥር 5) ፡፡ በጎረቤቶቻቸዉ ክርክሮችና በጠላቶቻቸው መሳለቂያዎች ነበሩ (ቁጥር 6) ፤ እንደ ገና አሳፍም እግዚአብሄርን እንዲታደጋቸዉ ጠየቀው (ቁጥር 7) ፡፡ እንዲያድን እግዚአብሄርን በተደጋጋሚ መጠየቅ ለማስታወስ አስፈላጊ ነው (ዘኁ 6፡ 24) ፡፡

መዝሙር (80፡ 8-19)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ ወይንህን አድስ/እንደ ገና አስነሳ “ በማለት ያስቀምጣቸዋል ፡፡ አሳፍ ከእረኛ መልክ ወደ ወይን እረዳት ተጓዘ ፤ ማክአርቱር “ ወይን እግዚአብሄር ከግብፅ በማዉጣት ኃያል ሕዝብ ላደረጋት ለእስራኤል ዘይቤአዊ አነጋገር እንደ ሆነ “ ይገልፃል (ኢሳ 5፡ 1-7) ፡፡ የእስራኤል ድንበሮች “ ከደቡብ ተራራማዉ አገር እስከ በሰሜን ታላላቅ የሊባኖስ ዝግባዎች ድረስ፣ ከሜዴትራሊያ ባህር ከምዕራብ እስከ በምስራቅ እስከ ኤፍራጠስ - ከዚያም የሚያልፍ ነበር “ ፤ እነዚህ ድንበሮች በቁጥር (10-11) ተዘርዝረዋል ፤ ይሁን እንጂ የእስራኤል ግንቦች ተሰባብረዉ ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ በአዉሬዎችና በጠላቶቻቸዉ የተወሰዱ ሆነዉ ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ አሳፍ እንደ ገና እግዚአብሄርን እግዚአብሄር ተክሏት ስለ ነበረዉ ወይን እንዲጠነቀቅ ጠየቀው (ቁጥር 14-15) ፡፡ ሆኖ በነበረዉ ጥፋት ምክንያት አሳፍ ተስፋ በመቁረጥ ጮኸ (ቁጥር 16) ፡፡ መዝሙር 80 የእግዚአብሄርን እርዳታ የመፈለግ የመጨረሻ የጠለቅ ጥረት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ በቀኝህ ሰዉ ላይ እጅህ ትሁን “ የሚለዉን ሀረግ “ እንደ እስራኤል ማሳያነት ይገልጧል ፤ በሁለተኛነት ትርጓሜዉ የሰዉ ልጅን ለዳዊት ስሮዉ መንግስት በመጥቀስ በአዲስ ኪዳን በዚያ ርዕስ በተደጋጋሚ በመጠራቱ እስከ መሲሁ ድር የተዘረጋ እንደሆነ “ ይገልፃል (ማቴ 2፡ 15) ፡፡ አሳፍ እንደ ገና ከእግዚአብሄር ዞር እንደማይሉ በመናገር እግዚአብሄርን እንደ ገና እንዲያስነሳቸዉ ጠየቀው (ቁጥር 18) ፤ ለሰዎስተኛ ጊዜ አሳፍ እግዚአብሄር እንዲያድናቸዉ ጠየቀው (ቁጥር 19) ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ “ ለእግዚአብሄር የነፃ ማዉጣት ስራ በምላሽ ገጣሚዉ በእግዚአብሄር ስም ላይ ያተኮረ ምስጋናን ለማደስ ተስፋ እንደ ገባ “ ይገልፃል ፡፡ ቁጥር 18 በቁጥር 17 ላይ የተመሰረተ ነው ፤ ያ ሲሆን መነሳት ይሆናል ፡፡

መደምደሚያ

የመጀመሪያን መነቃቃት እንዳመጣ እንደ እስራኤል አምላክ ስንመለከተው መነቃቃት/መነሳት ሊከሰት ይችላል ፡፡ እግዚአብሄርን እንደ እስራኤል አምላክ የማናየዉ ከሆነ እዉነተኛ መነሳት ሊሆን እንደሚችል ጥያቄ አለኝ ምክንያቱም እግዚአብሄር ማን እንደሆነ ሙሉ የሆነ ስዕል እጥረት ስለሚኖር ፡፡

9Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 702.

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 649.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 236.

  3. MacArthur, p. 642.

  4. Wiersbe, p. 236.

  5. Wiersbe, p. 237.

  6. MacArthur, p. 650.

  7. Wiersbe, p. 237.

  8. MacArthur, p. 650.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (79፡ 5-6) ስታነቡ ዛሬም ለእስራኤል የወቅቱ ጩኸት ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ?
  2. በመዝሙር 80 “ አቤቱ መልሰን ፊትህንም አብራ እኛም እንድናለን “ የሚለዉ ሀረግ ሰዎስት ጊዜ የተደጋገመ ነው ፤ መዝሙረኛዉ ይህ ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ? ለአሁኑ ጊዜስ ይህ ጮኸት ይሆናል ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም ?
  3. በመዝ (80፡ 17) ላይ አሰላስሉ ፤ ይህ ስለ መሲሁ ኢየሱስ እየተናገረ ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልነበረም ?
  4. በመዝሙር (79-80) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 80:2b–3

“Rally your power and come to save us. Restore us, God; look on us with favor, and we will be saved.”

ከእግዚአብሔር ፊትህን ዞር ለማድረግ መርጠሃልን ? በፈተና ውስጥ ወድቀሃልን ? በስጋህ በራስህ ጥንካሬ ህይወትን ለመኖር ትምክራለህን ? በእግዚአብሔር ታምናለህ ነገር ግን እርሱን በእለት ተእለት ህይወትህ ውስጥ አታስገባውም ? ከእግዚአብሔር በጣም እርቀህ ተንሸራተህ ታውቃለህ ? በሚያሳዝን ሁኔታ ያድንህና ይመልስህ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልግህ ተረዳህን ?

ፈጽሞ በጣም ርቀህ አልሄድክም ፡፡ እግዚአብሔር ሊመልስህ ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር ባለ ባዙ ኃይል ነው ፣ እርሱ ያለ ምንም ምክንያት ይወድሃል ፡፡ ሆኖም ግን ንስሃ ለመግባትና ወደ እርሱ ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን አለብህ ፡፡ አንተ ብቻ ነህ ይህን ውሳኔ ለመወሰን የምትችለው ፡፡ ዝግጁ ከሆንክ “ አዎ ጌታ ሆይ ፣ ወደ አንተ ለመመለስ ፈቃደኛ ነኝ “ በል ፡፡ ከዚያም በእምነት ከኃጢአትህ ፊትህን መልስና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ ፡፡ የእርሱን ጸጋና ምህረት ተቀበል ፡፡ በመገኘቱም አምሮዊ መታደስንና ለነፍስህ ደግሞ መነቃቃትን ፈልግ ፡፡ በእምነት እርምጃ ውሰድ ደግሞም ምርኮን እንደሚመልስልህና ጉልበትን እንደሚሰጥህ እመን ፡፡ የእግዚአብሔርን ታላቅ ፍቅር ካመንክ ዛሬ ያን ውሳኔ ወስን ፡፡

“ ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና ። አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን ። “

  • መዝሙር 80፡2-3

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘኍልቍ 6:24–26 — “እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም ፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም ፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ ። “

አሞጽ 9:14 — “የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ አታክልትንም ያባጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ ። “

ሐዋርያት 3:19 — “እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ ፤ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም ፡፡ ”