Wisdom Books Psalms

Remembering The Past, Present, And Future

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 77-78 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 427 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 78 ረጅም ነው - 72 ቁጥር ይረዝማል ፡፡ በ30 ደቂቃ ያን ያክል ክፍል ለመሸፈን በጣም ይፈትናል ነገር ግን ይህ እንዳስተምር እግዚአብሄር የነገረኝ ነው ፤ ዛሬም የዚህን መዝሙር መጨረሻ እናገኘዋለን ! ፅሁፉ በእስራኤል ታሪክ ላይ ይጓዛል - አንድ ታሪካዊ መዝሙር “ እግዚአብሄር ምንም እንኳን ቀድሞ የአባቶቻቸዉ አመፅና አለማመስገን ቢኖርም እንዴት እግዚአብሄር ሩህሩህ እንደ ነበር ልጆቹን ለማስተማር ተፃፈ “ ፤ ሀሳቡ ልጆቹን የኋላ ታሪካቸዉን ማስተማር ነበር ይህ ከሆነ ተመሳሳይ ስህተት አይደግሙም (ቁጥር 8) ፡፡ ይሁን እንጂ የጀርመን ፈላስፋ ጆርጅ ሄጌል እንደፃፈው ከታሪክ የተማርነዉ አንድ ነገር ከታሪክ የማንማረዉ ነዉ ፡፡ ዋይርስቤ ፀሀፊዉ አሳፍ የእስራኤልን ታሪክ በዳሰሰ ጊዜ “ የሚያበሳጭ የመርሳትነት፣ የአለመታመንነት፣ የደካማነትና የዉድቀት መዝገብን በማየት እነዚህ ሁሉ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት መመልከቱን “ ያጋራል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (78፡ 1-8)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ የወደፊቱን መጠበቅ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ አሳፍ አንባቢዎቹን ወደ እነዚህ ክፍሎች እንዲያደምጡ ነገራቸው (ቁጥር 1-8) ፤ ቀድሞ ምን ተፈጥሮ እንደ ነበር ልጆቹ ማስተዋላቸዉን እርግጠኛ መሆን አስፈላጊ ነበር ስለዚህም የሕዝቦቻቸዉም ታሪክ በትዉልድ መካከል ሊያልፍ ይችላል ፡፡ ያለፈዉን በመረዳትና በማወቅ ወደ ፊታችንን እንጠብቃለን ፡፡

መዝሙር (78፡ 9-64)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ ያለፈዉን መረዳት “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ቁጥር 9-11 ከዉጊያ በመመለስ የእግዚአብሄርን ኪዳን ባልጠበቁ ጊዜ የኤፍሬምን የኃይማኖት መተዉ ይሸፍናሉ ፡፡ ቁጥር 12-39 በምድረበዳ እንደ ነበሩ የእስራኤልን ኃጢዓት እንደ ገና ይናገራሉ ፤ ለምሳሌ ህዝቡ በምድረበዳ እግዚአብሄር ስለ ሰጣቸዉ መና አመስጋኞች አልነበሩም - ከመናም ዉጪ ከእግዚአብሄር ብዙ ነገርን ፈለጉ ፡፡ ይህ ንድፍ በመላዉ መዝሙር ዉስጥ የተንፀባረቁ ነበሩ ፤ እግዚአብሄር ሕዝቡን የሚያስፈልጋቸዉንና የሚገባቸዉን ሰጥቷቸዋል ነገር ግን በስጦታዉ አልረኩም ነበር ፡፡

ቁጥር 40-53 ዕብራዊያን በግብፅ በነበሩ ጊዜ የተፈጠረዉንና በዚያ ተምረዉት የነበረዉን ደግመው ይናገራሉ ፤ አሳፍ እግዚአብሄር በግብፅ ላይ አዉርዶት የነበረዉን መቅሰፍት በመጥቀስ ህዝቡን ነፃ ማዉጣት እንደቻለ አዉርቷል፡፡ ቁጥር 54-64 በተስፋይቱ ምድር እያሉ የሕዝቡን የቅርብ ጊዜ ኃጢዓቶች ደግሞ ይናገራል ፤ በመዝሙር ዉስጥ ባለመታዘዝ ከእግዚአብሄር ዞር ብለዉ በነበሩት ላይ የእግዚአብሄርን ቁጣ ተመዝግቧል ፡፡ ዋይርስቤ “ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሄር ታላቅ ፍርድ የምንፈልገዉን እንደሚሰጠን (ቁጥር 21, 31, 49-50, 58-59, 62) “ አመልክቷል ፡፡

መዝሙር (78፡ 65-72)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ የአሁኑን እንደ ማድነቅ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ አሳፍ እግዚአብሄር እንዴት ለእስራኤል ተገልጦ እንደ ነበር - ጠላቶቻቸዉን በእፍረት ወደ ኃላ መቷቸዉ እንደ ነበር፣ ለመሲሁ የዘር መስመር እንዲሆን የይሁዳን ነገድ እንደ መረጠ፣ ዳዊትን እንደ ንጉስ እንደ መረጠው እና ቤተ መቅደሱንለዘላለም በኢየሩሳሌም እንደ መሰረተ እንደ ገና ተናገረ (1ሳሙ 17፡ 34) ፡፡ ንጉስ ዳዊት የእግዚአብሄርን ምርጫ ህዝቦች እስራኤልን በንፁህ ልብ በመጠበቅ በእጁ ጥበብ/ብልኃት መራቸው (ቁጥር 72) ፡፡

መደምደሚያ

በዳዊት ላይ የሚገኙ ሁለት በእዉነት የተለኙ ነገሮች አሉ ፤ እግዚአብሄርን ለማገልገል ታማኝነቱና ንፁህ ልቡ አንዱ ሲሆን በ 1ሳሙ (13፡ 14) ላይ ይገኛል “ ….እግዚአብሄር እንደ ልቡ የሆነ ሰዉ መርጦአልና ፤ እግዚአብሄርም ያዘዘህን አልጠበቅህምና እግዚአብሄር በሕዝቡ ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አዝዞታል አለው “ ፡፡ ሁለተኛዉ ዳዊት ጎልያድን ሊገጥመዉ በሄደ ጊዜ ለመዋጋት በሰዉ ኃሳብ በመዘጋጀት (የሳዖልን ልብስ) ለበሰ ነገር ግን ዳዊት እግዚአብሄር በንፁህ ልብ እንዲያደርግ ሰጥጦት በነበረዉ እንዲያደርግ አስተዋለ፣ ያ ምን ነበር ገምቱ ? ጎልያዶች ይሞታሉ ፡፡ አይኖቻችንን በእርሱ ላይ በማድረግ ወደፊታችንን ለመከላከል ቀድሞ/በፊት እግዚአብሄር ያደረገልንን ስናስታዉስ እግዚአብሄር ብልሀተኛ እጅን ይሰጠናል ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 648.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 231.

  3. Wiersbe, p. 231.

  4. Wiersbe, p. 231.

  5. Wiersbe, p. 231.

  6. Wiersbe, p. 232.

  7. Wiersbe, p. 233.

ጥያቄዎች

  1. በመዝ (77፡ 9) አሳፍ እግዚአብሄር ደገ መሆንን ረስቶ/ትቶ እንደሆን ወይም ደግሞ በብስጭት ርህራሄዉን እንደተዉ ጠየቀ ፤ በባህሪዉ የፀና ይሆናል ? የእግዚአብሄር ድርጊት ወይም ባህሪይ በፍራት ወይም በሌሎች ዉሸት እንደሆነ እንድትጠይቁ ጠላት መቼ ምክንያት ሆናችሁ ?
  2. መዝሙር 77 የእግዚአብሄርን ተግባራት ስለ ማስታወስ ነው ፤ በላፈዉ ታሪካችን ያደረገልንን ማስታወስ ለምን አስፈላጊ ይሆናል ?
  3. የኤፍሬም ልጆች ለእነርሱ ያሳያቸዉን የእግዚአብሄርን ስራዎችና ተዓምራቶች በረሱ ጊዜ ምን ሆነ ? (መዝ 78፡ 9-10)
  4. መዝሙር 78 ብዙ የእግዚአብሄርን ታላቅ እና ድንቅ ስራዎችን ደግሞ ይናገራል ፤ አስፋ ስለ እስራኤላዊያን ምንድን ደግሞ ተናገረ ? በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ በጢሞ (2፡ 13) ያለዉን መርህ የት ላይ ልታዩት ትችላላችሁ? በራሳችሁስ ህይወት እንዴት ነው ? መታመንን በማጣታችሁ አሁንም የእግዚአብሄርን አለመታመንም መቼ አያችሁ ?
  5. በመዝሙር (77-78) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 78:2–4

“I will declare wise sayings; I will speak mysteries from the past—things we have heard and known and that our fathers have passed down to us. We must not hide them from their children, but must tell a future generation the praises of the LORD, His might, and the wonderful works He has performed.”

እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ታሪክ ከአንዱ ትውልድ ወደ ሌላኛው ያስተላልፉ ነበር ፡፡ እነርሱ እንዴት እግዚአብሔር ባህሩን እንደከፈለ ፣ እስራኤላውያንን ቀን በደመና አምድ ሌሊት ደግሞ በብርሃን አምድ እንደመራ ደግሞም እርሱ እንዴት ከአለት ውኃን እንደፈለቀ ይናገሩ ነበር ፡፡ እነዚህ በህይወታቸው መንፈሳዊ ምልክቶች ነበሩ እንድሁም የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያሳያሉ ፡፡ እንድሁም ደግሞ ታማኝ ስላልነበሩበትና እግዚአብሔርን ስለበደሉበት ታሪክ ያካፍሉ ነበር ፡፡ ከዚህም ሁሉም በኋላ እግዚአብሔር ሩህሩህና ይቅር ባይ ነበር እነርሱንም አላጠፋቸውም ፡፡

እያንዳንዱ ትውልድ የወደፊቱን ለመጠበቅ እንድሁም የአሁኑን ለማስቀጠል ያለፈውን ማስታወስና ካለፈው መማር አለበት ፡፡ ልክ እንደ እስራኤላውያን አንተም በህይወትህ መንፈሳዊ ምልክቶች አሻራዎች አሉህ ፡፡ ዛሬ የእግዚአብሔርን ታማኝነት ለመናገር ምን አይነት ታሪክ ነው ለዚህ ትውልድ የምታከፍለው ? ሌላ ቀን አታጥፋ ፤ በህይወትህ ያየኸውን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ዛሬ ምሽት በእራት ገበታ ዙሪያ ለልጆችህ ተናገር ፣ ለልጅ ልጆችህ መልዕክትን ላክ ወይም በሩቅ ላሉ ቤተሰቦችህ ተንቀሳቃሽ ምስልን አጋራ ፡፡ ገና እንደሆነና አስፈላጊ እንዳልሆነ ሊሰማህ ይችል ይሆናል ነገር ግን ጥልቅ በሆኑት ፣ በድካምና ሆድ በባሰህ ጊዜያት እግዚአብሔርን በግልጽና በኃይል አይተሃል ፡፡ እርሱ እንድሰራ ሰለፈለክ ሀፍረት አንዳይሰማህ ፡፡ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው ፤ እርሱ ይረዳል ይታደግማል ፡፡ አንተ እንዳደረከው ሁሉ ቀጣዩም ትውልድ በእነዚህ ተስፋዎች ላይ መቆም ያስፈልገዋል ! ሂድና ታሪክህን አካፍል ስለዚህም ሊረሳ አይችልም !

“አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ፥ ያለውንም ተምሳሊት እናገራለሁ ። የሰማነውንና ያውቅነውን፥ አባቶቻችንም የነገሩንን፥ ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም ። የእግዚአብሔርን ምስጋናና ኃይሉን ያደረገውንም ተኣምራት ተናገሩ ። “

  • መዝሙር 78፡2-4

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘዳግም 6:5–7 — “አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው ። “

መዝሙር 78:6–7 — “ የሚመጣ፥ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ ፤ ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ “

1ኛ ቆሮንቶስ 10:11-12 — “ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ ። ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ። “