Wisdom Books Psalms

It Beings And Ends In Jerusalem

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 75-76 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 426 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የመዝሙር መፅሀፍ በስሜታዊነት ከእግዚአብሄር ጋር ስለ መገናኘትና በመዝሙረኛዉ ህይወት እየሆነ ስለ ነበረዉ ነገር ነበር ፡፡ መዝሙር 76 ምናልባትም “ በ701 ከክርስቶስ ልደት በፊት የሰናክሬም የአሶር ሰራዊት ስለ መጥፋት ማክበርን እንዲሁም ደግሞ ራሱ በተከታይ የሰናክሬም ሞት ላይ ለማክበር “ የተጣመረ ነበር (2ነገ 19፡ 6-7, 36-37)፡፡ እንዲሁም ማክአርቱር መዝሙር 76 “ ሁሉን ቻይ አምላክ ጠላቶቹን በማሸነፍ ወደ ፍርድ በሚያመጣቸዉ ጊዜ “ ወደ መጨረሻዉ ዘመን እንደሚያመለክት ወደ አይምሯችን ያመጣል ፡፡ ዋይርስቤ የመዝሙር 76 ሂደት “ መዝሙሩ ከኢየሩሳሌም በአንድ ቦታ በመጀመር (ቁጥር 1-6) በመላዉ በእስራኤል ምድር ተንቀሳቀሰ (ቁጥር 7-9) እናም አሁን በመላዉ ምድር ላይ ደርሷል (ቁጥር 12) “ በማለት ያጠቃልለዋል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (76፡ 1-3)፡ዋይርስቤ የእነዚህን ቁጥሮች ጭብጥ “ እግዚአብሄር እንድናዉቀዉ ይፈልጋል “ በማለት ይገልፃቸዋል/ያስቀምጣቸዋል ፡፡ ቁጥር 1-2 እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም (በይሁዳ፣ በሳሌም፣ በፂዎን) የታወቀ እንደሆነ ይናገራሉ ፤ በኢየሩሳሌም እግዚአብሄር የጠላቶቹን መሳሪያዎች ጠራረጋቸዉ (ቁጥር 3) ፡፡ ቁጥር 3 በትናትናዉ ትምህርታችን ከመዝሙር 74 የተተወ ከሚለዉ ስሜት የተለዬ ነው ፡፡ በመዝሙር 76 እግዚአብሄር አለ/አብሮ አለ ፡፡

መዝሙር (76፡ 4-6)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ እግዚአብሄር እንድንታመነዉ ይፈልጋል “ በማለት ያስቀምጣቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር እንደ አሸበረቀ የተገለፀ ነዉ ይህ ማለት ብርሀንን በመስጠት ወይም በዕብራዊ መነቃቃት በመሆን “ ከሚታደንባቸዉ ተራሮች “ ወይም ከአጥቂዎች ወደ ታች መጥቷል ማለት ነው (ቁጥር 4) ፡፡ ጠላት ሙሉ በሙሉ ተሸንፏል በእግዚአብሄርም ላይ እጁን ማንሳት አይችልም (ቁጥር 5-6) ፡፡

መዝሙር (76፡ 7-9)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ እግዚአብሄር እንድንፈራዉ ይፈልጋል “ በማለት ያስቀምጣቸዋል ፡፡ መዝሙረኛው በእግዚአብሄር ድል አድራጊነት ኃይል ላይ በማንፀባረቅ “ የተፈራህ ነህ ፤ በተቆጣህ ጊዜ በፊትህ ማን ሊቆም ይችላል ? “ በማለት ፅፏል ፤ ይህ የመዝሙር 76 (ቁጥር 7, 8, 11, 12) ፍሬ ነገር ነው ፡፡ ዋይርስቤ ቁጥር 8-9 “ ከሰማይ ከዙፋኑ ላይ እግዚአብሄር ፍርዱና መከራዉ እንዳለቀ እንደተናገረ ፤ ይግባኝ/ልመና ሊኖር እንደማይችል ምክንያቱም የእግዚአብሄር ፍርድ በጣም ከፍ ያለ እንደ ሆነና ፍርዱም የሚናገሩት የሌላቸዉን ተከሳሾች እንደሚተዋቸው “ ነዉ የሚያወሩት በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ከኢየሩሳሌምና ከእስራኤል የእግዚአብሄር ኃይል በመላዉ ምድር ላይ የተፈራ ነው ፡፡

መዝሙር (76፡ 10-12)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ እግዚአብሄር እንድንታዘዘዉ/እንድናከብረዉ ይፈልጋል “ በማለት ያስቀምጣቸዋል ፡፡ ሁሉም ነገር እግዚአብሄርን ያመሰግናል “ የሰዉ ራስ እንኳን ሳይቀር “ (ቁጥር 10) ፤ ስለዚህም የእግዚአብሄር ሰዎች በእርሱ ፊት ስለታቸዉን በመጠበቅ ለእርሱ ስጦታቸዉንም ያመጣሉ (ቁጥር 11) ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት አለቆች እና ምድራዊ ነገስታቶችም ትሁታን ነበሩ (ቁጥር 12) ፡፡

መደምደሚያ

በመዝሙር 76 ጠላት ተሸንፏል እግዚአብሄርም ሁሉንም ስራ ሰርቷል ፡፡ የመዝሙር 76 ሂደት መላዉን አለም ለመሸፈን በሐዋ (1፡ 8) እና ማቴ (28፡ 18-20) ላይ የታዬ ነው ፤ በመዝሙሩ ላይ እግዚአብሄር በተለያዩ መንገዶች ይናገራል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግልፅ በሆነ ነገር ይናገራል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ግልፅ ባልሆነ መንገድ ይናገራል ፡፡

ሐዋ (1፡ 8)፡ “ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማሪያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ “ ፡፡

የሐዋ (1፡ 8) ትዕዛዝ ለእስራኤላዊያንም ትዕዛዝ ነበር - የእግዚአብሄርን ብርሃን እንዲያንፀባርቁ ተለይተዉ ነበር ፡፡

ማቴ (28፡ 18-20)፡ “ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዥኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው እነሆም እኔ እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ “ ፡፡

“ እንድንሄድ “፣ “ ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ “፣ “ እንድናጠምቅ” እና “ እንድናስተምር “ የታዘዝን ነን ፡፡

እነዚህን መፅሀፍቶች ዉስጥ በማንበብ የሐዋ (1፡ 8) ሂደቱ ላይ ተመልከቱ፡

  • ሮሜ (1፡ 16) - ወንጌል ለአይሁዶችና ለግሪኮች ለሁለቱም የተገባ ነው ፡፡
  • ዮሐ (1፡ 11) - ኢየሱስ ወዳልተቀበሉት አይሁዶች መጣ ፡፡
  • ዮሐ (1፡ 14) - አይሁዶች አልተቀበሉትም ፡፡
  • ሮሜ (10፡ 14-20) - የእግዚአብሄር መገኘት በኢየሩሳሌም በመጀመር በእስራኤል ዉስጥ ቀጠለ ኢየሱስም ተመሳሳይ ነገርን ተከተለ ፡፡
  • ሮሜ (11፡ 25) - የአሕዛብ ሙላት እስኪመጣ ድረስ አይሁዶች በኢየሱስ ላይ ልባቸዉ ደንድኗል ፡፡

እግዚአብሄር ለኢየሩሳሌም ከተማ ልብ እንዳለዉ አምናለሁ ፡፡ አላማዬ በምሄድበት ሁሉ ወንጌልን መናገር ነዉ፣ ምክንያቱም በመጨረሻ አይሁዶች እግዚአብሄር ለኑሮአቸዉ ያለዉን እቅድ ስለሚያዩ ፤ ስራችን አይሁዶችን በመዉደድ በሂደቱ ማገልገል ነው (ሮሜ 15፡ 25-27) ፡፡

በመጨረሻም ሁሉም በኢየሩሳሌም ይጀምራል፣ ሁሉም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በመምጣት በኢየሩሳሌም ያበቃል (ዘካ 14፡ 1-4) ፡፡ እግዚአብሄርም ይመለሳል ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 647.

  2. MacArthur, p. 647.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 229.

  4. Wiersbe, p. 227.

  5. Wiersbe, p. 228.

  6. Wiersbe, p. 228.

  7. Wiersbe, p. 228.

  8. Wiersbe, p. 228.

ጥያቄዎች

  1. በመፅሀፍ ብዙ ስፍራ ላይ ስለ እግዚአብሄር ስም ይወራል (2ሳሙ 7፡ 13) ፤ በመዝ (75፡ 1) ላይ መዝሙረኛዉ “ ስም ቅርብ ነዉ “ በሚለዉ ንግግሩ ምን ማለቱ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  2. መዝ (75፡ 7) እና ሮሜ (9፡ 11-28) አንብቡ ፤ ለመዝ (75፡ 7) በሮሜ ያለዉ ፅሁፍ ጥሩ ገለፃ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስለምን አታስቡም ?
  3. በመዝ (75፡ 8) ላይ የወይን ጠጅ ፅዋዉ ምን ይወክላል ? በመፅሀፍ ሌላ የት ላይ ተመሳሳይ ሀሳብ ልታገኙ ትችላላችሁ ?
  4. መዝ 76፡ 1) “ እግዚአብሄር በይሁዳ ታወቀ “ የሚለዉ መሲሀዊ ንግግር ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
  5. የመፅሀፍ ቅዱስ NASB ዕትም በመዝሙር 76 ላይ እግዚአብሄርን መፍራት ከሚለዉ ጋር በማጣመር ፍራ የሚለዉን ቃል አራት ጊዜ ተጠቅሞታል (መዝ 76፡ 7, 8, 11እና 12) ፤ እግዚአብሄርን ትፈራላችሁ ? አዎ ከሆነ በምን መንገድ ?
  6. በመዝሙር (75-76) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 76:1–3

“God is known in Judah; His name is great in Israel. His tent is in Salem, His dwelling place in Zion. There He shatters the bow’s flaming arrows, the shield, the sword, and the weapons of war. Selah”

የእግዚአብሔር ስም እንድታወቅ አድርግ ፤ የእርሱ ማንነት ፣ የእርሱ ዝና ፣ የእርሱ ባህሪ ፡፡ እንደ አማኝ ስሙ እንድታወቅ እንድታደርግና በኢየሱስ ባገኘኸው በዚያ ፍቅር ሌሎችን እንድትወድ ጌታ አደራን ሰጥቶሃል ፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ ፡- እግዚአብሔርን በደንብ አውቀዋለሁ ? በማለት ራስህን ጠይቅ ፡፡ እርሱን በማምንበት ፣ በምፈራበት እና በማከብርበት መንገድ እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ ?

እግዚአብሔርን ለማወቅ ጣር ፣ በትምህርታዊ መንገድ አይደለም ነገር ግን ጥልቅ በሆነ የግንኙነት መንገድ ፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ሰቶሃል ፡፡ እግዚአብሔር አንደ ብርቱ ጦረኛ ጠላትን በመውጋት ፣ ከፈተና ያስመልጥሃል ፡፡ የጠላትን ምክር ሴራ ያፈርሳል ፡፡ ብርታቱ ከእውቀትህ ይልቃል ፡፡ እግዚአብሔር በየቀኑ በማይለወጥ ፍቅሩ አማካኝነት ጸጋንና ምህረትን ያበዛልሃል ፡፡ ክርስቶስ እንደወደደህ ሰዎችን ውደድ ደግሞም እውነቱን ከሌሎች ጋር ተካፈል ፡፡ በህይወትህ በደስታ ፣ በሰላም እና ፍቅር ስትመላለስ ከጌታ ስለተቀበልከው ፍቅር ሌሎች ሊቀኑ ይችላሉ ፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም የሚያመሰግኑበት ደግሞም እርሱ በምድር ነገሥታት የሚፈራበት ጊዜ ይመጣል ፡፡ እስከዚያው ስሙን ለማወቅ ጣር እና ስሙ እንድታወቅ አድርግ ፡፡

“እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው ። ስፍራው በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው ። በዚያም የቀስትን ኃይል፥ ጋሻን ሰይፍን ሰልፍንም ሰበረ፤ በዚያም ቀንዶችን ሰበረ ። “

  • መዝሙር 76፡1-3

ተጨማሪ ጥቅስ

ዮሐንስ 13:34 — “እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ ። “

ሐዋርያት 1:8 — “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ ። “

ሮሜ 10:16–19 — “ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና ። እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ። ዳሩ ግን፦ ባይሰሙ ነው ወይ? እላለሁ። በእውነት፦ ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ ። ነገር ግን፦ እስራኤል ባያውቁ ነው ወይ? እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ፦ እኔ ሕዝብ በማይሆነው አስቀናችኋለሁ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣችኋለሁ ብሎአል ። “