Feeling Abandoned By God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 74 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 74 ሌለኛዉ የኃዘን መዝሙር ነው ፡፡ ይህ መዝሙር በአፃፍ የተፃፈ ነበር ፡፡ “ አሳፍ፣ ሄማን እና ኤታን በዳዊት ዘመን ጊዜ በቤተ መቅደሱ እንደ ሙዚቀኛና እንደ አምልኮ መሪዎች ያገለገሉ ሌዋዊያን ነበሩ “ ፤ እነዚህ ሰዎስቱ “ ማህበር “ ፈጥረዉ ስለ ነበር ልጆቻቸዉና ሌሎች ትዉልዶች እነርሱ ካለፉ በኋላ አምልኮን መምራት ለመቀጠል የሰለጠኑ ይሆናሉ ፡፡ አንዳንድ ምሁራን የመዝሙር 74 ፀሀፊ የአምልኮ መሪዉ አሳፍ እንዳልነበር ነገር ግን የእርሱ ሞግሼ እንደ ነበር ያመለክታሉ ፡፡ ማክአርቱር የመዝሙሩ ኃዘን “ የእስራኤል ጠላቶች ቤተ መቅደሱን አጥፍተዉት ስለ ነበር በቂ መጥፎ ነገር እንደ ነበር፣ በጣም የከፋ ቢሆንም መዝሙረኛዉ እግዚአብሄር ትቷቸዉ እንደ ነበር ተሰምቶት በነበረዉ “ ነገር ላይ ያተኮረ መሆኑን ይገልፃል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (74፡ 1-11)፡ ዋይርስቤ ይህ መዝሙር በሚገባ ለማሳየት ሰዎስት የቃላት ስዕሎችን ይጠቀማል ፡፡ ቁጥር 1-11 “ ጌታ ትቶት ወደ ነበረበት ወደ ድንኳኑ ማደሪያ “ ያመለክታል ፤ ቁጥር (1-2) በእግዚአብሄር የተጣለ የመሆን ስሜትን ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን እንደማይተዋቸዉ ቃል ገብቶ ነበር (ዘዳ 4፡ 29-31, 26፡ 18-19) ነገር ግን ትቷቸዉ እንደ ነበር እየተሰማቸዉ ነበር (ሰቆ.ኤር 5፡ 20-22) ፡፡ “ ሕዝብህን አስብ “ የሚለዉ ንግግር እግዚአብሄር ረስቷቸዋል ማለት አልነበረም ነገር ግን ለእነርሱ እንዲሰራ እግዚአብሄር ስለ መጠየቅ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሱ ረክሶ ከነበረዉ ተርፎ የነበረዉን ዉድመት እንዲያድሰዉ ጠየቁት (ቁጥር 3-4) ፤ አሁንም በኢየሩሳሌም ሆኖ የነበረዉን ጥፋት ለማየት በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንዲሄድ በመጠየቅ “ መንገዳችሁን አድርጉ “ (1ነገ 6፡ 18-22) ፡፡ ጥፋቱ ሰዉ ዛፎችንና ቆራርጦ በምሳር፣ በቆንጨራና በዶማ እንደሚጠርባቸው የተገለፀ ነው ፤ ቤተ መቅደሱ ብቻ አልነበረም የጠፋው ሁሉም የመገናኛ ቦታዎችና ምኩራቡም ተቃጥለዉ ነበር (ቁጥር 7-8)፡፡ በቁጥር 9-11 እና 19 እግዚአብሄር አዲስ ነቢይን አስነስቶላቸዉ ስላልነበር በዚህ ሁኔታ ዉስጥ ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆዩ ጠየቁ (ኤር 29፡ 10, ሰቆ ኤር 2፡ 9) ፡፡ ወደ እግዚአብሄር ሲለምኑ እግዚአብሄርን በመዉቀስ ይታይላቸዉ እንደ ሆ ጠየቁት ፡፡
መዝሙር (74፡ 12-17)፡ ቁጥር 12-17 “ የጌታ አስተዳደር/ዘመን ዙፋን ! “ ያመለክታሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ጌታ በምድር ላይ ባሉት ፍጥረቶቹ ባህሪያት ንጉስ እንደ ሆነ (መዝሙር 93) “ ይገልፃል ፡፡ አሳፍ እግዚአብሄር ባህሩን ከፍሎት እንደ ነበርና የባህሩን እባቦች ሰባብሮ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 12-14) ፡፡ ኮንስታብል “ በከነዓናዊያን አፈታሪክ/ጥናት ባህሩና እባቦቹ እንደ ባዖል ጠላት በአንድ ላይ እንደተጣመሩ፣ ምናልባትም ባዖል በእነዚህ ጠላቶች ላይ ድል በማድረግ በመጨረሻም ንጉስ ሆኗል ፡፡ የመፅሀፍ ቅዱስ ባለ ቅኔዎች/ገጣሚዎች በምድር አወቃቀር የእግዚአብሄርን ድል አድራጊነት ህዝቡን ከግብፅ ነፃ ሲያወጣና የወደፊት ዉጊያዉን ለመግለፅ የከነዓናዊያንን ቋንቋ ተጠቅመዋል “ ይገልፃል ፡፡ በብሉይ ኪዳን በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ ሌዋታን ከሰይጣን ጋር እኩል የተደረገ ነው (ቁጥር 14) (ኢሳ 27፡ 1) ፡፡ እግዚአብሄር ዕብራዊያንን የምንጭ ዉሃ ሰጥቷቸዉ ነበር መሻገር ባስፈለጋቸዉም ጊዜ ወንዞችን አደረቀላቸዉ (ቁጥር 15) ፡፡ አሳፍ በምድር ላይ የእግዚአብሄርን የበላይነት ያሳያል - ቀኑና ምሽቱ የእርሱ ነበር ምክንያቱም ጨረቃንና ፀሀይን ፈጥሯቸዉ ነበር (ቁጥር 16) ፡፡ እግዚአብሄር ወቅትን ፈጠረ የምድርንም ዳርቻ መሰረተ (ቁጥር 17) ፡፡
መዝሙር (74፡ 18-23)፡ ቁጥር 18-23 “ እግዚአብሄር እኛን የሚያስብበትን ኪዳን ! “ ያመለክታል ፡፡ ዋይርስቤ “ ፅድቅና ፍትህ የዙፋኑ መሰረቶች ከሆኑ በኃሳቡ ከእግዚአብሄር ዙፋን ወደ እግዚአብሄር ኪዳን ከእስራኤል ጋር ወዳለዉ መሄድ ለአሳፍ አሳማኝ/ተቀባይነት ነበረው (ዘኁልቁ 26፣ ዘዳግም 28፡ 30) ፡፡ አሳፍ ጠላቶቹ ያህዌን አፊዘዉበት እንደ ነበርና ስሞን እንደሰደቡት አብራራ (ቁጥር 18) ፤ እግዚአብሄርን የእርግቡን(የእስራኤልን) ህይወት አሳልፎ ለአዉሬዎቹ (ለጠላቶቻቸዉ) አሳልፎ እንዳይሰጣቸዉ ለመነው (ቁጥር 19) ፡፡ አሳፍ እግዚአብሄርን ከእነርሱ ጋር የነበረዉን ኪዳኑን በማስታወስ የተጨቆኑት እንዲያፍሩ እንዳያደርጋቸዉ ጠየቀው (ቁጥር 20-21) ፤ አሳፍ እግዚአብሄር በእርሱ ላይ ያለዉ ዘለፋ እንዲቀጥል ከመፍቀዱ ይልቅ ጉዳዩንና ሕዝቡን እንዲከላከል ተጣራ (ቁጥር 22-23) ፤ እነዚህበቁጥር 3 ላይ ከተደረጉት ጋር ተመሳሳይ ጥያቄዎች ናቸው ፡፡ ዋይርስቤ “ ሕዝቦቹ የተበቀሉ ሆነዉ ነበር፣ የኢየሩሳሌም ከተማም ፈራርሳ ነበር እንዲሁም ቤተ መቅደሱ ፈራርሶና ተቃጥሎ ነበር - ነገር ግን የሚያስፈልገዉ ነገር በጠላቶቻቸዉ አልተነካም ነበር ! ሕዝቡ አሁንምእንደ አምላካቸዉ ቃሉና ኪዳኑ ተቀይረዉ ያልነበሩት ሁሉን ቻይ አምላክ ነበራቸዉ፣ ሁሉን ቻይ አምላክም በአለም ላይ በስራ ላይ ነበር ! “ በማለት ይናገራል ፡፡
ስለ ቤተ መቅደሱ ታሪክ አስቡ፡
- የድንኳኑ ማደሪያ ተገንብቶ ነበር (ዘጸ 27፡ 8) ፡፡
- ለ440 አመታት የድንኳኑ ማደሪያ በእስራኤል ነበር (ዘሌ 26፡ 1) ፡፡
- ለ369 አመታት የድንኳኑ ማደሪያ በሴሎ ነበር (1ሳሙ 1፡ 3) ፡፡
- በ1004 ከክርስቶስ ልደት በፊት ዳዊት ኢየሩሳሌምን በመቆጣጠር (2ሳሙኤል) አንድ መሰዊያን በመመስረት የኪዳኑን ታቦት ወደ ሞሪያ ተራራ አንቀሳቀሰው (1ሳሙኤል 6) ፡፡
- ዳዊት ለእግዚአብሄር ቤትን ለመስራት አቀደ (1ነገ 28፡ 19) ፡፡
- ንጉስ ሰለሞን በ950 ከክርስቶስ ልደት በፊት የመጀመሪያዉን ቤተ መቅደስ በመገንባት (1ነገ 7፡ 46-51) ቀደሰው (1ነገ 9፡ 3) ፡፡
- የቤተ መቅደስ አምልኮ ለ426 አመታት ተከናወነ ፡፡
- በ586 ከክርስቶስ ልደት በፊት ባቢሎናዊያን የመጀመሪያዉን ቤተ መቅደስ አፈራረሱት ፤ ኤርሚያስ 34 አይሁዶችም ወደ ግዞት ተወሰዱ (ኤርሚያስ 31) ፡፡
- ዳንኤል ስለ ኢየሩሳሌም ፀለዬ (ዳን 6፡ 11) ፡፡
- መሰዊያዉ መልሶ ተገነባ (ዕዝ 1፡ 2) ፡፡
- ነቢዩ ሐጌ የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ መልሰዉ እንዲሰሩ ሕዝቡን አደፋፈራቸው (ሐጌ 1፡ 2-4) ፡፡
- በ365 ከክርስቶስ ልደት በፊት አርጤክስስ በተሰረቁት በቤተ መቅደስ ንብረቶች ግብዣን አደረገባቸው ፤ (አስ 1፡ 7) ፡፡
- የቤተ መቅደሱ መሰረት ተቀመጠ ሕዝቡም አለቀሱም ተደሰቱም (ዕዝ 2፡ 13) ፡፡
- ዕዝራ ለሕዝቡ የሕጉን መፅሀፍ በአደባባይ ላይ በማንበብ አስተማረ (ዕዝ 3፡ 12) ፡፡
- በ165 ከክርስቶስ ልደት በፊት ቤተ መቅደሱ ነፃ ፡፡
- በሄሮድስ ቤተ መቅደስ (ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ) ላይ ስራዉ በመጠናቀቁ (መዝ 48፡ 2) የአይሁዶች የሕይወት ማዕከል ሆነ ፡፡
- ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ በ70 ከክርስቶስ ሞት በኋላ በሮማዉያን ፈርሶ ነበር ፤ ኢየሱስ ቤተ መቅደሱ እንደሚፈርስ ተናግሯል (ማቴ 24፡ 1-2) ፡፡
- ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ እንዲገነባ እየጠበቅን ነው ፡፡ በጥቂቱም ቢሆን ሰላም ወደ እስራኤል ሲመጣ ቤተ መቅደሱ በቤተ መቅደሱ ተራራ ላይ መልሶ ይገነባል (ማቴ 24፡ 15, 2ተሰ 2፡ 3-4, ራዕ 11፡ 1-2)
መደምደሚያ
በአሁኑ ጊዜም በእኛ አለም ዉስጥ እግዚአብሄር አሁንም በስራ ላይ ነው ፡፡ አይረሳንም አይጥለንም ፤ በፍፁም አይረሳንም ! ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ በተገነባ ጊዜ ለእግዚአብሄር ትጮኻላችሁ ? ዝግጁ ትሆናላችሁ ?
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 221.
Wiersbe, p. 221.
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 646.
Wiersbe, pp. 224.
Wiersbe, pp. 224.
Wiersbe, pp. 224.
Wiersbe, pp. 224..
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 696.
Wiersbe, p. 186.
Constable, p. 288.
Wiersbe, p. 225.
Wiersbe, p. 225.
Wiersbe, p. 225.
ጥያቄዎች
-
በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮች ወደ እግዚአብሄር በአሳፍ ልመና ላይ የእግዚአብሄርን ህዝቦች ለመግለፅ ምን ተከታታይ የተወደደ/የፍቅር ቃል ተጠቀመ ? እግዚአብሄር እንዲያስታዉስ አሳፍ የጠየቀዉ እግዚአብሄር ስለ ሕዝቡ ምን ድርጊቶችን አድርጓል ? እግዚአብሄር እንዲያስታዉስ መጠየቁ ምን ማለት ነው? (ዘኁ 26፡ 42)
-
እንዴትም ቢኖሩ የይሁዳ ሰዎች ስለ ቤተ መቅደሱ መገኘት በምን አመኑ ? (ኤር 7፡ 4-11)
-
ጌታ በምን መንገዶች እንደ ንጉስ ሊገለጥ ችሏል ? (መዝ 44፡ 4, 93, 96፡ 13, 97፡ 1-6, 98፡ 6-9, 99፡ 1-3)
-
አሳፍ በቁጥር (12-17) እየገለፀዉ የነበረዉ የቀድሞዉ የእግዚአብሄር የማዳን ስራዎች ምን ነበሩ ? በአስቸጋሩ ሁኔታ ወይም ችግሮች ዉስጥ እናንተን ለመርዳት ድሮ/በፊት እግዚአብሄር አድርጎት የነበረዉን ደግማችሁ የጠራችሁበት ጊዜያት አሉ ?
-
በፍፁም እንደማይጥለን የሚያስታዉሱ በመፅሀፍ ላይ ለእግዚአብሄር ሕዝብ የተሰጡት ጥቂት ተስፋዎች ምንድን ናቸው ?
-
በመዝሙር 74 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ ያስረዳችኋል (ያሳያችኋል) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 74:11–12
“Why do You hold back Your hand? Stretch out Your right hand and destroy them! God my King is from ancient times, performing saving acts on the earth.”
ጠይቀህ ታውቃለህ ለምን እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ የታመሙትን እንደማይፈውስ ፤ ለምን በአለም ውስጥ ያለውን ክፉ እንደማያጠፋ ወይም ስቃይን እንደማያስወግድ ? በእምነት እርሱ እንደሚችል ታምናለህ ፡፡ በእምነት እርሱ እንደሚያደርግ ታምናለህ ፡፡ በእምነት እርሱ እቅድ እንዳለው ታምናለህ ፡፡ ባለፈው ጊዜ የእጆቹን ስራ አይተሃል ፣ ታምራቱን አይተሃል ደግሞም የኃይለኛውን የጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል ታውቃለህ ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አንተ እንደሚችል እንደምታምነው የሚንቀሳቀስ ላይመስል ይችላል ፣ እናም አንተ በእግዚአብሔር እንደተተውክ ይሰማህ ጀምሯል ፡፡
እና አሁንም ትጠብቃለህ ፡፡ ትጠብቃለህ ደግሞም የእጆቹን ስራ ታስታውሳለህ እንድሁም በህይወትህ በምድር ላይ የማዳንን ስራ ሲሰራ ስላየህባቸው ጊዜያት ታመሰግናለህ ፡፡ እናም ፍቃድህን አሳልፈህ ለጌታ ትሰጣለህ ፡፡ “ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ “ ትላለህ ፡፡ምክንያቱም ሲሰራ ማየት በማትችልበት ጊዜ እንኳ ፣ ጌታ እግዚአብሔር በመካከልህ ነው ፤ አንተ ልታያቸው በማትችላቸውም መንገድ ይሰራል ፡፡ ዛሬ በተስፋ ላይ ተጣበቅ ፣ ንቃ እናም የእግዚአብሔር ኃይል ለክብሩ በህይወትህ ላይ እንድነግስ ጠብቅ ፡፡
“ ቀኝህን በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ ? እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ ። “ - መዝሙር 74፡11-12
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኢሳይያስ 65:24 — “ እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ አመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ ። “
- ሉቃስ 22:42 — “ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር ። “
- ዮሐንስ 5:17 — “ ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።