A Prayer For The King
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 72-73 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 72 ስለ አንድ ሉዓላዊ/ከሁሉም ለሚበልጥ ስፍራ ዘዉድ የተፃፈ መዝሙር ነው (1ነገስት 2) ፤ ንጉሳዊ መዝሙር በመባልም ይጠራል ፡፡ ማክአርቱር መዝሙሩ “ በንግስናዉ መጀመሪያ ጊዜ ለሰለሞን ብልፅግና የተሰጠ/የተዘመረ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ሰለሞን በንግስናዉ/በክብሩ ከመዝሙሩ ጋር የተገናኘ ብቻ አልነበረም ነገር ግን ምናልባትም “ ፀሀፊ እና በሰዎስተኛ ወገን በራሱ ላይ የፃፉ ነበር…..በእስራኤል ላይ እንደ አስተዳዳሪ ሲደረገ ስለ እግዚአብሄር እርዳታ የተፀለዬ “ ነው ፡፡ ኮንስታብል መዝሙሩ “ የሰለሞንን ዘመን የሚገልፅ ነገር ግን ወደ ፊት በምድር ላይ የእርሱን ተተኪ አስተዳዳሪን ኢየሱስ ክርስቶስን ተስፋ እንደሚያደርግ “ ይናገራል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (72፡ 1-4)፡ ማክአርቱር እነዚህን ቁጥሮች “ እንደ አስተዳደር “ ይገልፃቸዋል ፤ በዚህ አገላለፅ መዝሙሩ ስለ ሰለሞን ነዉ ነገር ግን ይህ ወደ ክብር ንጉሱ ያመለክታል ፡፡ የቁጥር 1 የተፃራሪ ንግግር ይህን መዝሙር ማን እንደ ፃፈው ክርክርን ፈጥሯል ፡፡ ቁጥሩ ወደ አባትና/ልጅ ግንኙነት በማመልከት በእግዚአብሄር አብ እና በልጁ በኢየሱስ መካከል ያለዉን ግንኙነት ተስፋ ያደርጋል (2ሳሙ 7፡ 12-13, መዝ 2፡ 1-12) ፤ ቁጥር 1 “ ንጉሱ በሕዝቡ ላይ የእግዚአብሄርን ፍትህ በመታመን እንደሚያሰላስል አንድ ፀሎትን ያቀርባል (ዘዳ 17፡ 18-20) “ ፤ እግዚአብሄርም ንጉሱንም በፅድቁ ላይ ይዳኘዋል (ቁጥር 2) ፡፡ ኮንስታብል “ ኮረብቶችና ተራሮች መጥቀሱ ለመንግስቱ ዘይቤአዊ አነጋገሩን የሚያስታዉስ ሊሆኑ እንደሚችሉ “ ያመለክታል (ቁጥር 3) ፡፡ ፀሀፊዉ ሰለሞን ድሆችንና የተጎዱትን በመርዳት እንዲመራ ጠየቀው (ቁጥር 4) ፡፡
መዝሙር (72፡ 5-11)፡ ማክአርቱር እነዚህን ቁጥሮች “ እነደ አለማቀፋዊ አስተዳደር/አገዛዝ “ ይገልፃል ፤ ቁጥር 5 የንጉሱ አገዛዝ ከአካባቢዉ እስከ መጨረሻ እስከሌለዉ እንደሚቀጥል ያብራራል - ንጉሱ ረጅም ዘመን ይኖራል (መዝ 72፡ 5, 15) ፡፡ ዝናቡ በንጉሱ ላይ የእግዚአብሄርን በረከት በመወከል ወደ ሰላም ይመራል (ቁጥር 6) ፤ የንጉሱ መገኘት የሚያስደስትም ይሆናል ፡፡ “ ጨረቃ ከዚህ በኋላ አትኖርም “ የሚለዉ ሀረግ “ የዳዊታዊ ስሮዉ መንግስት እርዝማኔን እና ምናልባትም የመሲሁን ዘመን “ ያሳያል ፤ (2ሳሙ 7፡ 16, መዝ 89፡ 3, 4, 29, 36, 37፣ ሉቃ 1፡ 30-33) ፡፡ መንግስቱምከኤፍራጠስ ወንዝ አልፎ እስከ መላዉ ምድር ድረስ ይሰፋል (ቁጥር 8) ፤ በሚያናድድ ሁኔታ ሰለሞን እስከዚህ ፀሎት ድረስ አልኖረም፣ የእስራኤልም ሕዝብ የተከፋፈለ ሆነ ነገር ግን የመሲሁ መንግስት ይሆናሉ፡፡ ቁጥር (9-10) “ ከአከዛዙ ኃይል ማንም እንደማያመልጥ በምድረበዳም እንኳን ያሉት እንደማያመልጡ “ ያሳያሉ ፡፡ ቁጥር 11 የምድር ነገስታት ሁሉ በእርሱ ፊት ይሰግዳሉ በማለት ሲናገር በጣም ትንቢታዊ ነው - በተለዬ የመሲሁ መልክ ነው ፡፡
መዝሙር (72፡ 12-14)፡ ማክአርቱር እነዚህን ቁጥሮች “ እንደ ርህራሄ አገዛዝ “ ይገልፃቸዋል ፤ ቁጥር 12 ስለ ድሆችና ስለ ተጠቁ የቁጥር 4 ድጋሜ ነው ፡፡ “ ኑሮአቸዉ በፊቱ የከበረ እንዲሆኑ “ ከጨቋኞችና ከኃይለኞች ይቤዣቸዋል ፡፡ 1ጴጥ ( 1፡ 19) ኑሮዎች “ በፊቱ ዉዶች እንደሆኑ “ ያስተጋባል ፤ ይህ የከበሩ ሆነዉ ወዳገኛቸዉ ወደ ክርስቶስ ያመለክታቸዋል ምክንያቱም ሊቋቋመዉ በሚችለዉ ዉስጥ ያልፉ ስለነበር (ቁጥር 13-14) ፡፡
መዝሙር (72፡ 15-17)፡ ማክአርቱር እነዚህን ቁጥሮች “ እንደ በለፀገ አስተዳደር/አገዛዝ “ ይገልፃቸዋል ፤ ስለ ረጅም አስተዳደርና ስለ በለፀገ አስተዳደር የመቀጠል ፀሎት (ቁጥር 15-16) ፡፡ ከንግስት ሳባ ጋር ስለ ሰለሞን መገናኘትና ከእርሷ ሰለሞን ወርቅ ስለ መቀበሉ 1ነገ (10፡ 1-10) አንብቡ ፤ ሳባ በቁጥር 10 ተጠቅሳ ስለ ነበር የሰለሞንን የበለፀገ አገዛዝና የመሲሁን አገዛዝ ያመለክታል ፡፡ ቁጥር 17 የንጉሱ ስም ለዘላለም እንደሚቋቋም በሚናገሩ ብዙ ጥቅሶች ይጀምራል ፡፡
መዝሙር (72፡ 18-20)፡ ማክአርቱር እነዚህን ቁጥሮች “ እንደ ከበረ ዘመን/አገዛዝ “ ይገልፃቸዋል ፡፡
መደምደሚያ
የብልፅግናዉ የመጨረሻዉ አስተዳደር/ዘመን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የምንቀበለዉ የዘላለም ህይወት ነው ፡፡ ምድር በሙሉ በክብሩ ትሞላለች (ቁጥር 19) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የታላቁ ንጉስ ስም በአለም ላይ እንደ ታላቅ ስም እንደሚሆን “ ይናገራል ይህም በፊል (2፡ 9-11) የጳዉሎስ ፅሁፍ ትዉስታ ነው “ ፡፡
“ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሄር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለዉን ስም ሰጠው ፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሄር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው “ ፡፡
ሁሉም አካል፣ ምላስ ሁሉ፣ ሁሉም ነገድ፣ ሁሉም ሕዝብ በፊቱ ይሰግዳሉ ፡፡ ፀሎቶቹ፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት መዝሙሮች ተጠናቀቁ ፤ ይህመዝሙርን ከሚሰሩልን ሰዎስት መፅሀፎች ሁለተኛዉን ይዘጋል/ያጠቃልላል ፡፡
3 Robert B. Chisholm, Jr., “A Theology of Psalms,” in A Biblical Theology of the Old Testament, ed. Roy B. Zuck (Chicago: Moody Press, 1991), p. 270; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 276; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 644.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 218.
MacArthur, p. 645.
MacArthur, p. 645.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 277; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.
MacArthur, p. 645.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 695.
MacArthur, p. 645.
MacArthur, p. 645
Nelson’s Commentary, p. 695.
MacArthur, p. 645.
MacArthur, p. 645.
MacArthur, p. 645.
Nelson’s Commentary, p. 695.
ጥያቄዎች
-
መዝሙር 72 ስታነቡ በሰለሞን ፋንታ ኢየሱስ ሲናገር ታነቡታላችሁ ፤ ይህ ምዕራፍ አሁን እንዴት ይናገራችኋል ?
-
በመዝ (73፡ 3) እንደ ነበረዉ የክፉዎች ብልፅግና እንደቀናው ልክ እንደ አሳፍ በህይወታችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል ?
-
በመዝ (73፡ 1-16) አሳፍ አይኖቹ በአለም ላይ ነበሩ ነገር ግን በቁጥር 17ነገሮችን ያየበት ነገር እንደ ተቀየረ እናያለን ፤ ለዚህ መቀየሩ/ለዉጡ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ታስባላችሁ፣ የነበሩትስ ጥቂት መገለጦች ምንድን ናቸው ? አይኖቻችሁ ለአለም መነገዶች እና ለእግዚአብሄር መንገዶች የተከፈቱ ስለ ነበሩበት ጊዜ ፃፍ
-
በመዝሙር (72-73) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 72:11
“Let all kings bow down to him, all nations serve him.”
ኢየሱስ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስም ነው ፡፡ በደስታ ትወጣለህ በሰላምም ትሸኛለህ ፡፡ ድሆችን ይታደጋል የተጠቁትንም ይረዳል ፡፡ የተጨቆኑትን ነጻ ያወጣል አመጽንም ያስቆማል ፡፡ እያንዳንዱን ሰው ፍጹም እና ውብ ሆነ እንደተሰራ አድርጎ ያያል ፡፡ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ፊት ውድ ነህ ፡፡ በምድር ላይ ሌላ አምላክ የለም የነበረውን ፣ ያለውንና የሚመጣውን የጌታ የእግዚአብሔርን ያለወረት የሆነ ፍቅር የሚያቀርብ ፡፡ እርሱ የእምነትህ ባለቤት እና ፈጻሚ ነው ፤ እርሱም ምስጋና ይገባዋል ፡፡ ክብሩም መላውን ምድር ይሞላል ፡፡
ዛሬ ጉልበት ሁሉ ስለሚንበረከክበትና ምላስ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ስለሚመሰክርበት ቀን ጸልይ ፡፡ ክርስቶስ ጌታ ነው ፡፡ ትውልድ ሁሉ ይሰግድና ብቸኛ የሆነውን እውነተኛውን ህያው አምላክ የገለግል ዘንድ ! ና ጌታ ኢየሱስ ና ፡፡ በእምነትም ይህ እንደሚሆን እመን ፡፡ ስትጸልይ በምድር ያሉት ህዝቦች ሁሉ የአመላካችንን የእግዚአብሔን ስም ያውቁ ዘንድና ለእርሱ ይሰግዱ ዘንድ ኢየሱስን ለምን ፡፡ አሜን አሜን !
“ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፥ አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል ። “ - መዝሙር 72፡11
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 72:18–19 — “ ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ ። የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘላለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን ይሁን ። “
- ኢሳይያስ 55:12 — “ እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፥ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ ። “
- ፊልጵስዩስ 2:9–11 — “በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።