God's Help In Old Age
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 70-71 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሌለኛዉ የዳዊት መዝሙር ከነበረው ከመዝሙር 70 ይልቅ ባልታወቀ ትልቅ ሰዉ ተፅፎ የነበረዉን መዝሙር 71 ላይ ለመማር ወስነናል ፡፡ በመዝሙር 71 ተስቤአለሁ ፤ መዝሙሩ “ የእግዚአብሄር እርዳታ በሽምግልና ጊዜ “ የሚል ርዕስን ተሸክሟል ፡፡ ማክአርቱር “ በሕይወቱ አንድ ጊዜ ከተለያዩ ችግሮች ነፃ የወጣ መሆንን ባሰበ ጊዜ በግል ከአንዴም ሁለቴ ተጠቅጧል ፤ ጠላቶቹምእግዚአብሄር እንደተወዉ ቢደመድሙም መዝሙረኛው እግዚአብሄር የታመነ እንደሆነ እርግጠኛ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ መዝሙሩ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን በመታመኑ የተናቀ እንዳይሆን የጠየቀበት ሁለት የሚያግዙ/የተመዘገቡ ነገሮች አሉት (ቁጥር 1-24) ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (71፡ 1-4)፡ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ እግዚአብሄር አሁን እንደ ሚረዳዉ “ ይገልፀዋል ፡፡ መዝሙረኛው በፍፁም ያፈረ እንደማይሆን ነገር ግን በጌታ የዳነ እንደሚሆን ጠይቋል (ቁጥር 1-2) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ መዝሙረኛው በራሱ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ብቻ አላተኮረም በእግዚአብሄር ባህሪይም ላይ እንጂ “ እንደሆነ አመልክቷል ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን እንደ መፅናኛዉ/መሸሸጊያው፣ እንደ አለቱ እና እንደ ምሽጉ ገልፆታል (ቁጥር 3) ፡፡ “ የአመሸሸጊያ አለት “ መዝሙረኛዉ ሁል ጊዜ ደህንነት ወደ ሚሰማበት በእግዚአብሄር መገኘት የሚሄድበት ስፍራ ነበር ፡፡ ምንም ይግጠመን ሁል ጊዜ እንደ መጠጊያ ወደ እግዚአብሄር መሄድ እንችላለን ! መዝሙረኛዉ እግዚአብሄርን ከክፉዎች “ እንዲያድነዉ/አድነኝ “ ብሎ ጠየቀው (መዝ 17፡ 13, 37፡ 40, 144፡ 2) ፡፡ “ አድነኝ “ የሚለዉን “ ለማምለጥ ምክንያት ሁነኝ “ በማለት መረዳት ይቻላል ፡፡ ዋይርስቤ መዝሙረኛው “ በአምላክ አምልኮ መካከል ጣዖትን እንዲያመልክ ተገፍቶ የነበረ “ ከስራዉ የተገለለ አንድ ሌዋዊ እንደ ነበር ይጠቁማል ፡፡
መዝሙር (71፡ 5-13)፡ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ እግዚአብሄር ቀድሞም እንደረዳዉ “ ይገልፀዋል ፤ በቁጥር (5-6) መዝሙረኛው ህይወቱን መቃኘት ጀመረ፣ በእያንዳንዷ እርምጇዉ እግዚአብሄር እንዴት እንደረዳዉ እዉቅና በመስጠት- በእናቱ ማህፀን እያለ ከዉልደቱ እስከ ልጅነቱ ጊዜ (1ሳሙ 7፡ 12) ፡፡ ማክአርቱር በቁጥር 7 “ የሚያስፈራ ምልክት “ ወይም “ የሚያስደንቅ “ የሚለዉን ሀረግ “ ሰዎች በህይወቱ የተደነቁ እንደ ነበር፣ አንዳንዶች መከራዉን እንደ እግዚአብሄር ጥበቃ ሲተረጉሙት ሌሎች ደግሞ እንደ እግዚአብሄር ቅጣት እንደሚተረጉሙት “ ይናገራል ፡፡ ዋይርስቤ “ አንዳንድ ጊዜ ጌታ የተለዩ ሰዎችን የህዝብ ምልክት እንዲሆኑ እንደመረጣቸው “ ይገልፃል ፤ (ኢሳ 8፡ 18, ዘካ 3፡ 8) ፡፡ መዝሙረኛው ሁሉንም ቀን እግዚአብሄርን በማመስገኑ በእርጅናዉ ጊዜ እንዳይጥለዉ ጠየቀ (ቁጥር 8-9) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ መዝሙረኛው በመላዉ ህይወቱ በእግዚአብሄር ታመነ ፤ በእግዚአብሄር ቆይቶ በህይወቱ የተረሳ ከነበረ ብስጭት ይሆን እንደ ሚሆን “ ይናገራል ፡፡ መዝሙረኛው ጠላቶቹ እግዚአብሄር ትቶት እንደ ነበርና የሚቀጥል ጥበቃም የለዉም ማለታቸዉን ተናግሯል (ቁጥር 10-12) ፤ ጠላቶቹን እንዲያጠፋቸዉና እንዲያዋርዳቸዉ እግዚአብሄር ለመነው (ቁጥር 13) ፡፡
መዝሙር (71፡ 14-21)፡ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ እግዚአብሄር ወደ ፊት እንደሚረዳው “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ መዝሙረኛው በብዙና በብዙ እግዚአብሄርን ማመስገኑን እንደሚቀጥል ተስፋ ገባ (ቁጥር 14-16) ፤ መዝሙረኛው እንደ ገናእግዚአብሄር በልጅነቱ እንዴት አብሮት እንደ ነበር በማስታወስ የእግዚአብሄርን ኃይል ለሌላ ትዉልድ እየተናገረ እግዚአብሄር በእርጅና ጊዜዉ እንዳይተወዉ ለመነው (ቁጥር 17-18) ፤ ይህ የፍሬ ነገር/የህጉ/የሼማ መልክ ነው (ዘዳ 6፡ 4-9) ፡፡ በመልካም ነገሮቹ ምክንያት ፅድቆቹ ሰማይ እንደሚደርሱ እግዚአብሄርን ነገረው (ቁጥር 19) ፤ መዝሙረኛው መከራ ደርሶበት እንደ ነበረው እዉቅናን ሰጠ ነገር ግን እግዚአብሄር እንደ ገናያስነሳዋል (ቁጥር 20) ፡፡ እግዚአብሄር የእርሱን ክብር ለመጨመር ምጮትን ይሰጠዋል (ቁጥር 21) ፡፡
መዝሙር (71፡ 22-24)፡ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ እግዚአብሄር ስለ እርዳታዉ የተመሰገነ እንደሚሆን “ ይገልፀዋል ፤ ስለዚህም መዝሙረኛው የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሄርን ማመስገኑን ይቀጥላል ፡፡
መደምደሚያ
ይህ በሁሉም ሂደት ዉስ እግዚአብሄር ስለሚሰራዉ ስራ ትልቅ መልክ ነው ፡፡ 30 አመት፣ 50 አመት ወይም ደግሞ 70 አመት ይሁናችሁ ሁላችንም ስለ እግዚአብሄር የምንማረዉ ብዙ ነገር አለን ለመማርም በፍፁም ያረጀን አንሆንም ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 644.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 217.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 694.
Nelson’s Commentary, p. 694.
Wiersbe, p. 217.
Wiersbe, p. 218.
MacArthur, p. 644.
Wiersbe, p. 218.
Nelson’s Commentary, p. 694.
Wiersbe, p. 218.
Wiersbe, p. 218.
ጥያቄዎች
-
ዳዊት በእነዚህ መዝሙሮች በተደጋጋሚ እግዚአብሄር ነፃ እንዲያወጣዉና/እንዲታደገው ጠየቀወ ፤ ይህ ያለማቋረጥ እንድናኳኳ፣ እንድንፈልግና እንድንጠይቅ የነገረንን መፅሀፍት ይወክላል ብላችሁ ታምናላችሁ ማቴ (7፡ 7-8) ? ለምን ወይስ ለምን አታምኑም ?
-
ዳዊት ያለማቋረጥ እምነቱን በእግዚአብሄር ላይ እንዳስቀመጠ ተናገረ ፤ እምነታችሁ የት ላይ ነዉ የተቀመጠው ? በእግዚአብሄር ላይ፣ በሰዉ ላይ ወይስ በራሳችሁ ላይ ?
-
በመዝ (71፡ 20) ዳዊት “ ከምድር ጥልቅም እንደ ገና አወጣኸኝ “ አለ ፤ ከፍ በማለት በሰማይ ከእርሱ ጋር በተገናኘን ጊዜ የሚነገር ሊሆን እንደሚችል ታስባላችሁ ? (1ተሰ 4፡ 14-17)
-
በመዝሙር (70-71) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 71:17–18
“God, You have taught me from my youth, and I still proclaim Your wonderful works. Even when I am old and gray, God, do not abandon me. Then I will proclaim Your power to another generation. Your strength to all who are to come.”
እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔርን ኃይል ምስክርነት ሊያውጁለትና ሊያካፍሉት የሚችሉ የሆነ ከእነርሱ በእድሜ የሚያንስን ሰው ያውቃሉ ፡፡ ለደቂቃ ስለዚህ አስብ ፣ እያንዳንዱ ትውልድ ለቀጣዩ የሆነ ነገር ማቅረብ ይችላል ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው ከሆነ ሰው በእድሜ ይበልጣል ፡፡ አንተ ከኋላህ ወዳለ ትውልድ ያለህን ለማፍሰስ በጣም አላረጀህም ደግሞም በጣም ልጅ አይደለህም ፡፡ ምንም ማመካኛ ምክንያት የለም ፡፡
እግዚአብሔር ተስፋህን ሲቀጥልልህ ፣ ለሌሎች ስለ ኃይሉ ለማወጅ ጊዜን ውሰድ ፡፡ በእርሱ በጽኑ መሰረትህ ፣ በዓለትህና በመሸሸጊያህ ላይ ቆመህ የታማኝነቱን ድንቅ ስራዎች አውራ ፡፡ ከጌታ ምህረትንና ቤዛነትን ስትቀበል ፣ የእግዚአብሔርን ጸጋ አስደናቂነት ተርክ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ከመጓዝ ማረፍ ጉዞን ሟቋረጥ የለም ፡፡ ስለዚህም ማንም ግድ እንደማይሰጥ በምታስብበት ሰዓት እንኳ አስታውስ ጌታ ስሙን ለሌላ ትውልድ እንድታውጅ ሀላፊነት እንደሰጠህ ፡፡ ዛሬ ወደ ሆነ የእግዚአብሔርን ፍቅር ወደ ምታካፍለው ሰው አይኖችህ ይከፈቱ ጆሮችህም ያዘንብሉ ፡፡ ያይን መነጸርህን ማድረግ ወይም የማዳመጫ መሳሪያዎችህን መክፈት የሚያስፈልግህ ቢሆን እንኳ ፣ የሆነ ትውልድ ላይ ተጽዕኖ ፍጠር ! በመታዘዝ ስትመላለስ ፣ የእግዚአብሔርን ስራ በህይወትህ ተመልከት !
“አምላኬ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤ እስከ ዛሬም ተአምራትህን እነግራለሁ ። እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ፥ ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥ አቤቱ፥ አትተወኝ ። “
- መዝሙር 71፡17-18
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 71:6–8 — “ ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው ። ለብዙዎች መደነቂያ ሆንሁ፤ አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነህ ። አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ ። “
መዝሙር 119:90 — “እውነትህ ለልጅ ልጅ ናት፤ ምድርን መሠረትሃት እርስዋም ትኖራለች ። “
2ኛ ጢሞቴዎስ 2:2 — “ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።