David's Request To Be Saved
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 69 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ከመዝሙር 22 እና 110 በኋላ መዝሙር 69 በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ በብዛት የተደገመ ሰዎስተኛዉ መዝሙር ነው ፤ ያ ማለት መዝሙር 69 ከሌሎቹ መዝሙር በተሸለ አስፈላጊ ነዉ ማለት አይደለም ነገር ግን ስለሚሰማንና ስለሚገጥመን በኃይለኛዉ ይናገራል ማለት አይደለም ፡፡ መዝሙር 69 የተስፋ መቁረጥ ዝማሬና መሲሀዊ መዝሙር ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ መዝሙር 22 እና 69 ሁለቱም “ በዳዊት መከራ ጀመረ ነገር ግን በኢየሱስ መከራ ሙሉ ትርጉም እንዳላቸዉ “ ይገልፃል ፤ ሁለቱም መዝሙሮች ከኢየሱስ ዉልደት፣ ሞትና ትንሳኤ ከ1000 አመት በፊት የተፃፉ ነበሩ ፤ ይሁን እንጂ መዝሙር 22 በኢየሱስ አካላዊ መከራ ላይ ሲያተኩር መዝሙር 69 ደግሞ “ በብዙ በስሜቱ እና በመንፈሳዊ ስቃዩ ላይ ያተኩራል “ ፡፡
በዚህ ክፍል መጨረሻ ላይ በመዝሙር መፅሀፍ ዉስጥ በመሲሀዊ መዝሙሮች ላይ እንመለከታለን ፤ በመሲሀዊዉ መዝሙር ላይ ዳዊት የራሱን ልምድና መከራ ይገልፃል ነገር ግን እነዚህ መሲሁ ኢየሱስ ወደ ፊት ምን እንደሚገጥመዉ ይናገራሉ ፡፡ በሐዋ (2፡ 30-31) ዳዊት ይህን እንዴት እንዳደረገ መግለጫ ነው፡ “ ዳዊት ነቢይ ስለ ሆነ ከወገቡ ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሄር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ ፤ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ አስቀድሞ አይቶ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ስጋዉም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ “ ፡፡ ዳዊት በትንቢት በመናገር (2ሳሙ 7፡ 12-16) መሲሁ ከራሱ ቤት እንደሚመጣ ተረድቷል ፡፡
መዝሙሩን የሚናገረዉ ንዑስ ርዕስ “ ለጭንቅ “ ዜማ የተዘመረ እንደነበር ነው ፡፡ አራት ጊዜ ዳዊት የዳነ ለመሆን ጠይቋል በቁጥር 1 መጀመሪያ ላይ እንዲሁም በቁጥር 14፣ 16-17 እና ቁጥር 18 ፡፡ ማክአርቱር መዝሙሩን ወደ ሁለት ክፍል ይከፍለዋል፡ “ 1) ተስፋ የመቁረጥ መዝሙር (ቁጥር 1-28) እና 2) ስለ ድነት ተስፋ (ቁጥር 29-36) “ ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (69፡ 1-3)፡ ማክአርቱር ቁጥር 1-3 “ የዳዊትን ሁኔታ እንደ መግለጫ “ ይገልፀዋል ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን እንዲያድነዉ ጠየቀዉ ምክንያቱም እየሰመጠ እንደ ነበር ስለ ተሰማው (ቁጥር 1) ፡፡ በጥልቅ ጭቃ ዉስጥ እንደሰመጠና በዉሃ ማዕብል ዉስጥ እንደቀረ ተሰማው (ቁጥር 2) ፡፡ ዳዊት ለእግዚአብሄር በመጮኽና በማልቀስ በአካሉ ደክሞት ነበር (ቁጥር 3) ፡፡
መዝሙር (69፡ 4-12)፡ ማክአርቱር ቁጥር 4-12 “ ለዳዊት ሁኔታ እንደ ምክንያት “ ይገልፃቸዋል ፤ ዳዊት ያለ ምክንያት የሚጠሉት ሰዎች ቁጥር ከራስ ፀጉር እንደሚበልጥ ተናገረ (ቁጥር 4) ፡፡ ኢየሱስ በዮሐ (15፡ 25) ዳዊት ብሎት የነበረዉ እንደሆነ እንደ መፈፀም ዳዊትን ጠቅሶታል (ማቴ 5፡ 17) ፡፡ ዳዊት በዚህ ጉዳይ እግዚአብሄር ጥፋተኛ እንዳልሆነ ያውቃል (ቁጥር 5) ፤ ማክአርቱር ዳዊት “ የእርሱ የማይረቡ ሁኔታዎች ሌሎች አማኞችን የሚያደናቅፉ ድንጋዮች እንዳይሆኑ እንደሚፈራ “ አመልክቷል እና በእርሱ እየሆነዉ በነበረዉ እንዳያፍሩ ዳዊት ተጨነቀ (ቁጥር 6) ፡፡ ዳዊት ለወንድሞቹ እንግዳ እስኪሆን ድረስ በሌሎች በመሰደብ ወይም በመዘለፉ አፍሮ ነበር (ቁጥር 7-8) ፤ ይህ ሌለኛዉ መሲሀዊ ማሳያ ነው ፤ ኢየሱስም እንዲሁ ደርሶበታል (ማቴ 12፡ 46-50, ዮሐ 7፡ 3-5) ፡፡ ለቁጥር 9 ኮንስታብል “ በእርሱ ላይ የበዙ ህዝብ አስተያየትን መልሶበት የነበረዉን ቤተ መቅደሱን መገንባት የዳዊት የሁልጊዜ ሀሳብ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ገንዘብ የሚለዋወጥበት ቤተ መቅደሱን ባፀዳዉ ጊዜ ኢየሱስ ከዳዊት ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ነበረው (ማቴ 21፡ 12-13, ማር 11፡ 15-18) ፤ ዮሐ (2፡ 17) እና ሮሜ (15፡ 3) ሁለቱም ክርስቶስ ምን እንደሚገጥመዉ ቀድሞ ስለ ተነገረዉ በመዝሙር 69 ስላለዉ እዉነት ይናገራሉ ፡፡ ጳዉሎስ አማኞችን ስድቦች በጌታ ላይ እንጂ በእኛ ላይ እንዳልወደቁ አሳስቧቸዋል ፡፡ ዳዊት በአምልኮም ምን ነገር ቢያደርግ ሰዎች ዘለፉት (ቁጥር 10-12) ፡፡
መዝሙር (69፡ 13-18)፡ ማክአርቱር ቁጥር (13-18) “ ለዳዊት ሁኔታ እንደ ተስፋ “ ይገልፀዋል ፤ ዳዊት እግዚአብሄርን ስለ ሞገሱ፣ ስለ ድነቱ፣ ስለ መትረፍረፍ እና ስለ ሚታመን ፍቅሩ ጠየቀው (ቁጥር 13) ፡፡ ሊዉጠዉ ከሚችለዉ ከጭቃዉ፣ ከዉሃዉና ከሚጠሉት እንዲታደገዉ ጠየቀው (ቁጥር 14) ፤ በእርሱ ላይ ከቀረበዉ የሞት ጉድጓድ ዉስጥ እንዳይተወው ለመነው (ቁጥር 15) ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄር እንዲመልስለት ጠየቀው ምክንያቱም በታላቅ ጭንቀት ዉስጥ ስለሆነና ከጠላቶቹ መዳን ስለሚያስፈልገው (ቁጥር 16-18) ፡፡
መዝሙር (69፡ 19-21)፡ ማክአርቱር ቁጥር (19-21) “ የዳዊትን ሁኔታ እንደ ዘለፋ “ ይገልፃቸዋል ፤ ዳዊት እግዚአብሄር እየገጠመዉ የነበረዉን ነገር እንደሚያዉቅ ያውቃል (ቁጥር 19-20) ፡፡ በማቴ (26፡ 37) ዳዊት በእነዚህ ጥቅሶች ገጥሞት የነበረዉን የሚመስል በጌቴሰማኒዬ አትክልት ስፍራ ላይ ብቸኝነትንና ሀዘን ገጥሞታል ፤ በቁጥር 21 ዳዊት ለመብሉ ሐሞት ለሚጠጣዉ ደግሞ ሆምጣጤ ተሰጠው - ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰጥቶት እንደ ነበረው ጠንካራ መሲሀዊ ማሳያ ነው (ማቴ 27፡ 34) ፡፡
መዝሙር (69፡ 22-28)፡ ማክአርቱር ቁጥር (22-28) “ የዳዊት ሁኔታ እንደ በቀል “ ይገልፃቸዋል ፤ ዳዊት ጠላቶቹ በወጥመድ ዉስጥ እንዲወድቁና እግዚአብሄር መዓቱን በላያቸዉ ላይ እንዲያፈስስ ጠየቀ (ቁጥር 22-24) ፡፡ ዳዊት ምሽጋቸው የፈራረስ እንዲደረግና በድንኳናቸዉ ዉስጥ ማንኛቸዉም እንዲኖሩ እንዳይፈቅድላቸዉ ጠየቀ (ቁጥር 25) ፤ ይሁዳን ለመጥቀስ ሌላ መሲሀዊ ትንቢትን ለማመልከት ቁጥር 25 በሐዋ (1፡ 20) ተጠቅሷል ፡፡ የመሲሁ መከራ በግልፅ የእግዚአብሄር እቅድ ነበር (ኢሳ 53፡ 10) ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን አጥቅተዉት የነበሩትን ጠላቶቹን ህይወት እንዲያሳጥረዉ ጠየቀ (ቁጥር 26-28) ፡፡
መዝሙር (69፡ 29-36)፡ ዋይርስቤ “ የዳዊት የመጀመሪያ መዝሙሮች በቁጥር 29 ላይ ሲያበቃ ወደ ባቢሎን ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም በኋላ ነቢዮ ኤርሚያስ ቁጥር 30-36 እንዲጨምር መንፈስ ቅዱስ እንደ መራው “ አመልክቷል ፡፡ ስለ እነዚህ ጥቅሶች ጥያቄዉ በእነዚያ ጥቅሶች እየሆነ የነበረዉን ዳዊት እንዴት አወቀው ? ቁጥር 30-36 ምስጋና በመስጠት እግዚአብሄርን ስለ ማመስገን ይናገራል ምክንያቱም እግዚአብሄር በምርኮ በነበሩ ጊዜ ስለሚሰማቸዉና ስለ ማይንቃቸው ፡፡ ዋይርስቤ “ ዳዊት ምድሪቱ አንድ የተፈወሰችና እንደ ገና ከተማዋ በህዝብ የምትበዛበትን ጊዜ ያ ቀን እንደሚመጣ “ ይናገራል ፡፡
መደምደሚያ
ማክአርቱር መሲሀዊ መዝሙሮችንና የመፈፀማቸዉን ፍሬ ነገር ይሰጣል ፤ ፍሬ/ዝርዝር ነገሮቹ 20 መዝሙሮችን ያካትታል ፡፡ መዝ (69፡ 8) ለእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ለመገንባት ባለዉ መነሳሳት ምክንያት ዳዊት ለራሱ ቤተሰቦች እንግዳ እንደሆነ ይናገራል (ቁጥር 9) ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ለመሆን በብዙ መነሳሳት የተጠጋን ስትሆኑ ብዙ ሰዎች ምን እያደረጋችሁ ነዉ ብለዉ በመጠየቅስድብን በላያችሁ ላይ ይወረወሩባችኋል ይክዷችኋልም ፡፡ ያ በሚሆን ጊዜ በመልካም ካምፓኒ ትሆናላችሁ ! በብዙ ዳዊትን በሚመስልበት በጠቅላላ በክርስቶስ ነገሮችበብዙ ትመስላላችሁ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 693.
Nelson’s Commentary, p. 693.
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 643.
MacArthur, p. 643.
MacArthur, p. 643.
MacArthur, p. 643.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 269; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.
MacArthur, p. 643.
MacArthur, p. 643.
MacArthur, p. 643.
MacArthur, p. 643.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 215
Wiersbe, p. 217
ጥያቄዎች
-
መዝ (69፡ 3) ዘማሪዉ እንዴት ደክሞ እንደ ነበር፣ ጉሮሮዉ እንዴት ሰልላ እንደ ነበር እና ወደ እግዚአብሄር ከመጮኹ የተነሳ አይኖቹ እንዴት እንደፈዘዙ ይናገራል ፤ ዳዊት እዚህ ጋር እንዳደረገዉ በጣም ተስፋ በመቁረጥ ወደ እግዚአብሄር የጮኃችሁበት ጊዜ በህይወታችሁ ነበር ? አዎ ከሆነ ዉጤቱ ምን ነበር ? ሁኔታዉን አርቆት/ወስዶት ነበር ? በልቅሷችሁ ምክንያት ማግኘታችሁ ቀላል ነበር ?
-
ዳዊት በመዝ (69፡ 21) “ ለመብሌ ሐማት ሰጡኝ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ “ ባለ ጊዜ ዳዊት ምን እያመለከተ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? የሆነ ጊዜ ላይ እንዲጠጣ ሆምጣጤ ተሰጥቶት ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ ? በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ሆምጣጤ የተጠቀሰ ነው (ሩት 2፡ 14, ማቴ 27፡ 34)፣ ማንስ ጠጣው ?
-
በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ የሕይወት መፅሀፍ/መዝገብ(ቁጥር 28) የተጠቀሰ ነው ( ፊል 4፡ 3, ራዕ 3፡ 5, 13፡ 8, 20፡ 15, 21፡ 27) ? የሕይወት መዝገብ መፅሀፍ “ ምንድን ነው ? ስማችሁ በመፅሀፉ ዉስጥ እንዳለ እንዴት እርግጠኛ ልትሆኑ ትችላላችሁ ?
-
በመዝ (69፡ 30-31) መሰረት ጌታ ከእናንተ ከመስዋዕት ይልቅ የሚፈልገዉ ምንድን ነው ?
-
በመዝሙር 69 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 69:19–21
“You know the insults I endure—my shame and disgrace. You are aware of all my adversaries. Insults have broken my heart, and I am in despair. I waited for sympathy, but there was none; for comforters, but found no one. Instead, they gave me gall for my food, and for my thirst they gave me vinegar to drink.”
ዳዊት ስደት ተቀብሏል ፡፡ ኢየሱስ ስደት ተቀብሏል ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ውሸትን ፣ ስድብን ተቀብለዋል ደግሞም በወንድሞቻቸውና በእህቶቻቸው ዙሪያ ሰይቀር ባይተዋርነት ተሰምቷቸዋል ፤ ይህ ሁሉ ለኃያሉ እግዚአብሔር ካላቸው ቅናትና መሰጠት የተነሳ ነው ፡፡ ክርስቶስን ስትከተል አንተም መከራና ስደትን እንደምትቀበል ተናግሯል ፡፡ እርዳታን ፈልገህ ስትጮኽም በምላሹ ዝምታን ልትቀበል ትችላለህ ፡፡ እርዳታን ፈልገህ ስትጮኽ ልክ ክርስቶስ ሆምጣጤ እንደቀረበለት ሁሉ አንተም ደስ የማያሰኝ መራራ የሆነ ምክር ሊቀርብልህ ይችላል ፡፡ ቢሆንም ግን በክርስቶስ እና በቃሉ ተስፋን ስታደርግ ፣ ትዕግስትን ታገኛለህ ፡፡ እርሱ ለህዝቡ ኃይልና ጉልበትን ይሰጣል ፡፡
ዛሬ መከራና ስደትን እየተቀበልክ ከሆነ ፣ ብቻህን እንዳልሆንክ አስታውስ ፡፡ አለም ፣ ጣላቶችህና ድያብሎስ ሉዓላዊውን ፣ ኃይለኛውንና ባለ ግርማ የሆነውን የደህንነትህን አምላክ አይወዱትም ፡፡ ሆኖም ግን ወደ ጌታ አጠገብ ስትቀርብ እርሱ ህይወትህን ይቤዣል ፡፡ እርሱ ይታደግሃል ፡፡ አትፍራ ፡፡ ጌታ ስሙን ከሚወዱ ጋር ነው ፡፡ ምስጋና እና አምልኮ አቅርብ ደግሞም ስሙን አመስግን ያህዌ ፣ ኤሎሂ ፣ አዶናይ ፣ ጌታ እግዚአብሔር ፣ የደህንነቴ አምላክ ፡፡ ቅዱስ ስሙን አመስግን !
“አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ፤ የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው ። ነፍሴ ስድብንና ኃሣርን ታገሠች፤ አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ ። ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ ። “ - መዝሙር 69፡19-21
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 69:9 – “ የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና ። “
- ማቴዎስ 27:33–34 — “ ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም ፥ በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም ። “
- ሮሜ 15:3–4 — “ ክርስቶስ ራሱን ደስ አላሰኘምና፤ ነገር ግን፦ አንተን የነቀፉበት ነቀፋ ወደቀብኝ ተብሎ እንደ ተጻፈ ሆነበት ። በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።