Wisdom Books Psalms

God's Majestic Power

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 68 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 421 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 68 “ የፀሎት፣ የክብር፣ የምስጋና መስጠት፣ የታሪካዊ አስታዋሽ እና የእርግማን “ መሲሀዊ መዝሙር ነው፣ በተጨማሪም ወደ ክብር ንጉስ ያመለክታል ፡፡ ይህ መዝሙር ከዳዊት መዝሙሮች ለመዘምራን አለቃ የተዘመረ ነው ፤ ይህ መዝሙርታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም በመመለሱ ከዳዊት የደስታ ስሜት የተፃፈ ነበር ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (68፡ 1-6)፡ ይህን መዝሙር ዋይርስቤ ዋና ዋና ሀሳቡን በማዉጣት ቁጥር 1-6 “ አምላካችን ለእኛ እንደመጣ “ ይፅፋል ፡፡ በቁጥር 1 የእግዚአብሄር ኃይል ጠላቶቹ እንዲበተኑና እንዲሸሹ ምክንያት ሆነ (ዘኁ 10፡ 33-35) ፤ የመጣዉ የእግዚአብሄር መገኘት ታቦቱን ያመለክታል ፡፡ ፃድቃኖች በእግዚአብሄር ፊት ሲደሰቱ (ቁጥር 3) የእግዚአብሄር ጠላቶች በእግዚአብሄር ፊት ይጠፋሉ (ቁጥር 2) ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዎች ለማመስገን፣ ስሙን ከፍ ለማድረግ እና ማን እንደሆነና ለእርሱ የሚያስፈልገዉ ማን እንደሆነ በማስታወስ ይዘምራሉ፡ አባት ለሌላቸዉ፣ ለመበለቶች፣ ወደ ምድረበዳ ለወጡ እና ለእስረኞች (ቁጥር 4-6) ፤ እግዚአብሄር ሰዎችን ነፃ በማዉጣት ስራ ላይ እና በእነርሱ ላይ በመመልከት ላይ ነው ፡፡ ኮንስታብል እግዚአብሄርን እንዴት “ አንደ ባለ ግርማ ተዋጊ በበርሃ ምድረበዳ ሰረገሎቹን እንደሚያበራቸዉ “ በማቅረብ ይገልፀዋል ፡፡

ይህ መዝሙር ለእግዚአብሄር የተለያዩ ገላጮችና ስሞችን ይጠቀማሉ፡

  • ቁጥር 1፡ “ ያሕዌ “ እንደ “ ጌታ “ ሊተረጎም ይችላል (ዘጸ 3፡ 15) ፡፡
  • ቁጥር 1፡ “ እግዚአብሄር “ እንደ “ ኤሉሄ “ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ፡፡
  • ቁጥር 11፡ “ አዶናይ “ እንደ “ ጌታ “ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ፡፡
  • ቁጥር 14፡ እግዚአብሄር “ ሁሉን ቻይ “ ነው ፡፡
  • ቁጥር 18፡ “ እግዚአብሄር አምላክን “ ይጠቅሳል ፡፡
  • ቁጥር 20፡ እግዚአብሄርን እንደ “ ድነት አምላክ “ ይገልፀዋል ፡፡
  • ቁጥር 24፡ እግዚአብሄርን እንደ “ ንጉስ “ ይገልጧል ፡፡

መዝሙር (68፡ 7-18)፡ዋይርስቤ ቁጥር 7-8 “ አምላካችን ከፊታችን ቀድሞ እንደሚሄድ/እንደሚወጣ “ እንደሚያሳዩ ይፅፋል ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በምድረበዳ የመራበትን ጊዜ ዳዊት ዘጸዓት ላይ ተመልሶ ጠቀሰው (ቁጥር 7) ፤ የተትረፈረፈ ዝናብ እና መናን እንኳን በእግዚአብሄር በረከት ተሰጥቷቸዉ ነበር (ቁጥር 8-9) ፡፡ እግዚአብሄር ሁላችንንም ከኑሮአችን ምድረበዳ ዉስጥ አዉጥቶናል ፤ በፊታችን በማለፍ በምግብ ለግሶናል (መሳ 5፡ 4-5) ! እግዚአብሄር የሚያስፈልጋቸዉን ለግሷቸዋል (ቁጥር 10) ፡፡ ቁጥር 11-12 ወደ ዘጸዓት ተመልሶ ሴቶች ስለ እግዚአብሄር ተስፋ በምስጋና መዘመራቸዉን ይጠቅሳል (ዘጽ 15፡ 20-21፣ 1ሳሙ 18፡ 6) ፡፡ ቁጥር 13 በእግዚአብሄር ፊት መቀመጥን ይጠቅሳል ፡፡

በቁጥር 14 ሰልሞን ማለት ጥቁር ተራራ ማለት ሲሆን “ የእግዚአብሄር በረከት ስዕላዊ መግለጫ መሆን ሲችል ሴኬም አጠገብ በሰልሞን ተራራ ላይ ዳዊት የአቤሜሌክን ድል እየጠቀሰ ነው (መሳ 9፡ 48) “ ፡፡ በቁጥር (15-16) ዳዊት ረጃጅሞቹ የባሳን ተራሮች ቢቀኑም እንኳን እግዚአብሄር ሊያድርባቸዉ ስለመረጣቸዉ ስፍራዎች ፃፈ (ኤር 22፡ 20-21) ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄር በሺ ሰረገላዎች የተከበበ እንደሆነ ገለፀው (ቁጥር 17) ፤ እግዚአብሄር ወደ ላይ በመዉጣት ምርኮን ስለወሰደ እግዚአብሄር አምላክ በኢየሩሳሌም ሊኖር ይችላል (ቁጥር 18) ፤ ይህ መዝሙር በዚህ መዝሙር ትንቢታዊ ማጣቀሻ ነው ፡፡ ኢየሱስ ወደ ላይ በትንሳኤዉ/በእርገቱ ከፍ በማለት ለምርከኞች ነፃነትን ሰጠ ፡፡ ጳዉሎስ ይህን እግዚአብሄር ከሰዎች ስጦታን ከመቀበል ይልቅ ለሰዎች ስጦታን እንደ ሰጠ ጠቅሷል (ኤፌ 4፡ 8) ፡፡

መዝሙር (68፡ 19-35)፡ዋይርስቤ ቁጥር 9-35 “ አምላካችን በዉስጣችን እንደሚያድር “ እንደሚያሳዩ ይፅፋል፡፡ ዳዊት እግዚአብሄር በየቀኑ ሸክሙን ስለ ተሸከመለትናመድሀኒቱ ስለሆነ አመሰገነው (ቁጥር 19-20) ፤ በኃይሉም እግዚአብሄር ጠላቶቹን አደቀቃቸው (ቁጥር 21) ፡፡ በቁጥር 22-23 ማክአርቱር “ ጠላቶቹ በምድር (በባሳን) ወይም በባህር ለማምለጥ ሲሞክሩ እግዚአብሄር በህዝቡ ለማጥፋት መልሶ ያመጣቸዋል (አሞ 9፡ 2-4) “ በማለት ይናገራል፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት በቤተ መቅደሱ የተገኘ ነበር፣ ሙዘቀኞቹ ሲከተሏቸዉ ዘማሪዎቹ ስርዓቱን በመጠበቅ መሩ (ቁጥር 24-26) ፡፡ በቁጥር 27 የተጠቀሱት ሁሉም ወገኞች ክርስቶስንይጠቅሳሉ ፤ እግዚአብሄር ከአሕዛብ ሁሉ የአለምን ምስጋና ይቀበላል (ቁጥር 28-29) ፡፡ የክብር ንጉስ በተመለሰ ጊዜ ሁሉም ሰዉ ማን እንደ ሆነ ያውቃሉ ፡፡ ቁጥር 29-35 ሌላ ግልፅ መሲሀዊ ትንቢትን ይሰጣል !

መደምደሚያ

እግዚአብሄር በፊት እንዴት ተጉዞ እንደ ነበር፣ አሁን እንዴት እየተጓዘ እንደሆነና እንዴት እንደሚጓዝ አስደናቂ መልክን ይስላል ፤ ስለ እኛ እንደ መጣና ከፊታችን በመዉጣት በመካከላችን ያድራል ፡፡ በመዝሙር 68 ላይ ዋይርስቤ ማብራሪያውን “ አምላካችን ከአለም ሁሉ ምስጋና ይቀበላል “ በማለት ይደመድማል ፡፡ በክብር ንጉስ ላይ ማትኮርንላይ እንቀጥላለን !

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 642.

  2. MacArthur, p. 643.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 213.

  4. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 262; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  5. Wiersbe, p. 214.

  6. Constable, p. 263.

  7. Wiersbe, p. 214.

  8. MacArthur, p. 643.

  9. Wiersbe, p. 214.

ጥያቄዎች

  1. በመፅሀፍ ቅዱስ መዝ (68፡ 7) የትኛዉን ጊዜ ይጠቅሳል (ዘጸ 13፡ 21-22, 14፡ 19, ነህ 9፡ 19) ? በአሁኑ ስዓት እግዚአብሄር ከእኛ ጋር እንዳለ እንዴት እናዉቃለን ?
  2. በመዝ (68፡ 13) ዳዊት የእርግብ ክንፎችን ጠቅሷል ፤ በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ቦታ ላይ እነዚያ እርግቦች የተጠቀሱ ናቸው ምንስ ይወክላሉ ? (ዘፍ 8፡ 9-12, 15፡ 9, ዘሌ 5፡ 7, ማር 1፡ 10, ዮሐ 1፡ 32)
  3. በመዝ (68፡ 15) የባሳን ተራሮች ተጠቅሰዋል ፤ እነዚህ ተራሮች በምን ይታወቃሉ ዳዊት እንደ እግዚአብሄር መኖሪያ ወይም ማደሪያ ስፍራ ለምን እንደጠቀሳቸዉ ምን ትላላችሁ ? (ዘኁ 21፡ 33-35, ኢያ 21፡ 27, ሕዝ 27፡ 6, 39፡ 18)
  4. መዝ (68፡ 29) “ በኢየሩሳሌም ስላለዉ መቅደስህ ነገስታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ “ ይላል ፤ ምናልባትም ይህ ቁጥር የኢየሱስ ዉልደት ጥላ ይሆናልን ? (ማቴ 2፡ 11)
  5. በመዝሙር 68 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 68:1

“God arises. His enemies scatter, and those who hate Him flee from His presence.”

በጠላት እንደተከበብክ ይሰማሃልን ? ከጠላት ውሸቶችን ትሰማለህ ፤ ወደ ወጥመዱ እንድትወድቅ ይፈትንሃል ወይም በጌታ ሳይሆን በሌላ ነገር ምቾትን እንድትሻ ያባብልሀልን ? ምናልባትም በዙሪያህ ክብደት ጭንቀት ፣ ከሞላ ጎደል መንቀሳቀስ እንደማትችል እናም ምንም መስራት እንደማትችል ይሰማሃል ?

ተነስ ጓደኝዬ ተነስ ፡፡ ባለግርማው የእግዚአብሔር ኃይል በውስጥህ እንድንቀሳቀስ ፍቀድ ፡፡ በእርሱ ኑር ፡፡ እያንዳንዱን አሳብ ማርከህ ያዝ እና የእግዚአብሔርን እውነት እንድያስታውስህ አድርግ ፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜም ከአንተ ጋር እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡ ልክ የቃል ኪዳኑ ታቦት ዳዊት በሚሄድ ጊዜ አብሮ እንደሚሄድ ሁሉ መገኘቱም በምትሄድበት ሁሉ አብሮህ ይሄዳል ፡፡ የዳዊትም ጠላቶች ከእግዚአብሔር መገኘት የተነሳ ይበተኑ ነበር ፡፡ አስታውስ ለእግዚአብሔር ተገዛ ፤ ዲያብሎስን ተቃወም እርሱም በውስጥህ ካለው ከክርስቶስ ኢየሱስ ኃይል መገኘት የተነሳ ከአንተ ይሸሻል ፡፡ ተነስ ፡፡ አልተሸነፍክም ፡፡ ድሉ የእግዚአብሔር ነው ፡፡ እግዚአብሔር በውስጥህ ይነሣ ፡፡ ተነስ !

“እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ ። “ - መዝሙር 68፡1

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዘኍልቍ 10:35 — “ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር ። “
  • ማቴዎስ 28:20 — “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ። “
  • ያዕቆብ 4:7 — “ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል “