Wisdom Books Psalms

Seven Words of Praise

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 66-67 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 420 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ከመዝሙር 66-67 ስናጠና ኑሮአችን ላይ የምንተገብራቸዉ ጥቂት ነገሮች እንማራለን እንዲሁም ደግሞ በኑሮአችን ተጨባጭ ለዉጦችን እንመለከታለን ፡፡ በተለየ መልኩ እንጓዛለን ምክንያቱም ዳዊት እንዴት እንደተጓዘና እደን እግዚአብሄር ልብ ስላደረጋቸዉ ነገሮች ከመፅኀፍ ስለምናይ ፡፡ መዝሙሮቹ የዳዊትን ትግሎች፣ ድሎችን እና ስኬቶች በብዙ ያሳያሉ ፡፡ ዛሬ በምስጋና አስፈላጊነት ላይ መመልከትን እንፈልጋለን፡ እግዚአብሄር የማመስገን ሀሳብን፡፡

ትምህርት

መዝሙር (66፡ 1-4)፡ ምስጋና ለእግዚአብሄር አክብሮትን መግለፅ ነው ፡፡ እነዚህ በልባችን እንድንፀና ስለ እግዚአብሄር መልካም ስሜቶች አይደሉም ፤ በመሰረቱ ምስጋና ከዉስጥ የሚወጣ ገለፃ ነው ፡፡ ዳዊት የምስጋንና ኃይል ተረድቷል ፡፡ ምስጋና በእግዚአብሄር ቃል ላይ እምነትን ያሳያል ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ሚሰራባቸዉ መንገዶች በደንብ ስንማር በመፅኀፍ ዉስጥ ስለ ሰጠን ተስፋዎችና እዉነቶች በብዙ እንማራለን ፤ በብዙ በህይወት ዉስጥ፣ በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ስንጓዝ በኑሮአችን ዉስጥ በሁሉም ሁኔታ በብዙ ምስጋናን መናገር እንችላለን - በአሁኑ ሰዓትና በቅድመ በተጠራንበት በሁለቱም ፡፡ ምስጋና እግዚአብሄር ማን እንደሆነ ገለፃ ብቻ አይደለም ፤ በድል መሄድ እንድንችል ነገሮችን እንድንጣራና ነገሮችን በእንቅስቃሴ እንድናስቀምጥ የሚፈቅድልን በመሳሪያ ማስቀመጫችን እንዳለ መሳሪያ ነው ፡፡ መዝሙር 150 እግዚአብሄርን እንድናመሰግን ያዘናል ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስ አገላለፅ በህይወት መከራ/ፈተና እንደሚገጥመን እናዉቃለን - እየሆነም ነው ፤ ነገር ግን አማኞች የተሸነፉ መሆን መፅኀፍ ቅዱሳዊ አይደለም ፡፡ ምስጋና በድል መጓዝ እንድንችል የሚያስፈልገዉ ደረጃ ላይ ያስቀምጠናል ፡፡

ዛሬ በመፅኀፍ ዉስጥ ስለ ምስጋና የምናገኛቸዉን ሰባት የዕብራዊ ቃሎች ላይ እንመለከታለን፣ በተለይም በመዝሙር መፅሀፍት ዉስጥ ፡፡ መዝ (22፡ 3) እግዚአብሄር “ በእስራኤል ምስጋና ላይ የተቀመጠ “ እንደሆነ ይነግረናል ፤ ይህ ጥቅስ ምስጋና በሚሆን ጊዜ እግዚአብሄር ወደ ስፍራዉ ይገባል የሚለዉን ሀሳብ ይናገራል ፡፡ ያን በምንመለከት ጊዜ እግዚአብሄር በምስጋና ይኖራል ስለዚህ በኑሮአችን የሖነ ነገር እንዲለወጥ ሲያስፈልግ በመጀመሪያ ምስጋና በመስጠት እግዚአብሄር ስለ እናንተ ሲንቀሳቀስ እዩ ፡፡ የእግዚአብሄር ጆሮዎች በትኩረት ወደ ፀሎታችን እንደሆኑ በማወቅ ያለማቋረጥ ወደ እግዚአብሄር የሚፀልዩ የፀሎት ሰዎች መሆን ያስፈልገናል ፤ በዳን (6፡ 10) ዳንኤል ወደ እግዚአብሄር በቀን ሰዎስት ጊዜ እንደሚፀልይ ተነግሮናል ፤ በመዝ (119፡ 164-165) ዳዊት በቀን ሰባት ጊዜ እግዚአብሄርን እንደሚያመሰግን ተነግሮናል ፡፡ ሁለቱን በምናወዳድር ጊዜ በሁሉም አስር ደቂቃ ፀሎት እናደርጋለን፣ ምናልባትም ከ20-25 ደቂቃ እግዚአብሄርን በማመስገን ማሳለፍ ይኖርብናል ፡፡

በ 1ተሰ (5፡ 16-18) ጳዉሎስ መፀለይንና እግዚአብሄርን ማመስገንን ሁለቱንም አበረታቷል ፡፡በኃይለኛ ሁኔታዎች መካከል ላይ በነበረ ጊዜ ዳዊት የዚህ ተግባር ምሳሌ ሆኗል ፤ ሳዖል እንኳን ባለዉ ኃይል ሁሉ ከ3,000 የሚበልጡ ሰዎች በማምጣት ዳዊትን ሊገድለዉ ሲጥር ዳዊት ምርጫዉን እግዚአብሄርን ማመስገን አደረገ ፡፡ ጳዉሎስና ሲላስ በወህኒ ተቀምጠዉ በነበር ጊዜ በብቸኝነት እስራት ዉስጥ መካከል ላይ እግዚአብሄርን አመሰገኑ እግዚአብሄርም ስለ እነርሱ ተነሳ ፡፡ ምስጋና በዚህ በተፈጠረዉ አለም ላይ እየሆነ ካለዉ ነገር ላይ አይናችንን በማንሳት እግዚአብሄር በኑሮአችን እና በሁኔታዎቻችን በሚሰራበት መለኮታዊ አለም ሌላ ስፍራ ላይ ያስቀምጠናል ፡፡ መዝሙሮች የተፃፉ አምልኮዎች ናቸው ፡፡ በምስጋና ዉስጥ የታወቁት ገፅጻዎች - መዘመር፣ መጮኽ፣ መደነስ፣ መደስት፣ መዉደድ/ማጌጥ ናቸው ፡፡ እነዚህ እግዚአብሄርን የማመስገኛ መንገዶችን ለመግለፅ ሰባት የዕብራዊ ቃልን ይከተላሉ፡፡

የሚከተሉት ማስረጃዎች የተቀደሰ/ቅዱስ ጩኸት ተብሎ ከተሰየመዉ በክሪስ ቶምሊን እና በዳረን ዋይትሄድ ከተፃፈው መፅሀፍ የተወሰደ ነው፡

ያዳህ፡ በመዝ (67፡ 3) ላይ ይገኛል ፤ “ ያዳህ “ የሚለዉ ቃል በተዘረጉ እጆች ማምለክ ወይም ማመስገን ማለት ነው ፤ የምስጋና እጆችም ተብለዉ ይጠራሉ ፡፡ በዕብራዊ እጅን በመዘርጋት ብቻ አይደለም ድንጋይን በመወርወር ወይም ቀስትን በማስፈንጠርም ጭምር እንጂ ፡፡ ይህ ቃል በመፅሀፍ ላይ የዕብራዊያን ሰዎች በእግዚአብሄር ክብር ተሸንፈዉ/ቁጥጥር ስር በነበሩ ጊዜ እጆቻቸዉን የማንሳታቸዉን ክስተት ለመግለፅ 111 ጊዜ የሚገኝ ነው ፡፡

ሀላል፡ ምናልባትም ይህ ቃል የሞኝ ምስጋና ተብሎ በመጠራት በጣም የተለመደ ነው ፤ ይህ ማለት በመጎራት፣ በማክበር፣ በመታዬት፣ ትኩረትን በመሳብ ሞኝ በመሆን ማለት ነው ፡፡ መዝ (149፡ 3) “ ስሙን በዘፈን እንዲያመሰግኑ እንፍቀድላቸዉ “ የሚለዉን ቃል ተጠቅሟል ፤ ይህ “ ሀሌሉያ “ የሚለዉን ቃል የምናገኝበት ነው ፡፡ የኪዳኑ ታቦት ወደ ከተማዉ በመጣ ጊዜ የዳዊት ዳንስ የዚህ ቃል ማሳያ ነው (2ሳሙ 6፡ 13-16) ፡፡ እዉነተኛ ሀላል ስሜትን ከማፈንና የራስ አስተሳሰብን በመተዉ ላይ የተደገፈ ነው ፡፡ መዝ (150፡ 6)(የመዝሙር የመጨረሻዉ ጥቅስ) “ እስትንፋስ ያለዉ ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግን “ ይላል ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ይህ ቃል 165 ጊዜ ጥቅም ላይ ዉሏል ፡፡

ዛማር፡ ይህ ቃል የምስጋና ሙዚቃ ማለት ነው ፡፡ በመሰረቱ ሙዚቃ ለመስራት፣ በመዝሙር እና በሙዚቃ ለማክበር በግልፅ የመሳሪያዉን ክሮች ወይም አካላት በመንካት መሳሪያዎችን እንጠቀማለን ፡፡ መዝ (144፡ 9) “ አቤቱ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ ፤ አስር አዉታር ባለዉ በገና እዘምራለሁ “ ይህን ቃል ተጠቅሟል ፤ ይህ ቃል በመፅሀፍ ላይ 41 ጊዜ ጥቅም ላይ ዉሏል ፡፡ ባትጫወቱም እንኳን እግዚአብሄርን ወደ ምታደቁበትና ምታመሰግኑበት ስፍራ ለመወሰድ ሙዚቃ እየተጠቀማችሁ ነው ፤ ይህ ወደ እግዚአብሄር ዙፋን ክፍል ዉስጥምስጋናችሁን ለመሸከም/ለማድረስ ሙዚያ የሚያደርሰ ተሸከርካሪ እንዲሆን የሚፈቅድ ነው ፡፡

ቶውዳህ፡ ይህ ቃል የምስጋና ተስፋ ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ሚያደርግልን ነገር ተስፋ በማድረግ ማመስገን የምንችልበት ወይም በአሁኑ ስዓት ስለማላየዉ በህይወቴ ስላደረገዉ ተስፋ ነገር ግን በተስፋ በመሆን አመሰግነዋለሁ ፤ ይህን በመዝ (56፡ 11-12) ላይ እናየዋለን ፡፡ በተጨማሪም ይህ ቃል በምስጋናና በንስሀ እጆችን መዘርጋትም ነው፣ ነገር ግን ይህ እስካሁን ስላልተቀበላችሁት ነገር ነው ፡፡ ይህ በመፅሀፍ ዉስጥ 32 ጊዜ ጥቅም ላይ ዉሏል ፡፡ ሮሜ (4፡ 20) አብርሃም በሳራ ስለሚወለድለት ልጅ ተስፋ ለእግዚአብሄር “ ክብር ሰጠ “ ይላል ፡፡

ባራክ፡ ይህ ቃል የምስጋናን አቋም ያሳያል ፡፡ ይህ ቃል በመዝሙር ዉስጥ 289 ጊዜ ጥቅም ላይ ዉሏል ፡፡ ይህ ቃል በማድነቅር ድርጊት፣ በማክበር ድርጊት፣ ሰላምታ በመስጠት ድርጊት እና በማመስገን ድርጊት ለእግዚአብሄር መበርከክ ወይም ማክበር ማለት ነው ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት የመንበርከክ ሀሳብን ይሰጣል ፡፡ መዝ (72፡ 11) እና 15 ነገስታትና አሕዛቦች በእግዚአብሄር ፊት በመስገድ ተንበርክከዉ ያገለግሉታል ይላል ፤ በትህትና በጉልበቶቻችን ወደ ታች ከፊታችን ጋር በእግዚአብሄር ፊት መሬት ላይ እንበረከካለን ፡፡ በዚህ በትህትና ስፍራ እያለን በክብር ንጉሱ በእግዚአብሄር ላይ አይናችንን እናደርጋለን ፡፡ ስለ ትህትና እግዚአብሄር የሚከብርበት ነገር አለ ፤ በመዝሙር 103 ዳዊት ለማመስገን ይህን ቃል በተደጋጋሚ ተጠቅሞበታል ፡፡

ቴሂላህ፡ ይህ ቃል የመዝሙር ምስጋና ማለት ነው ፡፡ በቀላሉ ከልባችን የሚፈስስ መዝሙር ማለት ነው - ይህ በልቤ ከሚጥም ዜማ የሚዘመርና ቃል የሚጨመርበት ነው ፡፡ ይህ በተለምዶ ዝግጅት ያልተደረገበትና ያልታሰበ ነዉ ፡፡ ቴሂላህ ሁሉም መዝሙር የሆነና መጀመሪያ ለእግዚአብሄር መዘመር ከሚለዉ ቃል የሚመጣ ነው ፡፡

ሻባች፡ ይህ ቃል የምስጋና ጩኸት ማለት ነው ፡፡ ይህ ቃል በቃል/በግልፅ ወደ ለእግዚአብሄር ከፍ ባለ ድምፅ መጮኽ ማለት ነው ፤ 11 ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ቃል በቃል የተቀደሰ ጩኸት ማድረግ ማለት ነው ፡፡

መደምደሚያ

ዳዊት እንደ እግዚአብሄር የልብ ሰዉ እነዚህን ነገሮች ያውቃቸዋል ፡፡ የምስጋና ገለፃዎች ነበሩት ፤ በመዝሙር 66 እና 67 ዉስጥ ዳዊት እግዚአብሄርን ለማመስገን እነዚህን ቃላቶች ተጠቅሟል ፡፡ ከእነዚህ ምስጋና ከመግለጫዎች ቃላቶች በጥቂቶቹ ዉስጥ ተጭናችሁ እንድትገቡ፣ ከእግዚአብሄር ጋር በጥልቀት በመግባት የሚገባዉን ክብርና ምስጋና እንድትሰጡ አበረታታችኋለሁ ፡፡

  1. Chris Tomlin and Darren Whitehead, Holy Roar: 7 Words That Will Change The Way You Worship (Nashville: Thomas Nelson, 2017), n.p.

ጥያቄዎች

  1. መዝሙር 66 “ ለእግዚአብሄር በደስታ በመጮኽ “ ይጀምራል ፤ እንዲህ አይነት ጩኸት እንድናደርግ ሌላ የት ላይ መፅሀፍት ይነግረናል (መዝ 98፡ 4, 100፡ 1) ? በራሳችሁ ቃል በህይወታችሁ ይህ ምን ይመስላል ?
  2. በመዝ (66፡ 18) መፅሀፍ “ በልቤ ኃጢዓት ቢገኝ እግዚአብሄር አይሰማኝም “ ይላል ፤ ከዚህ ጥቅስ ጋር ትስማማላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አትስማሙም ? ከጌታ ጋር ጥቂት ደቂቃ በማሳለፍ በልባችሁ ማንኛዉንም ኃጢዓት ፈልጉ ፤ የሆነ ነገር ወደ አይምሯችሁ ከመጣ ንስሀ ግቡ ፡፡
  3. “ አሕዛቦች ያመስግኑህ “ የሚለዉ በመዝሙር 67 ዉስጥ ብዙ ጊዜ የተነገረ ነው ፤ ለፀሀፊዉ ይህን ሀረግ መደጋገሙ ለምን አስፈላጊ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? እግዚአብሄርን ታመሰግናላችሁ ? አዎ ከሆነ እንዴት ?
  4. በመዝሙር (66-67) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 66:16–17

“Come and listen, all who fear God, and I will tell what He has done for me. I cried out to Him with my mouth, and praise was on my tongue.”

በህይወትህ ዛሬ እግዚአብሔር በስራ ላይ መሆኑን አይተኸዋልን ? እግዚአብሔርን አመስግን ! አስቸጋሪ ቀን ገጥሞኻል እናም እየታገልክ ነው ? እግዚአብሔርን አመስግን ! ምስጋናውንም ዘወትር በአፍህ አኑር ፡፡ በውጊያ እንደ መሳሪያ አድርገህ እግዚአብሔርን አመስግን ! የሰጠውን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ ፣ እግዚአብሔርን አመስግን ፡፡

ዛሬ በተለያዩ መግለጫ መንገዶች እግዚአብሔርን ለማመስገን ጊዜን ውሰድ ፡- እጆችህን በማንሳት ፣ በመንበርከክ ፣ በመንቀሳቀስ ፣ በመጮህ ወይም አዲስ ዝማሬ በመዘመር ! ከልብህ ምስጋና ይፍለቅ ! እግዚአብሔርን ፍራ ደግሞም ፍቅሩን በህይወትህ አጣጥም ፡፡ አለም ሁሉ ታላቁንና ሃይለኛውን የደህንነትህን ጌታ ያውቅ ዘንድ ሁሉም ሰዎች ሁሉም ህዝቦች እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ አስችል !

“ እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ ። በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፥ በአንደበቴም አመሰገንሁት ። “

  • መዝሙር 66፡16-17

ተጨማሪ ጥቅስ

2ኛ ሳሙኤል 6:14–15 — “ዳዊትም በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይዘፍን ነበር፤ ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ለብሶ ነበር ። ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ ሆ እያሉ ቀንደ መለከትም እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡ ። “

መዝሙር 67:3–4 — “አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ ። ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ ። “

ዳንኤል 2:19–20 — “ የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት፤ ዳንኤልም የሰማይን አምላክ አመሰገነ ። ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ ፡፡ “