Knowing God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 63-65 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 63 በይሁዳ ምድረበዳ በነበረ ጊዜ የፃፈዉ የዳዊት አንድ መዝሙር ነው ፤ ከ 1 እና 2 ሳሙኤል የዳዊትን ታሪክ ስታስታዉሱ ብዙ ጊዜ ዳዊት በይሁዳ ምድረበዳ እንደ ነበር ታውቃላችሁ ፡፡ አብዛኞቹ ምሁራን ይህ መዝሙር ዳዊት እየሸሸ በነበረበት ጊዜ እንደተፃፈ ሲስማሙ ከዳዊት ከሁለቱ መሸሸ መከሰት የትኛዉ ክስተት ላይ ይህ መዝሙር ተፅፎ እንደ ነበር አይስማሙም ፡፡ አንዳንዶች ይህ መዝሙር ዳዊት ከሳዖል በሸሸ ጊዜ የተፃፈ እንደ ነበር ይከራከራሉ (1ሳሙኤል 23) ፤ ሌሎች ደግሞ ዳዊት ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ ተፅፎ እንደ ነበር ይከራከራሉ (2ሳሙኤል 15) ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (63፡ 1-2)፡ ዳዊት “ ደረቅ በሆነ ምድር “ እና “ ዉሃ በሌለበት “ ላይ ራሱን አገኘዉ (ቁጥር 1) ፤ ነገር ግን የዳዊት ምላሽ ሌሎች ሰዎች ከሚመልሱበት መንገድ የተለዬ ነበር ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን በግል ያውቀዋል ፤ ይህንን መዝሙር “ አምላኬ ነህ “ በማለት ጀመረ ፡፡ ዳዊት እረኛ በነበረበት ጊዜ በሁሉም ቀድሞ መንገዶ እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር እንደሚገናኝ ተምሯል ፡፡ በጎልያድ ፊት ሲፋለም ዳዊት ሳዖልን “ እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳና ድብ ይመጣ ነበር ከመንጋዉም ጠቦት ይወስድ ነበር ፡፡ በኋላውም እከተለዉና እመታው ነበር ከአፉም አስጥለዉ ነበር በተነሳብኝም ጊዜ ጉሮሮዉን ይዤ እመታዉና እገድለዉ ነበር ፡፡ እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ መታሁ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያዉን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል “ አለው (1ሳሙ 17፡ 34-36) ፡፡
ዳዊት ከእግዚአብሄር ጋር ያለዉን ግንኙነት በመናገር ጀመረ ከዚያም እግዚአብሄር የመፈለግ ፍላጎቱንም ተናገረ ፡፡ አዲሱ ኪንግ ጀምስ እትም የቁጥር 1 ክፍል “ በማለዳ አንተን እፈልጋለሁ “ በማለት ይተረጉመዋል ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ለመምሰል ራሱን አስተማረ ፤ 1ቆሮ ( 9፡ 24-27) “ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋዉን እንዲቀበል አታዉቁምን ? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ ፡፡ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰዉነቱን ይገዛል ፤ እነዚያም የሚጠፋዉን አክሊል ሊያገኙ ነው እኛ ግን የማይጠፋዉን ፡፡ ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም ፤ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ስጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ “ ይላል ፡፡
ዳዊት እግዚአብሄርን ለማግኘት ራሱን ባስተካከለ ጊዜ ለእግዚአብሄር የተሰጠ ሆነ ፡፡ የዳዊት ነፍስ እግዚአብሄርን ናፈቀችም ጓጓችም ፤ መሰጠቱ ፍላጎት በመሆኑ “ ስጋዬ አንተንናፈቀች “ (ቁጥር 2) ፡፡
መዝሙር (63፡ 3-5)፡ የእግዚአብሄር መገኘት ዳዊትን ቀየረው ፤ ዳዊት በእግዚአብሄር መገኘት ፍቅርን በመማር ተቀየረ ፡፡ የዳዊት ፍቅር ለእግዚአብሄር ያለዉ እግዚአብሄርን ወደ ማምለክ ቀየረው ፤ የዳዊት አምልኮ ወደ እግዚአብሄር ደስታ/እርካታ ተቀየረ ፡፡ በብዙ የእግዚአብሄርን ቸርነት ዳዊት በመረዳቱ በቀላሉ በእርሱ መገኘት ብቻ በብዙ የተደሰተ ነበር ፡፡ ዳዊት ይህን በፃፈ ጊዜ ከሁሉም ከቤተ መንግስት ምቸቶች በመራቅ በበርሀ ላይ እየሸሸ/እየሮጠ ነበር፣ ይሁን እንጂ በእግዚአብሄር መገኘት ዉስ በእግዚአብሄር ቸርነት የተደሰተ/የረካ ነበር ፡፡
መዝሙር (63፡ 6-8)፡ ዳዊት በእግዚአብሄር ቸርነትና በተስፋዉ ላይ በደንብ አሰበ ፤ ይህ የአሳቢነት ባህሪይ ነበር ፡፡ ዳዊት ወደ መኝታዉ ከመሄዱ በፊት አዕምሮዉን በእግዚአብሄር ቸርነትና ተስፋ ላይ ያስቀምጣል ፡፡ ዳዊት በእግዚአብሄር ላይ እንደ ተነጠላጠለ ከእግዚአብሄር ጋር ባለዉ ግንኙነት መጠጊያን አገኘ ፤ የዳዊት እምነት በራሱ እጆች ላይ አልነበረም ፤ የዳዊት እምነት ራሱን ለማቆም/ለማፅናት በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ ነበር ፡፡ በአስቸጋሪ ወቅት መካከል ላይ ዳዊት እግዚአብሄር እንደሚያፀናዉና እንደማይተወዉ ያምናል ፡፡
መዝሙር (63፡ 9-11)፡ ዳዊት በእግዚአብሄር አዳኝነት/ታዳጊነት ሙሉ እምነት ነበረው ፡፡ ዳዊት ስለ ራሱ ይህን በቀለ አላደረገም ፤ በራሱ በሳዖል ላይ በቀልን ባላደረገበት ተመሳሳይ መንገድ ስለ እርሱ ይህን እንደሚያደርግለት እግዚአብሄርን ታመነ ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር ህዝቡን ለመምራትና የሚያስደንቁ ነገሮችን ለማድረግ ዳዊትን ተጠቀመ ነገር ግን ያ በዳዊት እግዚአብሄርን በመፈለግ ባህሪዉ እና ራሱን የእግዚአብሄርን ተስፋ በማስታወሱ ዉስጥ ነበር ፡፡ ራሳችንን ስናስተካክል ፍላጎታችን ይቀየራል ፤ ፍላጎታችን ሲቀየር በመለወጥ እግዚአብሄርን እናመልካለን ፤ እግዚአብሄርን ስናመልክ በእርሱ ደስታን/እርካታን እናገኛለን ፡፡
2 The Holy Bible, King James Version. New York: American Bible Society: 1999; Bartleby.com, 2000.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson, 2005), p. 640.
ጥያቄዎች
-
የትኛዉ የአዲስ ኪዳን ፅሁፍ ስለ መጠማትና ዉሃ ያመለክታል (ማቴ 5፡ 6, ዮሐ 4፡ 10-14, 7፡ 37) ? በመዝ (63፡ 1) የትኛዉ ቃል ይህን የተለመደ መጠማት እንዳልሆነ ያመለክታል ? እንዲህ አይነት የቅንነት እግዚአብሄር መጓጓት ቀምሳችሁ ታዉቃላችሁ ?
-
በመዝ (63፡ 3) “ ምህረትህ ከህይወት ይሻላልና “ ስለ ማለቱ ምን ታስባላችሁ ? ከህይወታችሁ እንደ ተሻለ የምትገልፁት ነገር በህይወታችሁ አለ ?
-
የመዝሙር 65 አብዛኛዉ እግዚአብሄርን የሚገልፅ ነው ፤ ቁጥር 7 አንብቡ ፡፡ የትኛዉ የኢየሱስ ታሪክ ይህን ጥቅስ ወደ አይምሯችሁ ያመጣል (ማር 4፡ 39) ? በምዕራፍ 65 ሌላ ስለ መሲሁ የሚያመለክት ነገር አለ ?
-
መዝሙር (63-65) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 65:1–2, 5
“I will follow close to You; Your right hand holds on to me.”
ከኢየሱስ ጋር መጓዝ ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ ነው ፡፡ ተጠምተህ ከሆነ ፣ ጌታ ያረካሃል ፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ ሆነህ በእግዚአብሔር ላይ ስታተኩር ፣ ሃይሉንና ክብሩን ታያለህ ፡፡ የሚያስፈልግህን ነገር ለእግዚአብሔር ስታሳስበው ፣ እርሱ ረዳትህ ይሆናል ፡፡ በክንፎቹ ጥላ ስር ሲሸሽግህ ፣ በእርሱ ደስ ይበልህ ፡፡ እግዚአብሔርን በቅርበት ተከተል ፣ እርሱም እጅህን ይይዝሃል ፡፡
ከእርሱ ጋር ፈልገህ ጊዜን ስታሳልፍ ፣ ህይወትህ ይለወጣል ፡፡ በእርሱ ኑር እርሱም በአንተ ይኖራል ፡፡ እግዚአብሔርን ፈልግ ፣ በፍጹም ልብህም ስትፈልገው ታገኘዋለህ ፡፡ ቃሉን ብቻ አትወቅ የቃሉንም አምላክ እወቅ ፡፡ ዛሬ የደህንነትህን አምላክ ለማወቅ እሻ ፡፡
“ ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ ። “
- መዝሙር 63:8
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 63:1–2 — “ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ ። ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ ። “
ኤርምያስ 29:13 — “ እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ ። “
ያዕቆብ 4:8 — “ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።