Wisdom Books Psalms

Trust in God Alone

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 60-62 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 418 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ክፍል 54 መዝሙር 60, 61 እና 62 ይሸፍናል ፡፡ በእነዚህ ምዕራፎች በእያንዳንዳቸዉ ዉስጥ ስንሄድዝግ በማለት እግዚአብሄር ይናገረን - በእግዚአብሄር ላይ በታላቅ ስሜት እንድናድግ ፡፡ ዛሬ ማንኛዉም የገጠመንን ፈተና ዉስጥ መዝሙር 62 እንዴት ሊሸከመን እንደሚችል እናወራለን ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (62፡ 1-2)፡ “ በእግዚአብሄር ብቻ ላይ አርፋለሁ “ የሚለዉ ሀረግ በዝምታ እግዚአብሄርን መጠበቅ ማለት ነው ፡፡ ምንም ይግጠመን እግዚአብሄር በዚያ ዉስጥ እንዳለ እባ በቁጥጥሩ ስርም እንደሆነ ልበ ሙሉ ዎች መሆን እንችላለን ፡፡ በእግዚአብሄር ላይ በመደገፍ እረፍትን ማግኘት እንችላለን ፤ ስለዚህም በእግዚአብሄር የምንታመንበትና የምናርፍበት ስፍራን እንዴት ማግኘት በሚቻልበት ሂደት ዉስጥ እንሂድ ፡፡ ዳዊት መዝሙር 62 ለመዘምራን አለቃዉ ለኤዶታም ፃፈው ፤ በብዙ በሚመስል መልኩ ኤዶታም የመዘምራን አለቃ እንዲሆን የተሰየመ ነበር ፡፡ እንደ ኮንስታብል አገላለፅ ጭብጡ “ ነፍሴ በእግዚአብሄር ረፍትን አገኘች “ የሚል ነው ፡፡ በ 1ዜና (9፡ 16) አብድያ የኤዶታም እንደ የልጅ ልጅ የተዘረዘረ ነው ፡፡ በ 1ዜና (16፡ 37-42) ዳዊት አሳፍንና ዘመዶቹን በኪዳኑ ታቦት ፊት ተዋቸው ፤ ከእነርሱም መካከል በእግዚአብሄር ፊት ኤማንን እና ኤዶታም የሙዚቃ መሳሪያ ይጫወቱ ነበር ፡፡ በግልፅ ኤዶታም የመዘምራን አለቃ ነበር፣ መሳሪያም ይጫወት ነበር ወንዶች ልጆቹም በጣም ይሳተፉ ነበር ፡፡ 1ዜና (25፡ 1-3) የኤዶታምን ትልቅ የመሳሪያ መጫዎት ታሪክን ይገልፃል ፤ ኤዶታም አስደናቂ የአምልኮ መሪ፣ አስደናቂ የእግዚአብሄር ሰዉ እና እነዚህን ባህሪያቶች ወደ ልጆቹ አስተላልፎ የነበረ አስደናቂ ነቢይ ነበር ፡፡

አንዳንዶች ዳዊት ይህን መዝሙር የፃፈው ልጁ አቤሴሎም በኬብሮን በይሁዳ ላይ እየገዛ በነበረበት ጊዜ ነዉ ይላሉ ፤ ሌሎች ደግሞ ከሌላ ሰዉ ክህደት በተሰማዉ ጊዜ ፅፎታል ይላሉ ፡፡ ቁም ነገሩ በዚህ ሁሉ ተቃርኖ መካከል ላይ ዳዊት ድል እየመጣ እንደ ነበር የተደላደለ በራስ መታማመን እንደ ነበረዉ ነው ፤ ዳዊት “ በፍፁም አልናወጥም “ አለ (ቁጥር 2, 6) ፡፡

መዝሙር (62፡ 3-4)፡ በቁጥር 3 የዳዊት ጥያቄ የማይቀረዉን ዉድቀት የሚገልፁ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው ፡፡ የዳዊት ተጋጣሚዎች ከትልቅ ስፍራዉ ወደ ታች ሊያወርዱት አቀዱ በዉሸትም ክብርን ወሰዱ (ቁጥር 4) ፡፡ “ በአፋቸዉ ይባርካሉ ነገር ግን በልባቸዉ ይራገማሉ “ የሚለዉ ቋንቋ በዉጪ መልካም የሚመስሉ ነገር ግን በዉስጣቸዉ ከሀዲዎች የነበሩትን ኃይማኖተኛ ሰዎች ወደ ሀሳባችን ያመጣቸዋል ፤ ይህ የክህደት አስተሳሰብ አኪጦፌል ለዳዊት አንድ ነገር ባለ እና ለአቤሴሎም ደግሞ ሌላ ነገር በአለዉ ጊዜ የታዬ ነበር (2ሳሙኤል 15) ፡፡ እንዲሁም ይሁዳ ከወታደሮቹ ጋር በመምጣት ኢየሱስን እንዲያስሩት ባመቻቸና ኢየሱስን አንድ ነገር በአለዉ ጊዜም ታይቷል ፡፡

መዝሙር (62፡ 5-6)፡ እንደ ገና ዳዊት በእግዚአብሄር ላይ ብቻ መደገፍ/ማረፍ መፈለጉን፣ በእግዚአብሄር በዝምታና በልበ ሙሉነት እንደሚጠብቅ ገለፀ (የቁጥር 1 ድጋሜ) ፤ ከዚያም በቁጥር 6 ዳዊት እግዚአብሄር አለቱ፣ መድኃኒቱ እና መጠጊያዉ እንደ ነበር ቁጥር 2 ደገመው ፤ አይናወጥም ፡፡

መዝሙር (62፡ 7-8)፡ ዳዊት መፅናናቱ በእግዚአብሄር እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 7) ፡፡ በሁሉም ጊዜ ላይ እግዚአብሄርን በመታመን በእርሱ ፊት ልባቸዉን እንዲያፈሱ ሰዎችን ተጣራ (ቁጥር 8) ፤ በሌላ ቋንቋ …..መፀለይ፣ መፀለይ፣ መፀለይ፣ መፀለይ ፡፡

መዝሙር (62፡ 9-12)፡ “ የሰዉ ልጅ ከንቱ ነው ፤ ከፍ ያለዉ የሰዉ ልጅም ሐሰተኛ ነው “ (ቁጥር 9) ፤ ይህ ከጥቂት ቀናት በፊት ስናወራበት የነበርነዉን ባለፀጋ ሰዉ ያስታዉሰናል ፡፡ ታላቅ አክብሮት ላለን እነዚህ ሰዎች - ደህና የሚመጡና የሚሄዱት ፤ “ ከእንፋሎት ያነሱ ናቸው “ (ቁጥር 9) ፡፡

በእግዚአብሄር ብቻ ላይ እንዴት ታርፋላችሁ ? ዕብ (4፡ 11) “ እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ “ ይላል ፤ እንዴት ወደዚያ እረፍት መግባት እንችላለን ? እግዚአብሄርን ለመስማትና አሁንም በእርሱ ለመሆን ጥረት ማድረግ አለብን ፤ በራሳችን ድርሻ ላይ የትጋት ጥረት ይወስዳል ፡፡ ከእኛ ዉስጥ ለብዙዎቻችን ይህ በመቀመጥ ለማረፍ በጣም አስቸጋሪ ነው ፡፡

ዮሐንስ ፒፐር ይህ እንዴት እንዲደረግ የሚያስደንቅ ስራዎች ያደርጋል፡

  1. ስለ ሰማችሁት ነገር የቀረበ ትኩረት መስጠት ይህ ከሆነ ርቃችሁ አትሳቡም (ዕብ 2፡ 1) ፡፡
  2. ታላቅ ድነታችሁን አለመግፋት/አለመተዉ (ዕብ 2፡ 3) ፡፡
  3. ኢየሱስን መመለከት (ዕብ 3፡ 1) ፤ ረፍት ባገኛችሁ ጊዜ ብቸኛዉ ትኩረታችሁ ድነታችሁ መሆን አለበት - በራሱ በኢየሱስ ላይ ፡፡
  4. ልባችሁን አታደንድኑ (ዕብ 3፡ 8) ፤ ክርስቲያኖች እንዴት ልባቸዉን ያደነድናሉ ? ለአለም፣ ለስጋ እና ለሰይጣን በመፍቀድ የጠፋ በመሆን በኢየሱስ ላይ ትኩረትን በማጣት ፡፡
  5. ከማያምን ልብ ከክፉ መጠንቀቅ (ዕብ 3፡ 14) ፤ ትኩረት በማትሰጡ ጊዜ ቀስ በቀስ የደነደናችሁ ትሆናላችሁ ፤ የደነደነዉ ልባችሁም ስለ እግዚአብሄር ነገርም የማታምኑ/የምትጠራጠሩ ትሆናላችሁ ፤ አማኞችም እንኳን እግዚአብሄር አስደናቂ ነገር ማድረግ እንደሚችል መጠራጠር ይጀምራሉ ፡፡
  6. በኃጢዓት ሀሰተኝነቱ ላይ አንዱ ሌላዉን ማደፋፈር (ዕብ 3፡ 14) ፤ በእግዚአብሄር ላይ መፅናት እርስ በእርስ እንድንበረታታ ይፈቅዳል ፡፡
  7. ተስፋ ከተገባላችሁ እረፍት የሚያርቃችሁን አለማመን መፍራት (ዕብ 4፡ 1) ፤ እግዚአብሄር ዘላለማዊ እረፍት ሰጥቶናል ፡፡ በኢየሱስ ላይ ስታተኩሩ ይህን እረፍት ታገኙታላችሁ ?

ዳዊት ይህን መዝሙር በፃፈ ጊዜ ኤዶታምን “ እረፍቴን በእርሱ አገኛለሁ ፤ በእርሱ እረፍቴን ሳገኝ ሌላ የሚየያስቸግረኝ የለም “ ብሎ እንዲዘምር አበረታተው ፡፡

መደምደሚያ

ስለዚህ ቃል እግዚአብሄር ሆይ እናመሰግናለን እንዲሁም በዝምታህ እንድናገኝህና እንድንጠብቅህ ዳዊት እኛን ስለበረታታን እናመሰግንኀለን ፤ በአንተ እንድንታመን ከእነዚህ ሁኔታዎች እንደምታድነን ታውቃለህ ፡፡ ድል እየመጣ እንደሆነ ሙሉ በራስ መተማመን እንዲኖረን ስለፈቀድክልን አመሰግንሀለሁ ፡፡ በዚህ ምድር ላይ እንግኘዉም አናግኘዉም የመጨረሻዉ እረፍት በአንተ በኩል እንደሚመጣ እናዉቃለን ፤ በዘላለም ዉስጥ እንደምናገኘዉ እናዉቃለን ፡፡ በዚያ ምክንያት ብቻ ጌታ ሆይ በአንተ ሙሉ መተማመን ይኖረናል ፤ በፍፁም አንናወጥም ምክንያቱም ተስፋችን ከአንተ ስለሚመጣ ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 248; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 640.

  3. MacArthur, p. 640.

    John Piper, “Be Diligent to Enter God’s Rest”; available at https://www.desiringgod.org/messages/be-diligent-to-enter-gods-rest.

ጥያቄዎች

  1. በመዝ (60፡ 1) እና 10 ዳዊት “ እግዚአብሄር ጣለን “ ብሎ ተናገረ ፤ “ እኛ “ ማነን ? በቁጥር 11-12 ዳዊት ነፃ እንደሚወጡ እንዴት ተናገረ ? በአሁኑ ጊዜ ጠላቶቻችንን ወደ ታች ማን ይረገጣቸዋል ?
  2. በመዝ (62፡ 2) እና 6 ዳዊት “ አለቴና መድሀኒቴ ነዉ “ አለ ፤ “ አለት “ የሚለዉ ቃል ለመሲሁ ቀጥተኛ ባልሆነ ማጣቀሻነት መጠቀም ይቻላል ? “ አለት “ የሚለዉን ቃል ከመሲሁ ጋር እንዴት እናገናኘዋለን ? እግዚአብሄርን አለቴ ብሎ በመጥራት ዳዊት ምን አመለከተ ?
  3. በመዝ (62፡ 10) መሰረት ዳዊት በምን አትመኑ አለ ?
  4. የመዝ (62፡ 12) መጨረሻ ምን ማለት እንደሆነ የምታስቡት ግለፁ ፤ ቁጥር 10-12 የራሱን አገላለፅ ለመጠበቅ አንብቡ ፡፡
  5. “ በክንፎቹ ጥላ ስር አድራለሁ “ ማለት ምን ማለት ነው ? “ በቤተክርስቲያን “ ዉስጥ ላልሆኑት ይህን እንዴት ታብራሩታላችሁ ?
  6. በመዝሙር (60-62) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 62:5–8

“Rest in God alone, my soul, for my hope comes from Him. He alone is my rock my salvation, my stronghold; I will not be shaken. My salvation and glory depend on God, my strong rock. My refuge is in God. Trust in Him at times, you people; pour out your hearts before Him. God is our refuge. Selah”

በህይወትህ የህመም ፣ የውድቀት ፣ የኃጢአት ውጤት እንድሁም የፍርሃት አጋጣሚዎች ይገጥሙሃል ፡፡ በቃ ሮጠህ ለመደበቅ የምትፈልግባቸው ጊዜያት ይኖራሉ ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር በህይወትህ ከባዶቹን ጊዜያት ከመከልከል ያለፈ ለአንተ ብዙ አለው ፡፡ መንቃትና እውነታውን መጋፈጥ አለብህ ፡፡ ፈተናውን መጋፈጥ አለብህ ፡፡ ውጤቱን መቀበል አለብህ ፡፡ ፍርሃትህን መጋፈጥ አለብህ ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ይህን ማድረግ ትችላለህ ፡፡

በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ማረፍ ማለት በእርሱ ላይ የማያዋላውል እምነት ማሳደር ማለት ነው ፡፡ በልብህ እመን ደግሞም ምንም ቢፈጠር እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደሆነና እንደሚጠብቅህ በማወቅ በእምነት ኑር ፡፡ ያ በቂ ነው ፡፡ በሁሉም ነገር ኢየሱስን አስብ ፡፡ እርሱ ከበቂ በላይ ነው አንተን ከመርዳትም በላይ ይችላል ፡፡ ሁልጊዜም በእግዚአብሔር ላይ ታመን ፡፡ እናም በቃ እርሱን አውራው ፡- ጸልይ ጸልይ ጸልይ ከዚያም አብዝተህ ጸልይ ፡፡ እግዚአብሔር ፈጽሞ የህዝቡን ልብ ከማድመጥ አይዝልም ፡፡ አሳብህን በእግዚአብሔር ላይ ፣ በአለትህ ፣ በደህንነትህ ፣ በጋሻህና በመሸሸጊያህ ላይ ስታደርግ አትናወጥም ፡፡ መልካም ይሆናል ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ታመን ፡፡

“ ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና ። እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም ። መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው ። የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው ። “

  • መዝሙር 62፡5-8

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 118:6–8 — “ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል ? እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ እኔም በጠላቶቼ ላይ አያለሁ ። በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል ። “

ኢሳይያስ 43:1–2 — “ አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም ። “

ዮሐንስ 14:1 — “ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ ። “