Wisdom Books Psalms

Mercy, Trust, and Praise

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 57-59 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 417 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙሩ ከዳዊት ህይወት ታሪኮችን ሳይሆን እዉነተኛ ነገሮችን ይገልፃል ፡፡ መዝሙር 57 ከምዕራፍ 58, 59 እና 75 ጋር (በአሳፍ) አብሮ “ አታጥፋ “ ከሚለዉ ድምፅ ጋር የተያያዘ ከአራቱ አንዱ ነበር ፡፡ በመዝሙር 57 ዳዊት እየሸሸና ተስፋ በመቁረጥ ላይ ነበር ፡፡ ፊሊፕ ያንስ “ ዳዊት መዝሙሩን ለራሱ እንደ ማገገሚያ ፃፈዉም ዘመረዉም ፤ በጥቂቱም ቢሆን ራሱን ከፍራቱ በላይ ራሱን ከፍ ማድረግ እንደሚችልና በቁጥጥር ስር ያደረገዉን እግዚአብሄርን ለማየት እየነገረዉ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ በዚህ ሁሉ ኢየሱስን እንደ ክብር ንጉስ እናየዋለን ፡፡

ለዚህ መዝሙር መነሻ በ 1ሳሙኤል (20-24) የተመዘገበ ነው ፤ ዳዊት ከየት እንደ መጣና በእነዚህ መዝሙሮች እንዴት እንዳበቃ ማመለከቱን በመወያየት እንመለከታለን ፡፡

  • ዮናታን ታማኝነቱን ለዳዊት አሳዬ ፤ ዳዊት ከሳዖል እንደሚያመልጥ እንደ ምልክት ቀስትን ወረወረ ፡፡
  • ዳዊት ከካህኑ አቢሜሌክ ጋር የተቀደሰ እንጀራ ወደ በላበትና የጎልያድን ሰይፍ ወዳገኘበት ወደ ኖብ ሄደ ፡፡
  • በኖብ ኤዶማዊዉ ዶይቅ (የሳዖል የእረኞች አለቃ ) የዳዊትን ድርጊት በማየት ለሳዖል አቀረበ/ሪፖርት አደረገ ፤ ሳዖል በብስጭት አቢሜሌክን፣ 85 ካህናትን እና የኖብ ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችን፣ በሬዎችን፣ አህዮችንና በጎችን በመግደል ምላሽ ሰጠ ፡፡ ሳዖል የእግዚአብሄር ምርጫ ነበር ነገር ግን ማሰብ ከሚችለዉ በላይ ወዳደረጋቸዉ ነገሮች ድረስ ልብ የጠነከረ ነበር ፡፡ እኔና እናንተ ልባችንን ማጠንከር የሚችሉ በየቀኑ የምናደርጋቸዉ ምርጫዎች አሉ ፡፡ የክብር ንጉሱ ሁልጊዜ መልሶ ሊታደገን የሚታገስ ነው ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ሳዖል ወደ ዚያ ስፍራ በፍፁም አልመጣም ፡፡
  • ዳዊት ወደ ጌት ሸሸ (ወደ ፍልስጤም) ፤ ወደ ንጉስ አንኩስ በመሄድ ራሱን ለማዳን እብድ እንደሆነ አስመሰለ ፡፡
  • ዳዊት ወደ መጀመሪያዉ ዋሻ ከ400 ሰዎቹ ጋር በአዶላ ዋሻ በመሆን አመለጠ ፡፡
  • በዚህ ጊዜ ሳዖል ዳዊትን መከታተሉን ቀጠለ ፤ ከዳዊት ከተራራዉ በሌላኝዉ ወገን ላይ ሳዖል ቀርቦ ነበር ፤ ፍልስጤማዊያን ስላጠቁትም ሳዖል ሄደ ፡፡
  • ከዚያም ዳዊት በሁለተኛ ዋሻ በምድረበዳ በዓይንጋዲ ተደበቀ ፡፡
  • እንደ ገና ሳዖል ከተመረጡ 3,000 ወታደሮች ጋር ዳዊትን ተከተለው ፤ በትክክልም ሳዖል ሳያስበዉ ወደ ዳዊት ዋሻ ዉስጥ ሄደ ፤ ዳዊት የሳዖልን ህይወት ማዳንን በመምረጥ የዘርፉን ጠርዝ ቆረጠው ፡፡

ሁሉንም ለመከለስ ፈለኩኝ ምክንያቱም ዳዊት እየተሰማዉ የነበረዉን ለመረዳት አስፈላጊ ስለሆነ ፡፡ ስለ ህይወቱ እየሸሸ ነበር ! ይህ በህይወቱ እየሆነ የነበረዉ ነገር ነበር ፡፡ ዳዊት በቤተ መንግስት እንዲሆን የተመረጠ ነበር ነገር ግን በምድረበዳ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እያዘጋጀዉ ስለ ነበር ቀላል ነው ፤ ዋይርስቤ “ በእግዚአብሄር ፍቃድ በአንድ ዋሻ ዉስጥ መሆን ከእግዚአብሄር ፍቃድ ዉጪ በንጉስ ቤተ መንግስት ዉስጥ ከመሆን የተሸለ ነው “ በማለት ፅፏል ፡፡

የምዕራፍ 57 ቅርፅ፡

በአደጋ/በስጋት መካከል ስለ ምህረት መጣራት (ቁጥር 1-3)

በችግር መካከል ላይ መታመንን ማወጅ (ቁጥር 5-6)

በሰዎች መካከል እግዚአብሄርን ለማመስገን መወሰን (ቁጥር 7-11)

ትምህርት

መዝሙር (57፡ 1)፡ ዳዊት ምህረትን ለመነ ፡፡ “ በክንፎቹ ጥላ ስር “ የሚለዉን እወደዋለሁ ፤ ደህንነትን ለማግኘትና ለመፅናናት/ለማረፍ ልጆቿ በክንፎቿ ስር የሚመጡባትን የአንድ ወፍ ስዕል ይሰጣል ፡፡

መዝሙር (57፡ 2-3)፡ ዳዊት “ አላማዉን በእርሱ እንዲፈፅም “ ወደ እግዚአብሄር መጮኹን ቀጠለ ፤ እንዲፈፅም የሚለዉ ቃል “ ትክክል የሚሆን “ በማለት የተተረጎመ ነው ፤ ኃሳቡ እግዚአብሄር ስለ አገልጋዩ እንዲሰራ ነው ፡፡ ጋሜር ( “ መፈፀም “ ተብሎ የሚተረጎመው) ማለት “ መጨረሻ፣ መጨረስ፣ ፍፁም/ትክክል፣ ወደ ፍፃሜ መምጣት፣ ማሟላት “ ማለት ነው ፤ ይህ በአንድ ሰዉ ህይወት ዉስጥ የእግዚአብሄር ስራ ማሟላትን፣ መፈፀምንና ፍፁምነትን ያመለክታል ፡፡ ኃሳቡ እግዚአብሄር በአገልጋዮቹ ኑሮ ዉስጥ አላማዉን እንደሚሰራና በፍፁምነትና ሙሉ ለሙሉ እስኪፈፅምም ድረስ ስራዉን እንደሚቀጥል ነው ፡፡

መዝሙር (57፡ 4-6)፡ ዳዊት ጠላቶቹን ለአደን ከሚያደቡ አንበሶች ጋር አወዳደራቸው ፤ በጭንቀቱ መካከል ላይ ዳዊት እግዚአብሄርንን ከፍ ከፍ በማድረግ በምስጋናዉ ለእግዚአብሄር ጮኸ ፡፡ ዳዊት ጠላቶቹ “ ወጥመድን እያዘጋጁ እንደ ነበር “ ተናገረ ፤ ስለሆነም ጠላቶቹ ዳዊትን በቀላሉ እንደ አንድ ወፍ እንደሚያዝላቸዉ ጠበቁ በእግዚአብሄር ምህረትም በራሳቸዉ ጉድጓድ ዉስጥ ወደቁ ፡፡

መዝሙር (57፡ 7)፡ ዳዊት “ ልቤ ጨካኝ ነዉ “ ብሎ በተናገረ ጊዜ እዉነትን በጉልህለመስማት አስፈለገው ፡፡ ይህ በህይወቱ መጨረሻ ላይ ሲቀርብ የነበረዉን ጳዉሎስን እንዳስብ ያደርገኛል (2ጢሞ 4፡ 6-7) ፤ ዳዊት ከመጀመሪያዉ ጀምሮ ይለግሰዉ ለነበረዉ እግዚአብሄር ታምኖ የተቀመጠ እንደ ነበር እግዚአብሄርን አረጋገጠለት (1ቆሮ 15፡ 58) ፡፡

ጨካኞች እንድትሆኑ አበረታታችኋለሁ ! አንድ የጨከነ ልብ በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ የፀናን በጥርጣሬና በእምነት መካከል የማይወላዉል ነው ፡፡ በራሳችን እና በሁኔታዎች ላይ ስንመለከት ተፈጥሮ ለጥርጣሬ ምክንያት በመሆን ወደ አለማመን ወደ ሚመራን መንገድ ይመራናል ፡፡

መዝሙር (57፡ 8-11)፡ እነዚህ ጥቅሶች አዝማቹን ይይዛሉ ( ሀረጉን ወይም መስመሩን በጥቅሱ መጨረሻ ላይ በመገኘት የመዝሙሩን ዋና ሀሳብ ያጠነክራል) (ቁጥር 5, 11) ፡፡ “ አምላኬ ሆይ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን “ ፤ ዳዊት ሰዎች “ ይህ የእግዚአብሄር ስራ ነዉ ፤ በአይናችንም ድንቅ ነዉ “ እንዲሉ በእንዲህ አይነት መንገድ ታላቁነቱን እንዲገልጥ እግዚአብሄርን ተጣራ ፡፡

መዝሙር 58፡ ይህ መዝሙር በክፉዎች ፍርድ የተሰየመ ነው ( ኒዉ ኪንግ ጀምስ እትም) ፤ ዳዊት ክፉዉ ሳዖልና የእርሱ ሰዎች እንዴት እንደ ነበሩ አዘነ ፡፡

መዝሙር 59፡ ይህ መዝሙር ንዑስ ርዕስ ነው ፤ የክፈዎች የተረጋገጠዉ ፍርድ (ኒዉ ኪንግ ጀምስ እትም) ፡፡ ዳዊት ከሀዘን እግዚአብሄርን ወደ ማመስገንና ወደ መዘመር ዞረ ፡፡

መደምደሚያ

በራሳችሁ ላይ እዉነትን ሁል ጊዜ ተናገሩ ! ስሜትና ትልቅ ስሜት የችግር መሪዎች ናቸው ፡፡ ስሜት ወደ አለማመን የሚመራ በቀላሉ የጥርጣሬ መንስኤ ሊሆን ይችላል ፡፡ በእዉነት የምትመሩ ሁኑ (ኢዮ 13፡ 15) !

ለመታመን የዕብራዊ ቃል ይቻሀል ነው ፤ ኔልሰን “ ይቻሀል ማለት መጠበቅ፣ ተስፋ ማድረግ፣ መታመን፣ ታጋሽ መሆን፣ በተስፋ መጠበቅ ማለት ነው ፤ ብዙጊዜ ይቻሀል ለተስፋ የተተረጎመ እንደ ሆነ “ ይፅፋል ፡፡ እንዲሁም ዕብ (13፡ 5-6) እና ሮሜ (8፡ 28) አንብቡ ፡፡

ዮሐንስ ፒፐር “ ለዘላለም ካለዉ ክብር ጋር ሲወዳደር ሁሉም ችግሮቻችሁ/መከራዎቻችሁ ጊዜያዊ ብቻ አይደሉም፣ ሁሉም ችግሮቻችሁ ቀላልም ብቻ አይደሉም ነገር ግን ሁሉም ትርጉም ያላቸዉ ናቸው ፡፡ በሁሉም ሚሊዮን ሰከንዶች ከወደቀዉ አለም ወይም ከወደቀዉ ሰዉ የሚደርስባችሁ ህመም፣ በመታዘዝ መንገድ ዉስጥ በሁሉም ሚሊዮን ሰከንዶች ስቃያችሁ የተለዬ ክብር ታገኛላችሁ ስለዚህ …..ልባችሁን አትጡ/አትፍዘዙ ነገር ግን እነዚህን እዉነቶች ቀን በቀን በመዉሰድ በእነርሱ ላይ አትኩሩ ፡፡ ሁልጊዜ በማለዳ ለራሳችሁ ንግሯቸዉ/ስበኳቸው ፤ ከእግዚአብሄር ጋር ብቻ በመሆን ስለ ሚታሰብላችሁ በመታወቅ ልባችሁ በልበ ሙሉነት እስኪዘምር ድረስ ለአይምሯችሁ ቃሉን ስበኩት “ ብሏል ፡፡

  1. John C. Maxwell, The Maxwell Leadership Study Bible (Duluth: Maxwell Motivation, 2007), p. 503.

  2. Warren W Wiersbe, Be Worshipful (Psalms 1-89): Glorify God for Who He Is (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 195.

  3. Thomas Nelson, NIV, New Spirit Filled Life Bible (New York: Harper Division Publishing, 2014), p. 1145.

  4. John Piper, Sermon: Your Suffering is Working For You, Episode 741; available at https://www.desiringgod.org/interviews/your-suffering-is-working-for-you.

ጥያቄዎች

  1. ዳዊት በመዝ (57፡ 7-11) እንዳደረገዉ በተመሳሳይ መንገድ ራሳችሁን እግዚአብሄርን ስታመሰግኑት አግኝታችሁታል ? አዎ ከሆነ ምክንያቱ ምን ነበር ? በዚህ በብክነት/በማጋነን መንገድ እርሱን ለማመስገን የተለዬ ምክንያት ያስፈልገናል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  2. መዝ (57፡ 7) “ ልቤ ጨካኝ ነው አቤቱ ልቤ ጨካኝ ነው ፤ እቀኛለሁ እዘምራለሁ “ ይላል ፤ በመልካምና በመጥፎ ጊዜ በሁለቱም በእግዚአብሄር ላይ ጨክናችሁ ትቆማላችሁ ? አይደለም ከሆነ ይህን ለመቀየር ምን እርምጃ መዉሰድ ትችላላችሁ ?
  3. መዝሙር 58 የእርግማን (የእርግማን ንግግር) መዝሙር በመባል የሚጠራ ነው ፤ ለበቀል የሚሆን ጥሪ የሚመስል ስለ ፍትህ ኃይለኛ ጩኸት/ለቅሶ ነው ፡፡ በፍትህና በበቀል መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው ? በሌሎች ላይ በቀልን መፈለግ ልክ ነው ? (ዘዳ 32፡ 35, ሮሜ 12፡ 19, ዕብ 10፡ 30)
  4. በመዝሙር 59 ብዙ ጊዜ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን እንደ ጠንካራ ምሽጉ ጠቀሰው ፤ ጠንካራ ምሽግ ምን ማለት ነው ? ይህ ሁል ጊዜ መልካም ነገር ነው ?
  5. በመዝሙር (57-59) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 57:7, 10–11

“My heart is confident, God, my heart is confident. I will sing; I will sing praises . . .For Your faithful love is as high as the heavens; Your faithfulness reaches the clouds. God, be exalted above the heavens; let Your glory be over the whole earth.”

ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ መታመንን ምረጥ ፡፡ ለእግዚአብሔር መዝሙር መዘመርን ምረጥ ፡፡ ስለ ማይደረስበትና ስለ ታማኝ ፍቅሩ ሰለተናገረው ተስፋ እርሱን ማመስገን ምረጥ ፡፡ ፍቅሩ ይደርስበት ዘንድ ማንም ሩቅ አይደለም ፡፡ ፍቅሩ እስከ ሰማያት ከፍ ይላል ታማኝነቱም እስከ ደመናት ይደርሳል ፡፡

ምናልባት ዛሬ በጉድጓድ ውስጥ ያለህ ሊመስልህ ይችላል ፡፡ አሁንም ግን ጭንቅላትህን ቀና አድርግ እና ምስጋናን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ጀምር ፡፡ ምስጋናህ ያከብረዋል ከፍ ከፍም ያደርገዋል ፡፡ ጠላት ለክፋት ምን ይሆን ሚፈልገው ፣ ወደ ምስጋና መመለስ ትችላለህ ፡፡ ስለዚህ ጽና አትሸበርም ደግሞም አይኖችህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ ፡፡ በግራ መጋባት ውስጥ ሆነህ ምስጋናውን ለማወጅ ታማኝ ሁን እርሱም የሚያየውን ታይ ዘንድ አይን ይሰጥሃል ፡፡ ምርጫ ነው ፡፡ ራስህን ጠይቅ እስኪ ፡- አማርራለሁ እንድሁም በመጥፎ አስተሳሰብ ውስጥ እኖራለሁ ወይስ ተነስቼ ስለ ታማኝ ፍቅሩ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ? ጓደኛዬ ዛሬ መነሳትን ምረጥ ! ተነስ እና በአንድ ቀን በአንድ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ታመን !

“ልቤ ጨካኝ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጨካኝ ነው፤ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ ……… ምሕረትህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ ። አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን ። “ - መዝሙር 57፡7 ፤ 57፡10-11

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዘፍጥረት 50:19–20 — “ ዮሴፍም አላቸው፦ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን ? እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው ። “
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 15:58 — “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ ። “
  • 2ኛ ጢሞቴዎስ 4:6–7 — “በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል ። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ ፡፡ “