Wisdom Books Psalms

Seeking God in Betrayal

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 54-56 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 416 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 55 ሌላ የኃዘን መዝሙር የነበርና በክር መሳሪያዎች የተፃፈ ነበር ፡፡ በቅርብ ወዳጆቹ በዳዊት መከዳት ላይ የተመፈረተ ነው (መዝ 55፡ 12-14) ፤ በ 2ሳሳሙኤል 15 የዳዊት ልጅ አቢሰሎም በአባቱ ላይ አመፅን መራ ምክንያቱም ንጉስ ለመሆን ስለፈለገ ፡፡ ምናልባትም ይህ በዚህ በአቢሰሎም እና ዳዊት መዝሙር 55 በመፃፍ (ቁጥር 20-21) ከአቢሰሎም ጋር የወገነው የዳዊት አማካሪ አኪጦፌል መነሻ ላይ የታመፀ ነው (2ሳሙ 15፡ 31) ፡፡ በዚህ መዝሙር ዳዊት 2ሳሙ (15፡ 31) ደግሞ ፃፈው ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (55፡ 1-8)፡ ማክአርቱር ቁጥር 1-8 “ የጭንቀት ፀሎት “ በማለት ይገልፀዋል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህን ቁጥሮች “ በጭንቀት መካከል ላይ እንዲሰማ እግዚአብሄርን ስለ መጥራት “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ነቢዩ ናታን የዳዊት ቤተሰቦች በእርሱ ላይ እንደሚዞሩበት ትንቢትን ተናግሯል (2ሳሙ 12፡ 9-12) ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ለእርዳታ ከልመናዉ እንዳይከለከል/ዝም እንዳይል ለመነው (መዝ 10፡ 2, 13፡ 1, 27፡ 9, 44፡ 24, 69፡ 17143፡ 7) ፡፡ የዳዊት ፀሎት በእርሱ ላይ ጠላት ሆነዉ በነበሩት ጭንቀቱን የገለፀ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የዳዊት ድንጋጤ እንደ ገና በጭንቀት መሆኑ ወይም ብዙ ጠላቶች ስላሉት አይደለም ፤ ታላቁ ድንጋጤ ጠላቶቹ የራሱ ወዳጆች መሆናቸዉ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ የመከዳት ክብደት ዳዊትን መተኛት እንዳይችል እና ልቡ በፍራት እንዲናወጥ ምክንያት ሆነ (ቁጥር 2-4) ፡፡ በፍራት ቁጥጥር ስር በመሆን በመከዳቱ በመሰቃየት ወደ ደህንነት መብረርን ፈለገ (ቁጥር 5-8) ፡፡

ዛሬ/በአሁኑ ጊዜ ከእናተ ዉስጥ አንዳንዶች ወደ ዚህ ሲያዳምጡ ተስፋ መቁረጥ ይሰማቸዋል - አሰቃቂ ከሚያደርግባቸዉ ማንኛዉም ነገር ርቃችሁ መሄድ መፈለግ አለባችሁ ፡፡ ማክአርቱር የዳዊትን ስሜት “ እንደ ማምለጥ/መሸሽ ስሜት “ ይገልፀዋል ፤ ከዚህ ከሁሉም ርቆ ከምናገኘዉ ፍላጎት መተሳሰር አንችልምን ? ሌሎች በብሉይ ኪዳን ተመሳሳይ መንገድ ተሰምቷቸዋል (1ነገስት 19, ኤር 9፡ 2-6, 40፡ 1-6) ፡፡ ከመሮጥ ይልቅ ዳዊት ወደ እግዚአብሄር ተመለሰ ፤ በይበልጥ እንችላለን !

መዝሙር (55፡ 9-15)፡ ማክአርቱር ቁጥር 9-15 “ የፍትህ/የቅንነት ፀሎት “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ዳዊት የገጠመዉን ሁኔታ - ብጥብጥ, ሁከት, ወንጀል, ችግር, ጥፋት, ጭቆና እና ዉሸት በከተማዋ ዉስጥ እንዳለ ገለፀ (ቁጥር 9-11) ፡፡ በዚያ ላይ ሊሸከመዉ እንዳይችል ያደረገዉን የካዱትን የወዳጆቹን ጠላትነት ጨመረ (ቁጥር 12-13) ፤ በጣም የጎዳዉ አብረዉት አምልከዉ የነበሩት ወዳጆቹ በጠላት በእርሱ ላይ መዞራቸዉ ነበር (ቁጥር 14) ፡፡ ዳዊት በእርሱ ላይ በጠላትነት መጥተዉበት በነበሩት ላይ የእግዚአብሄርን ፍትህ ጠየቀ (ቁጥር 15) ፡፡

መዝሙር (55፡ 16-23)፡ ማክአርቱር ቁጥር 16-23 “ እንደ ማረጋገጫ ፀሎት “ ገልጧቸዋል ፤ ዳዊት ጌታ እንዲያድነዉ ተጣራ (ቁጥር 16) ፡፡ እግዚአብሄር ጥያቄዉንና ሀዘኑን እንደሚሰማዉ በእርግጠኝነት ያውቃል፣ የገጠመዉ ነገር እንደ ነበር እግዚአብሄር እንደሚቤዠዉ ያውቃል (ቁጥር 17-19) ፡፡ ዳዊት የወዳጆቹን የማታለል ተግባር አመለከተ (ቁጥር 20-21) ፡፡ ዳዊት ያን ሸክም ለጌታ መስጠት እንደሚችል ቢያዉቅም እግዚአብሄር ያፀናዋል፡፡ እግዚአብሄር ጠላቶቹን ይጠብቃቸዋል ፤ ምንም ይሁን ዳዊት በጌታ ይታመናል (ቁጥር 22-23) ፡፡

መደምደሚያ

ዛሬ ጥናታችን ስንዘጋ የእስራኤልን ንጉስ ዳዊት ከክብር ንጉሱ ከኢየሱስ ጋር ማወዳደር እፈልጋለሁ ፡፡

  • ዳዊት በልጁ በአቤሰሎምና በወዳጁና በአማካሪዉ አኪጦፌል ተከዳ/ተላልፎ ተሰጠ (2ሳሙ 15፡ 1-12) ፤ ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ በይሁዳ ተከዳ /ተላልፎ ተሰጠ (ሉቃ 22፡ 47) ፡፡
  • ዳዊት የቄድሮንን ሸለቆ ተሻገረ (2ሳሙ 15፡ 23) ፤ ኢየሱስ የቄድሮንን ሸለቆ ተሸገረ (ዮሐ 18፡ 1) ፡፡
  • ዳዊት ደብረዘይትተራራን እያለቀሰ ወረደ (2ሳሙ 13፡ 30) ፤ ኢየሱስ በደብረዘይት ተራራ ላይ አለቀሰ (ሉቃ 22፡ 39-44) ፡፡
  • ዳዊት በራሱ ሰዎች ተቀባይነት አላገኘም ነበር (2ሳሙኤል 15) ፤ ኢየሱስ በአይሁዶች ተቀባይነት አላገኘም ነበር (ዘካ 14፡ 4) ፡፡

ይህ ሁሉም መዝሙር 55 ወደ ኢየሱስ እንደሚያመለክት ያሳያል ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 636.

  2. MacArthur, p. 636.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 684.

  4. Nelson’s Commentary, p. 684.

  5. MacArthur, p. 636.

  6. MacArthur, p. 636.

  7. MacArthur, p. 636.

ጥያቄዎች

  1. ዳዊት በብዙ ችግሮቹ እንዳደረገዉ ጠላቶቻችንን እንዲያጠፋቸዉ እግዚአብሄርን የመጠየቅ መብት እንዳለን ታስባላችሁ ? (መዝ 54፡ 5)
  2. ዳዊት በመዝ (54፡ 7) “ ከመከራ ሁሉ አድኖኛልና “ አለ ፤ ስለ ህይወታችሁ ተመሳሳይ ነገር ማለት ትችላላችሁ ? ከችግራችሁ የዳናችሁ በመሆናችሁና በህይወታችሁ ምንም ችግር በአለመኖራችሁ መካከል ያለዉ ልዩነት ምንድን ነው ?
  3. በመዝ (55፡ 9-11) ዳዊት በኃይል፣ በሁከት፣ በኃጢዓት፣ በመጥፎ ፀባይ፣ በጥፋት፣ በጭንቀት እና በማታለል የተጠቃች ስለሆነችዉ ከተማ ቅዱስ እንድትሆን ስለ መመረጧ አዉርቷል ፤ ችግራችን በራሳችን በቤተ ክርስቲያናችን ግድግዳ ዉስጥ በወደቀ ጊዜ ኃጢዓት ከሞላበት አለም ለመራቅ ስለ እርዳታ እንደ ክርስቲያን ብዙ ጊዜ እንዴት እናደርጋለን ?
  4. በመዝ ( 55፡ 12-14) ዳዊት እንዲጎዳና ተስፋ እንዲቆርጥ ምክንያት የሆኑት እንዴት ጠላቶቹ እንዳልነበሩና ነገር ግን የወዳጆቹን ክህደት እንደ ነበር አወራ ፤ ይህ ስለ መሲሁና ይሁዳ ያመለክታል ፡፡ በጎዷችሁ ጊዜ ወዳጆቻችሁ እንደ ጠላት የተቃወሟችሁን ይቅር ለማለት ለእናንተ ምን ያክል ጠንካራ ነው ?
  5. መዝ (56፡ 8) ለእናንተ ስለ እግዚአብሄር ፍቅር ምን ይላል ?
  6. በመዝሙር (54-56) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 56:9b

“This I know: God is for me.”

እግዚአብሔር የአንተ ነው ፡፡ የአለም ሁሉ አምላክ ፣ ሁሉን ቻዩ የሰማይና የምድር ሰሪ እርሱ አምላክህ ነው ፡፡ እግዚአብሔር አብ ልጁን ኢየሱስን ስለ አለም ኃጢአት እንድሞት የላከው……… በርግጥ እርሱ አምላክህ ነው ፡፡ እርሱ ይወድሃል ፡፡ ህይወትህን በእጆቹ ይዟል ፡፡

የሚያስፈራህ ምንም ነገር የለም ፡፡ ምንም ነገር ፡፡ ስትፈራ ወደ ኢየሱስ ሩጥ እናም እርሱን እመነው ፡፡ እርሱ አምላክህ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ጓደኛህ ፣ ጠባቂህና ነጻ አውጪህ ነው ፡፡ እርሱ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነው ፈጽሞም አይተውህም ፡፡ እርሱ አምላክህ ነው ፡፡ ዛሬ በዚህ አንድ ነገር ላይ በተስፋ ተጣበቅ ፡- እግዚአብሔር አምላክህ ነው ፡፡ በልብህ ውስጥ በጥልቀት እስክታምነው ድረስ ይህንን ድገመው ፡- እግዚአብሔር አምላክህ ነው ፡፡ እግዚአብሔር አምላክህ ነው ፡፡ እግዚአብሔር አምላክህ ነው ፡፡ ዛሬ በትምህርት ቤት ፣ በስራ ፣ በቤት ውስጥ ወይም በመኪናህ ውስጥ በዚህ ተስፋ ተመላለስ ፡፡ ከጥላው ስር ተኝተህ ሳለ መነሳት ሳትፈልግ እንኳ ፣ ከባዱን ነገር አድርግ ፣ ተነስ እና እግዚአብሔር አምላክህ እንደሆነ አስታውስ ፡፡

“አንተ አምላኬ እንደ ሆንህ እነሆ፥ አወቅሁ ። “ - መዝሙር 56፡9

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 56:3–4 — “ እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ ። በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፤ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል ? “
  • መዝሙር 56:13 — “ ነፍሴን ከሞት፥ እግሮቼን ከመውደቅ አድነሃልና፥ በሕያዋን ብርሃን እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ ። “
  • ሮሜ 8:31 — “ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ? “