David's Confession of Sin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 51-53 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 51 በጣም ከሚታወቁት መዝሙር አንዱ ነው ፤ የንስሀና የይቅርታ መዝሙር ነው ፡፡ የመዝሙሩ አገባብ የዳዊት ኃጢዓት ከቤርሳቤህ ጋር እና በነቢዩ ናታን የተገሰፀ መሆኑን ነው (2ሳሙ 11፡ 26-29, 12፡ 1-20) ፡፡ ዳዊት ከዖሪዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ጋር ዝሙት ፈፀመ፣ ኃጢዓቱንም ለመሸፈን ዳዊት ዖርዮን በዉጊያ ፊት ላይ በማድረግ አስገድሎት ነበር ፡፡ ዳዊት ከኃጢዓቱ ለመራቅ አሰበ ፤ ናታን በዳዊት ላይ “ ያ ሰዉ አንተ ነህ ! አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሰራ ዘንድ የእግዚአብሄርን ነገር ለምን አቃለልህ ? (2ሳሙ 12፡ 7-9) በሚለዉ ቃል ከእግዚአብሄር የፍርድን ቃል የመናገር ጠንካራ ስራ ነበረው ፡፡ ዳዊትና መላዉ ቤቱ ከዳዊት ኃጢዓት የተነሳ ችግር ደረሰባቸው ፤ ይህ ለመዝሙር 51 አገባቡ/ሀሳቡ ነበር (2ቆሮ 7፡ 10) ፡፡ ጥያቄአችን በትክክለኛ ሁኔታ ወደ እግዚአብሄር እንመጣለን ነው የሚል ነው ? መዝሙር 51 እዉነተኛ የንስሀ ዝርዝር ነው ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (51፡ 1-2)፡ ዳዊት የማይገባዉን ነገር ቢያደርግም በእግዚአብሄር መታመንና በማይቀንስ ፍቅሩ ቀላል ስለ ነበረው ምህረት ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፡፡ እግዚአብሄርን ይቅርታ እንዲያደርግለት ጠየቀው ማለትም እንዲያነፃው/እንዲያጠራው ወይም ኃጢዓቱን እንዲያስወግድለት ጠየቀዉ ማለት ነው ፡፡ መንፃት/መጥራት የተፃፈበትን ወረቀት እንደ ገና ለመጠቀም ወረቀቱን ንፁህ ለማድረግ ፁሁፍን የማስወገጃ ብቸኛዉ መንገድ ነበር ፡፡ ዳዊት እንደ ገና ንፁህ እንዲደረግ ፈለገ - ጥፋተኝነቱ እንዲወሰድለት፣ ይቅርታ እንዲደረግለትና ከእርሱ እንዲወገድለት ፈለገ (መዝ 9፡ 5, ኢሳ 43፡ 25) ፡፡
መዝሙር (51፡ 3-6)፡ ከዚያም ዳዊት ኃጢዓቱን ተናዘዘ ፤ ስለ ኃጢዓቱም ኃላፊነትን በመዉሰደ (ቁጥር 3) በእግዚአብሄርም ላይ ኃጢዓትን አድርጎ እንደ ነበር አስተዋለ (ቁጥር 4) ፡፡ ዳዊት የኃጢዓቱን ዉጤት ለመቀበል ዝግጁ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ የዳዊት ኃጢዓት ቀጥተኛ ዉጤቶች ነበሩት በተለይም ከቤርሳቤህ ጋር በነበረዉ ጉዳይ ተወልዶ የነበረዉ ልጅ መሞት ፡፡ በቁጥር 5 ዳዊት ከዉልደቱ ጀምሮ ኃጢዓተኛ እንደ ነበር ተናገረ - ይህ ኃጢዓት አድርጎበት የነበረዉ ብቸኛዉ ጊዜ አልነበረም (ሮሜ 3፡ 10-12) ፡፡ ዳዊት የእግዚአብሄርን የፅድቅን ስርዓት አጠቃለለ (ቁጥር 6) ፡፡
መዝሙር (51፡ 7-12)፡ ዳዊት የነፃ ለመሆንና ንፁህ ለመደረግ ፈለገ (ቁጥር 7) ፤ ለይቅርታን ለመታደስ ለሁለቱም ፀለዬ (ዘጸ 12፡ 22) ፡፡ በቁጥር 8-9 ዳዊት ስለ ኃጢዓቱ ኃላፊነትን ወሰደ ፤ ለመታደስ እግዚአብሄርን ለመነ (ዮሐ 1፡ 9) ፡፡ ዳዊት ስለ ንፁህ ልብ እና ስለ ታደሰ መንፈስ ጠየቀ (ቁጥር 10) ፡፡ እንደገና በአምላኩ ደስታን ለማግኘት ዝግጁ ነበር ፤ ዳዊት በእግዚአብሄር ፊት መሆንን ፈለገ (ቁጥር 11)፣ በእግዚአብሄርም አዳኝነትም ታደሰ (ቁጥር 12) ፡፡
መዝሙር (51፡ 13-17)፡ ዳዊት ለእግዚአብሄር ሁለት ቃል ኪዳኖችን አደረገ ፤ መጀመሪያዉ ሌሎችን ስለ እግዚአብሄር መንገድ በማስተማር ሌሎች ኃጢዓተኞችን ወደ እርሱ እንደሚያመጣ (ቁጥር 13) ፤ ሁለተኛው እግዚአብሄርን ያመሰግናል ምክንያቱም እግዚአብሄር መስዋዕቱን እንደማይፈልግ የተሰበረ መንፈስን እንደሚፈልግ ስለሚያውቅ (ቁጥር 14-17) ፡፡ እግዚአብሄር በፊቱ በተዋረደና በተሰበረ ልብ እንድንመጣ ይፈልጋል ፡፡
መዝሙር (51፡ 18-19)፡ በመጨረሻም ዳዊት ፀሎቱን ወደ ፂዎን መለሰ (ኢየሩሳሌም ተብላ በምትጠራው) ፡፡ ፀሎቱ ለኢየሩሳሌም የመማለድ ስለሆነ እግዚአብሄር ይከብራል ፤ እግዚአብሄር ዳዊትን ፂዎንን እንዲያበለፅግ ጠራው፣ ያንን ጥሪ እንደ ገና ለማንሳት/ለመስማት ዝግጁ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
እስካሁን ካደረኩት ነገር ታላቁ እርምጃዬ ክርስቶስን በመቀበል በህይወቴ ላይ ይዞይ ከነበረዉ ኃጢዓት ተለይቼ መሄድ የቻልኩበት ምሽት ነበር ፤ ይህ የህይወቴ ማንፂ ነበር ፡፡ ሁላችንም ምህረት የተሞላ ይቅርታዉን ለመቀበል እና በእርሱ ፊት ንፁህ እንድንሆን በእግዚአብሄር ፊት መምጣት የሚያስፈልጉን ጊዜያቶች አሉ ፡፡
ጥያቄዎች
-
ዳዊት መዝሙር 51 እንዲፅፍ ምክንያቱ ወይም ሁኑታዉ ምን ነበር (2ሳሙኤል 11) ? ዳዊት በብዙ ሰዎች ላይ ኃጢዓት ቢያደርግም እንኳን ዳዊት በትክክል በማን ላይ ኃጢዓት ሰራሁ አለ ? (ዘፍ 39፡ 9)
-
በመዝሙር 51 ዳዊት ለእግዚአብሄር ያደረጋቸው ሰዎስት ዋና ዋና ጥያቄዎች ምን ነበሩ (መዝ 51፡ 2, 12, 13) ? በዚህ መዝሙር እንዳያችሁት በሙሉ ንስሃ ወደ እግዚአብሄር የጮኻችሁበት ጊዜ አላችሁ ?
-
መዝሙር 51 በምርጫ ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮአችንም ኃጢዓተኞች መሆንችንን እንዴት ይገልጣል (ማቴ 15፡ 19, 1ዮሐ 1፡ 8) ? በእዉነት ስንወለድ ኃጢዓተኞች ከሆንን መልካምነታችን ድነትን ሊያስገኘን እንደማይችልና ወደ እግዚአብሄር ቤተሰብ እንደማያስገባን እንዴት እናዉቃለን ? (ኤፌ 2፡ 8-9, ቲቶ 3፡ 3-7)
-
ዳዊት እግዚአብሄርን በዉስጡ ንፁህ ልብን እንዲፈጥርለትና በእርሱ ዉስጥ ያለዉን መንፈሱን እንዲያድስለት በጠየቀዉ ጊዜ ዳዊት ምን እያለ ነበር (ኤር 24፡ 7, ሕዝ 11፡ 19, 36፡ 25-27) ? ጌታ መንፈስ ቅዱስን ለዳዊት መቼ ሰጠው (1ሳሙ 16፡ 13) ? ይህን ጥያቄ በመጠየቁ የዳዊት ፍራት ምን ነበር ? (1ሳሙ 16፡ 14)
-
በመዝ (51፡ 17) እግዚአብሄርን እንደሚያከብር ወይም እንደማያከብር ስለ መስዋዕት የዳዊት መረዳት ምን ነበር ? እግዚአብሄር በምን ይደሰታል ?
-
በመዝሙር 14 እና 53 መካከል ልዩነት መጥቀስ ትችላላችሁ ?
-
በመዝሙር (51-53) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 51:2–4a
“Wash away my guilt and cleanse me from my sin. For I am conscious of my rebellion, and my sin is always before me. against You—You alone—I have sinned and done this evil in Your sight.”
መዝሙር 51 ዳዊት የዝሙት ፣ የመግደል እናም ከቤርሳቤህ ጋር ያለውን ግንኙነት በመሸፈን ኃጢአት ከፈጸመ በኋላ ስለጸለየው የንስሃ ጸሎት ያወራል ፡፡ በህይወትህ ኃጢአትን ደብቀህ ከሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ባለህ ግንኙነት አይከናወንልህም ፡፡ በመጨረሻም ሌሎች የተደበቀ ኃጢአትህን ያውቃሉ ፡፡ እግዚአብሔርም ሁሉን ያያል ፡፡ እርሱ ልብህን ያውቃል እንድሁም ኃጢአትህንም ያያል ፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይወደሃል ፡፡ ኃጢአትህን ለእርሱ ብትናዘዝ ፣ እርሱ ምህረትን ያደርግልሃል ፡፡ እርሱ አንተ ከኃጢአት ተመልሰህ ወደ እርሱ እንድተመለስ ይፈልጋል ፡፡
ዛሬ እግዚአብሔርን “ ንስሀ ልገባበት የሚያስፈልግ ነገር አለን ? ብለህ ጠይቅ ፡፡ ቆም ብለህ አይኖችህን ጨፍንና መንፈስ ቅዱስን አድምጥ ፡፡ ወደ አሳብህም የሆነ ነገርን ካመጣልህ ፣ ለእርሱ ግለጠው እናም በንጹህ ልብ ይቅርታውን ጠይቅ ፡፡ የማስመሰል ንስሀን አትግባ ፡፡ እግዚአብሔር ልብህን ያውቃል ፡፡ እናም ከዚያ ከኃጢአትህ ተመለስና ህይወትህን ለእግዚአብሔር ስጥ ፡፡ ንጹህ ልብን ይፈጥርልህ ዘንድ ደግሞም የቀናውን መንፈስ በውስጥህ እንድያድስ ጠይቀው ፡፡ እንድሁም የደህንነትህን ደስታ እንድመልስልህ ደግሞም የእሽታን መንፈስ በውስጥህ እንድያድስ ለምነው ፡፡ ኢየሱስ ለአንተ ያለውን ፍቅር ሊያስረግጥልህ ከኃጢአትህም ሊያድንህ እንደሞተ አስታውስ ፡፡ እርሱ ይቅር ይልሃል ደግሞም በጣም ይወድሃል ፡፡ ዛሬ ወደ እርሱ ተመለስ ፡፡
“ ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ ፤ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና ። አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ ፡፡
- መዝሙር 51፡2-4
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 51:10–13 — “ አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ ። “
ምሳሌ 28:13 — “ ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል ። “
ሮሜ 5:8 — “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።