Wisdom Books Psalms

Misplaced Trust in Wealth

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 49-50 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 414 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 49 የጥበብ መዝሙር ነው ፡፡ የቆሬ ልጆች ለመዘምራን አለቃ እንዲዘምሩ ለህዝቡ ፃፉት ፡፡ በኔልሰን ማብራሪያ መሰረት መዝሙር 39 ለሙዚቃ ከተቀመጡት ትዕዛዞች አንዱ ነው ፡፡ መዝሙሩ “ ከአስጨናቂ ባለጠጋ ምንም የሚያስፈራ ነገር እንደሌለ እንዲያስተዉል ጥበበኛ ሰዉን ይናገራል፡ ልክ እንደ እንሰሳቶች እነሱም ይሞታሉ ፤ ነገር ግን ፃድቅ ለዘላለም ይኖራል “ ፡፡ ለመዝሙር 49 ርዕሱ “ በሀብት ላይ ያለ ስፍራዉ የሆነ መታመን “ የሚል ነው፡፡

ፀሀፊዎቹ የቆሬ ልጆች ነበሩ ፤ የኃላ ታሪካቸዉ የሚያስደንቅ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴንና አሮንን ከ30 እስከ 50 አመት የሞላቸዉን የቀዓትዋዊያንን ወንዶች ቁጥር እንዲወስዱ ነገራቸው (ዘኁ 4፡ 1-5) ፡፡ አሮንና ወንድ ልጆቹ በጣም ቅዱስ ለሆነዉ እቃ ጥንቃቄ ለማድረግ ኃላፊነት ነበረባቸው ፤ እነዚህ እቃዎችም፡ ታቦቱን፣ የእግዚአብሄር መገኛ ገበታን፣ መስዋዕቱን በመጠጣት የሚጠቅሙትን ሳህኖችንና ማንቆርቆሪያዎች፣ ለድንኳኑ ማደሪያ የመብራት ማስቀመጫዉንና መብራቱን እና የወርቅ መሰዊያዉን ይይዛሉ (ዘኁ 4፡ 7-20) ፡፡ ሰፈሩ የትም ቢንቀሳቀስም እነዚህም በመታሸግ ይሄዳሉ ፤ ቀዓትዋዊያንም እቃዎቹን ያጓጉዛሉ/ይሸከማሉ ነገር ግን ራሳቸዉ እነዚህን እቃዎች መንካትም ሆነ ማየት አይችሉም ከዚያ ዉጪ ይሞታሉ (ዘኁ 4፡ 15, 20) ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴንና አሮንን የቀዓትዋዊያንን ዘር እንዲጠብቁ ስለ ነገራቸዉ በሌዋዊያን አይጠፉም ምክንያቱም ቀዓትዋዊያን የሚያደርጉት አስፈላጊ ተግባር ስለ ነበራቸው (ዘኁ 4፡ 17-20) ፡፡

በዘኁልቁ 16 ቆሬና ሌሎች የእስራኤል ታዋቂ ወንዶች በሙሴና በአሮን ላይ በማመፅ ሁሉም እስራኤላዊ ቅዱስ እንደ ነበር ነገሯቸው ፡፡ ለምን ሙሴና አሮን ራሳቸዉን በእስራኤል ህዝብ ላይ ከፍ ከፍ እንዳደረጉ ጠየቋቸው (ቁጥር 1-3)፡፡ ይህ በራሳቸዉ ድርሻ መቅናታቸዉ ነበር ምክንያቱም በጠቅላላ ህይወታቸዉ እነዚህን ቅዱስ ነገሮች ይሸከማሉ ነገር ግንመንካት አይችሉም ሙሴና አሮን ግን ይችላሉ ፡፡ ሙሴእግዚአብሄር እንዲያደርግ የጠራዉን እያደረኩ ነዉ በማለት መለሰላቸው ፤ እነዚህ ያመፁት ሰዎች ከኖሩና ሌላዉ ሰዉ እንደሚሞት ከሞቱ እግዚአብሄር እንዲሰራ የፈለገዉን እንዳልሰራ አያረጋግጥም አለ ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ተደርጎ የማያውቅ ነገር በማድረግ መሬት በመከፈት ካላቸዉ ሁሉም ነገሮች ጋር ሁሉንም ትዉጣቸዋለች የእስራኤልም ሰዎች እግዚአብሄር በስራ ላይ እንደ ነበር ያውቃሉ (ቁጥር 28-30) ፡፡ መሬትም ሙሴ እንዳለዉ ወዲያዉኑ በመከፈት ሁሉንም የቆሬ ሰዎችንበመዋጥ ያላቸዉ ነገር ሁሉ ወደ ሲዖል ወረዱ ከዚያም ተመልሳ በእነርሱ ላይ ተዘጋች (ቁጥር 31-35) ፡፡ ሁሉንም ተዉጠዉ እንደ ነበር ቢመስልም በዙኁልቁ 26 ያለዉ ቆጠራ ትንሽ የቆሬ ሰዎች እንዳልሞቱ ያሳያል (ቁጥር 9-11) ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (49፡ 1-4)፡ የኔልሰን ማብራሪያ ቁጥር 1-4 ለአለም ላይ ለሁሉም ሰዉ እንዲሰማ “ ለማስተዋል የሚደረግ ጥሪ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ “ አለም “ ለሚለዉ የዕብራዊ ቃል (ቁጥር 1) “ ህይወት የሚያልፍበት ሁሉም የስራ ስፍራ መላዉ የሰዉ ልጅ ሁኔታ “ ማለት ነው ፡፡ “ እንቆቅልሽ “ ወይም “ ያልተገለጠ ንግግር “ ማለት “ ሚስጥር “ ማለት ሲሆን “ ግራ የሚያጋባን የስነ ምግባር ችግር ይጠቅሳል፡ ለእግዚአብሄር አስተሳሰብ የሌላቸዉ ጨቋኝ ባለፀጋዎች ወደ ሚለዉ ቃል እንዴት ፃድቆች ይመጣሉ ? “ መዝሙረኛው ይህን አጣብቂኝ የሙዚቃ መሳሪያ በመጠቀም ይገልፁታል አለ ፡፡

መዝሙር (49፡ 5-9)፡ መዝሙረኛው የጠላቶቹን ኃጢዓት ተናገረ ነገር ግን ስለ እነርሱ ፍራት እንዳልነበረዉ ተናገረ ፤ መታመናቸዉን በግል ኃብታቸዉ ላይ አስቀመጡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት የሚቤዥ/ነፃ የሚያደርግ በቂ ገንዘብ የለም ፡፡ “ ጉድጓድ “ ሚለዉ ቃል (ቁጥር 9) “ በጨለማ ሁኔታ ላይ የሞትን ኃይል “ ጠቅሷል ፡፡ ማንኛዉንም ሰዉ ከሞት ኃይ ማዳን እግዚአብሄር ብቻ ነዉ የሚችለዉ ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር እንደሰጠን የምናስታዉልና የሰጠንን ለሌሎች ለመርዳት እና እግዚአብሄርን ለማክበር ከተጠቀምንበት “ ባለፀጋ መሆን ኃጢዓት እንዳልሆነ ይገልፃል ፤ (ማር 10፡ 24-25, ሉቃ 16፡ 15) ፡፡

መዝሙር (49፡ 10-12)፡ ባለፀጋ ያለ እግዚአብሄር ይሞታል ሌሎችም ብልፅግናቸዉን ይቀበሉታል ፡፡ ሁሉም ለኑሮአቸዉ የሚያሳዩአቸው የዘላለም ማረፊያ ስፍራቸዉ ነበር - መቃብሮቻቸው ፤ የሰዉ ልጅ ልክ እንደ እንስሳት ይሞታል ፡፡ ኃብት መኖር ያን ከመሆን አይከለክልም ፡፡

መዝሙር (49፡ 13-15)፡ ይህን መስመር የተከተሉ ትዕቢተኞች ነበሩ ሲዖልም ወረዱ ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ባለፀጋንና ድሀና ከሲዖል ኃይል የመታደግ/የማዳን ኃይል አለው ፤ ይህ “ ከኃጢዓትና ከሞት ኃይል ስለተቤዠን የጌታን የማዳን ስራ “ ያመለክታል ፡፡

መዝሙር (49፡ 16-20)፡ ስለዚህም በሚሞት ጊዜ ከእርሱ ጋር ምን ይዞ የማይሄደዉን እና በፍፁም መልሶ የቀንን ብርሃንን የማያየዉን ብልፅግና የነበራቸዉን አይፈሩም ነበር ፤ ነገር ግን “ አዕምሮ የሌለዉ ክቡር ሰው እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ “ (ቁጥር 20) ፡፡

መደምደሚያ

የቆሬ ልጆች የኃላ ታሪክ መኖር ይህን ፅሁፍ ወደ ህይወት ያመጣል ፡፡ የመዝሙር 49 ቃል በዘኁልቁ ተዘርዝሮ ከነበረዉ ቤተሰብ ከገጠመዉ ነገር ከመጣ ልትደነቁ ያስፈልጋችኋል ፡፡ የዚህ መዝሙር ጥበብ ሌሎች የነበራቸዉን የሚፈልጉትና የነበራቸዉን ስተዉ በነበሩት በቆሬ ሰዎች ላይ ስለሆነው ጥልቅ ስር አለው ፡፡ እነዚህ ግጥሞች ምን እዉነት እንደ ነበርና ምን አስፈላጊ እንደ ነበር ተረድቶ ከነበረዉ ሰዉ መጡ ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 680.

  2. Nelson’s Commentary, p. 680.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 187.

  4. Nelson’s Commentary, p. 681.

  5. Nelson’s Commentary, p. 681.

  6. Wiersbe, p. 187.

  7. Wiersbe, p. 188.

ጥያቄዎች

  1. ለመዝሙር 49 ትክክለኛዉ አድማጭ ማን ነበር ? መዝሙረኛዉ ለማድረስ እየሞከረ የነበረዉ ጠቅላላ መልዕክት ምንድን ነው?
  2. በኃብት መደገፍ ችግሩ ምንድን ነው (ማር 10፡ 23-24, 1ጢሞ 6፡ 17) ? እግዚአብሄር የሰጠን የኃብት አላማ ምንድን ነው ( ማቴ 6፡ 33, 2ቆሮ 9፡ 10-12, 1ጢሞ 6፡ 18-19) ? በኃብት ወይም በእግዚአብሄር መታመናችሁንእንዴት ልታዉቁ ትችላላችሁ ?
  3. በመዝሙር 49 ገንዘብ ማድረግና መግዛት የማይችላቸዉ ጥቂት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (ማቴ 16፡ 26, ሉቃ 12፡ 20-21, 1ጢሞ 6፡ 7)
  4. እግዚአብሄር ለምግብ የሚራብ/የሚፈልግ ካልሆነ ለምን “ እንደሚራብ / እንደሚፈልግ “ መፅሀፍ ምን ይላል ? (ሆሴ 14፡ 2, ሮሜ 12፡ 1)
  5. በመዝሙር (49-50) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 49:6–7

“They trust in their wealth and boast of their abundant riches. Yet these cannot redeem a person or pay his ransom to God.”

ጎረቤቶችህን ስታይና ህይወትህን ከእነርሱ ጋር ስታወዳድር አግኝተኸው ታውቃለህ ? ምናልባት በጣም ስኬታማ ወይም ከአለም አንጻር ሀብታም ሊመስሉ ይችላሉ ፡፡ አንተም በዚህ ምድር ብዙ ወይም ትንስ ይኖርህ ይሆናል ፤ ዋናው ነገር ግን ልብህንና አሳብህን በዚህ አለም ነገር ላይ ሳይሆን በጌታ ላይ ማድረግ ነው ፡፡ ኢየሱስ ባለጸጋ ወደ መንግስተ ሰማይ ከሚገባ ለግመል በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ እንደሚቀል ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ አይኖችህን በሌላ ነገር ላይ ወይም ብዙ ሀብት በማከማቸት ላይ ሳይሆን በኢየሱስ ላይ አድርግ ፡፡

ዛሬ በቁሳዊም በመንፈሳዊም እግዚአብሔር ስለ ሰጠህ ስጦታ አመስግን ፤ አስተውል የትኛውም መልካምና ፍጹም ስጦታ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ፡፡ ራስህን ከሌሎች ጋር የማወዳደርም ሆነ ሌሎችንና ስኬታቸውን የመተቸትን ፈተና ተቃወም ፡፡ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ እመን እናም እርሱ እንድትሰራው ለጠራህ ስራ በመታዘዝ ኑር ፡፡ ሀብታም ወይም ድሃ ጌታ ሁሉም ሰዎች ስለ ወንጌል ህይወታቸውን እንድተው ይፈልጋል ፡፡ ብዙ ስትተው ፣ በጌታ እያከማቸህ ሃብታም እየሆንክ ትመጣለህ ፡፡ እግዚአብሔርን ፈጽመህ ልትተወው አትችልም !

“በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚመኩ ፤ ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም፤ ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም “

  • መዝሙር 49፡6-7

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 16:25–26 — “ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል ። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል ? “

ማርቆስ 10:24–25 — “ ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ፦ ልጆች ሆይ፥ በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው ። ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል አላቸው ። “

ሉቃስ 16:14–15 — “ ገንዘብንም የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው ያፌዙበት ነበር ። እንዲህም አላቸው፦ ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና ። “