Wisdom Books Psalms

God's City of Jerusalem

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 46-48 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 413 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ስለ መዝሙር 48 ጥናት በጣም ጓጉቻለሁ ምክንያቱም ስለ ኢየሩሳሌም ስለሆነ ፡፡ ቡድናችን ማድረግ ከሚችለዉ አንድ ነገር በኢየሩሳሌም ጊዜ በማሳለፍ ስለ ኢየሩሳሌም ሰላም መፀለይ ነው ፤ ብዙ ሙሁራን ይህን መዝሙር እና ሌሎችን (መዝሙር 76, 84, 87, 122 እና 132) “ እንደ ፂዎን መዝሙር/ዜማ “ ይጠቅሷቸዋል ምክንያቱም “ ማብራሪያው በጌታና በፂዎን ተራራ ላይ ስለሆነ “ (የኢየሩሳሌም ሌላዉ ስም/ርዕስ የሆነዉን) ፡፡ በመዝሙር 48 ለማየት የምናገኘዉ ነገር እግዚአብሄር ኢየሩሳሌም ከጣላቶቿ ነፃ እንዳሚያወጣ ነው ፡፡ እስራኤል አዲስ ዳርቻ/ወደብ የምታክል ስትሆን ለምን ብዙ ሀገራት በአለም ላይ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ስለሚሆነዉ አተኮሩ ? ስለ ኢየሩሳሌም ከተማኃይለኛ የሆነ ዉጊያ አለ ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (48፡ 1-3)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች እንደ “ የእግዚአብሄር እና የእነርሱ ከተማ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ቁጥር 1 ኢየሩሳሌምን “ የአምላካችን የተቀደሰ ከተማ “ በማለት ይገልፃል ፤ አንዳንዶች ለምን ለኢየሩሳሌም በብዙ እንደማስብ ይጠይቁኛል ፤ መልሱ በ 1ነገ (14፡ 21) “ እግዚአብሄርምስሙን ለማኖር ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ኢየሩሳሌምን መርጧት ነበር “ የሚለዉ ነው ፡፡ ኤር (3፡ 17) ከተማዋን “ የእግዚአብሄር ዙፋን ብለዉ በመጥራት አህዛብ ሁሉ ወደ እርሷ ይሰበሰባሉ “ ይላል ፡፡ አሕዛቦች በአንድ ላይ ይሰበሰባሉ ምክንያቱም መሲሁ ይሁን እንጂ በአምላክ ስም ምክንያት ነው፤ ይህ ለመሲሁ ሁለተኛ መምጣት ግንባር ቀደም ይሆናል ፡፡ ኢየሩሳሌም የእግዚአብሄር ዘላለማዊ ከተማ ናት ፤ የክብር ንጉስም በኢየሩሳሌም ይኖራል ፡፡ በከነዓናዊያን ስነ ግጥም ሁል ጊዜ ንጉሱ ከከተማዋ በስተሰሜን ይኖራል ፤ እዚህ ጋር መዝሙረኛው የእግዚአብሄር ከተማ እዉን እንደ ነበረችና ኢየሩሳሌም እንደ ነበረች ገልጧል ፡፡

ዳዊት ኢየሩሳሌምን ከኢያቡሳዊያን ላይ በመዉሰድ (2ሳሙ 5፡ 6-9) ዋና ከተማዉ አደረጋት ፡፡ ከተማዋ ከባህር ወለል በላይ 2500 ጫማ ስለ ተቀመጠች ወደ ተፈጥሮአዊ ምሽግ ያደርጋታል፣ እንዲሁም በሰሜን- ደቡብ እና ምስራቅ-ምዕራብ ንግድ የሚያቋርጠዉ ስፍራ አጠገብ ነበረች ፤ ቅዱስ ያደረጋት የኪዳኑም ታቦት የመጣበት ስፍራም ነበረች ፡፡ ዋይርስቤ “ ታላቅነቱ በእግዚአብሄር እንጂ በከተማዋ እንዳልነበር እና በፀጋዊ ፂዎንን እንደ መረጣት “ ይናገራል ፡፡ ኢሳ (2፡ 2) የኢየሩሳሌም ከተማ ላለፈዉ ብቻ ሳይሆን የምታስፈልገዉ ለወደፊቱም እንደ ምታስፈልግ ይናገራል ፡፡ የክብሩም ንጉስ በዚያ ይኖራል ፡፡ ኢሳ (60፡ 1) የእግዚአብሄር ክብር በኢየሩሳሌም ላይ እንደሚያበራ ይናገራል ፡፡

መዝሙር (48፡ 4-7)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች “ እግዚአብሄር እና ጠላቶቻቸዉ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ የከበቡት የጦር ኃይሎች በኢየሩሳሌም ላይ ያለዉን ጠንካራዉን የእግዚአብሄርን ምሽግማሸነፍ መጣስ አይችሉም ፡፡ በተለዬ/በደንብ በቁጥር 7 ላይ ስንመለከት “ በኃይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ “ ነፋሱም ከምስራቅ፣ ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ ያነፍሳል ይላል ፡፡ የምስራቁ ነፋስ “ ከበርሀ በመምጣት በኃይለኝነቱ በጣም የታወቀ ነበር “ ፤ የምስራቅ ንፋስ ከኢዮብ ወንድ ልጆቹ የአንዱን ቤት ያነሳዉ እና ቀይ ባህርን የከፈለዉ ኃይል እንደ ሆነ ነው (ኤር 18፡ 17) ፡፡ የምስራቅ ንፋስ ሌሎች መዓቶች/መቅሰፍቶች እህልን ማድረቅ/መለብለብ፣ ምንጮችን ማድረቅ እና የአንበጣን መቅሰፍት ያካትታል ፤ ይሁን እንጂ የምዕራብ ንፋስ “ በህዳርና በየካቲት መካከል እርጥበትን ከሜደትራሊያ ባህር በማምጣት “ አንበጣዎችን በመንፋት/በመግፋት በከባድ ድርቅ የሚያበቃ ነው ፡፡ የሰሜን ንፋስ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታን በማምጣት በሰዎች ጤንነት ላይ ተፅዕኖን ያጠላል /ያመጣል ፡፡ የደቡብ ንፋስ ረጋ ያለ እና “ ምድርን ፀጥ “ ያደርግ የነበር እና በምንጭም አንድ ቀን ብቻ ይቆያል ፤ ይህ የኢየሩሳሌም በጎ መልክ ነዉ - ምክንያቱም ይህ ከተማዋንና የእስራኤልን ሕዝብ ተፅዕኖ የሚያደርግ በሁሉም አይነት ነገሮች እና አሕዛቦች ተከበዋል ፤ ይህ ኢየሩሳሌም ምን እንደሚኖራትና እንደሚገጥማት ትንቢታዊ መልክ ነው ፡፡

መዝሙር (48፡ 8-14)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 8-11 “ እግዚአብሄር እና አምልኳቸዉ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር የኢየሩሳሌምን ከተማ የዘላለም ከተማዉ በማድረግ ይመሰርታታል ፤ እግዚአብሄር ኢየሩሳሌምን በተፈጥሮ ወይም በመለኮታዊ በኩል እንደ ራሱ ከተማ የመመስረት ኃይል አለው ፡፡ እግዚአብሄር ይህን በጣላቶቿ በእስራኤል ላይ የመጣዉን ዉጊያ ዉስጥ ማድረግ ይችላል ወይም በመለዓክቶቹ ጣልቃ መግባት ይችላል ፡፡ አንድ ቀላል ምሳሌ እግዚአብሄር መለዓክቱን በሶሪያዊያን ካምፕ በላካቸዉ ጊዜ 185,000 ሰዎችን መግደላቸዉ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በቁጥር 9 “ ተማረን “ ለሚለዉ ሀረግ መግለጫው “ በአድሎነት ማሰብና መመልከት ለአንድነት ንፅፅር ለመጥቀስ ሲሆን ፤ ምንም ነገር ታማኝ ከሆነዉ ከእግዚአብሄር ፍቅር ጋር ሊወዳደር እንደማይችል ነዉ ሀሳቡ” ፡፡ ዋይርስቤ ቁጥር 12-14 “ እግዚአብሄርን እና ወደፊታቸዉን “ ይገልፃል ፤ አምላካቸዉ ሁል ጊዜ በኢየሩሳሌም ይመራቸዋል ፡፡

መደምደሚያ

በመዝሙር 48 እና በዛሬ መካከል ምን ሆነ/ተፈጠረ ? ይህ ዝርዝር ነገር ከታሪክ መንገድ ይመጣል፡

  • ከክርስቶስ ልደት 1000 አመት በፊት አካባቢ ዳዊት ኢየሩሳሌምን እንደ ዋና ከተማ መሰረታት ፡፡
  • ከ40 አመታት በኋላ ንጉስ ሰለሞን በዚያ የመጀመሪያዉን ቤተ መቅደስ ገነባ ፡፡
  • በ568ከክርስቶስ ልደት በፊት ባቢሎናዊያን ቤተ መቅደሱን በማፍረስ አይሁዶችን በምርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዷቸዉ ፡፡
  • ከ50 አመታት በኋላ አካባቢ የፋሪሳዊያን ንጉስ ቂሮስ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ እንዲሰሩ ፈቀደላቸዉ ፡፡
  • በ332 ከክርስቶስ ልደት በፊት ታላቁ አሌክሳንደር ኢየሩሳሌምን ያዘ ፤ ለብዙ መቶ አመታት የከተማዋ በቁጥጥር ስር መሆን በተለያዩ ቡድኖች መካከል አልፈዋል ለምሳሌም ሮማዉያን፣ ፋሪሳዊያን፣ አረቦች፣ በጦረኞች፣ ግብፃዊያን እና እስላሞች ፡፡
  • በ37 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሄሮድስ ሁለተኛዉን ቤተ መቅደስ ገነባ ፡፡
  • በ30 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ኢየሱስ ተሰቀለ ፡፡
  • በ70 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ሮማዉያን ሁለተኛ ቤተ መቅደሱን አጠፉት ፡፡
  • በ632 ከክርስቶስልደት በኋላየእስልምና ነቢዩ ሙሀመድ ሞተ ፤ እስላሞች ሙሀመድ ከኢየሩሳሌም ተራራ ከቤተ መቅደስ ከሰማይ እንደ ወረደ ያምናሉ ፡፡
  • በ691 ከክርስቶስ ልደት በኋላ የአለት ጉልት አንድ የእስልምናየተቀደሰ ስፍራን ሙሀመድ ከሰማይ ወርዶበታል ብለዉ በሚያምኑበት በቤተ መቅደሱ ተራራ ላይ ገነቡ ፡፡
  • በ1099-1187 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ኢሮፓዉያን ክርስቲያኖች ከተማዋን እንደ ገና በመቀበል መንፈሳዊ ጉዞን በማድረግ ከተማዋን እንደ ሀይማኖታዊ ስፍራ ጠበቋት ፡፡
  • በ1516-1917 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ኢየሩሳሌምና አብዛኛው መካከለኛዉ ምስራቅ በኦቶማን ስርዓት/አገዛዝ የተመራ ነበር ፡፡
  • በመጀመሪያዉ የአለም ጦርነት ጊዜ ታላቋ ብሪታኒያ ኢየሩሳሌምን እና በዚያን ጊዜ በፍልስጤማዊያን የነበረዉን ዙሪያዉን ክልል ተቆጣጠረች ፡፡
  • በ1948 ከክርስቶስ ልደት በኋላ እስራኤል ነፃነቷን በማወጅ በሁሉም በፍልስጤም ግዛት ላይ ከታላቋ ብሪታኒያ ተቀበለች ፡፡
  • በ1980 ከክርስቶስ ልደት በኋላ እስራኤል የኢየሩሳሌም ከተማ ዋና ከተማዋ እንደ ነበረች አወጀች ፡፡
  • በ1948 በመጀመሪያዎቹ 20 አመታት በኢየሩሳሌም መመስረት ጊዜ ኢየሩሳሌም ወደ አራት ክፍል ተከፋፍላ ነበር፡ እስራኤል የከተማዋን ምዕራብ ስትቆጣጠር ጆርዳን ደግሞ ምስራቅ ኢየሩሳሌምን ተቆጣጥራ ነበር ፡፡ በ1967 በእስራኤልና በአረብ አገራት በግብፅ፣ በሶሪያ እና በጆርዳን መካከል ከስድስት ቀን ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ እስራኤል አብዛኛዉን የኢየሩሳሌምን ክፍል ወሰደች/ተቆጣጠረች ፡፡
  • የቤተ መቅደሱ ተራራ በፍልስጤማዉያን እጅ ያለና የመስጊድ ስፍራ የሆነ እንዲሁም ደግሞ በእስላም ሰዎስተኛዉ ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡ ለአይሁዶች እንደ ቤተ መቅደስ ስፍራ ቅዱስ ስፍራ ሲሆን፣ ለክርስቲያንም ቅዱስ ስፍራ ነዉ ምክንያቱም መሲሁ የሚመለስበት ስፍራ ስለሆነ ፡፡

እስራኤል ሁሉንም ኢየሩሳሌም መቆጣጠርን አግኝታለች ከቤተ መቅደሱ ተራራ በስተቀር ፡፡ እስራኤል በቤተ መቅደሱ ተራራ ዙሪያ ደህንነትን ስትጠብቅ የእስልምና ኃይል ደግሞ በቤተ መቅደሱ ተራራ ላይ የሚሆነዉን ይጠብቃል ፡፡ በኢየሩሳሌም የግጭት አይነቶች ለምን እንዳሉ ለማየት ቀላል ነው ፤ አይሁዶች በቤተ መቅደሱ ተራራ ላይ የተፈቀደላቸዉ አይደሉም፣ የቀድሞዉ የአይሁድ መሪ የአሪየል ሻሮን ጉብኝት በእስራኤል ላይ ሁለተኛዉን የፍልስጤማዊያንን አመፅ አምጥቷል ፤ ግጭቱም እያለ ኢየሩሳሌም የእግዚአብሄር ከተማ ናት ፡፡ ሰዎችን ለኢየሱስ መመለስ ማዘጋጀት አለብን ፡፡

12 Available at https://www.history.com/topics/ancient-middle-east/history-of-jerusalem.

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 679.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 185.

  3. Wiersbe, p. 185.

  4. Wiersbe, pp. 185–186.

  5. Wiersbe, p. 186.

  6. Nelson’s Commentary, p. 680.

  7. Nelson’s Commentary, p. 680.

  8. Nelson’s Commentary, p. 680.

  9. Wiersbe, p. 186.

  10. Nelson’s Commentary, p. 680.

  11. Wiersbe, p. 186.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (46፡ 1) ካነበባችሁ በኋላ ቁጥር ሁለትንና ሰዎስትን በልበ ሙሉነት መድገም ትችላላችሁ ? አይደለም ከሆነ ለምን እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  2. መዝ (46፡ 8) እና መዝ (19፡ 1) ላይተመልከቱ ፤ እነዚህ ጥቅሶች እንዴት ይመሳሰላሉ ? አነዚህስ “ ስራዎች “ ምንድን ናቸው ?
  3. መዝ (46፡ 10) “ እረፉ እኔም አምላክእንደ ሆንሁ እወቁ “ ይላል ፤ በዚያ ፋንታ ሌሎች ትርጉሞች “ ጥረትን ማቆም “ ይላሉ ፤ ይህን እንዴት ታደርጋላችሁ ?
  4. መዝሙር 47 በሁለት ወይም በሰዎስት ንግግሮች እንዴት ታጠቃልሉታላችሁ ? በተለዬ መልኩ ይህ ምዕራፍ ስለ እግዚአብሄር ምን ይላል ?
  5. በመዝሙር (46-48) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 46:10–11

“‘Stop your fighting—and know that I am God, exalted among the nations, exalted on the earth.’ Yahweh of Hosts is with us; the God of Jacob is our stronghold. Selah”

እንዴት ልታልፈው እንደምትችል ለማወቅ ለአንተ በጣም ከባድ እንደሆነ በሚሰማህ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለኸው ? ፈተናው ከባድና ተስፋ አስቆራጭ ይመስላል ፡፡ በቃ ምን እንደምታደረግ ፣ ምን እንደምትል ፣ ወደ ማን ፊትህን እንደምታዞር አታውቅም ፡፡ ብቸኝነት ይሰማሃል ፣ እንደተነጠልክ ፣ እንደተያዝክ መውጫ እንደሌለህ ፡፡

የምስራች ፡- እግዚአብሔር ወጊያህን ስለ አንተ አንደሚዋጋ ይናገራል ፡፡ እርሱ በፊትህ ይቀድማል ፡፡ እርሱ ከኋላህም ይከተልሃል ፡፡ እርሱ አትፍራ ይልሃል ፡፡ በተጨማሪም ዝም እንድትል ይነግርሃል ፡፡ መሞከሩን አቁም ፡፡ እንደገና መፈለጉንም አቁም ፡፡ “ ቢሆንስ “ እያልክ ማሰቡን አቁም ፡፡ ልክ ለመሆን መሞከሩን ወይም ማመካኘቱን አቁም ፡፡ በቃ አቁመው ፡፡ እረፍት ውሰድ ፡፡ ለእግዚአብሔር ምርኮኛ ሁን ፡፡ በህዝቦች ላይ ከፍ ከፍ ያለው ያ እግዚአብሔር ራሱ ሊያግዝህ ፣ ሊወድህና በምትሄድበት ሁሉ አብሮህ ሊሆን ቃል ገብቷል ፡፡ እግዚአብሔር ውጊያህን ይዋጋ ዘንድ ይችላል ፡፡ ጠላቶችህን ማቆም ይችላል ፡፡ እርሱ የብረት ሰንሰለትን መበጠስ ይችላል ደግሞም ጠንካራ ምሽግን እንድሁም የዘመናት ባርነትን ይሰብር ዘንድ ይችላል ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከቀን ወደ ቀን እግዚአብሔርን ታመን ፡፡ አቅጣጫንና ምሪትንም ሲሰጥህ እርምጃን ውሰድ ፣ ቃሉንም ተናገረው ፣ መጽሀፍ ቅዱስንም አንብብ ፡፡ ነገር ግን እስከዚያ ድረስ ፣ በእርሱ እረፍ ፡፡ እርሱ በፍቅር እጆቹ ይዞሃል !

“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ ። የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው ። “

  • መዝሙር 46፡10-11

ተጨማሪ ጥቅስ

2ኛ ዜና 32:7–8a — “ ጽኑ፥ አይዞአችሁ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም ። ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ብሎ አጸናናቸው ። “

መዝሙር 46:1–3 — “አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው ። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም ። ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ ። “

ኢሳይያስ 45:2 – “በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ “