Wisdom Books Psalms

A Royal Wedding Song

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 43-45 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 412 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ስለ መዝሙር 45 እናወራለን - ንጉሳዊ የሰርግ መዝሙርን ፡፡ በኔልሰን ማብራሪያ መሰረት የንጉሳዊ ሰርግ ዜማ የአዲስ ኪዳን ፀሀፊዎች ይህ በኢየሱስም ላይ እንደ ተገበሩት አይነት ሁኔታ የሰዉን ጋብቻ የሚያከብር/የሚያደምቅ ነው ፡፡ በመዝሙር 45 የተከናወነዉ የሰርግ መዝሙር ለሙሽራዉ ተመልሶ ወደ ሚመጣው የክብር ንጉስ ያመለክታል ፤ ይህ መዝሙር የሰዉን ጋብቻ ያከብራል በተጨማሪምየክርስቶስን የከበረ ዘመን ያከብራል ፡፡

የንጉሳዊ ጋብቻ መዝሙርን ጥንካሬዉን/ዜማዉን ለማስቀመጥ ኮንስታብል ብዙ ታሪካዊ ምልከታዎችን አድርጓል ፤ ንጉሱ ለሰርጉ ይዘጋጃል በተመሳሳይ ስዓትም ሙሽራዋ ሰርጉን ተስፋ እንዳደረገ የሚያግዛትን መካሪ ተቀብላለች ፡፡ ንጉሱና ሙሽራዋ እንደ ተዘጋጁ ህዝቡ ከእርሱ በሚወለዱት ልጆች ምክንያት ንጉሱን ለዘላለም እንደሚያከብሩት መዝሙሩ አመልክቷል ፡፡ ይህ ሁሉ ከክርስቶስ ጋር ስላለዉ ለመጨረሻ የጋብቻ ድግስ በትንቢታዊ ንግግር ተከስቷል ፡፡ የሰዉ ጋብቻ የክርስቶስና የክርስቶስ አካልን የሚያምል መልክ ነው ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚመራ ሰዉ ሚስቱን የሚመራ ነው ፡፡ የቆሬ ልጆች ይህን የፍቅር መዝሙር ለመዘምራን አለቃ ፅፈውታል ፡፡ የቆሬ ልጆች ይህን መዝሙር በፃፉ ጊዜ በኃሳባቸዉ ዉስጥ ሰለሞን ነበር ፡፡ ሰለሞን የግብጢያንን ቆነጃጅቶች/ሉዑላንን አግብቷል ፤ ሰለሞን እንደ ንጉስ የተቀባ ነበር ፤ በወርቅ ኃብቱ በጣም የታወቀ ነበር ፤ ከጢሮስ ከተማ በቅርብ የተገናኘ/የተወዳጀም ነበር ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (45፡ 1-2)፡ ዋይርስቤ ይህን ንጉስ ለመግለፅ አራት መንገዶች አሉ ብሏል ፡፡ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮች ዋይርስቤ የሰዉ ታላቅ/የከበረ ልጅ በማለት ይገልፀዋል (ቁጥር 1-2) ፤ እዚህ ላይ መዝሙሩ ንጉሳዊ ሙሽራዉን እንደ አንድ ደስታና መነሳሳት ይገልፀዋል ፡፡ ንጉስ ሳዖል “ እንደ ሚማርክ መልካም ልጅ “ ተገልጧል (1ሳሙ 9፡ 2) ፤ ንጉስ ዳዊት ደግሞ እንደ መልከ መልካም ተገልፆ ነበር (1ሳሙ 16፡ 12) ፡፡ የሚመጣዉን መሲህ ኢሳያስ “ መልክና ዉበት የለዉም ባየነዉም ጊዜ እንወድደዉ ዘንድ ደም ጋባት የለዉም “ (ኢሳ 53፡ 2) ባለ ጊዜ በሚያስደንቅ ሁኔታ ይበቃል ፤ ነገር ግን እነዚህ ጥቅሶች በኢሳያስ በመከራዊ ጊዜ ኢየሱስን ገልፀዉታል ፡፡ “ ሞገስ በከንፈሮቹ ፈሰሰ “ የሚለዉ ሀረግ ንጉሱ በሚገባ ይናገራል ማለት ነበር ፡፡

መዝሙር (45፡ 3-5)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዋይርስቤ ንጉሳዊ ሙሽራዉን እንደ ድል አድራጊ ተዋጊ ገልፆታል ፤ ንጉሱ ስለ እዉነት፣ ስለ ትህትናና ስለ ፍትህ ይቆማል (ቁጥር 4) ፡፡ አንድ ተዋጊ በእዉነት፣ በትህትና በፍትህ መጓዝ ብዙ ጊዜ አይሆንም/አይደለም ፡፡

መዝሙር (45፡ 6-7)፡ ቀጥሎም ዋይርስቤ ንጉሳዊዉ ሙሽራን እንደ ፃድቅ ንጉስ ገልፆታል ፡፡ እዚህ ላይ መዝሙሩ ስለ አንድ ሰዉ ከማዉራት ስለ እግዚአብሄር ማዉራት ተለወጠ ፡፡ ሮበርት ቺሾልም መዝሙረኛው “ ንጉሱ እግዚአብሄር ነዉ እያለ ሳይሆን በእግዚአብሄር ስፍራ በመቆም እግዚአብሄርን ይወክላል ማለቱ እንደ ነበር “ ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሄርን የወከለዉ የሰዉ ንጉስ ኢየሱስን ይገልፃል ፤ በቁጥር 6 ግልፅ የሆነ አንድ መሲሀዊ አቅጣጫ ነበር ፡፡ የንጉሱ በትር “ የፍትህ/የቅንነት በትር “ ተብሎ ይጠራ ነበር (ቁጥር 6) ፤ በራዕ (11፡ 15) ከሰማይ የሆነዉ ድምፅ “ የዓለም መንግስት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሳል ! “ ይላል ፤ ይህ በእርግጠኝነት ከመዝ (45፡ 6) በሚመሳሰል መልኩ ይናገራል ፡፡ ዕብ (1፡ 3) ኢየሱስን “ እንደ እግዚአብሄር ክብር ነፀብራቅና የመልኩ ትክክለኛ መገለጫ “ እንደ ሆነ ይገልፀዋል ፡፡ ኢየሱስ ስለ እኛ ለመሞት በምድር ላይ የመጣ አምላክ/እግዚአብሄር ነበር፣ ከዚያም “ በታላቁ በክብር በቀኝ እጁ በኩል በመቀመጥ “ አበቃ ፤ ይህ ስዕል ዙፋኑ ለዘላለም ከሆነበት እና የመንግስቱ በትር የቅንነት ከሆነዉ ከመዝ (45፡ 6) ጋር ይሄዳል ፡፡

መዝሙር (45፡ 7-17)፡ ከዚያም ዋይርስቤ ንጉሳዊዉን ሙሽራ እንደ ታላቅ ሙሽራ ገለፀው ፤ በቁጥር 7 እግዚአብሄር እንደ አባት እና እንደ ልጅ በሁለቱም እግዚአብሄር የቀረበ ነው ፡፡ አንዳንዶች “ ከእናንተ ወዳጆች በላይ “ የሚለዉ ሀረግ የእግዚአብሄር ልጅ ከመለዓክት በላይ ነዉ ማለት ነዉ ይላሉ ፡፡ ዕብ (1፡ 5-9) በዚህ መዝሙር የተደረጉትን ንግግሮችን ይደግማል ስለሆነም መዝ (45፡ 6-7) ወደ ኢየሱስ ይጠቁማል ፡፡ የቆሬ ልጆች ሙሽራዉን ለማግኘት ስለ ተዘጋጀዉ ሙሽራ ፅፈዋል ፡፡

በቁጥር 8-9 ንጉሱ በተዋቡ ሴቶች የተከበበ ነበር ፤ ሙሽራዉም በወርቃማ ልብሶች የተዘጋጀች ነበረች ፡፡ በቁጥር 10 የመዝሙሩ ሽግግር በሙሽራዋ ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን ተግባራችን ለሙሽራዉ መመለስ ዝግጁ ማድረግ ነው ፡፡ መላዉ ኑሮአችን እና ስራችንን ለእርሱ ማድረግ ያስፈልገናል ፡፡

ኮንስታብል ሙሽራዋን “ እርሱን በጣም የሳበች ራሷን በማድረግ “ “ ባሏን የፍቅሯ መጀመሪያ አላማ የምታደርገው “ እንደ ነበረች ይገልፃል ፡፡ የሰዉ ጋብቻ ጤነኛ አመለካከት ሲኖራችሁ የክርስቶስ መመለስ ጤነኛ አመለካከት ይኖራችኋል ፡፡ ቁጥር 12 ሙሽራዋ ሙሽራዉን የመጀመሪያዋ ምርጫ /መጀመሪያ ስታደርገው ሰዎች ወደ እርሷ ይሳባሉ ምክንያቱም ከንጉሱ ጋር ስለተገናኘች ፡፡ መዝሙሩ ሙሽራዋንና በደስታና በሀሴት ወደ ንጉሱ ቤት ለመግባት ስለ ተመሩት ጓደኞቿ በመግለፅ ይጠቀልላል (ቁጥር 13-15) ፡፡ ህዝቡም ንጉሱን ከዘላለም እስከ ዘላለም ያመሰግኑታል (ቁጥር 17) ፡፡

ሮስ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ራዕ (19፡ 6-21) በፃፈ ጊዜ መዝሙር 45 በሀሳቡ ዉስጥ እንደ ነበር ይናገራል፡ “ በሰማይ የበጉን የክርስቶስን ሰርግ ወደ ፊት ሲመለከት ለእርሱ ሙሽራዋ ፅድቅን በመልበስ ራሷን እንዴት እንደ ምታዘጋጅ እንደ ገና ይናገራል “ ፤ ራዕ (19፡ 6-8) የበጉን ሰርግ ይገልፃል፡ ሙሽራዋ “ ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጎናፀፍ ተሰጥቶአታል ፡፡ ቀጭኑ የተልባ እግርየቅዱሳን ጽድቅ ስራ ነውና “ (ራዕ 19፡ 8) ፡፡ ከዚያም በራዕ (19፡ 11-12) ዮሐንስ ንጉሳዊዉ ሙሽራ በፅድቅ ለመዋጋት ወደ ፊት እንደሚሄድ ገልፆታል ፡፡

መደምደሚያ

ይህ ንፁህ መልክ ነው ፤ እስካሁን ተመልሶ እንዳይመጣ ብቸኞቹ ምክንያቶች ከሆንን ይህ ደግነት እንድንደነቅ ያደርገናል ፡፡ እንደ ሙሽሪት/እንደ ሙሽራዋ ለሙሽራዉ ራሳችንን እንዴት ማዘጋጀት እንደ ምንጀምር እንፀልይ ፤ ይህ ከንስሀ መዝሙር በአንዱ ዉስጥ በመሄድ አሁንም በኑሮአችን ኃጢዓት እንዳለ የምናስተዉልበት ነዉ ማለት ነው ፤ ይህ ከቤተሰቦቻችን፣ ከወዳጆቻችን፣ ከጎረቤቶቻችን ተለይተን መሄድ ሲሆን በእርሱም ላይ ማትኮር እንችላለን፡፡ ምንም ይሁን ለእርሱ መመለስ እንዴት እንድትዘጋጁ መንፈስ ቅዱስ እንዲያሳያችሁ ጥጠይቃላችሁ ?

2 Kidner, p. 170; McGee, 2:750; Seth D. Postell, "A Literary, Compositional, and Intertextual Analysis of Psalm 45," Bibliotheca Sacra 176:702 (April-June 2019):146-63; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 197; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

6 Robert Chisholm, “A Theology of the Psalms,” in A Biblical Theology of the Old Testament, p. 266, edited by Roy B. Zuck, Chicago: Moody Press, 1991; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 198; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

10 Allen P. Ross, “Psalms.” In The Bible Knowledge Commentary: Old Testament, p. 828, edited by John F. Walvoord and Roy B. Zuck, Wheaton: Scripture Press Publications, Victory Books, 1985; quoted in Constable, p. 200; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 678.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 179.

  3. Wiersbe, p. 180.

  4. Wiersbe, p. 180.

  5. Wiersbe, p. 181.

  6. Constable, p. 198.

  7. Constable, p. 199.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (44፡ 6) “ በቀስቴ የምታመን አይደለሁምና ሰይፌም አያድነኝም “ ይላል፤ ያ ጥቅስ እንደ ድል አድራጊነትናድነትም ከራሳችን ዉጪ እንደሚመጣ ይናገራል ፡፡ በመፅሀፍ ይህን እዉነት የት ላይ ታገኙታላችሁ ? (ዘዳ 20፡ 4, መዝ 44፡ 7, ምሳ 21፡ 31, ሮሜ 10፡ 9-10, 1ቆሮ 15፡ 57, ዕብ 7፡ 25)
  2. መዝ (45፡ 2-8) ስታነቡ እነዚህ ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ እንደ ሆኑ ትስላላችሁ ? ከመዝሙር 45 የቀረዉ ሌላዉ ከኢየሱስ መመለስ በኋላ የእስራኤል መልክ የሚስል ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይችልም ?
  3. በመዝሙር (43-45) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 45:10–11

“Listen, daughter, pay attention and consider: forget your people and your father’s house, and the king will desire your beauty. Bow down to him, for he is your lord.”

ሙሽራ መሽራዋን ለማግባት እንደምትዘጋጅ ሁሉ ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ከእርሱ ጋር ለመገኛኘት ቤተ ክርስቲያንም መዘጋጀት አለባት ፡፡ መሽራው ይዘጋጃል አባትና እናቱንም ይተዋል መሽሪትም ከእርሱ ጋር አንደ ባልና ሚስት ለመጣመር አንድ ለመሆን ቤቷን ትተዋለች ፡፡ የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችው ቤተ ክርስትያን ከርስቶስን እንደገና ለማየት ራሷን ከኃጢአት አጥባ ፣ በቅድስና እየተመላለስችና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ በመሆን ራሷን ማዘጋጀት አለባት ፡፡ ለክርስቶስ ዳግም መምጣት ዝግጁ ነህ ?

ከትላንትናህ ጋር እየታገልክ ነው ? በዚህ አለም ምቾት ላይ እየተጣበክ ነው ፤ በሙሉ ልብህ ለእግዚአብሔር አልቆረጥክም ? እንደ አማኝ ለክርስቶስ ዳግም መምታት ለመዘጋጀት ያቀድሞ መንገድህን ከኋላህ በመተው በክርስቶስ ያለውን ተስፋ ልታጠብቅ ይገባል ፡፡ መንፈሱ ወደ አዲስ ፍጥረት እንድለውጥህ ፍቀድለት ፡፡ እግዚአብሔር ወደ ውስጥህ እንድገባና በውስጥህ ውበቱን እንድፈጥር ፍቀድለት ፡፡ እርሱ እንደሚችል እመን ፡፡ እንደ አማኝ ክርስቶስን እንድትመስል እግዚአብሔር ይቀርጽሃል ፡፡ ስለዚህም ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ የክብር ንጉሥ የሆነውን ለማግኘት ዝግጁ ሆነህ መቆም ትችላለህ ፡፡ ሊመጣ ላለው ለእርሱ ክብር መዘጋጀት ትችላለህ ፡፡ ኢየሱስ ተመልሶ ስለሚመጣ ተዘጋጅ ፡፡

“ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና ። “ - መዝሙር 45፡10-11

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኤፌሶን 5:25–27 — “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ ። “
  • ራእይ 19:7–8 — “ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ ። ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና ። “
  • ራእይ 21:1–2 — “አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም ። ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ ። “