Wisdom Books Psalms

Thanksgiving And A Cry For Help

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 40-42 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 411 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሁሉም በእነዚህ መዝሙሮች እያንዳንዱን ሳምንንት ላይ ስንመለከት ስለ ሚመጣዉ መሲህ ወደ ሚያመለክተዉ አንድ ምዕራፍ አጉልተን ለማየት እንሞክራለን ፡፡ በዚህ መዝሙር ዉስጥ መሲሁን የት ላይ እንደምናየው አወያያችኋለሁ ፤ በመዝሙር 40 ዳዊት በአመስጋኝ ልብ በመጀመር ወዲያዉኑ ስለ እርዳታ ወደ መጮኽ ሄደ ፡፡ ደግሞ ደግሞ ይህን በመዝሙር ዉስጥ እናየዋለን ፡፡ ዋይርስቤ በመዝሙር 40 “ ዳዊት እግዚአብሄርን ስላደረገለት ሁሉ እንዳመሰገነው “ ፅፏል ፡፡ ይህ የዳዊት መዝሙር ለመዘምራን አለቃ ትዕዛዝ በመስጠጥ ይጀምራል ይህ ማለት ይህ ፅሁፍ በመዘመር የሚጀመር ነበር ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (40፡ 1)፡ እግዚአብሄር ፀሎቱን ስለ መለሰለት ዳዊት አመሰገነው ፡፡ እግዚአብሄር ዳዊት የሚያስፈልገዉን ሰጥቶትም ነበር ከአደጋም ጠብቆታል ፤ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር ዳዊትን ከጠላቶቹና ከሳዖል እንዳዳነው “ ፅፏል ፡፡ እግዚአብሄር የዳዊትን ጩኸት በመስማት መለሰለት ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ወደ እኔ ያዘነበለዉ ቃል የአለም ፈጣሪ መልክ ረዳት የሌላቸዉን ለማዳን ከዙፋኑ ላይ የሚያስቆመውን የሰማዩን ንጉስ የሚያቀርብ እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡ የሚያስገርመዉ ነገር ይህን ሁሉ እግዚአብሄር ማድረጉ ነው ! ወደ እግዚአብሄር በመመለስ እና በልበ ሙሉነት በመታመንና በማመን በምንጠብቀዉ ጊዜ ፀሎታችንን ይመልሳል (መዝ 130፡ 5) ፡፡ ወደ እግዚአብሄር እንዴት እንደምንፀልይ ዳዊት የሚያስደንቅ ምሳሌ ነው ፡፡

መዝሙር (40፡ 2)፡ ዳዊት እግዚአብሄር ከረግረግ ጉድጓድ/ጭቃ ዉስጥ እንዳወጣዉ ተናገረ ፡፡ ዳዊት በግልፅ በሚያሟልጥ ጉድጋድ ጭቃ ዉስጥ አልነበረም ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ዳዊት ይህን ግጥም በአስቸጋሪ ጭንቀት ሁኔታ ዉስጥ እንደፃፈው፣ በአንድ ጉድጓድ ወይም አረንቋ ዉስጥ እንደወደቀ እንደ ተሰማው ፤ መዉጣት ባለመቻሉ ለመሞከር አስቸጋሪ ቢሆንበትም ችግር እንዳልነበረው “ ይገልፃል ፡፡

መዝሙር (40፡ 3)፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ለማመስገን ለመዘመር ስለ አንድ መዝሙር ጠየቀ ፤ እዚህ ጋር “ እግዚአብሄር አሁንም በእኔ ዉስጥ አዲስ ነገር አስቀመጠ “ ሲል ዳዊትን አየዋለሁ ፡፡ ዋይርስቤ “ አንድ የቀድሞ ሀገር ሰባኪ ቁጥር 2-3 ለስብከት ፅሁፍ እንደ ተጠቀማቸዉናሀሳቡም፡ እግዚአብሄር እንዳመጣው፣ እንዳነሳውና እንዳ ስቀኘው/እንዳዘመረዉ ! “ ፅፏል ፤ ይህ ዝማሬ ዳዊት አዲስ ዝማሬ እንደ ተቀበለ ይገልፃል ፡፡ በአፉ ዉስጥ አዲስ ዝማሬ ማን አስቀመጠ ? በዚያ እንዴት አገኘው ? እግዚአብሄር ፤ እግዚአብሄር ዳዊትን አዲስ መዝሙር ሰጠው ፡፡ ኬ.ጃሰን ፍሬንች “ መዝሙሩ በዚያ በእግዚአብሄር ተቀመጠ ፤ እግዚአብሄር ! በሰዉ በደከመ ስራዉ አልተገኘም ፤ መዝሙረኛዉ “ አዲስ መዝሙር ተማርኩኝ ! አዲስ መዝሙር አገኘሁኝ ! የምስጋና መዝሙር በኔና ስለ እኔ በጥረቴ፣ በጥበቤ፣ በብልፅግናዬና በታላቅነቴ ! “ እንዳላለ ፅፏል ፡፡ ያ እንዴት እንደተፃፈ እንደሆነ ታውቃላችሁ ? ይህ ማለት እግዚአብሄር በእያንዳንዱ አንድ ቀን በእኛ ላይ ማፍሰሱን ይቀጥላል ማለት ይቻላል ፡፡ በዚህ አዲስ መዝሙር አሳብ ላይ እንመልከት ፤ እነዚህ መዝሙሮች ምስጋናን ያቀርባሉ፡ መዝ (33፡ 3, 96፡ 1, 98፡ 1, 144፡ 9, 149፡ 1) ፤ እነዚህ ጥቅሶች መዝሙር መዘመር ወይም ሙዚቃ መሳሪያ መጫዎት እንደ ምስጋና እንደሚቆጠር ያመለክታሉ ፡፡

“ በአፌም አዲስን ዜማ አስቀመጠ “ በሚለዉ ሀረግ ላይ ብዙ ጊዜዬን እያሳለፍኩ ነው ምክንያቱምበትክክል ወደ ወንጌላት ያመለክታል ብዬ ስለ ማስብ ፡፡ ኑሮአችንን በፍጥነት የሚቀይረዉ እግዚአብሄር ብቻ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ለድነት እድልን ይሰጠናል፡፡ የኔ ቀላሉ እቅድ አዲሱ ዜማ /መዝሙር የወንጌል ትንቢታዊ መልክ እንደ ሆነ ነው (1ቆሮ 1፡ 18-19፣ 2ቆሮ 5፡ 17) ፡፡ ስንድን በደም ታጥበናል (ሕዝ 36፡ 25-28, ዮሐ 3፡ 3, 5-8) ፡፡ ከጌታ በመምጣት ህዝቡን ወደ ጌታ በሚስበዉ አንድ መዝሙር መታደስነት እና አዲስነት አለ ፤ ህይወታችሁን ከአሮጌዉ ወደ አዲሱ እንዲቀይረዉ ክርስቶስን ከፈቀዳችሁለት ብዙዎች በማየት በጌታ ይታመናሉ ፡፡ የዚህ የሚቀጥለዉ አዲስ ዜማ በራዕ (14፡ 3, 15፡ 3) አንድ ጭብጥ አለው ፤ ራዕ (5፡ 9) ሁል ጊዜ ሰዎችን ወደ ራሱ ለማምጣት እግዚአብሄር አዲስ ነገር እንደሚያመጣ ያሳያል ፡፡

መዝሙር (40፡ 4-6)፡ “ ጆሮዬን ክፈት “ በሚለዉ ሀረግ ላይ ሁለት የተለያዩ አመለካከቶች አሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እግዚአብሄር ቃሉን እንድንሰማዉ ጆሮ ብቻ አይደለም የሚሰጠን እንድንረዳዉም እንጂ ስለዚህም በትክክል ልንታዘዘዉ እንደምንችል “ ይናገራል ፡፡ ኮንስታብልአንድ የተለዬ አመለካከት ፅሁፍ ያቀርባል “ ጆሮቼ በቶሎ/በኃይል ተከፈቱ (ተበሳ) የሚለዉ ሀረግ ዳዊት እግዚአብሄርን ለእርሱ በጣም የከበረ በማድረግ የፍቃዱ ባሪያ እንደ ሚያደርገዉ ተመለከተው (ዘጸ 21፡ 6) “ ፤ ወደ መጀመሪያዉ አመለካከት ለመደገፍ አዘነብላለሁ ፡፡

መዝሙር (40፡ 7-8)፡ ስለዚህ መዝሙር የመሲሁ መዝሙር ይሆናል በሚል ብዙ ክርክሮች አሉ ፤ ከክርክሮቹ አንዱ በሉቃ (24፡ 27) የሚገኝ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ዳዊት መስዋዕቱን ያመጣል ነገር ግን ትኩረቱ የራሱን ህይወት ለጌታ ማቅረብ እንደ ሆነ (ሮሜ 12፡ 1-2) “ ይናገራል ፡፡ ከመዝሙር አብዛኞቹን በአዲስ ኪዳን ዉስጥ መታየታቸው ማየት የሚያስደንቅ ነው ፤ በዕብ (10፡ 4-10) ኢየሱስ የዚህን መዝሙር ቃል ለአባቱ/ለአብ ተናግሮታል ፡፡

መዝሙር (40፡ 9-10)፡ የዳዊት ንግግር ስለ እግዚአብሄር ባህሪያት፡ ስለ ፅድቁ፣ ስለ መታመኑ፣ ስለ አዳኝነቱ፣ ስለ ፍቅሩ እና ስለ እዉነቱ ፡፡

መዝሙር (40፡ 11-17)፡ ዳዊት ከማመስገን እንዴት ለእርዳታ ወደ መጮኽ እንደ ሄደ ማዉራታችንን ቀድሞ እናስታውሳለን ፡፡ ያን የምናይበት እዚህ ነው ፤ ሙሉ ለሙሉ የተለዬ ፅሁፍ ይመስላል - አብዛሀኛው የኑሮአችንን ከፍ እና ዝቅ ማለትን ይመስላል ፡፡ ችግሮቹ እያሉ ዳዊት እግዚአብሄርን ታመነ ፤ ችግሮቻችን እያሉ እግዚአብሄርን መታመን እንችላለን ፡፡

መደምደሚያ

በክርስቶስ እንደ አማኝ ተስፋችን በእግዚአብሄር ላይ በስሜታዊነት ያስቀመጥንበት ስፍራ ችግር እንደ ሌለዉ እናዉቃለን ፡፡ ተስፋ ተሰጥቶናል ፤ ያ ለእኔ ረጋ ያለ መልክ ነው ! ዳዊት እግዚአብሄርን ሲያመሰግን እግዚአብሄርም የጠየቀዉን ሁሉ ሲሰጠዉና ሲታመንለት አይተናል ፡፡ ለመከተል ይህ ታላቅ ምሳሌ ነው ፤ ይህ የክብሩን ንጉስ ክርስቶስን ከሚያመለክቱ መዝሙሮች አንዱ ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 923.

  2. Wiersbe, p. 923.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 675.

  4. Nelson’s Commentary, p. 675

  5. Wiersbe, p. 923.

  6. K. Jason French, God Put a Song in Your Heart; available at https://www.desiringgod.org/articles/god-put-a-song-in-your-heart.

  7. Nelson’s Commentary, p. 675.

  8. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 183; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  9. Nelson’s Commentary, p. 675.

ጥያቄዎች

  1. በመዝሙር 40 ዳዊት ለእኛ የእግዚአብሄርን “ እቅድ ለመዘርዘር በጣም ብዙ “ ነዉ አለ ፤ ጌታ ለእናንተ ያለዉን እቅድ አስባችሁት ታውቃላችሁ ? በህይወታችሁ ያለዉን እቅድ ለማሰብ አሁን ትንሽ ደቂቃ ውሰዱ ፤ ምን እንደ ሆኑ ምን ታስባላችሁ ?
  2. በመዝ (42፡ 1) ላይ አሰላስሉ ፤ ነፍሳችሁ ስለ እግዚአብሄር ናፍቃ ታውቃለች ? አዎ ከሆነ መታደስን/መፅናናትን የት አገኛችሁ ?
  3. በመዝ (42፡ 5-6) ዳዊት ስለ ራሱ ነፍስ ተናገረ ፤ ራሳችሁ ነፍሳችሁን “ የደስታ ንግግር “ ስትሰጡ ታገኙታላችሁ ? ዳዊት ተስፋ በእግዚአብሄር ላይ አደረገ ፤ እናንተም ናችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አይደላችሁም ? ይህን እንዴት ታደርጉታላችሁ ?
  4. በመዝሙር (40-42) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 40:1–3

“I waited patiently for the LORD, and He turned to me and heard my cry for help. He brought me up from a desolate pit, out of the muddy clay, and set my feet on a rock, making my steps secure. He put a new song in my mouth, a hymn of paise to our God. Many will see and fear and put their trust in the LORD.”

ህይወት በውጣ ውረድ የተሞላች ናት ፡፡ አንድ ጊዜ ራስህን በተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ ውስጥ ስታገኘው በቀጣዩ ጊዜ ደግሞ በተራራ ጫፍ ላይ እንዳለህ ይሰማሃል ፡፡ ህይወት ባልተጠበቁ ደስታዎችና ፈተናዎች ውስጥ እንደምትቀጥል ሁሉ ሁሉም ሰው በእነዚህ ስሜቶች ውስጥ ያልፋል ፡፡ አንድ ነገር እርግጥ ነው ክርስቶስ የመጣው አዲስ ዝማሬን በአፍህ ሊጨምር ነው ፡፡ ክርስቶስ የመጣው የእርዳታ ጥሪህን ሊሰማ እንድሁም በታላቅ ፍቅሩ ሊሞላህ ነው ፡፡ ክርስቶስ የመጣው ከሸክላ ጭቃ ጉድጓድ ውስጥ ሊያወጣህ ነው ፣ እግሮችህን በደህንነት ዓለት ላይ ሊያጸና ነው ደግሞም እርምጃህን ሊያቀና ነው ፡፡ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ነህ ፡፡

ስለዚህ በችግር ውስጥ ሳለህ ወደ እርሱ ጩኽ እርሱም ይሰማሃል ፡፡ የከበበህ ፈተና ምንም ያህል ይሁን ኃጢአትህ ተቆጣጥሮህ ከሆነ ወይም አጥርተህ ማየት ካልቻልክ እግዚአብሔር ይታደግሃል ፡፡ እርሱ ያስመልጥሃል ይረዳህማል ፡፡ ጓደኛዬ እግዚአብሔር በአንተ ደስ ይሰኛል ፡፡ በጨለማ ስፍራ መመላለስ አያስፈልግህም ፡፡ ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ ፡፡ አዳኝህና አምላክህን አመስግን ፡፡ በወጀቡ ፣ በጭጋጉ በከባዱ ቀን እርሱን አመስግነው ፡፡ የእግዚአብሔርን ስም ባርክ !

“ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ ። ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና ። አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ፤ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል፥ በእግዚአብሔርም ይታመናሉ ። “

  • መዝሙር 40፡1-3

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 40:17 — “እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል፤ አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ፤ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ ። “

መዝሙር 42:11 — “ ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ ። “

2ኛ ቆሮንቶስ 5:17 — “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል ። “