Wisdom Books Psalms

Focusing On God Rather Than God Or Others

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 38-39 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 410 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የመዝሙር 38 መልዕክት በጣም የሚያበረታታ ነው ፤ ይህ መዝሙር ኃጢዓት መስራቱን ስለማመኑና ተቀብሎት ስለ ነበረዉ ቅጣት ነው ፡፡ ኮንስታብል “ ይህ ቅጣት ዳዊት እግዚአብሄር እንዲያስወግዳቸዉ ጠይቆት ከነበሩት ጠላቶቹ ተቃዉ እንደ መጣ “ ይገልፃል ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ጠላቶቹን እንዲያስወግድ ጠየቀው ነገር ግን በኃጢዓቱ እንደ ተቀጣበት አስተዋለ ፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ኃጢዓት ስናደርግ ዉጤት ይኖረዋል ፡፡ ኢየሱስን የማታዉቁት ከሆነ ያ ዉጤት ሞት ነዉ የሚሆነው ፤ ይህ የመፀፀት ፀሎት ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የፀፀት መዝሙር ለራሳችን ንስሀና እግዚአብሄር ሊያስተካከለን የሚፈልገዉን አይነት ባህሪይ ማስጠንቀቂያአንድ ምሳሌ እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡

ሰባት የፀፀት መዝሙሮች አሉ፡ መዝሙር (6, 32, 38, 51, 102, 130 እና 143) ፡፡ መዝሙር 51 የዳዊትን የንስሃ ፀሎት ያቀርባል፡ “ በዉስጤ ንፁህ ልብን አድርግልኝ “ ፡፡ ዋይርስቤ “ ሁሉም መዓቶች/መቅሰፍቶች ካለመታዘዝ አይመጡም ነገር ግን አካላዊ ችግሮች/መከራዎች የኃጢዓት ዉጤት ሊሆኑ እንደ ሚችሉ “ ያመለክታል (ዮሐ 9፡ 1-3, 5፡ 14) ፡፡ በመዝ (38፡ 18) ዳዊት ኃጢዓቱን ለመናዘዝ ባለማመነታት “ ባለምህረት የሆነዉ እግዚአብሄር ይቅር እንደሚለዉና እንደሚያድሰው “ ጠብቋል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (38፡ 1-8)፡ዋይርስቤ ከእነዚህን ቁጥሮች የሚወሰደዉን መልዕክት “ በራሳችን ላይ ማትኮር እንድንችልና የኃጢዓትን ህመም እንደምንቀምሰው “ ይገልፃል ፡፡ ዳዊት በእግዚአብሄር ቅጣት በጭንቅ እንደ ነበርና “ እግዚአብሄር ከባድ የሆነዉን እጁን በቁጣ በክፉዎች ላይ እንዳደረገው እንደሚያስቀምጥበት ተሰማው “ ፡፡ የእግዚአብሄር ቅጣት ወደ እርሱ እያደከመዉ እንደሆነና ጤንነቱና ጥንካሬዉም እንኳን በኃጢዓቱ እንደ ተጎዱ ተሰማው (ቁጥር 2-3, 7) ፤ ይህ ማለት እግዚአብሄር ሁሉንም ጤንነታችንን በመዉሰድ ይቀጣናል ማለት አይደለም፡፡ አብዛሀኛው ህመም በቀላሉ በወደቀ፣ በተሰበረ እና በአረጀ አለም የመኖር ዉጤት ነው ፡፡ የዳዊት ኃጢዓት ለመሸከም ለእርሱ ታላቅ ሸክም ሆኖበት ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ ዳዊት ከተሸከመዎ የቁስል መግል የሰዉነት ሽታ እንኳን ነበረኝ አለ (ቁጥር 5) ፡፡ ከባዱ ሸክም ቋሚ በሆነ ኃዘን የታጠፈ እንዲሆን ምክንያት ሆነው (ቁጥር 6) ፡፡ ዋይርስቤ የዳዊትን ድርጊት “ዘመኑን ሁሉ በቀብር ስርዕታ ላይ በመሆን እንደተጓዝ አንድ ሰው “ ይገልፀዋል ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄርን ላለመታዘዝ ነፃ ነን ነገር ግን ዉጤቱን መቀየር አንችልም “ በማለት አጠቃሏል ፡፡

መዝሙር (38፡ 9-14)፡ዋይርስቤ ከእነዚህን ቁጥሮች የሚወሰደዉን መልዕክት “ በሰዎች ላይ ማተኮር እንደ ምንችላና የኃጢዓትንብቸኝነትን እንድንቀምሰው “ ይገልፃል ፡፡ ዳዊት ስለ ጤንነቱ ጉዳይ ማዉራቱን ቀጠለ - ስለ ልቡ፣ ስለ ጥንካሬዉ እና ስለ እይታው (ቁጥር 9-10) ፤ወዳጆቹና ዘመዶቹ ከእርሱ ርቀዉ ቢቀመጡም እንኳን (ቁጥር 11) ፡፡ ዳዊት እያለፈበት የነበረዉ በዙሪያዉ ባሉት በሌሎቹ ላይ ተፅዕኖ እያመጣ ነበር (ኢዮ 2፡ 9-10) ፤ ዳዊትን በማሳደድ ወጥመድ ያስቀመጡበት እና በእርሱ ላይ ያሴሩበት ሰዎች ነበሩ (ቁጥር 12) ፡፡ መስማት እንደ ማይችልና እንደማይናገር ሰዉ ተሰማው (ቁጥር13-14) ፤ በንግግር የሚያደርገዉ ክርክር አልነበረዉም ፡፡ አንዳንድ ስነ መለኮታዊያን ይህ በከሳሾቹ ፊት የኢየሱስ ዝምታ ጥላ እንደ ሆነ ያመለክታሉ (ማር 14፡ 61) ፡፡

መዝሙር (38፡ 15-22)፡ ዋይርስቤ ከእነዚህ ቁጥሮች የሚወሰደዉን መልዕክት “ በእግዚአብሄር ላይ ማተኮር እንደ ምንችልና የኃጢዓትን ምህረት እንደ ምናገኝ “ ይገልፃል ፡፡ ኮንስታብል ስለነዚህ ቁጥሮች “ ዳዊት እግዚአብሄርን በመጠበቅ በችሎታዉ የሚያስደንቅ እንደ ነበር “ ይፅፋል (ቁጥር 15) ፡፡ ዳዊት በጌታ ያለዉን ተስፋ አሳወቀ ፤ ተስፋ የሚለዉ ቃል “ በተስፈኝነት መጠበቅ “ ሊሆን እንደሚችልና በልበ ሙሉነት ሊገለፅም ይችላል (ኢዮ 13፡ 15, ዕብ 10፡ 23) ፡፡ በመፅሀፍ ዉስጥ ለተስፋ ሌሎች ማጣቀሻዎች አሉ (ዘፍ 8፤ 12, ኢዮ 29፡ 21, ሕዝ 13፡ 6) ፤ ሁል ጊዜ የተስፋ ዓላማው/ግቡ እግዚአብሄር ነው - ቃሉ፣ ፍርዱና ምህረቱ ፡፡ የዳዊት “ በሳዖል እጅ የአመታት መከራው፣ በቢንያም ነገድ መተቸቱ/መገፋቱና በአቤሴሎም በተደረገበት ይህን እንዲያደርግ አስተማረው “ ፤ ዳዊት እግዚአብሄርን ጠላቶቹ በመከራዉ እንዲደሰቱ እንዳይፈቅድላቸዉ ጠየቀው (ቁጥር 16) ፡፡ ዳዊት በገመዱ/በዘመኑ መጨረሻ ላይ ደርሶ እንደ ነበር እዉቅና በመስጠት (ቁጥር 17) ኃጢዓቱን ተናዘዘ (ቁጥር 18) ፤ ዳዊትም እግዚአብሄርንእንዲቀርበዉና እንዲረዳዊ እንዲመጣ ጠየቀው (ቁጥር 19-22) ፡፡ ዋይርስቤ እዚህ ጋር ሰዎስት ኃሳቦችን እንዳደረገ ይናገራል፡ “ ከኔ ጋር ሁን……አጠገቤ ሁን……የኔ በመሆን እርዳኝ “ ፤ እነዚህ ንግግሮች የዳዊትን የኃጢዓት ንግግሮችና በእግዚአብሄር መገኘት የመታደስ ጥያቄን ያቀርባሉ ፡፡

መደምደሚያ

ዳዊት አንድ አዳኝ አስፈለገው - በአካላዊም በስሜታዊዉም የዳነ ለመሆን - በሁሉም የህይወቱ ክፍል ላይ ጣልቃ እንዲገባ እግዚአብሄርን ለመነው ፤ ታዳጊዉ እንዲሆን እግዚአብሄርን ጠየቀው ፡፡ ኮንስታብል “ አንዳንድ ጊዜ አማኞች በአካላቸዉ፣ በስሜታቸዉ እና የእርስ በእርስ ግንኙነታቸዉ ላይ በኃጢዓታቸዉ መከራን እንደሚያመጣ ፤ በእንደዚህ አይነት ጉዳይ እግዚአብሄር በህመም ስለሚቀጣን ተመሳሳይ ነገር ላለ ማድረግ እንማራለን ፤ በሂደቱም በእግዚአብሄር እና ከሁሉም ኃዘናችን በሚታደገን ላይ እምነታችንን እንደ ገና እንደ ምናረጋግጥ “ ይፅፋል ፡፡

ይህ ክርስቶስ በመጨረሻ ስለ እኛ ያደረገው ነው ፤ ክርስቶስ ድነትን ሊሰጠን ፈለገ ፡፡ ለአሁን ጥያቄው፡ በአሁኑ ሰዓት በህይወታችሁ ላይ ያተኮረዉ ማነው ? በክርስቶስ ደስታን ለመፈለግ የፀፀትን መዝሙር ማንበብ ያስፈልጋችሁ ይሆናል ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 177; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 674.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 167.

  4. Nelson’s Commentary, p. 674.

  5. Wiersbe, p. 168.

  6. Nelson’s Commentary, p. 674.

  7. Wiersbe, p. 168.

  8. Wiersbe, p. 168.

  9. Wiersbe, p. 168.

  10. Nelson’s Commentary, p. 674; John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 623.

  11. Wiersbe, p. 169.

  12. Constable, p. 179.

  13. Nelson’s Commentary, p. 674.

  14. Constable, p. 179.

  15. Wiersbe, p. 169.

  16. Constable, p. 177.

ጥያቄዎች

  1. የእግዚአብሄር እጅ በዳዊት ላይ “ ወደ ታች የሚጫንበት “ ምክንያቱ ምን ነበር ?
  2. በመዝሙር 38 ኢየሱስን ደርሶዉበት የነበሩትን ጥቂት ነገሮች የሚያስታዉሱ ጥቂት ቁጥሮች እነማን ናቸው ?
  3. የአለምና የእግዚአብሄር በሆነዉ ጭንቀት መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው (2ቆሮ 7፡ 9-10) ? እግዚአብሄር ይቅር እንደሚለዉ ዳዊት ሙሉ በራስ መተማመን አለው ? ምን አይነት ልበ ሙሉነት ነዉ ያላችሁ ? (1ዮሐ 1፡ 9)
  4. በክፉዎች ዙሪያ ዳዊት ምላሱን ለምን ገታ ? በአንዳንድ ሁኔታዎች ምላሳችሁን መግታት ለምን አስፈላጊ ነው ? (ያዕ 3፡ 2, 5-12)
  5. በመዝሙር 39 ዳዊት እንዴት ተስፋ ከማጣት ወደ ተስፋ ተጓዘ ? ከመዝሙር 39 በቁጥር 8-13 ለዉጥ ስለ ማምጣት ዳዊት ምን አደረገ ? በአስቸጋሪ ጊዜም እንኳን ቢሆን በክርስቶስ ተስፋ በዘላለማዊ እይታ እንኖራለን ትላላችሁ ? (1ዮሐ 2፡ 17)
  6. በመዝሙር (38-39) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 38:17–18, 21–22

“For I am about to fall, and my pain is constantly with me. So I confess my guilt; I am anxious because of my sin. LORD, do not abandon me; my God do not be far from me. Hurry to help me, LORD, my Savior.”

የኃጢአት ጥፋት እንደ ከባድ ሸክም በትከሻህ ላይ ይቀመጣል ፡፡ ታውቃለህ በኃጢአት ውስጥ ከኖሩ በኋላ ምርጫን መምረጥ ከእግዚአብሔር ፍቃድ ጋር እንደሚጋጭ ፤ ሰውነትህ እንኳ ሳይቀር በአካል ሊጎዳ ይችላል ፡፡ ይህ የኃጢአት ህይወት ለመሸከም የሚከብድ ቀንበር ይሆናል አካላዊ ጥንካሬህንም ጭምር ይወስድብሃል ፡፡ እንደተያዝክና ተስፋ እንደሌለህ ይሰማሃል ፡፡

ዛሬ ይህን ስማ ፡- በክርስቶስ ተስፋ አለህ ፡፡ ይህም በእግዚአብሔር ፊት ንስሀ በመግባት ይጀምራል ፡፡ እርሱ አልተወህም ፡፡ ልክ ልጁን ወደ ቤት እንደሚቀበል አባት እጆቹን ዘርግቶ ቆሟል ፡፡ ነገር ግን አንተ ወደ አባትህ እጆች ልትሄድና የፍቅር ሰላምታውን ማቀፉን ልትቀበል ያስፈልጋል ፡፡ ወደ ፊት ያሉት እርምጃዎች ከባድ ቢመስሉ እንኳ ደግሞም ከዚያ ሁሉ የጥፋት ስሜት መውጣት መፈወስ የሚቻል ባይመስልም ……. በኢየሱስ ባለው ተስፋ ላይ ተጣበቅ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር የማይቻል ምንም ነገር የለም ፡፡ አንተ እንድትኖር እርሱ ሞተ ፡፡ አንተ ነጻ እንድትወጣ እርሱ ሞተ ፡፡ ስለዚህ ራስህን ዝቅ አድርግ እንድሁም ፍቅሩን ትቀበል ዘንድ ከኃጢአት መንገድህ ተመለስ ፡፡ ወደ ፍቅር እጆቹ ስትሄድ ይመልስልሃል ፤ በደልህን እጠብ እንድሁም ራስህን ከኃጢአት አንጻ ፡፡ በፊትህ ባሉት እርምጃዎች ላይ እርሱ እንደ አዳኝ እንደ ቤዛ ያግዝሃል ፡፡ ወደ ተዘረጉ የፍቅር እጆቹ ሩጥ ፡፡ እርሱ በዚያ እየጠበቀህ ነው ፡፡ ታድያ ምን ትጠብቃለህ ?

“ እኔስ ወደ ማንከስ ቀርቤአለሁና፥ ቍስሌም ሁልጊዜም በፊቴ ነውና ። በደሌን እናገራለሁና፥ ስለ ኃጢአቴም እተክዛለሁ …….. አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፤ አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ ። አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፤ አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ ። “

  • መዝሙር 38፡ 17-18 ፤ 38፡21-22

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 38:15 — “ አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና፤ አቤቱ አምላኬ፥ አንተ ትሰማኛለህ ። “

መዝሙር 51:1–3 — “አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ ። ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ ፤ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና ። “

1ኛ ዮሐንስ 1:9 – “ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ። “