Wisdom Books Psalms

The Need For Patience In the Lord

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 37 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 409 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 37 አንዱ የምወደዉ መዝሙር ነው ፡፡ ለመዝሙር መፅሀፍ ቃላችን በዚህ በምድር ላይ የሰዉን ስጋ በመዉሰድና የእግዚአብሄርን ክብር የመሸከሙ የአምላክ ምስል የሆነዉ የክብር ንጉስ ነው ፡፡ መዝሙር 37 አንድ የጥበብ መዝሙር የሆነናበስርዓት እንደ ተደረደረ ቃላት የተፃፈ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ዳዊት ይህን መዝሙር ሰለሞን እንደ ንጉስ ስፍራዉን እንዲወስድ እያዘጋጀ በነበረበት ጊዜ እንደፃፈዉ ይናገራል (1ነገ 2፡ 1-3) ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ “ የመዝሙሩ ቀላል መልዕክት በችግሮች መካከል ዉስጥ በትዕግስት መቆየት የሚል እንደሆነ “ ይናገራል ፤ ይህ ስለ እግዚአብሄርና ስለ እስራኤል እንዲሁም ስለ ግንኙነታችን ካሉት መዝሙሮች ቁልፍ ምልዕክት ጋር የሚጣጣም ነው ፡፡ እስራኤል በዙሪያቸዉ እየሆነ በነበረዉ ነገር ሁሉ ትዕግስተኛ ሆነዉ መጠበቅ ቢችሉ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ባደረገዉ ኪዳን ዉስጥ ራሱን መግለጥ በሚፈልገዉ መግለጥ መጀመር ይችላል ፡፡ ዋይርስቤ የነበሩበት ምድር የእግዚአብሄር የራሱ ስለ ነበር ታዛዦች ከነበሩ በእርሷ ላይ እንዲኖር እንደሚፈቅዱለት ይገልፃል ፡፡ “ እስራኤል እግዚአብሄርን ባለመታዘዟ በመጀመሪያ በምድራቸዉ ይቀጣቸዋል ነገር ግን በአመፃቸዉ ከቀጠሉከምድራቸዉ ያስወጣቸዋል (በምርኮ) “ ፤ እግዚአብሄር እንዲታመኑት እየጠየቃቸዉ ነበር ፡፡ ይህ ከእስራኤል ጋር ታላቅ የእግዚአብሄር ኪዳን ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ መዝሙሩን በእነዚህ ክፍሎች ያቀርበዋል፡ “ 1) በቀላሉ ግልፅ በሆነዉ በክፈዎች ስኬት ትዕግስት ስለማስፈለጉ (ቁጥር 1-11)፣ 2) የክፉዎችን የመጨረሻ ፍርድ በቀላሉ ስለ ሚያስፈልገዉ ትዕግስት (ቁጥር 12- 22)፣ 3) በክፉዎች ተግባር እይታ ፃድቆችን ስለ ማበረታታት (ቁጥር 23-33) እና 4) በክፉዎች ግልፅ/ታይቶ በሚጠፋዉ ስኬት እይታ ስለ ትዕግስት የታደሰዉን ጥሪ “ ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (37፡ 1-11)፡ በበለፀጉ ክፉ አድራጊዎች አይበሳጩም ወይም አይጨነቁም (ቁጥር 1) ፤ “ አይሸበሩም/ አይናወጡም “ እንዲሁም እንደ አለመበሳጨት ተብሎ መረዳት ይቻላል ፡፡ “ መዝሙረኛው ስለ ትዕግስት፣ በእግዚአብሄር ላይ ስለ ታደሰዉ መደገፍ ሁኔታ እና እርሱን በማወቅ ስላዉ የታደሰ ሁኔታ ይጣራል “ ፡፡ ክፉዎች በአጭር ጊዜ/ለአጭር ጊዜ ይበለፅጋሉ ነገር ግን በፍጥነት ጠዉልገዉ ይሞታሉ (ቁጥር 2) ፤ ስለሆነም መዝሙረኛው በእግዚአብሄር እንዲታመኑ፣ ትክክል የነበረዉን እንዲያደርጉ እና በእግዚአብሄር ምድር በደህና ኑሩ አላቸው (ቁጥር 3) ፤ ይህ በተግባር የድነት መልክ ሳይሆን እምነት ነው ፡፡ በጌታ ደስ ይላቸዋል እርሱም በጣም ያስፈልጋቸዉ የነበረዉን ይሰጣቸዋል (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ፃድቆች ከእግዚአብሄር የሚመነጩ ፍላጎቶች በሚኖሯቸዉ ጊዜ እግዚአብሄር ፍላጎቶቹን በሚገባ ይፈፅምላቸዋል “ ፤ ( 1ተሰ 5፡ 16-18) ፡፡

ቁጥር 5 “ ማድረግና “ “በእግዚአብሄር ላይ ጣለዉ “ ይላል ፤ ያ ማለት እንዲይዝልን/እንዲያደርግልን ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሄር እንስጥ ማለት ነው (1ጴጥ 5፡ 7) ፡፡ ከቁርጠኝነት በኋላ በእግዚአብሄር ላይ መታመን ይመጣል ፤ እግዚአብሄር ፅድቃችንን ለመደገፍ ይሰራል (ቁጥር 6) ፡፡ መዝሙረኛዉ አሁንም በእርሱ ፊት በመሆን በተስፋ እንጠብቀዉ ብሏል (ቁጥር 7) ፤ በተጨማሪም ከንዴትና ብስጩ ካለመሆን እንዲቆጠቡ (ቁጥር 8) ምክንያቱም ክፉ አድራጊዎች ስለሚጠፉ እናየእግዚአብሄር ሰዎች ምድራቸዉን ስለሚወርሷት (ቁጥር 9) ፡፡ ስለ እነዚህ ቁጥሮች ሀሳብ ሲታሰብ በቁጥር 10-11 ዳዊት ሰለሞን ዙፋኑን እንዲወስድ እያዘጋጀዉ ነበር፡ ክፉዎች ይጠፋሉ ነገር ግን የዋሆች የእግዚአብሄርን ምድር ይወርሳሉ ፤ ኢየሱስ ይህን ጥቅስ በማቴ (5፡ 5) ጠቅሶታል ፡፡

ዋይርስቤ “ ምድሪቱን መዉረስ በተስፋይቱ ምድር የወደፊቱን ትዉልድ ደህንነት ያመለክታል፣ በእግዚአብሄር ኪዳን መሰረት እግዚአብሄርበሚመጣው መሲህ በተደመደመዉ በዚያ ምድር በሚደረገው ለፃድቅ ቅሬታዎቹ የሚያደርገዉ ታላቅ ስራ እንደ ነበረው “ ይገልፃል ፡፡ ( ዘፍ 12፡ 1-3, 13፡ 14-18, 15፡ 7-21) ፤ መዝሙር 37 መሲሁ በሚመለስ ጊዜ የምድሪቱ ተግባር ትንቢታዊ መልክ ነው ፡፡ ክፉዎች ይጠፋሉ (ቁጥር 9, 22, 28, 34, 38) ፡፡

መዝሙር (37፡ 12-21)፡ የክፉዎች ተግባር በጣም ያልተለመደ ስለ ነበር እግዚአብሄር ይስቅባቸዋል (ቁጥር 12-13)፡፡ ክፉዎች የሚፈልጉትን ለማግኘት ትክክለ የሆነዉ ላይ ተቃዉሞን በመጠቀም እርስ በእርሳቸዉ በተመሳሳይ መንገድ ይጠፋሉ (ቁጥር 14-15) ፡፡ እግዚአብሄር ፃድቆችን ሲረዳቸዉ የክፉዎች ክንድ ግን ይሰበራል (ቁጥር 16-19) ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር በማወቅ በነገሮቹም ላይ ይመለከታል ፤ “ 1) እግዚአብሄር ሁኔታዎቻችንን በማወቅ ለእኛ ይሰጠናል/እኛን ይታደገናል፣ 2) እግዚአብሄር ምን ያክል እንደ ምንኖር በማወቅ እስከ መጨረሻዉ ይደግፈናል፣ 3) እግዚአብሄር በምድር ላይ ዘመናችን በዘላለም ላይ ከእርሱ ጋር የዘመናችን መጀመሪያ ብቻ እንደሆነ ያውቃል “ ፡፡ ክፉዎች ይጠፋሉ ፃድቃን ግን ይለመልማሉ/ይበለፅጋሉ (ቁጥር 20-21) ፡፡

መዝሙር (37፡ 22-23)፡ እግዚአብሄር የባረካቸዉ ምድሪቱን ይወርሳሉ፣ እግዚአብሄር የረገማቸዉ ደግሞ ይጠፋሉ (ቁጥር 22) ፡፡ ቁጥር 23 የቁጥር 4 እዉነታ ነው፡ በእግዚአብሄር ደስ ይበለን መንገዳችንን ስለሚያቀና ፡፡

መዝሙር (37፡ 24-40)፡ እግዚአብሄር መንገዳችንን በማስተካከል ከመዉደቅ ይጠብቀናል (ቁጥር 24) ፤ በህይወቱ ዉስጥ መዝሙረኛው ለፃድቆች የእግዚአብሄርን የተትረፈረፈ ስጦታን አይቷል (ቁጥር 25-26) ፡፡ የእግዚአብሄርም ህዝቦች ከክፉ ይመለሳሉ ለዘላለምም በእግዚአብሄር ምድር ያድራሉ (ቁጥር 27-29) ፤ በእግዚአብሄር ቃል ላይም ይፀናሉ (ቁጥር 30-31) ክፉዎችን ግን እግዚአብሄር ይፈርድባቸዋል (ቁጥር 32-33) ፡፡ እግዚአብሄርን ይጠብቃሉ ምድሪቱንም ይሰጣቸዋል (ቁጥር 34) ፡፡

መደምደሚያ

ይህ መዝሙር በእዉነት ስለ ሰለሞን ከነበር ብዛኞቹን ረስቷቸዋል ፤ በዘመኑ ሰለሞን ምድሪቱን ከሌሎች ሴቶች ጋር በመጋባቱ ወደ ምድሪቱ የጣዓት አምልኮ እንዲገባ በመፍቀድ ለያት ፡፡ እንደ እግዚአብሄር ትምህርት ስንሄድ እግዚአብሄር ለሁሉም ለእርሱ ክብር ለሚበልጥ ነገር እያዘጋጀን እንደሆነ ማረጋገጥ እንችላለን ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 672.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 164.

  3. Nelson’s Commentary, p. 672.

  4. Wiersbe, p. 164.

  5. Nelson’s Commentary, p. 672.

  6. Nelson’s Commentary, p. 672.

  7. Nelson’s Commentary, p. 672.

  8. Nelson’s Commentary, p. 672.

  9. Wiersbe, p. 166.

  10. Nelson’s Commentary, p. 673.

ጥያቄዎች

  1. በቁጥር 3 በ 7 ዉስጥ ለማድረግ ዳዊት ያላቸዉ አራት ነገሮች ምንድን ናቸው ? እነዚህ ጥራቶች እናንተ ይገልፁአችኋል ?
  2. ጌታ አሁንም እንድትጠብቁት በጠየቃችሁ ጊዜ እንዲሰራ በህይወታችሁ ዉስጥ የጠበቃችሁበት አንድ ጊዜ ወይም አሁንም ቢሆን አለ ? ጠብቃችኋል ወይስ በራሳችሁ አድርጋችኋል?በዚያ ሂደት ዉስጥ ምን ተማራችሁ ?
  3. መዝ (37፡ 11) በጠቀሰ ጊዜ በማቴ (5፡ 5) ኢየሱስ ምን እያደረገ ነበር ? ምን ያክል ባርኮቶች/በረከቶች አሉ ? ይህ የተለየዉ ጥቅስ የትኛዉ ቁጥር ነበር ? በማቴ (5፡ 5) ዉስጥ ኢየሱስ ምን ሊያስተምረን እየሞከረ ነበር?
  4. ጌታ ፅድቅን በምን መንገድ ተሸከመ/ጠበቀ ? (መዝ 37፡ 17, 23-24, ኢሳ 41፡ 10)
  5. ለጌታ ከክፉ ወይም ከኃጢዓት መለየት ለምን እንደሚያስፈልገዉ ምን ታስባላችሁ ? (መዝ 34፡ 14, ማቴ 6፡ 13, ዕብ 3፡ 9-13, 1ዮሐ 3፡ 6-7)
  6. በመዝሙር 37 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ ያሳያችኋል (ያስረዳችኋል) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 37:5

“Commit your way to the LORD; trust in Him, and He will act.”

መንገድህን ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት አሳልፎ መስጠት ፣ ማስረከብ ወይም እቅድህን ፣ ጊዜህን ፣ ልብህን እና አሳብህን ለእግዚአብሔር ማዋል መሰዋት ማለት ነው ፡፡ ሁሉም ነገር ገለልተኛ ፣ ያልተሟለ አይደለም ይህ ጥቂት የሆነ ነገር እንደሆነ ሲሰማህ ብቻ ነው ፡፡ ይህ መሰጠት ነው ፤ ምናልባትም ለእግዚአብሔር ያለህን ትጋት ቁርጠኝነት ለማስቀጠል ሌላውን ነገር መተው ማለት ሊሆን ይችላል ፡፡ ቁርጠኝነት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም ፡፡ “ ሁልጊዜም አለሁ “ ይለናል ፡፡ በዚህ አለም ቁርጠኝነት በጊዜ ሂደት ውስጥ እየደበዘዘ የሚሄድ ባህሪን ይመስላል ፡፡ የሆነ ነገር እየሰራህ እንደሆነ ካልተሰማህ አለም የቅርጠኝነት እጥረት እንዳለብህ ይቀበላል ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ከእርሱ የምታደርገውን ጉዞ እንዴት እንደዘየደው አይደለም ፡፡

ለእግዚአብሔር መሰጠት ማለት ከእርሱ ጋር እንዴት ነው የምትጓዘው ማለት ነው ፤ ይህ ከኢየሱስ ጋር ያለህ ግንኙነት እንዴት ነው ማለት ነው ፡፡ የምትገለጠው እንደተመቸህ ሲሰማህ ብቻ ከሆነ ወይም ተስፋ ስትቆርጥ ፣ ከኢየሱስ ጋር የመራመድን ውበትና ሰላመዊነትን ሲጠፋብህ ከሆነ ፡፡ ከእርሱ ጋር ለመሄድ ቁርጠኛ ትሆን ዘንድ እርሱ ይናፍቃል ፡፡ እግዚአብሔር “ በፍጹም ልብህ እመነኝ “ ይላል ፡፡ ለእርሱ ስትቆርጥና ስታምነው እርሱ እንደሚሰራ ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ድርሻህ ምንድን ነው ? መንገድህን ለእርሱ አደራ ስጥ ደግሞም እመነው ፡፡ ከመንገዱ ውጣ ፡፡ መቆጣጠሩንና ድርጊቶችን መፈጸሙን አቁም ፡፡ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው ፡፡ እርሱ አይቶታል ይመልሳልም !

“መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል ። “

  • መዝሙር 37፡5

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 37:23-24— “ የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል ። ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም፥ እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና ። “

ምሳሌ 3:5–6 — “ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል ። “

ኢሳይያስ 40:28–29 — “ አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም ። ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል ።