Prayer for Deliverance
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 35-36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመዝሙር መፅኀፍት ዉስጥ መሲሁን እንደ የክብር ንጉስ የሚያመለክቱን ላይ ማትኮራችንን እንቀጥላለን ፤ መዝሙር 35 ዳዊት በጠላቶቹ ላይ ድልን ለመቀዳጀት እንደ ፀለየዉ በጣም እዉነትነት ያሰማል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ዳዊት በጠላቶቹ ተግባር ላይ ያልተለመደ ማብራሪያ እንዳስቀመጠባቸው “ ይገልፃል ፤ ዋይርስቤ ይህ መዝሙር ዳዊት በሳዖል እና በራሱም ሰዎች ሳይቀር ሲሳደድ የተፃፈ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ዋይርስቤ “ ዳዊት የእግዚአብሄር ምርጫ ንጉስ እንደ ነበር ስለ ትክክለኛ ነገር እየታገለ በነበረበት ጊዜ ሳዖል ሊገድለዉ እየሞከረ ስለ ነበር የራሱ ልጆች ንጉስ እንደሚሆኑ “ ይገልፃል ፡፡ የሳዖል ትዕቢት በዳዊት ዘር ቀጣይ ንጉስ መሆን ላይ ብቻ አልነበረም ነገር ግን የሳዖልም ቤተሰብ ዘርም ነበር እንጂ ፤ በዚህ መዝሙር ዳዊት እግዚአብሄርን በጠላቶቹ በመሳደዱ እንደደከመና በመንገር እግዚአብሄር እነርሱን ስለ እርሱ እንዲዋጋለት ጠየቀው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ዳዊት “ ተዋጊዉን እግዚአብሄርንይግባኝ በማለት ጉዳዩን እንዲፈርድለት እንደ ለመነ “ እና በጠላቶቹ ላይ ስለ እርሱ ጣልቃ እንዲገባ እግዚአብሄርን ጠየቀ ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (35፡ 1-3)፡ ዳዊት መዝሙሩን የሚቃወሙትን እንዲቃወምለት እግዚአብሄርን በመጠየቅ ጀመረ (ቁጥር 1) ፡፡ ከዚያም ዳዊት እግዚአብሄርን የዳዊትን ዉጊያ ለመዋጋት የጦር መሳሪያዉን እንዲጠቀም ጠየቀው (ቁጥር 2) ፤ የዳኛ እና የተዋጊ የሁለቱም ስዕል በእነዚህ ቁጥሮች የታዩ ናቸው ፡፡ በቁጥር 2 የጋሻ ስዕል በኤፌ (6፡ 10-18) የእግዚአብሄር እቃ ጦር ብሎ ጳዉሎስ የገለፀዉን ያሳዬ ነው ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ሰይፉንና ጦሩን በመምዘዝ ለዳዊት የእግዚአብሄርን አዳኝነት ለማረጋገጥ በሚያሳድዱት ላይ እንዲጠቀመዉ ጠየቀው (ቁጥር 3) ፡፡ ስለ ህይወቱ በመሮጥ በመድከሙ ዳዊት የእግዚአብሄርን ማረጋገጫ ፈለገ ፡፡
ብዙ ሰዎች በኑሯቸው ከእግዚአብሄር ሳይሰሙ መጓዛቸዉ የተሰማባቸዉ ጊዜ ዉስ አልፈዋል ፤ ብዙዎች ከእምነታቸዉ ዞር ይላሉ ፡፡ በዚያ ክስተት ላይ ከእግዚአብሄር መስማት ስላስፈለገዉ ስለ ነገሩ ጠየቀው !
መዝሙር (35፡ 4-8)፡ ዳዊት ሊገድሉት የሚፈልጉት በማፈር ወደ ኃላቸዉ እንዲመለሱ እግዚአብሄር እንዲያዋርዳቸዉናእንዲያጎሳቁላቸዉ ጠየቀው (ቁጥር 4) ፤ ዳዊት “ በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ እንዲሆኑ፣ የእግዚአብሄርም መለዓክ እንዲያስጨንቃቸው “ እና እንዲጠረጉ ፈለገ (ቁጥር 5) ፡፡ በመዝ (34፡ 7) “ የእግዚአብሄር መለዓክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዉማል “ ፤ የእግዚአብሄር መለዓክት የሚያደርጉት ወጥ የሆነዉን ፍሬ ነገር አስተዉሉ ፡፡ ይህ ቅድመ ክርስቶስ ነበር ወይስ አልነበረም፣ የጌታ መለዓክቶች ለሚፈሩት ትድግናንና ነፃ መዉጣትን ይሰጣሉ ፤ የእግዚአብሄር መገኘት በዚያ እንደ ነበር አምናለሁ ፡፡ በቁጥር 6 ዳዊት ያሳድዱት የነበሩት በሚከታተሏቸዉ በእግዚአብሄር መለዓክቶች የሚሳደዱ ይሆናሉ ፤ ኢየሱስ ጠላቱ ማን እንደ ነበር ስለሚያዉቅ ስለ እኛ እንኳን ሲል እስከ መስቀል ጠላቶቹን ተከታተላቸው ፡፡
ዳዊት በቁጥር 7 ጠላቶቹ “ ያለ ምንም ምክንያት “ እንዳጠቁት አመለከተ ፤ ጠላቶቻችን እኛንም ያለማቋረጥ ለመሰባበር ሰለሚሞክሩ እና በሂደቱም ዉሸትንና ማጭበርበርን ስለሚጠቀም ይህ የተለመደ ስሜት ሊሰማን ይችላል ፡፡ ዳዊት ጠላቶቹ በመክሰር በመረብና በጉድጓድ ዉስጥ አጥመድዉበት በነበረዉ እንዲወድቁ ጠየቀ (ቁጥር 8) ፡፡
መዝሙር (35፡ 9-14)፡ ዳዊት በጌታ ደስተኛ መሆን እንደሚችልና በማዳኑም ደስታን እንደሚወስድ ተናገረ (ቁጥር 9) ፤ ባለፈዉ ሳምንት (ክፍል 37) ለመፀለይ ስምት ምክንያቶች ላይ ተመልክተናል፡ ለመልስ፣ ለእርዳታ፣ ስለ መፅናት፣ የታወስን እንድንሆን፣ የተሰጠን እንድንሆን፣ ስለሚያስፈልገን እና የፈፀመልን እንዲሆን ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ስለ እስራኤል እየተጠነቀቀ በተለይም ስለ ችግረኞች እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 10) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ችግረኛ የሚለዉ በመዝሙር መፅሀፍ ዉስጥ ብዙ ጊዜ እንዴት ይታዩ እንደ ነበር 25 ጊዜ ተጠቅሷል ፤ ችግረኛ “ እግዚአብሄርን በማክበር በረከትን ለመቀበል በማንኛዉም ህዝብ እና ማህበረሰብ ጉዳይ ላይ ከፍያሉ ሊሆኑ ይገባቸዋል “ ፡፡ በመዝሙር 35 ዉስጥ ማብራሪያው በእግዚአብሄር በኩል ስላሉ የችግረኞች ስራ ዉጤት ላይ የተቀመጠ ነው፡ የሚጠፉትን ማዳን (መዝ 35፡ 17)፣ ፍትህ የማይወዱትን ዝም ማለት (መዝ 35፡ 19-25) እና እግዚአብሄርን ስለ ማክበር (መዝ 35፡ 18, 27-28) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ለእነዚህ ዉጤቶች አንድ ንግግርን ይጨምራል፡ “ ከአንድ ጥረት ኋላ ያለ መንፈስ ሰለ ፍትህና ስለ ፅድቅ እዉነተኛ አመለካከት እንደሆነ መገመትን “ ፡፡
ዳዊት በጥያቄዎቹ ቀጠለ ፤ ምንም እንኳን ለእነርሱ መልካም ያደረገላቸዉ ቢሆንም በእርሱ ላይ ያሉት ምስክሮች በእርሱ ላይ ክፉ ያደረጉና ተንኮለኞች ነበሩ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ዳዊት ለእነርሱ እንዴት መልካም እንደ ነበር በመግለፅ ቀጠለ ፤ በታመሙ ጊዜ ማቅ ልብስ በመልበስ ስለ እነርሱ ፆመ ፀለየም፣ በጥልቅም ስለ እነርሱ አዘነ (ቁጥር 13-14) ፡፡
መዝሙር (35፡ 15-28)፡ ዳዊት አስቦላቸዉ/ተንከባክቧቸዉ የነበሩት ከሳዖል ጋር ችግር ዉስጥ በነበር ጊዜ በእርሱ ላይ ዞሩበት (ቁጥር 15) ፡፡ እርሱን በመዝለፍ በእርሱ ላይ ጥርሳቸዉን አፋጩበት (ቁጥር 15, ኢዮ 16፡ 9-10, መዝ 112፡ 10, ሰቆ ኤር 2፡ 16) ፡፡ ዳዊት ይህ ሲሆን እስከመቼ ድረስ እግዚአብሄር እንደሚመለከት ጠየቀው ፤ በዚያም ፋንታ ዳዊት ከጠላቶቹ እንዲያድነዉ እግዚአብሄርን ጠየቀው (ቁጥር 17) ፡፡ በምላሹም ዳዊት እግዚአብሄርን በሕዝቦች መካከል ከፍ ከፍ እንደሚያደርገዉ ቃል ገባ (ቁጥር 18) ፤ ዳዊት እግዚአብሄርን ያለ አግባብ “ ያለ ምክንያት “ ከሚጠሉት እንዲታደገው ጠየቀው (ቁጥር 19-21) ፡፡ ዳዊት በእርሱ ላይ እየሆነ የነበረዉን እግዚአብሄር እያዬ እንደ ነበር አዉቃለሁ በማለት ወደ እርሱ እንዲቀርበዉ እግዚአብሄርን ለመነው (ቁጥር 22-23) ፡፡ በመጨረሻም ዳዊት እግዚአብሄርንነፃ እንዲያወጣዉና በዉድቀቱም ላይ ጠላቶቹም ደሰተኛ መሆን እንዳይችሁ (ቁጥር 24-26) ፡፡ እግዚአብሄር አይተኛም (መዝ 121፡ 4) ፡፡ ዳዊት እንዲፀድቅ/እንዲድን የሚፈልጉት እግዚአብሄር በስራ ላይ እንደ ነበርና እግዚአብሄርን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉት ጠየቀ (ቁጥር 27) ፤ ዳዊትም የእግዚአብሄርን ፅድቅ ይናገራል (ቁጥር 28) ፡፡
ሳዖል ሰባት አመታትን በእነዚህ አመታት ዉስጥ ዳዊትን ለማሳደድ መንገድን ለማግኘት በመሞከር እንደኖረ እናስታውሳለን ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ዳዊትን ሙሉ በሙሉ አከበረው /አፀደቀው ፡፡ ፅድቅ/ክብር ሁል ጊዜ በአንድ ምሽት አይሆንም ፤ በእግዚአብሄር ጊዜ እንጂ በኛ ጊዜ አይሆንም ፡፡
መደምደሚያ
ነቢዩ ኤልያስ ከኤልዛቤል ስለ ህይወቱ በማምለጥ በአንድ ዋሻ ዉስጥ ሙሉ ለሙሉ ብቸኝነት እየተሰማው ተደበቀ ፡፡ በ 1ነገ (19፡ 17-18) እግዚአብሄር በእስራኤል 7000 ተከታዮቹን እንደሚያኖር አሳሰበው ፡፡ እግዚአብሄርን ከጠላቶቻችን እንዲያድነን እየጠየቅን በምናልፍበት ጊዜት ዉስጥ ሊረዱንና ሊያግዙን በዚያ ያሉ ሌሎች ይኖራሉ (ልክ በእስራኤል እንደቀሩት 7000) ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 671.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 160.
Nelson’s Commentary, p. 671.
Jim Erwin, www. Patheos.com; available at https://www.patheos.com/blogs/jimerwin/2016/04/18/psalm-201-9-trusting-god-prayer/.
Nelson’s Commentary, p. 671.
Nelson’s Commentary, p. 671.
Nelson’s Commentary, p. 671.
ጥያቄዎች
-
ዳዊት በመዝ (35፡ 12) እንዳለዉ አንድኛው ሰውለመልካም ነገር መጥፎ ነገር ከፍሏችሁ ያውቃል ? እንዴት ምላሽ ሰጣችሁ ? ስለዚህ ነገር መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል ? (ማቴ 5፡ 44, ሉቃ 6፡ 29, ሮሜ 12፡ 19)
-
በመዝሙር 35 መሰረት ዳዊት ራሱን ዝቅ በማድረግ በመፆም ስለ ጠላቶቹ ፀለዬ ፤ ለጠላቶቻችሁ ይህን ስታደርጉ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ዉጤቱ ምን ነበር፣ ይህስ እንዴት ቀላል ነበር ?
-
መዝሙር (36፡ 5-7) ስለ ሚወዳቸዉና ወደ እርሱ ስለ ሚመለሱት የእግዚአብሄር ተፈጥሮ ምን ይላል ?
-
በመዝ (36፡ 9) ዳዊት እግዚአብሄርን “ የሕይወት ምንጭ “ በማለት ጠቅሶታል ፤ በዚህ አለም ስላለዉ ህይወት ወይም ስለ ቀጣዩ አለም ወይም ስለ ሁለቱም እየተናገረ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? እንደ ምንጭ ለምን እንደ ገለፀዉ ምን ታስባላችሁ ? በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ይህን ሀረግ ወይም ተመሳሳይ ነገር ልናገኝ እንችላለን ? (ምሳ 10፡ 11, 13፡ 14, ኤር 2፡ 13, ራዕ 7፡ 17)
-
በመዝሙር (35-36) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 35:1–3
“Oppose my opponents, LORD; fight those who fight me. Take Your shields—large and small—and come to my aid. Draw the spear and javelin against my pursuers, and assure me: I am your deliverance.”
በእግዚአብሔር እንደሚያምን ሰው መጽሀፍ ጠላቶች እንደሚገጥሙህ ይናገራል ፣ እነርሱም አለም ፣ ስጋ እና ሰይጣን ናቸው ፡፡ መንቃት ፣ በመንፈስ መመላለስና የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር እቃ መልበስ አለብህ ፡፡ አስታውስ ሰይጣን ሊያጠፋህ በዙሪያህ ያደባል ፡፡ ቢሆንም ግን እግዚአብሔር ከእነዚህ ጠላቶች እንደሚያስመልጥህና እንደሚጠብቅህ እመን ፡፡ እግዚአብሔር ይዋጋልሃል ፡፡ እግዚአብሔር ረዳትህና ታዳጊህ ይሆናል ፡፡ እርሱ ወጀቡን ጸጥ ያደርገዋል ፡፡
በዙሪያህ ምንም አይነት ጉዳት ይኑር ፣ ምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጠር ፣ በእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር ላይ መታመንን አስታውስ ፡፡ የዚህ አለም ነገርን እና ጌታን ሁለቱንም መውደድ አትችልም ፡፡ እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ ፣ ነፍስህና አሳብህ መውደድን ምረጥ ፡፡ ምሕረቱ በሰማይ ነው ፡፡ እውነቱም ወደ ደመናት ትደርሳለች ፡፡ ጽድቁ እንደ እግዚአብሔር ተራሮች ፍርዱም እጅግ ጥልቅ ናት ፡፡ ጓደኛዬ በዚህ ታላቅ ፍቅር እግዚብሔር ስለ አንተ ይዋጋል ፡፡ በህይወትህ ላይ አሸናፊ መሆን ይፈልጋል ፡፡ በደህንነትህ በሰላምህም ደስታን ያገኛል ፡፡ በክርሰቶስ አሸናፊ ነህ ፡፡ ስለዚህ አትፍራ ፡፡ ይልቁንም ባገኘኸው በእግዚአብሔር መዳን ደስ ይበልህ ፡፡
“አቤቱ፥ የሚበድሉኝን በድላቸው፥ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው ። ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ ። ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ፤ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት ። “
- መዝሙር 35፡1-3
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 36:5–6 — “ አቤቱ፥ ምሕረትህ በሰማይ ነው፥ እውነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች ። ጽድቅህም እንደ እግዚአብሔር ተራሮች፥ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ናት፤ አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ ። “
1ኛ ጴጥሮስ 5:8 — “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና ፤ “
1ኛ ዮሐንስ 2:15–16 — “ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።