Praising God For His Provision
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 33-34 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በእነዚህ መዝሙሮች ላይ መሲሁ የት ላይ እንዳለ ማየት የምንችልበትን መመልከታችንን ቀጥለናል ፡፡ ስለ መዝሙር 34 ኮንስታብል “ በዚህ ዉህደት በግላዊ ምስጋና የመስጠትና የጥበብ መዝሙር ዳዊት እግዚአብሄርን ህዝቡን ስለታደገለት በማክበር እንደ እግዚአብሄር የሆኑትን በረጅም እድሜ ለመባረክ በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ ምላሽ እንደ ሰጠ “ አለ ፡፡ የዚህ መዝሙር ንዑስ ርዕስ ረጅም ነው፡ ባሳደደው በአቤሜሌክ ፊት መልኩን በለወጠ ጊዜ በሄደም ጊዜ ፡፡ መዝሙር 34 በ 1ሳሙ (21፡ 10-15) ላይ ስለ ተሸፈነዉ ክስተት ይነግረናል ፤ በ 1ሳሙ (21፡ 10) መሰረት ዳዊት በመሸሽ በፍልስጤም ላይ ንጉስ ወደ ነበረዉ ንጉስ አንኩስ ሮጠ ፡፡ ዋይርስቤ የፍልስጤም መንግስት ስሮዉ መንግስት ርዕስ አቤሜሌክ ስለ ነበር ይህም ንጉስ አንኩስን ይጠቅሳል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (34፡ 1-7)፡ ዳዊት እግዚአብሄርን በማመስገን ጀመረ (ቁጥር 1) ፡፡ ዋይርስቤ ጌታን ማመስገን እንዳለብንአራት ምክንያቶችን ይሰጣል ከእነዚህ ዉስጥ ሁሉም በመዝሙር 34 ተደግፈዋል፡ 1) እግዚአብሄር ፀሎትን ይመልሳል (ቁጥር 4, 15)፣ 2) እግዚአብሄር የሚያስፈልገንን ይሰጠናል (ቁጥር 9-10)፣ 3) እግዚአብሄር ከችግር ያድነናል (ቁጥር 17) እና 4) እግዚአብሄር ከአደጋ ይጠብቀናል (ቁጥር 7) ፡፡ እነዚህ አራቱ የጠቅላላ የመዝሙር መሰረታዊ ሀሳቦች ናቸው ፤ ምስጋናችን በሚሰማን በትሁቶች/በገሮች የተሰማ ነው (ቁጥር 2) ፤ ዳዊትም ህዝቡን ከእርሱ ጋር እግዚአብሄርን እንዲያመሰግኑት ጠየቀ (ቁጥር 3) ፡፡ ጳዉሎስ የዳዊትን ቋንቋ ተጠቀመ፡ “ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ ፤ በሁሉ አመስግኑ ፤ ይህ የእግዚአብሄር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነዉና “ (1ተሰ 5፡ 16-18) ፡፡ ቶማስ ዋተሰን “ በፀሎት እንደ ሰዉ መስራት እንደምንችል ፤ በምስጋና ደግሞ እንደ መለዓክት ማድረግ እንችላለን “ ብሏል ፡፡
ዳዊት እግዚአብሄርን ፀሎቱን ስለመለሰለትና ከፍርሃቱ ስላዳነዉ አመሰገነው (ቁጥር 4) ፡፡ በ 1ሳሙ (21፡ 12) ዳዊት የፍልስጤም አገልጋዮች ስለ እርሱ ለአንኩስ በነገሩት ጊዜ ፈራ ፤ እዚህ ጋር ዳዊት እግዚአብሄር እነዚህን ፍራቶች ስለ ወሰደለት አመሰገነው ፡፡ ዳዊት በደስታ ደማቅ በመሆን እግዚአብሄርን የታመነባቸዉን ገለፀ (ቁጥር 5, ዘጸ 34፡ 29) ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ኑሮአችን በመቀየሩ የእግዚአብሄርን ክብር እናፀባርቃለን (2 ቆሮ 3፡ 18) ፡፡ ዳዊት ህዝቡን ሁሉም በእግዚአብሄር ፊት የተቸገሩ እንደ ነበሩና ሰምቶም እንደሚያድናቸው አሳሰባቸው (ቁጥር 6) ፤ ከዚያም ዳዊት የእግዚአብሄር መለዓክቶች እግዚአብሄርን በሚፈሩት ዙሪያ እንደሚሰፍሩና እንደሚያድኗቸዉም ተናገረ (ቁጥር 7) ፡፡ ምናልባትም ይህ ቅድመ ክርስቶስ መልክ ወይም የራሱ የጌታ መልክነው ፡፡
መዝሙር (34፡ 8-10)፡ ቁጥር 8 ሽግግር ይሰጣል “ እግዚአብሄር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም “ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ስለ ቁጥር 8 “ በብሉይ ኪዳን የመፅሀፍ ቅዱስ ተልዕኮ ማዕከል መቅመስና ማየት በሚሉት ቃል ላይ ይገኛል ፤ የእስራኤል ተግባር አሕዛቦችን ወደ አምላካቸዉ መሳብ ነበር “ ይላል ፡፡ ህዝቦቹ ጣዖትን እና ብቁ ያልሆኑትን አማልክትን ሲያመልኩ የአይሁዶች አምላክ ምን ይመስል እንደነበር በማየት ያን በይበልጥ ፈለጉት ፡፡ ዋይርስቤ የቃሉን ጣዕም “ በቃሉ በኩል እግዚአብሄርን እንደ መመገብናለእኛ ያለዉን ሁሉንም እንደ መቅመስ ነዉ ፤ ይህ ማለትም በተሻለ እርሱን ማወቅና በእርሱ በደንብ መደሰት ማለት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ሰዎች በክርስቶስ ያለንን በሚያዩ ጊዜ በብዙ ሊኖራቸዉ እንደሚችል ይደነቃሉ ፤ ዳዊት እግዚአብሄርን የሚፈሩትና እግዚአብሄርን የሚያመልኩት ምንም ነገር አያጡም አለ (ቁጥር 9) ፡፡ ጌታን የሚፈልጉ/የሚሹ አንዳች ነገር አያጡም (ቁጥር 10) ፡፡
የስነ መለኮታዊዉ ዮሐንስ ፒፐር “ እግዚአብሄር ሁልጊዜ በህይወታችሁ 10,000 ነገሮችን እያደረገ ነው ነገር ግን ከእነዚህ ዉስጥ ምናልባትም ለሰዎስቱ ብቻ እዉቅና እንደምንሰጥ “ ይገልፃል ፡፡ ፒፐር እግዚአብሄር እንዴት እንደሚሰጠን አራት እዉነቶችን ይሰጣል፡ 1) “ እግዚአብሄር ከምንጠብቀዉ በተለዬ መንገድ ይሰጠናል “ (መዝ 37፡ 25)፣ 2) “ እግዚአብሄር በብዙ ስለ ራሱ ይሰጠናል (መዝ 37፡ 4, ማቴ 7፡ 9-11)፣ 3) “ የእግዚአብሄር የመጨረሻ ስጦታ ቀድሞ በወንጌል ተሰጥቶናል “ (ያዕ 1፡ 17) እና 4) “ እግዚአብሄር መጨረሻም በዘላለም ይሰጠናል “ (1ጴጥ 2፡ 9) ፡፡
መዝሙር (34፡ 11-22)፡ ዳዊት ልጆቹን በአንድ ላይ በቁጥር 11እግዚአብሄርን መፍራት ለማስተማር ጠራቸው ፤ ከዚያም ዳዊት ሊያደርጉት የሚያስፈልጋቸዉን አስቀመጠላቸው፡ በህይወታቸዉ እንዲደሰቱ፣ አንደበታቸዉን ከክፉና ምላሳቸዉን ከሽንገላ እንዲከለክሉ፣ ከክፉ በመሸሽ መልካምን እንዲያደርጉ እና ሰላምን እንዲሹ (ቁጥር 12-14) ፡፡
ቁጥር 19-20) ስለ መሲሁ ይተነብያል፡ “ የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው እግዚአብሄርምከሁሉ ያድናቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር አጥንቶቻቸዉም ሁሉ ይጠብቃል ከእነርሱም አንድ አይሰበርም “ ፤ ይህ ስለ ክብሩ ንጉስ ስለ ኢየሱስ የተተነበዬ መዝሙር ነው ፡፡
በዮሐ (19፡ 33-36) ዮሐንስ የመዘገበዉ/የፃፈው ፡
“ ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈፅሞ እንደ ሞተ አይተዉ ጭኑን አልሰበሩም ፤ ነገር ግን ከጭፍሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ፤ ወዲያዉም ደምና ዉሃ ወጣ ፡፡ ያየዉም መስክሮአል ፤ ምስክሩም እዉነት ነው ፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እዉነት እንዲናገር ያውቃል ፡፡ ይህ የሆነ ፡፡ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈፀም ነው “ ፡፡
ኢየሱስ መዝ (34፡ 20) በዮሐ (19፡ 36) ተናገረው/ጠቀሰው ፡፡
መደምደሚያ
መዝሙር 34 በህይወታችሁ ዉስጥ ምንም ነገር ይሁን በእዉነት እግዚአብሄርን ስለ ማመስገን ነው ፡፡
7 John Piper.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 164; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 158.
Wiersbe, p. 158.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 670.
Wiersbe, p. 159.
John Piper, “Four Truths About God’s Provision,” www.desiringgod.org; available at https://www.desiringgod.org/articles/four-truths-about-gods-provision.
ጥያቄዎች
-
መዝሙር 33 በተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያ እግዚአብሄርን በማመስገንና በማምለክ ይጀምራል ፤ ለእግዚአብሄር አምልኮና ምስጋና እንዴት ያስፈልጋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለእናንተስ ማመስገንና ማምለክምን ጥቅም አለው ? እግዚአብሄርን ማመስገንና ማምለክ የምትችሉበት ሌሎች መንገዶች ምንድን ናቸው ?
-
መዝ (33፡ 6-9) ከየትኛዉ የመፅኀፍ ቅዱስ ክፍል ይነፃፀራል (ዘፍጥረት 1) ? ይህን ዳዊት ለምን እንደጠቀሰ ምን ታስባላችሁ ? ተፈጥሮ በራሱ የእግዚአብሄርን መኖር ያረጋግጣል ብላችሁ ታምናላችሁ ?
-
መዝ (34፡ 1) “ ምስጋናዉንም ዘወትር በአፌ ነው “ ይላል ፤ በአፋችሁ ዘወትር እግዚአብሄርን ማመስገን ለመቻል እንዴት ታስባላችሁ ?
-
መዝ (34፡ 8) “ እግዚአብሄር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም “ ይላል ፤ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ታስባላችሁ ? እግዚአብሄርን “ ለመቅመስ “ እናመልካም እንደ ሆነ አለማየት ቀላል ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? ኢየሱስን በመከተላችን ምክንያትምንም መጥፎ ነገር አይገጥመንም ማለት ነው ? (መዝ 34፡ 19)
-
በመዝሙር 34 አገላለፅ “ እግዚአብሄርን መፍራት “ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? የተበሳጨ አምላክ እናገለግላለን ብላችሁ ታስባላችሁ ? የማያምኑ እግዚአብሄርን ይፈራሉ ? (መዝ 1፡ 4-6, ራዕ 21፡ 8)
-
መዝሙር (34፡ 20) የኢየሱስ ስቅለት ትንቢታዊ ቃል ሊሆን ይችላል ? (ዘጸ 12፡ 46, ዮሐ 19፡ 36)
-
በመዝሙር (33-34) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 33:20–22
“We wait for Yahweh; He is our help and shield. For our hearts rejoice in Him because we trust in His holy name. May Your faithful love rest on us, Yahweh, for we put our hope in You.”
ስለ ሆነ ሁኔታ እያሰብክ ከእንቅልፍህ ትነቃለህ ? እግዚአብሔር በሆነ ለየት ባለ መንገድ እንድሰራ መጠበቁን ትቀጥላለህ ? ልብህን የሚጎዳ ነገር አለን ? የወደፊቱን ማየት አትችልም ፡፡ ነገ የሚመጣውን የሚፈጠረውን አታውቅም ፡፡ ማድረግ የምትችለው አንድን ቀን በጊዜው መኖር ነው ፡፡ እውነቱን ታውቃለህ ፡- አለመጨነቅ ፣ ስጋቶችህን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ መጣል እንድሁም የማይቻለውን እርሱ ማድረግ እንደሚችል ማመን ነው ፡፡ አሁንም ማድረግ የምትችለው መጠበቅ ፣ ተስፋ ማድረግ ፣ ማታመንና በእግዚአብሔር ደስ መሰኘት ፡፡ በቂ ላይመስል ይችላል ነገር ግን ሁኔታው ከቁጥጥርህ ውጭ ነው ፡፡
ዛሬ እግዚአብሔር ረዳትህና ጋሻህ እንደሆነ ይህንን ተስፋ አስታውስ ፡፡ በድካምህ ስለ ሚያበረታህ ፤ ጥበብን እና ጥበቃን ስለ ሚሰጥህ በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ ፡፡ በመከራ ጊዜያት ፣ በመጠበቅ ጊዜ ሳይቀር ፣ በዚህ ፈተና ውስጥ እንኳ በቅዱስ ስሙ ደስ ይበልህ ፡፡ በመከራህ ሀሴት ስታደርግ እግዚአብሔር ትዕግስትን እና የተፈተነ ባህርይን እንድሰጥህ ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሔር የማያልቅና የማይቋርጥ ፍቅሩን ሲያፈስ ቀን በቀን ተስፋህ እያደገ ይሄዳል ፡፡ ስትጠብቅ የእግዚአብሔርን ፍቅር በላይህ ለይ እንዳለ እንደ ሞቃት ብርድ ልብስ አድርገህ ሳለው ፡፡ ፍቅሩ በላይህ እየፈሰሰ መሆኑ እንድሰማህ ቁጭ ልትልና በደንብ ልታርፍ ይገባል ፡፡ አዎን በርግጥ ዙሪያህ አሁንም ከባድ ሊሆን ይችላል ነገር ግን እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር ይበልጣል ፡፡ ተስፋህን አጥብቀህ ያዝ እንዳትለቅ ፡፡
“ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና ። ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥ በቅዱስ ስሙም ታምነናልና ። ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥ በቅዱስ ስሙም ታምነናልና ። “
- መዝሙር 33፡20-22
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 34:1 — “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው ። “
ሮሜ 5:3–5 — “ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን ፤ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም ። “
1ኛ ተሰሎንቄ 5:16–18 — “ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።