Faith, Hope, and Love
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 31-32 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመዝሙር በሁሉም ምዕራፍ ዉስጥ መሲሁ ታይቷል ፡፡ መዝሙር እግዚአብሄር ለሚሰራው ምስጋናን በመግለፅ ነገሮችን በራሳቸዉ ለማድረግ በሚሞክሩት በዘማሪዎቹ አሳብ ምትክ ስሜታዊ ተቀያያሪ ነው ፡፡ ማክአርቱር በዛሬዎ ጥናታችን መዝሙር “ በብዛት የዳዊትን ችግሮች፣ ፀሎቶቹን እና ምስጋናዎቹን እንደሚይዝ ፤ ዳዊት እንደገና ከጭንቀት ወደ ማረጋገጫ በሚወስደዉ አንድ መንገድ እንደሚጓዝ “ ፅፏል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (31፡ 1-5)፡ዋይርስቤ ሌሎች ክፉ ባደረጉ ጊዜ ስለ ጥንካሬዉ እግዚአብሄርን መታመን እንደምንችል አስረድቷል ፡፡ በእግዚአብሄር ሲጓዝ የዳዊት አላማ ለጌታ መሆን ስለ ሆነ ልበ ሙሉነቱም አይናወጥም ፡፡ ምንም እንኳን እግዚአብሄር ወደ አስቸጋሪ ስፍራ ቢመራውም ዳዊት እግዚአብሄር አላማዉን በዳዊት በኩል እያደረገ እንደ ነበር እርግጠኛ ነበር ፡፡ 1ጴጥ (4፡ 19) “ ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸዉን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ “ ይላል ፡፡
መዝሙር (31፡ 6-8)፡ ዳዊት “ ምናምንቴ ጣዖቶችን “ ስለ መጥላቱ ገለፀ በተለይም ከእዉነተኛዉ እግዚአብሄር ጋር ባነፃፀሩአቸዉ ጊዜ (ቁጥር 6) ፡፡ እግዚአብሄር ከጠላቶቹ ነፃ በማዉጣት “ በሰፊ ስፍራ እግሮቼን አቆመ “ (ቁጥር 8) በዚህም ምክንያት ዳዊት ተደሰተ ፡፡ ዋይርስቤ “ ሌሎች ለህመም ምክንያት በሆኑ ጊዜ እግዚአብሄርን ስለ ምህረቱ እንድንጠይቅ “ ያብራራል ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ሲታመነዉ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ በማለዳ ምህረቱ አዲስ እንደሆነ ያውቃል ፡፡
መዝሙር (31፡ 9-18)፡ ዳዊት “ በኃጢዓቴ ምክንያት “ (ቁጥር 10) የደረሰበትን መጥፎ ዉጤት ገልፃል ፡፡ ዳዊት በጣም የተጨነቀ (ቁጥር 9)፣ በጥልቅ ኃዘን (ቁጥር 10)፣ ተዘለፈም ፍርሃትም ሆነ (ቁጥር 11)፣ ተረሳ (ቁጥር 12) እና ስድቦችንም ሰምቶ ነበር (ቁጥር 13) ፤ ይህ ሁሉ እያለ ዳዊት በእግዚአብሄር ላይ እምነቱን ገለፀ (ቁጥር 14) ፡፡ ዋይርስቤ “ ሌሎች ድልን ሲያዩ እግዚአብሄር እንደሚከብር “ ይናገራል ፡፡
መዝሙር (31፡ 19-24)፡ ዳዊት በጥቃት ስር እንኳን እንዳለ ቢሰማው እግዚአብሄር በፍፁም ለእርሱ ፍቅሩን ለማሳየት ችላ ያለ እንዳልነበር ገለፀ ፡፡ ዳዊት መዝሙሩን በመታመኑ ምክንያት በእግዚአብሄር እምነት እንዲኖረን በማበረታታት ጨረሰ (ቁጥር 23-24) ፡፡
በአጠቃላይ በመዝሙር ዉስጥ ዳዊት እምነትን፣ ተስፋን እና ፍቅርን ገለፀ፡
- እምነት፡ ቁጥር 1, 6, 14 እና 19 ሁሉም ስለ እምነት ያብራራሉ ፡፡ “ አቤቱ አንተን ታመንሁ ፤ ለዘላለም አልፈር በጽድቅህም አድነኝ “ (ቁጥር 1) ፤ “ ከንቱ ምናምንቴነትን የጠበቁትን ጠላህ ፤ እኔ ግን በእግዚአብሄር ታመንሁ “ (ቁጥር 6) ፤ “ አቤቱ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ ፤ አንተ አምላኬ ነህ አልሁ “ (ቁጥር 14) ፤ “ በአንተ ለሚያምኑ በሰዉ ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት ቸርነትህ እንደ ምን በዛች ! “ (ቁጥር 19) ፡፡ ይህ ሁሉ እምነት እግዚአብሄርን ከመታመን ጥላ ስር ነበር ፡፡
- ፍቅር፡ “ ሁላችሁ ቅዱሳንእግዚአብሄርን ዉደዱት ፤ እግዚአብሄር እዉነተኞችን ይፈልጋል ትዕቢተኞችንም ፈፅሞ ይበቀላቸዋል “ (ቁጥር 23) ፡፡
ተስፋ፡ “ በእግዚአብሄር የምታምኑ ሁላችሁ በርቱ ልባችሁም ይጥና “ (ቁጥር 24) ፡፡
መደምደሚያ
ከእምነት፣ ከተስፋና ከፍቅር አንፃር የት ናችሁ ? ኢየሱስም “ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ሾላ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት ይታዘዝላች ነበር “ አለ (ሉቃ 17፡ 6) ፡፡ ዕብ (11፡ 1-2 ) “ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገዉ ነገር የሚያስረግጥ የማናየዉንም ነገር የሚያስረዳ ነው ፤ ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነዉና “ ይላል ፡፡ ኬይሌ ብሌቪንስ “ የእምነት አላማ የእግዚአብሄርን ልብ እንድናዉቅ የሚመራን እንደሆነ “ አስረድቷል ፡፡ ዕብ (11፡ 6) “ ያለ እምነት ደስ ማሰኘት አይቻልም ፤ ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ እግዚአብሄር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና “ ይላል ፡፡ ብሌቪንስ “ እምነት የሚፈለግ የተሸለ ነገር እንዳለ ማመን ሲሆን ተስፋ ደግሞ ነገሩ እንዳለ መጠበቅ/ተስፈኛ መሆን ነው ፤ ተስፋ በፍላጎታችን/በፍለጋችን ፍቅርን ለማግኘት እምነት ህያዉ ሆኖ እንዲኖር የሚያደርግ ነዳጅ ነዉ “ በማለት አብራርቷል ፡፡ ምሳ (24፡ 14) “ ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል ተስፋህም አይጠፋም “ ይላል፡፡
1ቆሮ (13፡ 13) “ እንዲህም ከሆነ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ጸንተዉ ይኖራሉ ፤ ከእነዚህም የሚበልጠዉ ፍቅር ነው “ ፡፡ ፍቅር ሰብዓዊነት ያለዉ የእግዚአብሄርን ግልፅ መልክ ያሳዬ ነው ፤ በተሰሎንቄ ላለች ቤተ ክርስቲያን የጳዉሎስ ገለፃ “ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለዉን የተስፋቸዉን መፅናት “ ያስታውሳል (1ተሰ 1፡ 3) ፤ በተሰሎንቄያዊያን እምነት, ተስፋና ፍቅር ምክንያት “ በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው ፡፡ ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ በእግዚአብሄር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደ ነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና ፤ ለሕያዉና ለእዉነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ ከሙታንም ያስነሳዉን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቅ ዘንድ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሄር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ “ (1ተሰ 1፡ 7-10) ፡፡
6 Blevins.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 617.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 151.
Wiersbe, p. 152,
Wiersbe, p. 152,
Kyle Blevins, Why “Faith, Hope, and Love” Are So Important and Will Last Forever, www.crosswalk.com.
ጥያቄዎች
-
መዝሙር 31 በመላዉ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የተጠቀሰ ነው ፤ በአዲስ ኪዳን መዝ (31፡ 5) የት ልናገኘዉ እንችላለን እነዚህንስ ቃሎች የተናገረዉ ማነው ? (ሉቃ 23፡ 46, ሐዋ 7፡ 59)
-
መዝሙር 31 ምን ያብራራል (መዝ 31፡ 1, 6, 14, 19) ? ሁሉም ነገር በእናንተ ላይ በክፋት በሚሄድ ጊዜ በሚገባ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር ላይ እንዴት ትታመናላችሁ ?
-
በመዝሙር 31 አንድ ስፍራ ላይ ዳዊት በችኮላና በጭንቅ ምን አለ ? ፍራቱ ምን ነበር ? የእግዚአብሄር መገኘት እንደሌለ በተሰማዉ ጊዜ ዳዊት ምን አደረገ ? ህዝቡንና እኛ እንድናደርገው በምን አበረታታ ? (1ቆሮ 13፡ 13)
-
እግዚአብሄር ኃጢዓቱን ስለ ማይቆጥርበት ሰዉ ዳዊት ምን አለ (መዝሙር 32) ? በመጨረሻ በተናዘዘ ጊዜ ምን ተፈጠረ ? የእግዚአብሄር ቅጣት ለምንድን ነዉ ጥሩ የሆነው ? (ዕብ 12፡ 1-13)
-
በመዝሙር 32 እንዳለዉ እንዳንመስል ዳዊት ምን አዘዘን ? በዚያ ፋንታ ምን እናድርግ ? “ የማይረባ አንድ ፈረስ “ የሆናችሁባቸዉ ጊዜያት መቼ መቼ ናቸው ? ጌታን የመታመን አንፀባራቂዉ ተስፋ ምንድን ነው ?
-
በመዝሙር 31-32 በትምህርትና በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 32:3-5
“When I kept silent, my bones became brittle from my groaning all day long. For day and night Your hand was heavy on me; my strength was drained as in the summer’s heat. Selah Then I acknowledged my sin to You and did not conceal my iniquity. I said, ‘I will confess my transgressions to the LORD,’ and You took away the guilt of my sin. Selah”
ንስሀ ያልገባህበትን ኃጢአት በመደበቅ ድካም ተሰምቶህ ያውቃል ? ሌሎች እውነቱን እንዳያውቁ ለማድረግ ውሸትን ተናግረህ ታውቃለህ ? ኃጢአትን መደበቅ አካልህን አድክሞታል ? ጓደኛዬ ህይወት ከክርስቶስ ጋር እንደዛ አይደለም ፡፡ ኢየሱስ የመጣው ኃጢአትህን ይቅር ሊል ነው ስለዚህም በነጻነት ፣ በደስታ እና በሰላም መመላለስ ትችላለህ ፡፡ ኃጢአትህንም ለእርሱ ብትናዘዝ ብታሳውቅ ምንም ያህል ከባድ ቢመስል እንኳ ወይም ምንም አይነት ቆሻሻ ውስጥ ራስህን ብታገኘው እንኳ እርሱ ኃጢአትህን ይቅር ሊልና ህይወትህን ሊቤዥ ተናግሯል ፡፡ እርሱ ከየትኛውም አይነት እድፍ የነጻሃል እንድሁም የደህንነትህን ደስታ ይመልሳል ፡፡ እግዚአብሔር በደልህንና ጨኹትህን ከአንተ ያርቃል ፡፡
ከእግዚአብሔር መሸሽህን አቁምና ወደ እርሱ ለመመለስ እርምጃ መውሰድ ጀምር ፡፡ ራስህን ዝቅ አድርግ ፣ ኃጢአትህን እመን ፣ ለእግዚአብሔር ግለጠው እናም ቀጥሎ ስለሚሆነው ነገር እርሱን እመነው ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ ፡- “አቤቱ፥ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ አልሁ ። ርስቴ በእጅህ ነው፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ ። “ በእርሱ ስትታመን እግዚአብሔር በየጊዜው ሕይወትህን አንድ እርምጃ ይመልሳል ፡፡ ዘሬ ለምን አትጀምርም ? የመጀመርያውን እርምጃ ውሰድ ፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሆናል ፡፡
“ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ ፤ በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ እርጥበቴም ለበጋ ትኵሳት ተለወጠ ። ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ ። “
- መዝሙር 32፡3-5
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 31:14–15 — “ አቤቱ፥ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ አልሁ ። ርስቴ በእጅህ ነው፤ ከጠላቶቼ እጅና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ ። “
ሐዋርያት ሥራ 3:19 — “እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ ፣ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም ። “
1ኛ የዮሐንስ 1:9 — “ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።