Wisdom Books Psalms

Dedicating the House to God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 29-30 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 405 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ በሚያስደንቅ ሁኔታ በሪቫይቭ ት/ቤት ዉስጥ 405ተኛ ክፍላችን ነው ፡፡ መሲሁ በእያንዳንዱ መፅሀፍ እንዴት እንደቀረበ እንደለየነዉ የመፅሀፍ ቅዱስን ጥናት እንድናገኝ የሚያስደንቅ እድል ነው ፡፡ መዝሙር 30 በራሳችን ስለ ራሳችን በራስ መተማመን አይደለም ነገር ግን እግዚአብሄር ስለ እኛ ስላደረገዉ ነው ፤ በመዝሙር 30 ዳዊት ይህን ተናገረ ፡፡ ዳዊት በፃፋቸዉ መዝሙሮች ስሜቱን ለመግለፅ መንገድ አገኘ ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (30፡ 1-3)፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ዳዊት እግዚአብሄርን ለማመስገን በጠንካራ ዉሳኔ መዝሙሩን እንደጀመረ “ ያመለክታል ፡፡ የዳዊት ምስጋናለእግዚአብሄር ጥበቃና ፈዉስ ምላሽ ነበር (ቁጥር 1-2) ፡፡ በመዝሙር 20 ጥናታችን መፀለይ የምንችልባቸዉን ስምንት ቃላቶች ላይ ተመልክተናል፡ ስለ መልስ፣ ስለ እርዳታ፣ ስለ መረጋጋት፣ ስለ ማስታወስ፣ ስለ መሰጠት፣ ስለ መሞላት እና ከፍ ከፍ ስለ ማለት ፡፡ ዳዊት እነዚህን ቃላቶች በመዝሙሮቹ በተደጋጋሚ ተጠቅሟል፣ በቁጥር (1-2) ሁለቱን (ከፍ ከፍ ለማለትና ለመፈወስ) ፡፡ በእነዚህ በመጀመሪያዎቹ ጥቅሶች መሰረት ዳዊት ጠላቶች ገጥመዉት ነበር፣ እንደ ማክአርቱር አገላለፅም “ ለመሞት ቀርቦ “ የዳነ ነበር ፡፡ ዳዊት ጥፋተኛ መሆኑን አምኖ ስለ ነበር እግዚአብሄር ከታላቅ ቅጣት አዳነው (ቁጥር 3) ፡፡

መዝሙር (30፡ 4-5)፡ ዳዊት ህዝቡም እግዚአብሄርን እንዲያመሰግኑት ጠራቸው (ቁጥር 4) ፡፡ ዳዊት ህዝቡንየእግዚአብሄር ቁጣ ለአጭር ጊዜ እንደ ነበርና በማለዳ ደስታዉን ማግኘት እንደሚችሉ አሳሰባቸው (ቁጥር 5, ሰቆ ኤር 3፡ 22-23) ፡፡ ዳዊት “ ቁጣውለጥቂት ጊዜ ነዉ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነዉ “ በማለት ፅፏል (ቁጥር 5)፡፡

መዝሙር (30፡ 6-10)፡ ዳዊት በእርሱ(በእግዚአብሄር) አንዴ ደህንነቱን አገኘ የማይበገርም እንደ ነበር አሰበ (ቁጥር 6) ፡፡ ማክአርቱር የዳዊትን አመለካከት “ ራሱን የቻለ አመለካከትና የትዕቢት ንግግር “ በማለት ይገልፀዋል ፤ (ምሳ 1፡ 32, ኤር 22፡ 21) ፡፡ ዳዊት “ ልክ እንደ ትዕቢተኞቹ ጠላቶቹ እያደረገ እንደ ነበር አስተዋለ “ (መዝ 10፡ 6) ፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሄር ሞገስ በኩል ዳዊት እግዚአብሄር ማን እንደ ነበር በመረዳት ጌታዉ እንዲሆን ፈለገ (ቁጥር 7-10)፡፡

የዚህ መዝሙር ርዕስ ለቤቱ መመረቅ የምስጋና መዝሙር ነው ፤ ለዳዊታዊዉ ቤት ፤ በዚህ ርዕስ በኩል እንስራ ፤ ዳዊት እያመለከተ የነበረው የትኛዉን/ምን ቤት ነበር ? መፅሀፍ ቅዱስ አዋቂዎች እርግጠኞች አይደሉም ፡፡ አመለካከቶች የሚያካትቱት፡

  1. ቤቱ ከዳዊት ቤተ መንግስቶች አንዱ ነበር ማለትም ዳዊት የሚኖርበትን ስፍራ የሚያመለክት ነው ፡፡
  2. የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ፡፡ አብዛኞቹ ምሁራን ከዚህኛዉ አሳብ ጋር ይወግናሉ ፡፡ 1ዜና (21፡ 1-21) ሰይጣን እንዴት ዳዊት የእስራኤልን ህዝብ እንዲቆጥር ያነሳሳበትን ታሪክ ይነግረናል ፤ የዳዊት ዉሳኔ በትዕቢት የተነዳ ነበር፣ እግዚአብሄር እንዲያደርግ በነገረዉ ነገር የተመለስ ነገር አልነበረም ፡፡ በዳዊት ዉሳኔ ምክንያት እስራኤል በመቅሰፍት ተመታ ፤ ይህ ዳዊት በመዝ (30፡ 6) የገለፀዉ መልክ ነው ፡፡ በ1ዜና (21፡ 9-15) ዳዊት ሁኔታዉን ለማስተካከል በእግዚአብሄር ፊት ሰዎስት ምርጫዎች ተሰጠው ከእነዚህ ዉስጥ አንዱ የዳዊትን ህይወት ይወስዳል ፡፡ ዳዊት ምርጫ ማድረግ እንደማይችል እግዚአብሄርን ስለጠየቀው እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ አንድ መቅሰፍት ላከ ፡፡ መዝሙር 30 ከራሱ ችሎታ ከትዕቢት በእግዚአብሄር ኃይል እምነት ወደ መኖር እንዲያድግ የዳዊት የትምህርት ሂደት መቀጠል ነው (2ሳሙ 24፡ 10, 14) ፤ በ 1ዜና (21፡ 16) ዳዊት በመዋረድ በእግዚአብሄር ፊት መሬት ላይ ተደፋ ፡፡ መዝ (30፡ 11) “ ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል ልቅሶዬን ለደስታ ለወጥህልኝ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ “ በማት ይመዝግባል ፡፡ መዝሙር 30 ከ 2ሳሙኤል 24 ክስተት በኋላ የተፃፈ እንደ ነበር በእርግጠኝነት መናገር አልችልም ነገር ግን የትዕቢትና የግትርነትን ስሜት የሚያሰሙ ክስተቶችን ይከተላል ከዚያም ዳዊት የተናገረዉ ብስጭትና ትህትና ይከተላል ፤ በዚህም ምክንያት ዳዊት እግዚአብሄርን ለማምለክ ስፍራ አንድ እጣ መሬት ገዛ (1ዜና 22፡ 1) ፡፡

መደምደሚያ

ሁላችንም አንዳንድ የኃጢዓት ነገሮችን አድርገናል ፡፡ የዳዊት ኃጢዓት 77,000 ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት ሆነ ፡፡ ከኛ ዉስጥ አንድኛችንም በዚህ ልክ ራሳችንን መለከታ እንችላለን ብዬ አላስብም ፡፡ እግዚአብሄር የሚቤዥ አምላክ ነው፣ ዳዊት እንዳደረገው በእርሱ አንድ አዲስ አምልኮ ማለት ምን እንደሆነ መልመድ የምንችል እንድንሆን ይፈልገናል ፡፡ ስለ እናንተ ተስፋዬ የዚያን ኃጢዓት ሸክም በማምለጥ ነጻነትን መቅመስ እንድንችል ነው ስለዚህም በእግዚአብሄር መደሰት እንችላለን ፡፡

መዝሙር 30 በእነዚህ ቃላቶች ያበቃል “ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ ፡፡ አቤቱ አምላኬ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ “ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ዳዊት ስለ እርሱ እንዳልነበር ነገር ግን እንዴት እግዚአብሄርን ማክበር እንደሚችል አስተዋለ ፡፡ ክርስቶስን መከተል ማለት የምትችሉትን ነገር ሳይሆን እንዴት እግዚአብሄርን በአካላችሁ ማክበር እንደምትችሉ ነው (1ቆሮ 6፡ 19-20) ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 668.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 617.

  3. MacArthur, p. 617.

  4. MacArthur, p. 617.

ጥያቄዎች

  1. በመዝሙር 29 ብዙ ጊዜ የእግዚአብሄር ድምፅ ተጠቅሷል ፤ መዝሙረኛዉ እንዴት ገለፀው ይህን ያነፃፀረባቸዉ ጥቂት ነገሮች ምን ነበሩ ? ዳዊት ይህን መዝሙር እንዲፅፍ በዳዊት ላይ ምን እየሆነ እንደነበር ምን ታስባላችሁ ?
  2. በመዝ (29፡ 10) መሰረት ጌታ እንደ ንጉስ ለዘላለም ይቀመጣል ፡፡ በ 1ሳሙኤል ጌታ በህዝቡ እንደ ንጉስ ተቀባይነት ባለማግኘት ስለ ምድራዊ ንጉስ ጠየቁ (1ሳሙ 8፡ 7) ፤ ዉሳኔአቸዉ እግዚአብሄርን ከዙፋኑ አስወግዶታል ? ቤተ ክርስቲያን “ እግዚአብሄርን እንደ ንጉስ ሳትቀበለዉ “ አይታችሁ ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የወደፊት ዉጤት ምንድን ነው ?
  3. በመዝሙር 30 መዝሙረኛዉን እግዚአብሄር ያደናዉ ከምን ከምን ነገር ነበር ? እግዚአብሄር አድኖናል ብላችሁ የሚሰማችሁ ከምን ከምን ነገር ነው ? እግዚአብሄር ሊያድናችሁ የማይችለዉ ወይም የማያድናችሁ ነገር አለ ብላችሁ ታምናላችሁ ? አዎ ከሆነ እሱ ምንድን ነው ? ከአንዳንድ ሁኔታዎች ለምን እግዚአብሄር ላያድናችሁ ይመርጣል ?
  4. በመዝሙር 30 ቁጥር 5 እና 11 ከደስታ እና ከዳንስ/ከፈንጠዝያ ጋር የሚመጣ ሞገስ እንዳለን ይገልፃል ፤ ቁጥር 12 አላማችንና ምላሻችን ምን መሆን እንዳለበት ይናገራል ? ይህን በራሳችሁ ህይወት ታዩታላችሁ ? አናየዉም ካላችሁ በህይወት ዘመናችሁ ያላችሁን የእርሱን ሞገስ በለመያዛችሁ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?
  5. በመዝሙር (29-30) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 30:5, 11–12

“For His anger lasts only a moment, but His favor, a lifetime. Weeping may spend the night, but there is joy in the morning You turned my lament into dancing; you removed my sackcloth and clothed me with gladness, so that I can sing to You and not be silent. LORD my God, I will praise You forever.”

እግዚአብሔር ፈጽሞ አይተውህም ፡፡ እርሱ ይወድሃል ፡፡ ወደ ጉድጓድ የወደክበት ርቀት ምንም ያህል ይሁን ፣ እርሱ ይወድሃል ፡፡ በጣም ጥልቅ ቢሆን እንኳ እርሱ ያነሳሃል ፡፡ ወደ እርሱ እርዳታን ፈልገህ ብትጣራ ፣ እርሱ ይፈውስሃል ፡፡ እርሱ አንተን መውደድ ፈጽሞ አያቆምም ፡፡ በድለህ ሊሆን ይችላል ፡፡ ወጥመድ ውስጥ እንደገባህ እንደተያዝክ እና መውጫ መንገዱን ማየት እንደማትችል ይሰማህ ይሆናል ፡፡ ጠቅላላ ሕይወትህ የጨለመ ሊመስል ይችላል ፡፡

አስታውስ ከእግዚአብሔር ጋር ሁልጊዜም መውጫ መንገድ አለ ፡፡ እርሱ ነገርን ሁሉ እንደገና ሊመልስ ፣ ሊያስታርቅ እንድሁም እያንዳንዱን ሁኔታ ሊቤዥ ተናግሯል ፡፡ ስለ እርዳታ በመጮህ ጀምር ፤ ማንኛውንም ትምክህት ራስ ወዳድነት ተው እናም የእግዚአብሔር ብርሃን በስብራትህ ቁስል ውስጥ እንድገባ ፍቀድ ፡፡ በሀዘንህ ለሊቱን ሙሉ ልታለቅስ ትችላለህ ፡፡ ትዳርህን ፣ ስራህን ፣ ልጆችህን እንድሁም የምትወዳቸውን ሁሉ ልታጣ ትችላለህ ፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዷን ለቅሶ ይሰማል ፡፡ እርሱ ሀዘንህን ወደ ደስታ እንደሚለውጥ ተናግሯል ፡፡ የማቅ ልብስህን ይቀዳል ደስታንም ያለብስሃል ፡፡ እያንዳንዷን ቀን ለመጀመር ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፣ ምህረቱ አያልቅም ፣ በየማለዳውም አዲስ ነው ፡፡ ታማኝነቱም ሁልጊዜ ታላቅ ነው ፡፡ ስለ ታላቅ ታማኝነቱ እግዚአብሔርን አመሰግን ፡፡

“ቍጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፤ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል ። …. ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል ልቅሶዬን ለደስታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ ። አቤቱ አምላኬ፥ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ ። “

  • መዝሙር 30፡5 ፣ 30፡11-12

ተጨማሪ ጥቅስ

ሰቆቃው ኤርምያስ 3:22–23 — “ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና ። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው ። “

ሮሜ 8:28 — “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ። “

ኤፌሶን 1:7 — “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ። “