This One Thing
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 26-28 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ ሰዎስት ምዕራፎች አሉን ነገር ግን በትምህርቱ ላይ አንዱን ብቻ እንሸፍናለን ፤ ስለዚህ ሰዎስቱንም ለማንበብ እና በሰዎስቱም ዉስጥ መሲሁ ምን እንደሚመስል ማየት ለመቻል ዝግ በማለት ጊዜ ዉሰዱ ፡፡ ለመዝሙር መፅሀፍ ቃላችን መገኘቱን የሚያንፀባርቅ የክብር ንጉስ መሆኑን አስታዉሱ ፡፡ መዝሙር 27 “ በጠንካራ ንፅፅር ለምሳሌ ኃዘንንና ሙገሳን ሁለቱንም፣ ስቃይ/መከራና ምስጋናን እና ዉጊያንና አምልኮን ሁለቱንም የሚያመለክት ነው “ ፤ እንዲሁም ዳዊት እንዳረጋገጠው “ በህይወቱ የእግዚአብሄርን እዉነት…. በእግዚአብሄር መገኘት ፊት ለመኖር ጠንካራ ፍላጎት እና እግዚአብሄርን በመጠበቅ እንዲቀጥሉ ለአማኞች እየሆኑ ወዳሉት ፍላጎቶች የሚያመለክት የእምነት መዝሙር ነው “ ፡፡ ዋይርስቤ “ በረጅም እድሜ እንደተመዘገበው በዚህ መዝሙር ርዕስ መሰረት ዳዊት ከመቀባቱ በፊት ፃፈው ፤ ይህ ማለት ምናልባትም ከቤቱ በሸሸና በንጉስ ሳዖልና በሰዎቹ በሚሳደድበት ጊዜ የተፃፈ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ይህ በ 2ሳሙኤል ከዳዊት ሁለተኛ ጊዜ ከመቀባቱ በፊት የሆነ ነበር ፤ መዝሙር 27 ለማጠቃለል ዳዊት በተንኮለኞች ተሳደደ (ቁጥር 2)፣ በሀሰተኛ ምስክሮች ተዛተበት/አስፈራሩት (ቁጥር 12) እና ሁሉም ሊገድሉት ፈለጉ (ቁጥር 2, 12) ፡፡ ይሁን እንጂ ዳዊት “ ሰራዊትም ቢሰፈርብኝ ልቤ አይፈራም ፤ ሰልፍም ቢነሳብኝ በዚህ እተማመናለሁ “ (ቁጥር 3) ፤ በዚህ ሂደት ስድስት እንቅስቃሴዎች ይካሄዳሉ ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (27፡ 1-5)፡ የመጀመሪያዉ እንቅስቃሴ በቁጥር 1-3፡ “ በእግዚአብሄር መገኘት ምክንያት ጠላቶችን ላለመፍራት መወሰን “ ፤ ዳዊት በእርሱ ላይ የሚጎዳ ሊያደርጉበት የሚፈልጉትን ክፉዎችን አልፈራም ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄር ብርሃኑ፣ መዳኛዉ እና ጥንካሬዉ ስለ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ጠላቶችና አስጨናቂዎች በፊቱ ተደናቀፉ (ቁጥር 2)፣ እርሱም ያልፈራና ልበ ሙሉ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ ዳዊት አንድ ፍላጎትና ትኩረት ብቻ ነበረው፡ በህይወት ዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሄር ቤት መኖር (ቁጥር 4) ፡፡ በህይወቴ ስለ እግዚአብሄር የተሸጡ ታዋቂ ሰዎች አሉኝ - የሁሉንም ቀን ሁሉንም ደቂቃ በእግዚአብሄር ፊት መኖር የፈለጉ (ዮሐ 15፡ 1-8) ፡፡ ዛሬ በቁጥር 4 ላይ እናተኩራለን ፡፡
“ እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንሁት “ (ቁጥር 4)፡ ካምደን ማክፌ በመፅሀፍ ላይ “ አንድ ነገር “ የሚለዉ ቃል አምስት ጊዜ ተገልፆ እንደሚገኙ ያመለክታል፡
- አንድ ነገር እጠይቃለሁ (ቁጥር 4)፡ እግዚአብሄር የፀሎት ልብን ስለሚያውቅወቅ ፡፡
- አንድ ነገር ጎደለህ (ማር 10፡ 21)፡ እግዚአብሄር የሚማረክን ልብ ስለሚያዉቅ ፤ ጎበዙ ሰዉዬ አንድ ነገር ይጎድለዋል - ክርስቶስን ለመከተል መጀመሪያ እግዚአብሄርን ማስቀመጥ ፡፡
- የሚያስፈልገዉ አንድ ነገር ነው (ሉቃ 10፡ 41-42)፡ በእግዚአብሄር ፊት መሆን ፤ እግዚአብሄር የአገልግሎት ልብን ስለ ሚያውቅ ፡፡
- አንድ ነገር አዉቃለሁ (ዮሐ 9፡ 25)፡ እግዚአብሄር የምስክርነት ልብን ስለ ሚያውቅ፡ “ ዕዉር ነበርሁ ነገር ግን አሁን ማየት ቻልኩ ፤ ተቀየርኩ ! “
- አንድ ነገር አደርጋለሁ (ፊል 3፡ 13-14)፡ እግዚአብሄር የልብን ምኞት ስለ ሚያውቅ ፤ ጳዉሎስ ወደ ተጠራበት ግብ ወደፊት ገፋ ፡፡
መደምደሚያ
በክብር ንጉስ ላይ በምናተኩር ጊዜ ሁሉም ጊዜ ማሳለፊያዎች ይጠፋሉ - ሁሉንም ነገር ፍፁም ለማድረግ በመሞከር፣ እንድናደርገዉ የተጠየቅነዉን ሁሉንም ነገር ለማድረግ በመሞከር፣ ሌሎችን ለመሳብ በመሞከር ፡፡ ፀሎቴ ከእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ጥቂቶቹ ለእናንተ ለእምነት ምሳሌ በሚሆናችሁ መንገድ እንዲናገራችሁ ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 615.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 666.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 144.
Nelson’s Commentary, p. 666.
Camden McAfee, “Just One Thing—God Asks of You”; available at https://marmarthunder.wordpress.com/2015/12/02/just-one-thing-god-asks-of-you/.
ጥያቄዎች
-
በመዝ (26፡ 2) ዳዊት እግዚአብሄርን እንዲፈትነዉ፣ እንዲመረምረዉና እንዲሞክረዉ ጠየቀው ፤ በእናንተ ላይ እግዚአብሄር ይሄን እንዲያደርግ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ ? ይህ ለመፀለይ ቀላል ፀሎት ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ወይስ ለምንስ አታምኑም ?
-
መዝ (26፡ 8) “ እጆቼን በንጽህና አጥባለሁ ፤ አቤቱ መሰዊያህን እዞራለሁ “ ይላል ፤ ይህ የእግዚአብሄር ክብር የት እንደሚገለጥ እንዲሰማን / እንደሚመስል ምን ታስባላችሁ ? በእግዚአብሄር ክብር ፊት ሆናችሁ ታውቃላችሁ ?
-
መዝሙር 27 በእግዚአብሄር ላይ ያለ ፍራት የመታመን መዝሙር ነው ፤ በእግዚአብሄር ላይ እንዲህ አይነት እምነት አለን ትላላችሁ ? ከሌላችሁ በእርሱ እንዲህ አይነት እንዲኖራችሁ ምን ይረዳናል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
መዝሙር 27 የእግዚአብሄርን ፊት ስለ መሻት ይናገራል ፤ የእግዚአብሄርን ፊት ለመፈለግ ምን ታደርጋላችሁ?
-
መዝ (27፡ 14) እግዚአብሄርን መጠበቅ ይላል ፤ እግዚአብሄር በእርሱ ተስፋ እንድታደርጉ አድርጓችሁ ያውቃል ? ቀላል ወይስ ከባድ ነበር ? አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር ተስፋ እንድናደርገዉ ለምን እንደሚያደርገን ቢያንስ ሰዎስት ምክንያቶችን ማሰብ ትችላላችሁ ?
-
በመዝሙር 28 ዳዊት እግዚአብሄርን ጋሻዬ፣ ኃይሌ፣ አለቴና እረኛዬ በማለት ይጠቅሰዋል ፤ ስትፀልዩ የእግዚአብሄርን የተለያዩ ስሞች ተጠቅማችሁ ታውቃላችሁ ? ይህ እግዚአብሄርን ላይ ለመመልከትና እንዴት ለመፀለይ ምን አስፈላጊነት ሊኖረዉ እንደሚችል ታስባላችሁ ?
-
በመዝሙር (26-28) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 27:4
“I have asked one thing from the LORD; it is what I desire: to dwell in the house of the LORD all the days of my life, gazing on the beauty of the LORD and seeking Him in His temple.”
እግዚአብሔርን አንድ ነገር መጠየቅ ብትችል ፣ የምትጠይቀው ምን ይሆን ነበር ? ዳዊት በህይወት ዘመኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረትን ስለማድረግ ጸለየ ፡፡ ዛሬ ትኩረትህን በአንድ ነገር ላይ አድርግ እርሱም ፡- ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ፡፡ መኖር ማለት ጊዜን ማሳለፍ መቆየት ማለት ነው ፡፡ በርግጥ አሁንም በቀንህ ውስጥ መለፍ አለብህ ነገር ግን ይህን ስታደርግ በኢየሱስ እረፍ ፡፡ ቅርንጫፍ በውይን ግንዱ እንደሚኖር አንተም በጌታ ኑር ፡፡ ቃሉን አንብብ ፡፡ ከዕለት ወደ ዕለት እግዚአብሔርን ለማወቅ ጊዜ ውሰድ ፡፡ እግዚአብሔርን በይበልጥ ባወከው መጠን ፣ ለመጽናት የበለጠ ብርታት ይኖርሃል ፡፡
ስለሚመጣው ፈተና በተጨነክ ጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ማስተዋልና ሰላም ጠይቅ ፡፡ ከባድ ሀላፊነትን በተሸከምክ ጊዜ በራስህ ማድረግ እንደምትችል እመን እግዚአብሔርም እንድረዳህ ጸልይ ፡፡ በፊትህ ፈተና በተጋረጠ ጊዜ ቆም በልና መንፈስ ቅዱስ ጠላትን የምትቋቋምበትንና የምታመልጥበትን ኃይል እንድሰጥህ ጸልይ ፡፡ በክርስቶስ ላይ አትኩር እናም ደግሞ በአለም ነገር አትታወክ ፡፡ አለም ሊያባብልህ ይችላል ነገር ግን ጌታ ይበቃሃል ፡፡ ከእርሱ ጋር ኑር ፡፡
“እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ ። “
- መዝሙር 27፡4
ተጨማሪ ጥቅስ
ሉቃስ 10:39, 41–42 — “ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች ።
……… ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት ። “
ዮሐንስ 15:4 — “ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም ። “
1ኛ ዮሐንስ 3:6 — “ በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።