Wisdom Books Psalms

The King of Glory

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 23-25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 403 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 23 የተወደደ መዝሙር ሲሆን መዝሙር 24 ደግሞ ከሪቫይቭ ት/ቤት ከትልቁ ጭብጥ ጋር የሚገናኘዉን የመሲሁን መልክ ይስላል ፡፡ ዋይርስቤ መዝሙር 22 ከመዝሙር 23 እና ከመዝሙር 24 ከሰዎስቱ እንደ መጀመሪያ አካል እንደታዬ ያስታውቃል ፡፡ በመዝሙር 2 መልካሙ እረኛ ስለ በጎቹ ሞተ ፤ በመዝሙር 23 ታላቁ እረኛ ስለ በጎቹ ተጠነቀቀ ፤ በመዝሙር 24 ታላቁ እረኛ በመመለስ በጎቹን ሸለማቸው ፡፡ ኤፍ.ቢ. ሜየር መዝሙር 23 ስለ መስቀሉ እንደሚናገር፣ መዝሙር 24 ስለ ጠመዝማዛነት/ስለ ችግር እንደሚናገርና በመዝሙር 25 ስለ ዘዉዱ እንደሚናገር ያስረዳል ፡፡

መዝሙር 24 ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ በነበረበት ጊዜ ተፅፏል ፤ የቀድሞ ቤተ ክርስቲያን መዝሙር 24 እንደ እርገት መዝሙር ተሰይሟል ፡፡ ዋይርስቤ መዝሙሩ በቁጥር 1-2 በሚናገሩት ሰዎች፣ በቁጥር 3, 8, 10 ጥያቄዎችን በሚጠይቀዉ መሪ እና በቁጥር 4-6, 8 እና 10 የመሪዉን ጥያቄዎች በሚመልሱት ሰዎች እንደሚከፈት ያስረዳል ፡፡ ይህ መዝሙር በሄሮድስ ቤተ መቅደስ ሁል ጊዜ ይዘመር ነበር ፤ ይህን መዝሙር ቤተ ክርስቲያን ከፋሲካ ከ40 ቀን በኋላ በሆነዉ በእርገት ቀን (ሐዋ 1፡ 9) የሚነበብ እንዲሆን ሰይማዋለች ፡፡ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ከትንሳኤ በኋላ ወደ ሰማይ የተመለሰና መንግስቱን ሊመሰረት የሚመለስ “ እግዚአብሄር ክብር “ እንደሚሆን ተረድተዋል ፡፡

ቆላ (2፡ 15) “ አለቅነትንና ስልጣናትን ገፎ ድል በመንሳት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው “ ፤ እርገቱ/ከፍ ከፍ ማለቱ በድል አድራጊነት ሀሳብ ተደረገ ፡፡ ኤፌ (4፡ 8-10) “ ስለዚህ ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል ፡፡ ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው ? ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያዉ ነው “ ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (24፡ 1-2)፡ ማክአርቱር መዝሙር 24 ወደ ሁለት ደረጃዎች ይከፍለዋል ፤ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ቁጥሮች የመጀመሪያዉን ይይዛሉ፡ “ በኃሳብ ዉስጥ ፈጣሪን ማምለክ “ ፤ ዳዊት በአለም ላይ ሁሉም ነገር የእግዚአብሄር እንደሆነ ያውቃል ፡፡ እግዚአብሄር በሁሉም ፍጥረት ላይ “ አለማቀፋዊ ባለቤት “ ነበር ፡፡ ዘጸ(19፡ 5) “ አሁንም ቃሌን በእዉነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ “ ይላል ፤ መዝ (50፡ 12) “ ብራብም ለአንተ አልነግርህም ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና “ ፡፡

መዝሙር (24፡ 3-6)፡ “ የአዳኙ አምልኮ “ የመዝሙሩ የማክአርቱር ሁለተኛዉ ደረጃ ነበር (ቁጥር 3-6) ፤ ዳዊት እግዚአብሄርን ስለ ሚያመልኩት ሁለት ማጣሪያዎችን ያስቀምጣል፡ ንፁህ እጆችና ንፁህ ልብ ሊኖራቸዉ ይገባል (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ንፁህ እጆች የአንድን ሰዉ ድርጊቶች እንደሚያመለክትና ንፁህ ልብ ደግሞ የዉስጥ አመለካከትን እንደሚያመለክት “ ያሳስባል/ያስረዳል ፡፡ ንፁኅ እጆችና ንፁህ ልብ የዳዊት መግለጫ ሆነ፡ “ ዳዊትንም ባሪያዉን መረጠው ከበጎቹም መንጋ ዉስጥ ወሰደው ፤ ከሚያጠቡ በጎችም በኋላ ባሪያዉን ያዕቆብን ርስቱንም እስራኤልን ይጠብቅ ዘንድ ወሰደው ፡፡ በልቡ ቅንነት ጠበቃቸው በእጁም ብልሃት መራቸው “ መዝ (78፡ 70-72) ፡፡ ማክአርቱር “ እነዚህ ማጣሪያ ናሙናዎች ኃጢዓት የሌለበት ፍፁምነትን እንደማያጎሉ ነገር ግን የዉስጥ ሀቀኛ ፍላጎትንና የዉጪ ሁኔታን እንጂ እንደሆ “ ይፅፋል ፡፡ ዳዊት ጽድቅን ከአዳኙ ተቀብሎ እንደ ነበር ያውቃል (ቁጥር 5) ፡፡

መዝሙር (24፡ 7-10)፡ በመዝሙሩ በሰዎስተኛ ደረጃ ላይ ማክአርቱር “ የንጉሱ አምልኮ “ ብሎ ጠራዉ፣ ዳዊት የከተማይቱ በሮች “ መሪያቸዉን ለማንሳት “ በሮቹ “ እንዲከፈቱ “ (ቁጥር 7) አዘዘ ፡፡ ማክአርቱር “ እነዚህ ለታላቁ ንጉስ መግቢያነት መንገድን ለመስራት በራሳቸዉ በመዘርጋት የከተማዋ በሮች እንዳስፈለጋቸዉ የሚያመለክት ህያዉ ያልሆነ ነገር ድፍረቶች እንደሆኑ “ ያመለክታል ፡፡ ኮንስታብል “ በተለመደ መልኩ ሰዎችእንደ ባለሞገስ ማሳለፍ ራሳቸዉን ዝቅ በማድረግ ይሰግዳሉ ነገር ግን በዚህ ስዕል በሮቹ ተቃራኒዉን እንዳደረጉ “ ያስረዳል ፡፡ የክብሩ ንጉስ በጠላቶቹ ላይ ድል አድራጊ ነበር (ቁጥር 8) ፤ ኮንስታብል “ የክብሩን ንጉስ “ ከያህዌ ጋር በማስተካከል “ እግዚአብሄር ታላቅ ነዉ ምክንያቱምበጣላቶቹ ላይ ባደረገዉ ድልመንሳት እና ድነትን ስለ መስጠቱ ስናየው ሁሉን የሚችል ስለሆነ ፤ የእስራኤል መለኮታዊ ንጉስ ታላቅ ነበር ምክንያቱም የሚሸነፍ ስላልነበር “ በማለት ያስቀምጣል ፡፡

ቁጥር 9 ቁጥር 7 ይደግመዋል እንደገና ንጉሱን በማመለክ ላይ በሮቹ እንዲሳተፉ ይጠራቸዋል ፡፡ በተመሳሳይ ቁጥር 10 የቁጥር 8 ሀሳብን በመድገም ጌታን የክብር ንጉስ በማለት ይለየዋል ፡፡

ዋይርስቤ በሮቹ ኢየሱስን ለመጥቀስ ሁለት ጊዜ ተደርሰዉ/ተነግረዉ እንደ ነበር ያሳያል ፤ ኢየሱስ በዘንባባ ላይ እሁድ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ምናልባትም ይህ መዝሙር በዚያ ማለዳ ተዘምሮ እንደ ነበር ነገር ግን ለእርሱ ይህ አልተተገበረም ነበር ፤ ይልቁንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ኢየሱስ በጎልጎልታ ላይ ተሰቀለ ፡፡ ይሁን እንጂ ከስቅለቱና ከትንሳኤዉ በኋላ እንደ ድል አድራጊ የክብር ንጉስ ወደ ሰማይ አረገ/ሰማይ ተቀበለችዉ ፤ ቆይቶም ኢየሱስ ከአለም ሰራዊት ጋር ሊዋጋ ተመልሶ ወደ ምድር ይመጣል፣ በማሸነፍም የራሱን መንግስት በምድር ላይ ይመሰርታል ፡፡ ራዕ (19፡ 11) ይህን ስዕል ይገልፀዋል፡ “ ሰማይም ተከፍቶ አየሁ እነሆም አምባላይ ፈረስ የተቀመጠበትም የታመነና እዉነተኛ ይባላል በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም “ ፡፡ ዘካ (14፡ 9)፡ “ እግዚአብሄርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሳል ፤ በዚያ ቀን እግዚአብሄር አንድ ስሙም አንድ ይሆናል “ ፡፡

መደምደሚያ

ለክብር ንጉስ መመለስ እንዴት ትዘጋጃላችሁ ? ስቴቨን ኮል ለኢየሱስ መመለስ ዝግጁ ለመሆን ሰዎስት ዋና ዋና መንገዶችን ያስቀምጣል፡

  1. ጌታችሁ ስለሚሆን ለኢየሱስ መምጣት የተዘጋጃችሁ መሆን ፡፡
  • “ በዚያ ቀን ብዙዎች ፡፡ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን ? ይሉኛል ፡፡ የዚያን ጊዜም ፡፡ ከቶ አላወቅኋችሁም ፤ እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ “ (ማቴ 7፡ 22-23) ፡፡
  1. የእርሱ አገልጋዮች ስለምትሆኑ ለኢየሱስ መምጣት የተዘጋጃችሁ መሆን ፡፡
  2. መመለሱን ተስፋ በማድረግ ለኢየሱስ መምጣት የተዘጋጃችሁ መሆን ፡፡
  • “ ጌታቸዉ በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው …….እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ የሰዉ ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና “ (ሉቃ 12፡ 37, 40) ፡፡
  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 132.

  2. F.B. Meyer, “Through the Bible Commentary,” www.studylight.org; available at https://www.studylight.org/commentaries/fbm/psalms-24.html.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 613.

  4. Wiersbe, p. 138.

  5. MacArthur, p. 613.

  6. MacArthur, p. 613.

  7. MacArthur, p. 613.

  8. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 665.

  9. MacArthur, p. 614.

  10. MacArthur, p. 613.

  11. MacArthur, p. 614.

  12. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 129; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  13. Constable, p. 130.

  14. Wiersbe, p. 140.

  15. Steven J. Cole, “Lesson 61: Are You Ready for Christ’s Return?”; www.bible.org, available at https://bible.org/seriespage/lesson-61-are-you-ready-christ%E2%80%99s-return- luke-1235-48.

ጥያቄዎች

  1. መዝሙር 23 አንብቡ ፤ በእያንዳንዱ ጥቅስ መጀመሪያ ላይ በመቆም ጥቅሱ ለእናንተ እንዴት ተገቢ እንደሚሆን አስቡ ፤ ምልከታችሁንም ፃፉ
  2. መዝ (24፡ 4) ኢየሱስን ይጠቅሳል /ያመለክታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
  3. መዝ (25፡ 22) “ አቤቱ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነዉ “ ይላል ፤ እስካሁን እግዚአብሄር እስራኤልን ታድጓል ወይስ ትድግናዉ ይመጣል ? ለምን ወይስ ለምን አልታደገም ?
  4. በመዝሙር 23-25 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 24:7–8

“Lift up your heads, you gates! Rise up, ancient doors! Then the King of glory will come in. Who is this King of glory? The LORD, strong and mighty, the LORD, mighty in battle.”

ቆም ብለህ አስበኸው ታውቃለህ “ የክብር ንጉሥ “ የሚለው ሀረግ ምን ማለት አንደሆነ ? ክብር የሚለው ቃል የሚገለጸው ልክ እንደ ክብደት ነው ፡፡ ሰውን ለመግለጽ ስንጠቀመው ደግሞ ኃይልን የሚሸከም ሰው ደግሞም አስፈሪ ክብር የሚገባው የሚለውን ይወክላል ፡፡ እግዚአብሔርን የክብር ንጉሥ አድርጎ መግለፅ እርሱ በህይወትህ ውስጥ አስፈሪ ፣ ሀያል ፣ አንድ እና ብቸኛ እንደመሆኑ መጠን የሚገባውን ክብርና መፈራት እንድትሰጥ ያነሳሳሃል ፡፡ “ ቀና በል “ እና “ ተነስ “ ለሚመጣው ንጉሥ ራስህን አዘጋጅ ፡፡

መዝሙራኛው ንጹህ እጆች ይኑርህ እንድሁም ንጹህ ልብ ይኑርህ ፣ ነፍስህንም ለከንቱ እታንሣ ይላል ፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም እንድትሆን አይጠይቅህም ነገር ግን ይልቁንም በተግባር እና እግዚአብሔርን በሚያከብር የውስጥ አመለካከት እንድትኖር ነው ፡፡ ተነስና ኢየሱስን የህይወትህ ንጉሥ አድርግ ፣ በሙሉ ልብህም አገልግለው ከዚያም የክብር ንጉሥን መገለጥ ጠብቅ ፡፡ የእግዚአብሔርን ፊት ፈልግ እናም እመነው ፡፡ እርሱ ይህ ሁሉ ይገባዋልና ፡፡

“እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ ። ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል ። “

  • መዝሙር 24፡7-8

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 24:3-4 — “ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል ? እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ ። “

ማቴዎስ 17:5 — “ እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ ። “

ራእይ 19:1 — “ ከዚህ በኋላ በሰማይ፦ ሃሌ ሉያ ፤ ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ ። “