Wisdom Books Psalms

The Fifth Gospel

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 402 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዳዊት መዝሙር 22 ፅፏል ነገር ግን ይህን መዝሙር እንዲፅፍ ምን ክስተት እንደመራዉ አናውቅም ፡፡ ኮንስታብል መዝሙር 22 ከመዝሙር 69 ጋር እንደሚመሳሰል ይናገራል ፡፡ ዋይርስቤ መዝሙር ከመዝሙር 23 እና 24 ጋር ከሰዎስቱ እንደ መጀመሪያ አካል መመልከት እንደምንችል ያስቀምጣል ፡፡ በመዝሙር 22 መልካሙ እረኛ ስለ በጎቹ ይሞታል ፤ በመዝሙር 23 ታላቅ እረኛ ስለ በጎቹ ይጠነቀቃል ፤ በመዝሙር 24 ታላቁ እረኛ በጎቹን በመመለስ ይሸልማቸዋል ፡፡ ማክአርቱር መዝሙር 22 በመከራ ላይ በኃዘን በመጀመር በማጠቃለያው እግዚአብሄር ወደ ማመስገን ይጓዛል ፡፡ የመጀመሪያዎቹ 21 ቁጥሮች መከራን/ችግርን ሲገልፁ የመጨረሻዎቹ አስሩ ለእግዚአብሄር ምስጋናን ይይዛሉ ፡፡ ማክአርቱር አዲስ ኪዳን “ በቀድሞዉ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ መዝሙር እንደ አምስተኛ ወንጌል እኩል በመሆን 15 መሲሀዊ ጥቅሶች ወይም የሚያወሱ እንደሚይዝ “ ይናገራል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ይህ መዝሙር ስለ ዳዊት ስለራሱ ጭንቀትና ስለ እግዚአብሄር ነፃ አዉጪነት የሚናገር ቢሆንም በሚያስገርም ዝርዝር ስለ ኢየሱስ ስቅለትና ትንሳኤ በትንቢታዊነት ይገልፃል “ ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (22፡ 1)፡ ኢዮብ 3, መዝሙር 69 እና ኤርምያስ 23 የመዝሙር 22 የመጀመሪያዎቹ 21 ቁጥሮች እንዳደረጉት ሁሉም የኃዘን ተመሳሳይ ገለፃ ይይዛሉ ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንደሚሰቀል መዝሙር 22 ጥቅሷል፡ “ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ ፡፡ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ፤ ይህም አምላኬ አምላኬ ስለ ምን ተዉኸኝ ? ማለት ነው “ (ማቴ 27፡ 46) ፡፡ ማክአርቱር በቁጥር 1 “ ለምን ተዉኸኝ “ ብሎ የተጠቀመበት ቃል “ በኃይል በዳዊት ተሰምቶት የነበርና በኃይልም በመስቀል ላይ በክርስቶስ የተቀመሰ ስለ ግላዊ መተዉ ጠንካራ ገለፃ እንደሆነ “ ይፅፈዋል ፡፡

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ እነሆ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል አሁንም ደርሶአል ፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለሆነ ብቻዬን አይደለሁም “ (ዮሐ 16፡ 32) በማለት ነግሯቸዉ ነበር ነገር ግን በመስቀል ላይ ሲሰቀል እግዚአብሄር ትቶት እንደነበር ጮኸ ፡፡ በመስቀል ላይ እየተሰቀለም እንኳን እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር እያለ የዓለምን ኃጢዓት በእርሱ ላይ በመዉሰድና ዋይርስቤ እንደፃፈው “ በአንዳንድ በማይገለፁ መንገዶች ከእግዚአብሄር መገኘት ፊት ርከዉ የጠፉት ኃጢዓተኞች የሚደርስባቸዉን ፍርድ እንደደረሰበት “ እግዚአብሄር እንደተወዉ ተሰማው ፡፡

መዝሙር (22፡ 2-5)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ማክአርቱር የዳዊትን ቅሬታዎች “ ለእኔ ባትመልስልኝም እንኳን ለህዝብህ የቸርነት ጊዜን ደግሞ ያሳይ የነበረ አሁንም የእስራኤል ቅዱስ እንደሆነ “ ያስረዳል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በታላቅ መከራ/ህመም ዉስጥ እንኳን እያለ ዳዊት በአባቶቹ አምላክ እምነቱን እንዳወጀ/እንደተናገረ “ ያስታውቃል ፡፡

መዝሙር (22፡ 6-11)፡ዋይርስቤ የዳዊት የችግሩ መደረስ/መከራ በሰዎቹ እንዲተዉ እንዳደረገዉ ያመለክታል ፡፡ መሲሁን እንደገለፀው ኢሳያስ “ ፊቱ ከሰዎቹ ሁሉ ይልቅ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጎሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ እንዲሁ ብዙ አሕዛብ ያስደንቃል “ በማለት ፅፏል (ኢሳ 52፡ 14) ፡፡ ዳዊት “ የሰዉ ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ “ ብሎ እንደ ነበረው ኢየሱስም “ ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር ፡፡ መኳንንቱም ደግሞ ፡፡ ሌሎችን አዳነ ፤ እርሱ በእግዚአብሄር የተመረጠዉ ክርስቶስ ከሆነ ራሱን ያድን እያሉ ያፌዙበት ነበር “ (ሉቃ 23፡ 35) ፡፡

በችግሩ መካከል ላይ ዳዊት በእግዚአብሄር ላይ መደገፉን ቀጠለ፣ በእግዚአብሄር ላይ ያለዉን እምነት አልተወዉም ፤ ለቁጥር 1 እንደ ድግግሞሽ በቁጥር 11 በእግዚአብሄር ላይ መታመኑን/መደገፉን ገለፀ ፡፡

መዝሙር (22፡ 12-21)፡ዋይርስቤ ዳዊት “ በህጉ እየተወቀሰ/ እየተነቀፈ እንደ ነበር “ ያስታዉቃል ፡፡ ዳዊት ጠላቶቹን እንደ በሬዎች (ቁጥር 12)፣ እንደ አንበሶች (ቁጥር 13)፣ እንደ ዉሾች (ቁጥር 16) እና እንደ ቀንድ እንዳላቸዉ ከብቶች (ቁጥር 21) ይገልፃቸዋል ፡፡ ዳዊት “ እንደ ዉሃ ፈሰስሁ…..ልቤ እንደ ሰም ሆነ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ “ ብሎ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የዳዊት መሰቃየት ህይወቱ አንድ ሰዉ የማሰሮ ዉሃን እንደሚጨርስ ከእርሱ እንደደረቀች በመረዳት ጥልቅ እንደሆነ “ ያስታዉቃል ፤ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሰቀል ሲሞት አንድ ወታደር ጉኑን ወጋዉ ደምና ዉሃም ከእርሱ ፈሰሰ (ዮሐ 19፡ 34) ፡፡ ዳዊት “ ምላሴ ከአፌ ትናግ ጋር ተጣበቀች “ አለ ፤ “ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈፀመ አዉቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ፡፡ ተጠማሁ አለ “ (ዮሐ 19፡ 28) ፡፡

በቁጥር 16 እንደገለፀዉ የዳዊት እጆችና እግሮች በግልፅ አልተወጉም ነበር ፤ ይህ ስለ መከራዉ የንግግሩ መልክ ነበር ፤ ነገር ግን እንደ አንድ ነቢይ ዳዊት ወደፊት መሲሁ የሚደርስበትን ተመለከተ፡ “ ነቢይ ስለ ሆነ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ “ (ሐዋ 2፡ 30) ፡፡ ኢሳ (53፡ 5) “ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ ፤ የደኅንነታችንም ተግሳፅ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን “ ይላል ፡፡ ዘካሪያስ “ በዳዊትም ቤት ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ ፤ ሰዉም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል ሰዉም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኃዘን ያዝኑለታል “ በማለት ፅፏል (ዘካ 12፡ 10) ፡፡ ቁጥር 18 ስለ ኢየሱስ በግልፅ የሚያወሳ ነበር ፤ “ ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለዉ ተካፈሉ “ (ማቴ 27፡ 35) ፡፡

መዝሙር (22፡ 22-31)፡ዋይርስቤ ዳዊት ታላቅ ጉባኤ ለመግለፅ እንደ ጀመረ (ቁጥር 22-25) ይናገራል ፡፡ ዳዊት ዝም ብሎ መቆየት አልቻለም ፤ ከመከራዉ የዳነ ለመሆን የወጣ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ መነቃቃቱ ተላላፊ የሚሆን ማለት እንደ ሆነ “ ያስመለክታል ፡፡

በመጨረሻም ዋይርስቤ “ ስለ ታላቁ ያሸበረቀዉ መንግስት “ ፅሁፍን አድርጓል (ቁጥር 26-29) ፤ “ እግዚአብሄርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሳል ፤ በዚያ ቀን እግዚአብሄር አንድ ስሙም አንድ ይሆናል “ (ዘካ 14፡ 9) ፡፡ ይህ ታላቅ ክብር ያለበት መንግስት በመከራ ዉስጥ ወደ ምስጋና ለመምራት መጥቷል ፤ ይህ ታላቅ ክብር ያለበት መንግስት የሚመጣዉን ትዉልድ ተፅዕኖ ያደርግበታል ፡፡ የወንጌል መልዕክት በምድር አቀማመጥ ሁኔታ እና በጊዜ ዉስጥ ሁሉ ይሰራጫል ፡፡

መደምደሚያ

መዝሙር 22 ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ እንደሚናገሩት ተመሳሳይ መልዕክት ያዉጃል፡ “ ኢየሱስም ሆምጣጤዉን ከተቀበለ በኋላ ፡፡ ተፈጸመ አለ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ “ (ዮሐ 19፡ 30) ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 132

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 108; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  3. Wiersbe, p. 132.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 612.

  5. MacArthur, p. 612.

  6. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 662.

  7. MacArthur, p. 612.

  8. Wiersbe, p. 133.

  9. MacArthur, p. 612.

  10. Radmacher, p. 662.

  11. Wiersbe, p. 133.

  12. Wiersbe, p. 133.

  13. Radmacher, p. 663.

  14. Wiersbe, p. 134.

  15. MacArthur, p. 612.

  16. Wiersbe, p. 134.

  17. Wiersbe., p. 134.

ጥያቄዎች

  1. ዳዊት እግዚአብሄር “ የልቡን ፈቃድ እንደ ሰጠው ተናገረ “ (መዝ 21፡ 2) ፤ ይህን በመዝ (37፡ 4) ደግሞታል፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች ትስማማላችሁ ? የዳዊትን ንግግር ከኤርምያስ ማረጋገጫ “ የሰዉ ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ እጅግም ክፉ ነው “ ከሚለዉ ጋር እንዴት ታመጣጥኑታላችሁ (ኤር 17፡ 9) ? ከመቀበላችን በፊት መሻቶቻችን ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የሚጣጣዉ ናቸው ? ለምን ወይስ ለምን አይገጥሙም ?
  2. በመዝ (21፡ 3-6) እያንዳንዱ ጥቅስ በግላቸዉ እንዴት ወደ ኢየሱስ ያመለክታሉ ?
  3. በመዝ (22፡ 1) ዳዊት ያለዉ ሌላ የት ላይ በመፅኀፍት ማን ይደግመዋል (ማቴ 27፡ 46) ?
  4. የመዝሙር 22 ሙሉነት ስለ ኢየሱስ ዉልደት፣ ህይወት፣ መቀበርና ትንሳኤ ነው ፡፡ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ዳዊት ይህን ትዉልድ በዝርዝር እንዴት መፃፍ እንደ ቻለ ታስባላችሁ ? እየፃፈ ስለ ነበረዉ ነገር ያውቃል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  5. በመዝሙር (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 22:1–5

“My God, my God, why have You forsaken me? Why are You so far from my deliverance and from my words of groaning? My God, I cry by day, but You do not answer, by night, yet I have no rest. But You are holy, enthroned on the praises of Israel. Our fathers trusted in You; they trusted, and You rescued them. They cried to You and were set free; they trusted in You and were not disgraced.”

ማንም ህመሜን ፣ ምሬቴን እና ጭንቀቴን የሚረዳኝ የለም ብለህ አስበህ ታውቃለህ ፡፡ በቃ ብቻዬን እንደሆንኩ ነው ሚሰማኝ ብለህ ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር የት ነው ያለው ? ዳዊት የመሲሁን መከራና ስቃይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወደ ምድር ከመላኩ ከትውልዶች በፊት ተንብዮ ነበር ፡፡ ይህም ሊፈጸም ሲል ኢየሱስ ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፤ ልክ ዳዊት እንደጻፈው ፡- “አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ ? “ ዳዊት ቀድሞ ተንብዮት ነበር እናም አንተ የኢየሱስን ታሪክ ስታነብ እርሱ በርግጥ መከራን ተቀብሏል ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ኢየሱስን ከመከራው አዳነው ፡፡ ኢየሱስ ተነሳ ፣ ከሞት ወደ ህይወት ተሻገረ ፡፡ በርግጥ መዝሙር 22 በአዲስ ኪዳን ለአስራ አምስት ጊዜ ተጠቅሷል ፣ተጠቁሟል እንድሁም ተገልጻል ፡፡ በጥንትቷ ቤተ ክርስቲያን አንዳንዶች “ አምስተኛው ወንጌል “ ብለው ይጠሩታል ፡፡

እናም ልክ መጽሀፉ ኢየሱስን እንደተነበየው ሁሉ ፣ ለአንተም እንድሁ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ህይወትህን ከጉድጓድ እንድሁም ከሞት ያስነሳል ፡፡ በማንኛውም ሁኔታም ውስጥ ስታምነውም እርሱ ስቃይህን ይፈውሳል ፡፡ አንድ ቀን እርሱ ወደ ላይ ያነሳሃል አንተም ስሙን ታወድሳለህ ፡፡ ስለ ታላቅ ስሙ ለሌሎች ትመሰክራለህ ፡፡ ስለዚህ ጽና ፡፡ ልክ ኢየሱስ በአባቱ ላይ ያለውን ተስፋ አጥብቆ እንደያዘ ሁሉ አንተም በክርስቶስ ያለውን ተስፋ ጠብቅ ፡፡

“አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ ። አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ፥ አልመለስህልኝም፤ በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም ። በእስራኤል የተመሰገንህ አንተ ግን በቅድስና ትኖራለህ ። አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፥ ተማመኑ አንተም አዳንሃቸው ። ወደ አንተ ጮኹ አመለጡም፥ አንተንም ተማመኑ አላፈሩም ። “

  • መዝሙር 22፡1-5

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 22:27–31 — “ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሱ፤ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ ። መንግሥት ለእግዚአብሔር ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል ። የምድር ደንዳኖች ሁሉ ይበላሉ ይሰግዳሉም፤ ወደ መሬት የሚወርዱት ሁሉ በፊቱ ይንበረከካሉ፤ ነፍሴም ስለ እርሱ በሕይወት ትኖራለች ። ዘሬ ይገዛለታል፤ የምትመጣው ትውልድ ለእግዚአብሔር ትነግረዋለች ፤ ጽድቁንም ለሚወለደው ሕዝብ፥ እግዚአብሔር ያደረገውን ጽድቁን፥ ይነግራሉ ። “

ማቴዎስ 27:46 — “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው ።

ሐዋርያት ሥራ 2:29–30 — “ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው ። ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፥ ፡፡ “