Words to Pray
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በጥበብ መፅኀፍት ጥናታችን ላይ ቀጥለናል በተለይም በመዝሙር መፅሀፍ ጥናታችን ፤ በመዝሙር 18 ዳዊት በጠበቀ መቀራረብ በፀሎት እግዚአብሄርን እንዴት እንዳመሰገነ ተመልክተናል ፡፡ እኔ የምፈልገዉ አንዱ ይህ የዳዊት የፀሎት ህይወት ነው ፡፡ በፀሎት የዳዊትን ቀረቤታና ግንኙነት ከእግዚአብሄር ጋር እፈልገዋለሁ ፡፡ ዛሬ እንዴት መፀለይ እንዳለባችሁ እንድታስቡ የሚረዷችሁን ስምንት ቃላቶች እሰጣችኋለሁ ፤ ያ ማለት ስለ ዉጊያዉ ጥቂት መረጃዎች ያስፈልጉናል ማለት ነዉ ነገር ግን በመዝሙር ወይም በመፅሀፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች በተለዬ የተሰጠ የለም ፡፡ በመዝሙር 21 የደስታ/የማሞገሺያ ቃላቶች ምክንያት ዉጊያዉ በደህና እንዳለቀ እናዉቃለን ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (20፡ 1-5)፡ ዋይርስቤ የመጀመሪያዎቹ አምስት ቁጥሮች ለንጉሳቸዉ የህዝቡን ፀሎት ይሸፍናሉ ፤ በቁጥር 1 ሰዎቹ እግዚአብሄር ንጉሳዉን በችግሩ ቀን ጊዜ እንዲጠብቀዉ ፀለዩ ፡፡ በፀሎት የምንጠቀማቸዉ ስምንት ቃላቶች ላይ በመመልከት ጠቅሻቸዋለሁ ፤ የመጡት ከጂሚ እርዊን ሲሆን በእነዚህ ፅሆፎች ዉስጥ ለየት ተደርገዉ ይፃፋሉ ፡፡ የመጀመሪያው ስማኝ /መልስልኝ (መዝ 20፡ 1, 9) ነው ፤ ስንፀልይ እንዲመልስልን እግዚአብሄር በሚያስፈልገን ላይ መግለፅ እንችላለን ፡፡ የሁለተኛዉም በቁጥር 1 ሲሆን ጠብቀኝ ነው ፤ እግዚአብሄርን ስለ ጥበቃ መጠየቅ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ፀሎት ነው !
በመዝሙር 20 በዘጠኙ ቁጥሮች ላይ ስድስት ጊዜ “ ያድርግልህ “ በሚል የፀሎት ጥያቄ ይጀምራል ፡፡ በቁጥር 2 ሰዎቹ ይርዳህ አሉ ፤ ማክአርቱር “ ከመቅደሱ “ እና “ ከፂዎን “ የሚሉት ቃላቶች “ ዳዊት መልሶ በመያዝ በፂዎን ተራራ የታቦቱ ማደሪያ ላይ በመሰረተው የእግዚአብሄር መገኛን ስፍራ በታቦቱ ላይ እንደሚያመለክት “ ይገልፃል ፡፡ ይህ እንዴት ሁል ጊዜ እንደምንፀልይ ነዉ ምክንያቱም ሁሉንም ቀን በዉጊያ ላይ ነን ፤ በቁጥር 2 ሰዎቹ ያጥናህ ብለዉ ፀለዩ ፡፡
በቁጥር 3 ሰዎቹ እንዲያስበዉ ፀለዩ ፡፡ አዎ እግዚአብሄር ያስበናል ነገር ግን ለማስታወስ እግዚአብሄርን በመጠየቅ ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነታችንን እናስታውሳለን ፡፡ ሰላህ በመቆም ስለ እግዚአብሄር ማንፀባረቅ ማለት ነው ፡፡
ከዚያም እንደ ልብህ ይስጥህ(ቁጥር 4) ይፈፅምልህ (ቁጥር 4-5) በማለት ፀለዩ ፡፡ ቁጥር 4 እንዲቀርብልን የምንፈልገዉን የብልፅግና አይነት ፀሎት ሊሰማ ይችላል ፤ ስለ ልብ በስጋና በተንኮል እናስባለን (ኤር 17፡ 9, ማቴ 15፡ 19, ማር 7፡ 20-23, ሮሜ 7፡ 18-20) ፤ ነገር ግን “ ልብ “ የሚለዉ ቃል ሌላ ትርጓሜ አለው (ዕብ 4፡ 11-13) ፤ መዝ (37፡ 4) “ በእግዚአብሄር ደስ ይበልህ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል “ (መዝ 37፡ 5-7) ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ልባችንን በመቀየር ንፁህ በማድረግ ከእግዚአብሄር ጋር የተገናኘ ይሆናል (ማቴ 5፡ 8, ዮሐ 15፡ 7) ፡፡
መዝሙር (20፡ 6-9)፡ የመጨረሱ ቃል በቁጥር 5-8 የተሰጡ ናቸው፡ አንሳኝ/ከፍ ከፍ አድርገኝ ፤ ፍቃዱን ለሌሎች እስክናቀርብ ድረስ እግዚአብሄር ከፍ እንዲያደርገን መፀለይ ፡፡ ይህ ጠቅላላዉ መዝሙር እግዚአብሄር ፀሎታችንን እንደሚሰማና ለፍላጎቶቻችን መልስ ለመስጠት እንደሚፈልግ ስለ መታመን ነው ፡፡
መደምደሚያ
ይህ በዉጊያ ፊት እንዴት መፀለይ እንደምንችል የሚያስደንቅ መልክ /ስዕል ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 131.
Jim Erwin, www. Patheos.com; available at https://www.patheos.com/blogs/jimerwin/2016/04/18/psalm-201-9-trusting-god-prayer/.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 611.
ጥያቄዎች
-
በመዝ (19፡ 1) ዳዊት የእግዚአብሄርን ክብር ይናገራሉ ምንን አለ ? ፍጥረት እንዴት የእጆቹን ስራ በመናገር እዉቀትን ይገልጣሉ ? ሮሜ 1፡ 20 አንብቡ ፡፡ እነዚህ ሁለት ጥቅሶች እንዴት አንዱ ሌላዉን ይደግፋል ተመሳሳይ እዉነቱንም ተናገሩ ?
-
የእግዚአብሄር ህግ ህይወትን እንዴት ያድሳል ወይም ይመልሳል (መዝ 19፡ 7, 23፡ 3) ?
-
ዳዊት ጌታን የተሰወረ ኃጢዓቱን እንዲያጠፋለት ጠየቀ (መዝ 19፡ 12) ፤ የተሰወሩ ኃጢዓቶች ምንድናቸዉ? እነዚህን ከሚታወቁ/ከድፍረት ኃጢዓተኞች ጋር አነፃፅሩ ፤ (መዝ 19፡ 13) ፡፡
-
ያል ስልጣን፣ ሆን ተብሎ ወይም በድፍረት የሚደረግ ኃጢዓት እንዴት ይገዛችኋል ወይም በላያችሁ ላይ ይሰለጥንባችኋል (መዝ 19፡ 13, ሮሜ 6፡ 12-14) ? ለማሸነፍ የታገላችሁ ኃጢዓት ነበራችሁ ? ከዚያ እንዴት ነፃ ወጣችሁ ?
-
መዝ (19፡ 14) አንብቡ ፤ ዳዊት የአፉ ቃልና የልቡ ሀሳብ በእግዚአብሄር ፊት የሚያስደስት እንዲሆን ለምን ጠየቀ ? ከልባችሁ ጋር በማይገጥመዉ በቃላችሁ ከእግዚአብሄር ጋር ታግላችሁ ታውቃላችሁ ? ወደ መጋጠም/መመሳሰል እንዴት ልታመጡት ትችላላችሁ ? (ምሳ 4፡ 23, ኤር 17፡ 9, ሉቃ 6፡ 45, ዕብ 3፡ 13)
-
መዝ (20፡ 7) “ እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሄር ስም ከፍ ከፍ እንላለን “ ይላል ፤ በችግርና በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ መጀመሪያ ወደ እግዚአብሄር ትመለሳላችሁ/ትዞራላችሁ ? ወይስ እንዲረዷችሁ በሰዎች ወይም በሌሎች ነገሮች “ ትታመናላችሁ “ ?
-
በመዝሙር (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 20:4–5
“May He give you what your heart desires and fulfill your whole purpose. Let us shout for joy at your victory and lift the banner in the name of our God. May Yahweh fulfill all your requests.”
በየቀኑ የእግዚአብሔርን መንግስትና ጽድቁን ስትሻ መንፈሳዊ ውጊያ ይገጥምሀል ፡፡ ልብህን ፣ ህይወትህንና አሳብህን ያጠፋ ዘንድ ደግሞም ከእግዚአብሔር የተሰጠህን ስራ ከማሳካት ይከለክልህ ዘንድ ጠላት ያቅዳል ፡፡ ይሁን እንጅ ስትጸልይ ሊመልስልህ ፣ ሊጠብቅህ ፣ ሊረዳህ ፣ ሊያጸናህና ከፍ ከፍ ሊያደርግህ ከጎንህ እግዚአብሔር አለ ፡፡ አትፍራ ፡፡
በንጹህ ልብ በእርሱ ደስ ይልህ ዘንድ እግዚአብሔር ይጠይቅሀል ፡፡ ይህንን ስታደርግ የአንተ መሻት እርሱ ለአንተ ካለው ፍለጋ ጋር ይስማማል ፡፡ የእርሱ ኃይል ፣ ጊዜ ፣ ማስተዋልና ጥበቃ ከእግዚአብሔር የተቀበልከውን ተልዕኮ እንድትወጣ ያስችልሀል ፡፡ አንዳንዶች በሰረገሎቻቸውና በፈረሶቻቸው ይታመናሉ ነገር ግን አንተ እንደ አማኝ ፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር ታመን ፡፡ ነገሮች በዚህ ምድር ላይ ሲጠፉና ሲወድቁ ፣ማን ለዘላለም ጸንቶ እንደሚቀር ገምት ? የክብር ንጉሥ ! ብርቱና ኃያል የሆነው ጌታ ድልን ይሰጥሃል ፡፡ በእግዚአብሔር ስም ሰንደቅዓለማህን ከፍ አድርገህ አንሳ ፡፡ እርሱ መመስገን ይገባዋል ፡፡
“እንደ ልብህ ይስጥህ፤ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ ። በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ ። “
- መዝሙር 20፡4-5
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 20:7–9 — “እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን ። እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን ። አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥ በጠራንህም ቀን ስማን ። “
መዝሙር 37:4 — “ በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል ። “
ኤፌሶን 6:12 — “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።