The Head of the Nations
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የመዝሙር መፅሀፍን ማንበብ ለኔ ስሜትን የሚነካ ወደታችና ወደላይ የሚያደርግ ነው ፡፡ ስሜትን የሚነኩ ፅንፎች ታላቅ ናቸው ፡፡ መዝሙር 18 ምስጋና እንደሚሰጥ መዝሙር ስሜትን በሚነካ ሁኔታ የሚነሳና አንዱ የንጉሳዊ መዝሙር ነው ፤ “ ርዕሱ አንድ የተወሰነ ክስተትን (በቀኑ ላይ) ብቻ የሚጠቅስ ቢመስልም እንኳን የእግዚአብሄር ነፃ ማዉጣት ከጠላቶቹ እጅ እና ከሳዖል እጅ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ በቀድሞዉ ህይወቱ የዳዊትን ጠቅላላ ህይወት ምስክርነት ለማጠቃለል የዚህን ዋና ኃሳብ (ራስጌ) ቋንቋ ለማስተዋል የተሻለ ነው “ ፡፡ በመዝሙር ዉስጥ ይህ ሁለተኛው ረጅም/ትልቅ (የሚበልጠው መዝሙር 60 ብቻ ነው) ራስጌ ነው ፤ መዝሙር 18 በኃይለኛዉ 2ሳሙ (22፡ 1-2) ይመስላል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (18፡ 1-18)፡ ዋይርስቤ የመዝሙር የመጀመሪያዎቹ 18 ጥቅሶች “ ስንጠራዉ እግዚአብሄር እንዴት እንደሚደርስ “ የሚያወሩ ናቸው ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ጥቅሶች የዳዊትን የምስጋና ግጥሞችን ያቀርባሉ ፡፡ ዳዊት “ ጌታ ሆይ እወድሀለሁ “ ይላል ፤ ማክአርቱር “ ፍቅር “ ለሚለዉ ዕብራዊ ቃል እዚህ ጋር የተጠቀመዉ “ ብዙ ጊዜ ኪዳናዊ ትርጉም የሚሸከም የተለመደ ቃል አልነበረም ነገር ግንበጣም የቀረበን ግንኙነት ለመግለፅ የአንድ የቃል ቡድን ያልተለመደ የግስ ቃል እንደሆነ “ ይገልፃል ፤ (በዮሐ 21፡ 15-17 ተመሳሳይ የፍቅር አይነት ተገልጾአል) በቁጥር 2 ዳዊት እግዚአብሄር ለእርሱ ምን እንደሆነ ለመግለፅ ሰባት ዘይቤዎችን ይጠቀማል፡ አለቴ፣ አምባዬ፣ መድኃኒቴ፣ አምላኬ፣ የደህንነት ቀንዴና መጠጊያዬ (መዝ 84፡ 9, 89፡ 18) ፡፡ የህይወት ዉጊያ/ፈተና በገጠመዉ ጊዜ ዳዊት በሚፈልገዉ እግዚአብሄር ሁሉም ነው ፤ እግዚአብሄር ለጥሪዉ በመመለስ ከጠላቶቹ ያድነዋል (ቁጥር 3) ፡፡ ዳዊት ተስፋ በመቁረጥና በድንጋጤ ሞትና ጣር ገጠመዉ (ቁጥር 4-5) ፤ ዳዊት ሞት ሲገጥመዉ ጮኸ እግዚአብሄርም ሰማው (ቁጥር 6) ፡፡
በቁጥር (7-15) ዳዊት “ ስለ እግዚአብሄር መገኘት አምላክነቱን በግልፅ/በጉልህ ግጥማዊ የቅኔ መልክ …. በብዛትም/በኃይልም በሁሉም ፍጥረቶች መቅሰፍታዊ በሆኑ መልሶች በመግለፅ ያቀርበዋል “ ፡፡ ዳዊት ምድር ስትናወጥና ተራሮች ሲንቀጠቀጡ የእግዚአብሄርን ኃይልና ቁጣ አየ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ሰማያት ዝቅ አሉ እግዚአብሄር ወደ ምድር መጣ፣ በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ በንፋስም ላይ መጠቀ (ቁጥር 9-10) ፤ ከሰማያትም በማንጎድጎድ ፍላጻዎችን አወረደ መብረቆችንም አበዛ (ቁጥር 13-14) ፡፡ የአለም መሰረቶችና የዉኆች በእግዚአብሄር ግሳፄ ይታያሉ (ቁጥር 15) ፡፡ እግዚአብሄር ዳዊትን ከዉኆች ጥልቀትና ከኃይለኛ ጠላቶቹ ታደገው (ቁጥር 16-17) ፡፡ እግዚአብሄር ዳዊትን አዳነው (ቁጥር 18) ፤ ( እነዚህ መፅሀፍቶች ከእግዚአብሄር ጋር የፍቅር መቀራረብን ምሳሌ ይሰጣሉ፡ መዝ 102፡ 13, 103፡ 13, ኢሳ 49፡ 15, ሆሴ 1፡ 7) ፡፡
መዝሙር (18፡ 19-27)፡ዋይርስቤ ቁጥር 19-27 ስንታዘዘዉ እግዚአብሄር እንዴት እንደሚሸልመን የሚያወሩ እንደሆኑ ይገልፃል ፡፡
መዝሙር (18፡ 28-45)፡ዋይርስቤ እነዚህ ቁጥሮች ለእርሱ በምንታዘዝ ጊዜ እግዚአብሄር እንዴት እንደሚያሰለጥነን የሚያወሩ እንደሆኑ ያመለክታል ፤ ዳዊት እዚህ ስፍራ (ቦታ) ላይ ለመድረስ በህይወት በብዙ ልምምዶች ዉስጥ ሄዷል እግዚአብሄርም በእነዚያ ልምምዶች እንዲያድግ አስተማረዉ/አሰለጠነው ፡፡
ቁጥር 43 እግዚአብሄር ዳዊትን በማዳን የህዝቡ አለቃ እንዳደረገዉ ይናገራል ፤ በተጨማሪም ይህ በሁሉም ህዝብ ላይ አለቃ ለሚሆነዉ ስለ ሚመጣዉ መሲህ የተነገረ ነው ፡፡ ማቴ (25፡ 31-34) የህዝቡ አለቃ (መሪ) የሆነው የመሲሁ ትንቢታዊ መልክን የመዝ (18፡ 43) መልክ ይሰጣል፡ “ የሰዉ ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላዕክቱ ሁሉ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል ፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል ፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል ፡፡ ንጉሱም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል ፡፡ እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁመንግስት ዉረሱ “ ፡፡ ቀሪዉ ማቴዎስ 25 በበግ የተመሰሉት ሕዝቦች ከእስራኤል ጋር የተሰለፉ እንደ ሆኑ ይገልፃል ፡፡
ራዕ (7፡ 9-10) ይህን መልክ ይደግፋል፡ “ ከዚህ በኋላ አየሁ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ ፤ በታላቅም ድምፅ እየጮሁ ፡፡ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ ! “
መደምደሚያ
ዋይርስቤ “ ስናመልከዉ እግዚአብሄር እንደሚከብር “ ይናገራል ፤ በዚህ ሁሉ እግዚአብሄር በአምልኳችን ይክብራል፡፡ የዳዊት መዝሙሮች “ በአሕዛብ መካከል አምላኬን አመሰግነዋለሁ፣ ስለ ስሙም እዘምራለሁ ፤ ለንጉስ ታላቅ ድልን ይሰጣል፣ ለቀባዉም ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ታማኝነቱን ያሳያል “ ከሚሉት ከእነዚህ ቃላቶች ጋር ይቀርባል ፤ ይህ ወደ ዳዊት ኪዳን በማመልከት ወደ መሲሀዊ ኪዳን የሚያመለክት ንጉሳዊ መሲህ ትንቢት ነው ፡፡ በሮሜ (15፡ 9) ጳዉሎስ መዝሙር 18 ወደ ትኩረት ያመጣዋል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 609.
James A. Johnston and R. Kent Hughes, Psalms 1–41, v. 1 (Wheaton: Crossway, 2015), p. 193.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 123.
MacArthur, p. 609.
MacArthur, p. 609.
Wiersbe, p. 123.
Wiersbe, p. 124.
Wiersbe, p. 125.
ጥያቄዎች
-
መዝሙር 18 ከ 2 ሳሙኤል 22 ጋር በጣም አንድ አይነት ነው፣ ነገር ግን በጣም ዋናዉ ሀሳብ በ 2ሳሙኤል ላይ የሚገኝ አይደለም ፤ ያ ሀሳብ/ፍሬ ነገር ምንድን ነው ? እግዚአብሄር ጥንካሬአችን ነዉ ባላችሁ ታስባላችሁ ? ምን ይመስላል ?
-
መዝ (18፡ 20-24) ላይ ተመልከቱ፣ በትክክል እንደ ኢዮ (23፡ 11-12) እና 27፡ 6 ተመሳሳይ መልዕክት አለው ፤ እነዚህን የፅድቅ ጥያቄዎች ሁለቱም እንዴት ሊያደርጉ ቻሉ ?
-
በመዝሙር 18 ከሰዎስት እስከ አራት ጊዜ በትርጉሙ መሰረት ዳዊት እግዚአብሄርን እንደ አለቱ ጠቀሰው (መዝ 18፡ 2, 31, 46) ፤ “ አለት “ በማለት ያጠናነዉ መፅሀፍ የትኛዉ መፅሀፍ ነው ? እግዚአብሄርን በዚህ መንገድ ታስቡታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡትም ?
-
መዝሙር (18፡ 26) ቢያንስ በሰዎስት የተለያዩ ትርጓሜዎች ላይ በመመልከት የዚህ ጥቅስ ሁለተኛዉ አካል ምና ማለት እንደሆነ አብራሩ
-
በመዝሙር 18 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 18:1
“I love you, LORD, my strength.”
ወደ እግዚአብሔር በስሜት የተጣራኽበትን ፣ ከልብ የሆነ ጸሎት የጸለይክበትን ጊዜ አስታውስ ፡፡ ምናልባት ፈውስን ፣ የማይቻል ስጦታን ፣ መለኮታዊ ጥበብን ወይም ከጥፋት መንገድ መከልከልን ፈልገህ ሊሆን ይችላል ፡፡ እናም እግዚአብሔር ተንቀሳቀሰ “ የእግዚአብሔር ብቻ “ በሆነ መንገዱም መለሰ ፡፡ እናም ቆም ብለህ እግዚአብሔርን አወድሰህ ለእርሱም ምስጋናን አቅርበህ ነበር ? ምናልባትም እግዚአብሔርን ለማመስገን ቃላት አልነበሩህም ይሆናል ? ወደ ደጁ በምስጋና በአምልኮም በፊቱ መቅረብ ፈልገህም ይሆናል ነገር ግን በግልጽ ለመናገር ስትሞክር ግራ ትጋባለህ ፡፡ ደቂቃ ውሰድና መዝሙር 18 ጮክ ብለህ አንብበው ፡፡ የምር አድርገው ፡፡ ዳዊት ጥልቅ በሆነ አምልኮና ምስጋና እግዚአብሔርን ያመሰግናል ፡፡ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ወደ እግዚአብሔር ከሚጣራውና የእግዚአብሔርን ኃይል በማይታመን “ የእግዚአብሔር ብቻ “ በሆነ መንገድ ሲያስመልጠውና ሲፈውስው ካያ ከዚህ ሰው ፣ መማር ትችላለህ ፡፡
ዛሬ እግዚአብሔርን እንድህ በማለት ጀምር “ ጉልበቴ ሆይ እወድሀለሁ ፡፡ “ ቀላል ሊመስልህ ይችላል ፣ ነገር ግን ጮክ ብለህ ድገመው ፣ ለእግዚአብሔር ከሆነ እውነተኛ አድናቆት እስኪመነጭ ድረስ ደጋግመው ፡፡ ስታመልከው እግዚአብሔር ይከብራል ፡፡ ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን ተጣራ ፣ ትድናለህም ፡፡
“አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ ። “ - መዝሙር 18፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 18:2-3 — “ እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ ። “
- ማርቆስ 12:30 — “ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ። “
- ራእይ 14:7 — “በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።