Finding Eternal Joy
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 16-17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የመዝሙር መፅሀፍ ለህይወታችን የማይናገርበት አንድ ጊዜም አይኖርም ፡፡ ብዙ አይነት መዝሙሮች ላይ ተመልክተናል ፤ አንዳንድ ምሁራን መዝሙር 16 በእግዚአብሄር ቸርነት እንደ ግለሰብ ደስታ ሲለዩት ሌሎች ደግሞ ይህን እንደ ኃዘን መዝሙር ይለዩታል ፡፡ በዚህ መዝሙር ዉስጥ ስንጓዝ የኢሳያስ 53 የመከራ አገልጋይ የሚመስል ይሰማል ፤ በመዝሙር 16 የኃዘን ቋንቋ እና በዚያ የደስታ መግለጫ ነው ፡፡ በመዝሙር ዉስጥ “ የኔ “ የሚለዉ 12 ጊዜ ተጠቅሟል ለምሳሌም “ የኔ ድርሻ “፣ “ የኔ ተስፋ “፣ “ የኔ ህሊና “ እና “ የኔ ቀኝ እጅ “ ፡፡ የዳዊት ደስታ በደስታዉ፣ በፍላጎቱ ወይም ደስተኛ በመሆኑ የተገለፀ ነው ፡፡ የዚህ ቋንቋ ሁሉም እግዚአብሄር በዳዊት ህይወት የተለዬ ነገር እያደረገ እንደነበር ያሳያል ፤ በተጨማሪም ይህ መሲሀዊ መዝሙር ስለሆነ አብዛኛዉ የመዝሙር መጨረሻዎች ኢየሱስን እንደ መሲህ ለመግለፅ በጳዉሎስና በጴጥሮስ በሁለቱም ጥቅም ላይ ዉለዋል ፡፡ ለመዝሙር 16 ንዑስ ርዕሱ “ የዳዊት ቅኔ “ ነው ፡፡ በመዝሙር መፃሀፍት ከእነዚህ ዉስጥ ስድስቱ ናቸው ፤ ምሁራን/መፅሀፍ ቅዱስ አዋቂዎች ቃሉ ምን ማለት እንደሆነ አይስማሙም ነገር ግን “ በወርቅ የተሰራ ድብቅ ኃብት ወይም ቁም ነገር አባባሎችን የያዘ አንድ ግጥም “ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ ፡፡ ዋይርስቤ በእያንዳንዱ ክፍል ዉስጥ ጭብጡን ለመግለፅ ሰዎስት መግለጫዎችን ይጠቀማል፡ “ የህይወት ጌታ “ (ቁጥር 1-8)፣ “ የሞት ድል አድራጊነት/አሸናፊ “ እና “ የዘላለም ደስታ “ (ቁጥር 11) ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (16፡ 1-8)፡ በቁጥር 1 ዳዊት ስለ ጥበቃ ወይም ስለ መጠበቅ ይጠይቃል ማለትም እግዚአብሄርን “ እንደ እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቃቸው “ እንዲጠብቀዉ ወይም በሚገባ እንዲከታተለው “ ይጠይቃል ፡፡ በቁጥር 2 ዳዊት እግዚአብሄር በሰጠዉ በሁሉም መልካም ነገሮች መደሰት ፈለገ (መዝ 21፡ 3, 23፡ 6, 73፡ 25, 28፣ ማቴ 19፡ 17) ፤ ዳዊት እግዚአብሄር የሁሉም ጥሩና ፍፁም ስጦታዎች ሰጪ እንደሆነ አዉቋል (ያዕ 1፡ 17) ፡፡
በተጨማሪም ዳዊት በምድሪቱ የነበሩ፣ በእግዚአብሄር የታመኑና ኪዳኑን ባከበሩት ቅዱስ ህዝቦች (የሚያምኑ ቅሬቶች) ላይ ደስተኝነትን ወሰደ (ቁጥር 3) ፡፡ እግዚአብሄር ቅዱስ እንድንሆን ይጠራናል (ዘጸ 19፡ 6, ዘሌ 19፡ 2, 20፡ 7-8, 26, ዘዳ 7፡ 6) ፤ በራሳችሁ ዙሪያ ቅዱስ የሆኑትን አደርጉ ፡፡ በምድሪቱ ሌሎቹ ቡድኖች በማያምኑ ጣዖት አምላኪዎች የተሰራ ነበር ፡፡ ዳዊት ስማቸዉን አልናገርም አለ (ቁጥር 4) ፤ ቅዱስ በሆኑት ራሳችንን ስናስከብብ ግን ከአለም ወጥተን እንድንሄድ ተጠርተናል (ሮሜ 12፡ 2, ያዕ 1፡ 27, 4፡ 4) ፡፡ ስለ ክርስቶስ ብርሃንና ጨዉ ለመሆን በአለም እንሆናለን ፡፡
በቁጥር 5 ዳዊት እግዚአብሄር እድል ፋንታዉ እንደሆነ ያስተዉላል ፤ “ እድል ፋንታዬ/ድርሻዬ “ የሚለዉ ሀረግ በተስፋይቱ ምድር የተቀበሉትን የእያንዳንዱ የ11 ነገዶችን (ከሌዊ በስተቀር) ዉርስ ያሳያል ፡፡ ለዳዊት ራሱ እግዚአብሄር ድርሻዉን ተስፋዉ ነበር ፡፡ ዳዊትም ስለ ተቀበላት ምድርና የምድሪቱ እንደ ባላደራ ተግባሩን ይገነዘባል (ቁጥር 6) (ስለ ምድሪቱ አስተዳደር፡ ዘዳ 19፡ 14, 27፡ 17, ምሳ 15፡ 25, 22፡ 28) ፡፡ ዳዊት ስለ ምክርና “ በቅጣቱና በተግሳፅ “ ምሽቱን ስለማሳለፍ በእግዚአብሄር ላይ ተደገፈ ፤ በሚኖርበት ህይወት እግዚአብሄር መሰረቱ እንደሆነ ይለያል (ቁጥር 8) ፡፡
መዝሙር (16፡ 9-10)፡ እነዚህ ጥቅሶች በዚህ መዝሙር መሲሀዊ ትንቢትን ይጀምራሉ ፡፡ ዋይርስቤ “ ስጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች “ የሚለዉ ሀረግ ስለራሱ ስለዳዊት ሳይሆን ስለ መሲሁ የተነገረ እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡ ልየታዉ በቁጥር 10 ይቀጥላል “ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም “ ፡፡ በበዓለ ኃምሳ ቀን ላይ የጴጥሮስ ጠቅላላ መልዕክት በመዝ (16፡ 9-10) ላይ የተመሰረተ ነው (ሐዋ 2፡ 22-31) ፡፡ ዳዊት የሚመጣዉ መሲህ ሞትን ድል እንደሚያደርገዉ ተንብዩአል ፤ ጳዉሎስም በሐዋ (13፡ 35) የመሲሁ አካል እንደማይበሰብስ በገለፀ ጊዜ መዝሙር 16 ጠቅሶታል (ሉቃ 24፡ 28-31, 36-43) ፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤ በጳዉሎስና በጴጥሮስ በሁለቱም ጥምህርት ላይ ዋና/ጭብጥ ነገር ነበር ፡፡
መዝሙር (16፡ 11)፡ ቁጥር 11 ዘላለማዊ ደስታ ባለበት በሰማይ ስላለዉ የተትረፈረፈ ደስታ የሚያስደንቅ ስዕልን ይሰጣል ፡፡ የዘላለም ህይወት እዉነት በክብር ንጉስ መገኘት ፊት ለዘላለም መሆን ነው ፡፡
መደምደሚያ
ዳዊት በፍፁም መማርን፣ መፀለይንና ከእግዚአብሄር መስማትን አላቆመም ፡፡ ተመሳሳይ እድል አለን - የመማርና የማዳመጥ እንዲሁም በእግዚአብሄር ደስታን የማግኘት ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 118.
Wiersbe, pp. 118–120.
James A. Johnston, Psalms 1—41, v. 1 (Wheaton: Crossway, 2015), p. 175.
Wiersbe, p. 119.
Wiersbe, p. 119.
ጥያቄዎች
-
መዝሙር (16፡ 8 እና 11) ሁለቱም ቀኝ እጅን ይጠቅሳሉ ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ የቀኝ እጅ አስፈላጊነት ምንድን ነው፣ በመፅሀፍ ቅዱስ ቀኝ እጅ የተጠቀሰ ሆኖ ሌላ የት ቦታ ላይ ትሰማላችሁ ? (ዘፍ 48፡ 13-14, መዝ 110፡ 1, 118፡ 16, ሐዋ 2፡ 33, ሮሜ 8፡ 34, ኤፌ 1፡ 20-21, ዕብ 10፡ 12-13)
-
መዝሙር (16፡ 9-10) እንዴት ስለ ኢየሱስ ትንሳኤ እንዲሁም ደግሞ ስለ መዳናችን ያመለክታል ? በአዲስ ኪዳን ስለ መሲሁ እነዚህን ጥቅሶች የጠቀሳቸው ሌላ ማነው ? (ሐዋ 2፡ 25-28)
-
በመዝሙር 17 ዳዊት ከጠላቶቹ እንዲያድነዉ ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፤ በእግዚአብሄር ፊት ጉዳያችሁን ስትለምኑ ወይም ደግሞ በእናንተ ላይ ስህተት ሰርቶብናል ብላችሁ ያሰባችሁትን ሰዉ በቀል ለመዉሰድ ስትፈልጉ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? መፅሀፍ ቅዱስ ስለዚህ ምን ይላል ? (ዘዳ 32፡ 35-36, ሕዝ 25፡ 17, ሮሜ 12፡ 17-19, ያዕ 1፡ 19-20)
-
ለዘላለም ኢየሱስን ፊት ለፊት ወደ ምናገኝበት ጊዜ ወደ ፊት ከመመልከት ይልቅ ብዙ ጊዜ እንዴት በዚህኛዉ ጊዜ መማላትን /ስኬትን እንመለከታለን (መዝ 17፡ 14)
-
በመዝሙር (16-17) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 16:8–9,11
“I keep the LORD in mind always. Because He is at my right hand, I will not be shaken. Therefore, my heart is glad and my spirit rejoices; my body also rests securely . . .You reveal the path of life to me; in Your presence is abundant joy; in Your right hand are eternal pleasures.”
እንደ ክርስቶስ ተከታይ ሀልጊዜ እግዚአብሔርን በልብህ አሰላስል ፡፡ ሁልጊዜ ፡፡ ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፣ ለቤተሰብህ ቁርስ ስታዘጋጅ ፣ ወደ ቦርድ ስብሰባ ስትሄድ ፣ የስፓርት ጨዋታ ስትጫወት ፣ ስብከት ልትሰብክ ወደ መድረክ ስትወጣ ፣ የዶክተር ሪፓርት ለመስማት ስትጠብቅ ፣ ማታ ልጆችህን ወደ መኝታ ክፍል ስትወስድ ፣ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ለትምህርት ቤት ወረቀት ስትዘጋጅ……… ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በአሳብህ አሰላስል ! ለምን ? ምክንያቱም ይህን ስታደርግ አትናወጥም ወይም በህይወትህ ሽንፈት አይሰማህም ፡፡ ጨዋታ ስትሸነፍ ወይም ልጆችህ አልሰማ ሲሉህ አትናወጥም ፡፡ ከአቻዎችህ ፣ ከስራ አጋሮችህ ወይም ከመምህራኖችህ ድጋፍ ሳይኖርህ ሲቀር ወይም የጤና ምርመራ ውጤትህ ደስ የማይል ውጤትን ሲያሳይ አትናወጥም እንደተሸነፍክ አይሰማህም !
አሳብህን ሰብስብ እንድሁም አይኖችህን የህይወትህ ባለቤት በሆነው በኢየሱስ ላይ አድርግ ፡፡ እርሱ ለአንተ እቅድ አለው ሊጎዳህ ለክፉ አይደለም ሊያበለጽግህ ለመልካም እንጅ ፡፡ ፍጻሜህን እርሱ ይዟል ደግሞም በፈተና ውስጥ እንኳ የህይወትን መንገድ ለአንተ ይገልጣል ፡፡ በአሳብህ እግዚአብሔርን ስታሰላስል እና በመገኘቱ ስታርፍ ፣ ደስታን እንደምታገኝ እርሱ ይናገራል ፡፡ ዛሬ ሞክረው ፡፡ በእያንዳንዱ ሰዓት በአሳብህ እግዚአብሔርን አሰላስለው ፡፡ ቃሉን እንብብ ፡፡ በራስህ አይደለም ፤ በነገሮችህ ወይም በእቅድህ አይደለም ፤ በሁከት ወይም በመነጫነጭ አይደለም ፡፡ በእርሱ እረፍ ፡፡ በእርሱ አትናወጥም ፡፡
“ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም ። ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች ………. የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ ። “ መዝሙር 16፡8-9 ፤ 16፡11
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 16:5–6 – “እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ ። ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ፥ ርስቴም ተዋበችልኝ ። “
- ኤርምያስ 29:11 – “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም ። “
- ዕብራውያን 12:2 – “ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን ፥ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።