Living Righteously
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 13-15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መፅሀፍ ሁልጊዜ የክፉዎችን መንገድ ከፃድቃን መንገድ ጋር ያነፃፅራል ፤ ኢየሱስ “ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነዉና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው “ (ማቴ 7፡ 14) ፡፡ ለዛሬ በተመደበዉ ፅሁፍ ላይ መዝሙር 14 የክፉዎችን መንገድ ሲገልፅ መዝሙር 15 ደግሞ የፃድቃንን መንገድ ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር በመዝሙር 15 “ የዳኑት ኃጢዓተኞች የስነ ምግባርን ሀቀኝነትን እንደ ፍንጭ ማሳያነት በመግለፅ “ ያስቀምጠዋል ፤ ዋይርስቤ “ መዝሙር 15 ለመዳን የመዳኒት ትዕዛዝ ሳይሆን እግዚአብሄርን ለማመስገን እና ከእርሱ ጋር ህብረት ለማድረግ ሲፈልጉ የዳኑ ሰዎች እንዴት መኖር እንዳለባቸዉ መግለጫ ነዉ “ በማለት ይናገራል ፡፡
ዋይርስቤ “ መምህራኖቹ/ህግ አዋቂዎቹ ፃድቅ ለመሆን ከፈለጉ አይሁዶች የሚታዘዟቸዉ 613 ትዕዛዛት እንደ ነበሯቸዉ እንደሚያስቡ “ ይፅፋል ፡፡ መዝሙር 15 እንዲከበሩ 15 ትዕዛዝትን ይዘረዝራል ፡፡ ኢሳ (33፡ 15-16) ስድስት መስፈርቶችን ይዘረዝራል፡ “ በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቁር ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው ፡፡ እርሱ ከፍ ባለ ስፍራ ይቀመጣል ፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል ፤ እንጀራም ይሰጠዋል ዉኃዉም የታመነች ሆናለች “ ፡፡ ሚክ (6፡ 8) ሰዎስት ይዘረዝራል፡ “ ሰዉ ሆይ መልካሙን ነግሮሃል ፤ እግዚአብሄርም ከአንተ ዘንድ የሚሻዉ ምንድር ነው ? ፍርድን ታደርግ ዘንድ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን ? ዕባ (2፡ 4)ሁሉንም ዝርዝሮች በማቃለል መስፈርቶቹን ወደ አንድ አምጥቷቸዋል፡ “ እነሆ ነፍሱ ኮርታለች በዉስጡም ቅን አይደለችም ፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል “ ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (15፡ 1)፡ ዳዊት ንጉስ ቢሆንም እንኳን እንደ ደስተኛ/እንደ ተደሰተ ሰዉ ወደ እግዚአብሄር ቤት ሊሄድና ሊመጣ ነፃ አልነበረም ፤ ካህናቶች ብቻ ያን ማድረግ ችለዋል ፡፡ “ በቅዱሱ ተራራ “ ላይ ያለዉ “ ድንኳን “ የጌታን መገኘት ፈልገዉ የእግዚአብሄር ሰዎች የሚሄዱበት ስፍራ ነበር ፤ ዳዊት “ በማለዳ ድምጼን ትሰማለህ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እጠብቃለሁ “ አለ (መዝ 5፡ 3) ፡፡ በየቀኑ ጌታን ለማየት ምን አይነት ስርዓት መስርታችኋል ?
መዝሙር (15፡ 2-5)፡ ጌታን ለመፈለግ የመሰረትናቸው ስርዓቶች በፅድቅ ህይወት እንድንኖር ተፅዕኗቸዉን መቼ ሲጀምር ማየት እንችላለን ፡፡ ማክአርቱር እነዚህን ቁጥሮች “ በሰዎስት ጥሩና መጥፎ መግለጫዎች “ የመልስና የጥያቄ ቅርፅ አይነት እንደሚከተሉ ይናገራል ፡፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶችን “ የእግዚአብሄርን መመሪያ ለማክበር “ እንዴት እንደሚኬድ እንደ መግለጫ ያስረዳቸዋል ፡፡ አስራ አንድ መመሪያዎች ተቀምጠዋል፡
- በቅንነት መኖር (ቁጥር 2) ፡፡
- ፅድቅን መለማመድ/ማድረግ (ቁጥር 2) - የዳኑ ሰዎች ቅዱስ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው፣ በእግዚአብሄር ፊት በፅድቅ/በሚገባ በመቆም እና በሁሉም ሁኔታዎች የእርሱን ሀሳብ/አመለካከት በማንፀባረቅ የታወቁ መሆን ፡፡
- በልቡ እዉነትን የሚናገር (ቁጥር 2) ፡፡
- በአንደበቱ የማይሸነግል/የማያማ (ቁጥር 3) - የዳኑ ሰዎች በብዙ የተንኮል መንገዶች ሌሎችን አይቦጭቁም፡፡
- ባልንጀራዉን የማይጎዳ (ቁጥር 3) - የዳኑ ሰዎች የሚቀርቧቸዉ ላይ ህመም/በሽታ እንዲመጣባቸዉ ፍላጎት አይኖራቸውም ፡፡
- ዘመዶቹን የማይሰድብ (ቁጥር 3) - የዳኑ ሰዎች ስለ ዘመዶቻቸዉ መጥፎ ነገር አይናገሩም ፡፡
- በእግዚአብሄር የተናቀዉን የሚነቅ እግዚአብሄርንም የሚፈሩትን የሚያከብር (ቁጥር 4) ፡፡
- ምንም ዋጋ ያስከፍል ለቃሉ የሚታመን (ቁጥር 4) - የዳኑ ሰዎች ምንም ያግኙም ወይም ይጡም ከጌታ ጋር በጉዞአቸዉ በመፅናት ይቀጥላሉ ፡፡
- ገንዘብ በአራጣ የማያበድር (ቁጥር 5) ፡፡
- እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ በፍፁም አይናወጥም (ቁጥር 5) - ዋይርስቤ የዕብራዊ ቃል “ መናወጥ “ የሚለዉ “ ታላቅ/ኃይለኛ መናወጥ/መወዛወዝ “ የሚለዉን እንደሚገልፅ አመለከተ ፡፡
በእነዚህ መመሪያዎች መሰረት ህይወታቸውን የሚያስገዙ/የሚያኖሩ ፃድቅ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት በእምነታቸዉ ደህንነት አላቸው ፡፡
መደምደሚያ
በተራራዉ ስብከት ላይ ሲያጠቃልል ኢየሱስ “ ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሰራ ልባም ሰዉን ይመስላል ፡፡ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው በዓለት ላይም ስለ ተመሰረተ አልወደቀም ፡፡ ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሰራ ሰነፍ ሰዉን ይመስላል ፡፡ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው ወደቀም አወዳደቁም ታላቅ ሆነ “ (ማቴ7፡ 24-27) ፡፡
መዝሙር 15 ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜን በማሳለፍ እና የፅድቅን ህይወት በመኖር መሰረታቸዉን የመሰረቱ እንደማይናወጡ እንደሚያስተምረው ኢየሱስም እንደትምህሩቱ የሚኖሩትም ተመሳሳይ ዉጤት እንደሚሆን አስተምሯል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 607.
Warren Wiersbe, Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004). p.116.
Wiersbe, p. 115.
Wiersbe, p. 116.
MacArthur, p. 607.
Wiersbe, p. 116
Wiersbe, p. 117.
ጥያቄዎች
-
ዳዊት “ እስከመቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰዉራለህ ? “ አለ (መዝ 13፡ 1) ፤ እንዳለዉ እግዚአብሄር ፊቱን ከእናንተ እየደበቀ እንደ ነበር ተሰምቷችሁ ያውቃል ? ይህ እንዴት እንዲሰማችሁ አደረጋችሁ ? ይህ በእርሱ ተስፋ እንድትቆርጡ ወይስ በይበልጥ እንድትፈልጉት አድርጓችኋል ?
-
ዳዊት በከባድ ጊዜ ዉስጥ እያለፈ ነበር ነገር ግን በዚያ ዉስጥ አሁንም እግዚአብሄር አመሰገነ (መዝ 13፡ 5-6) ፤ በህይወታችሁ በመከራዉ ዉስጥ ስታመሰግኑት ራሳችሁን አግኝታችሁት ታዉቃላችሁ ?
-
በእግዚአብሄር የማያምኑትን ሰዎች ዳዊት በምንድን ጠራቸው (መዝ 14፡ 1) ? እዉነተኛ የሆነ አምላክን የማያዉቅ ሰዉ ይኖራል ብላችሁ ታምናላችሁ ?
-
መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሌላ የት ላይ መልካም የሚያደርግ ማንም የለም ይላል ? (መዝ 14፡ 3, ሮሜ 3፡ 23)
-
ዳዊት በፅድቅ ወይም ያለ ነቀፋ ለመኖር አስር መመሪያዎችን ሰጥቷል (መዝሙር 15) ፤ በመፅኀፍ ቅዱስ ላይ ሌላ የት ላይ የፅድቅና እንከን የሌለበት ህይወት ለመኖር አስር መመሪያዎች ይሰጣል ? እስከነዚህ ስርዓቶች/ደረጃዎች ድረስ መኖር የሚችል አለ ?
-
በመዝሙር (13-15) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 15:1, 5b
“LORD, who can dwell in Your tent? Who can live on Your Holy Mountain?. . . The one who does these things will never be moved.”
የት ሆነህ ነው አስበህበት የእግዚአብሔርን መገኘት የምትሻው ? ጸሀይ ከመውጣቱዋ በፊት በወንበር ላይ ተቀምጠህ ነው ? ወደ ሻወር ከመጋባትህ በፊት በመታጠቢያ ክፍልህ ወለል ላይ ሆነህ ነው ? ወደ ስራ በመሄድ ላይ ሳለህ ራድዮንህን በመዝጋት ነው ? ምናልባት የእግዚአብሔርን መገኘት መፈለግ ለእያንዳንዱ የተለያየ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ቁም ነገሩ ከልብ በመዘጋጀት ታስቦበት መሆኑ ነው ፡፡
የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ መገኘት ውስጥ ካሳለፍክበት ጊዜ ጀምሮ በህይወትህ ውስጥ ይፈሳል ፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ ፍቃድህ ፣ ፍላጎትህና መሻትህ ምንም ነው ፡፡ በእርሱ ኃይል እና ብርታት ላይ ስትደገፍ መንገድህ እንደ እግዚአብሔር አሳብና ትክክል ይሆናል ፡፡ በታማኝነት ትኖራለህ ፣ ጽድቅን ትለማመዳለህ እንድሁም በመገኘቱ በምታሳልፈው ጊዜ በልብህ የእግዚአብሔርን እውነት ትገነዘባልህ ፡፡ እነዚህን ባህርያት የምታገኛቸው በልፋትህ አይደለም ይልቁንም በእርሱ የማይቋረጥ መገኘት እና በውስጥህ ባለው ኃይል አማካኝነት ለእግዚአብሔር ያለህ ፍቅር ስለሚጨምር እንጅ ፡፡ አለትህ እና የጸና መሰረትህ በእርሱ መገኘት ነውና በኢየሱስ እረፍ ፡፡ በመጨረሻም እንደ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ለዘላለም ትኖራለህ ፡፡ ያ ጊዜ እስኪመጣ ድረስም በሙሉ ልብህ የማይቋረጥ መገኘቱን እሻ ከዚያም ፍቅርና ጸጋው ከህይወትህ በሙላት ይፈሳል ፡፡
“አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል ? ……… እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም ። “
- መዝሙር 15፡1 ፤ 15:5
ተጨማሪ ጥቅስ
ሚክያስ 6:8 — “ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን ? “
ማቴዎስ 7:24–25 — “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል ። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 3:16 — “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ? “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።