Wisdom Books Psalms

Atheists or God-followers

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 10-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 397 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ መዝሙር 10-12 እናጠናለን ነገር ግን መዝሙር 10 የምናጠና ይሆናል ፡፡ በመዝሙር መፅሀፍ ዉስጥ ስናጠና በተለየ ትኩረት ሰጥተን ባናነነብ እንኳን ዝግ በማለት እያንዳንዱን መዝሙር እንድታጠኑ አበረታታችኋለሁ ፡፡ የመረጥነዉን መዝሙር ስናጠናየመጣዉ መሲህ እንዴት እንደቀረበ እንመለከታለን ፤ ያ በሁሉም መዝሙር አይሆንም ነገር ግን በብዛት ይሆናል/ይከሰታል ፡፡ በመዝሙር ጥናታችን የጀመርንበት ሀረጋችን/ቃላችን የክብር ንጉስ ነው ፡፡ መዝሙር 10 ሲጀምር/በመጀመሪያነት የመዝሙር 9 አካል ነበር ፡፡ አሁን መዝሙር ዘጠኝ “ ትክክለኛ መለኮታዊ ፍትህ በመምጣት “ ላይ ልበሙሉነትን ሲያቀርብ የመዝሙር አስር ትኩረት ደግሞ “ በደልወንጀል እንደሆነና እግዚአብሄር ፍላጎት የሌለዉ እንደ ሚመስል ነው “ ፡፡ መዝሙር 10 የአስቸኳይ ሁኔታ ዎችን በመናገር እግዚአብሄር በፍጥነት ከጠላቶቻቸዉ እንዲያድናቸዉ ይጠይቃል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (10፡ 1-11)፡ መዝሙር 10 ርዕስና ትዕዛዝ የለዉም በተጨማሪም ለዚህ መዝሙር በተለዬ እዉቅና የተሰጠዉም ፀኃፊ የለም ፤ እግዚአብሄርን ለምን እንደ ራቀ እናመዝሙረኛዉ ችግር ዉስጥ በሆነ ጊዜ ለምን እንደተደበቀ በመጠየቅ ይጀምራል (ቁጥር 1-3) ፡፡ እነዚህ የኃዘን ቃላት ናቸው፣ ፀሀፊዉ ሲፅፈዉ የተበሳጨ ስለ ነበር ትኩረቱ በእግዚአብሄር ላይ ሳይሆን በክፉዎች ጉዳዮች ላይ የሚሆን ይመስላል ፡፡ ጥያቄዎ እግዚአብሄር ለምንለፍላጎቱ ምንም ስሜት የሌለዉ እንደመሰለ ነው ፤ በእርግጥ ትኩረቱ ክፉዎች እግዚአብሄር መኖሩን እንደ ማያምኑና በእግዚአብሄር የሚዳኙ እንዳልሆኑ በማሰባቸዉ ላይ ነበር (ቁጥር 4-11) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ክፉዎች “ ክፉን በማመስገን እና እግዚአብሄርንበመጥላት እዉነትን ከላይ ወደ ታች እንደሚቀይሩት “ ያመለክታል ፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚል የእምነት ትዕቢት አለ ፤ ይህ የእግዚአብሄርን ስለ መኖር ጉዳይ ከሌላቸው ይልቅ በእግዚአብሄር የማያምኑትን ይናገራል ፡፡

ማህበረሰባችን አምላክን ወደ አለማመን እየተጓዘ እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡ በምንም የማያምኑ “ የምንሞች “ መነሳት አለ ፤ ጥናት አድራጊ/ተመራማሪ ገርቬስ ጥናቱ ከሚያመለክተዉ በላይ ብዙ አምላክን የማያምኑ እንዳሉ ደምድሟል፡፡ አንድ 2018 የ2000 ሰዎች ጥናት 26 ፐርሰንት አምላክ የለሽ እንደሆኑ ተለይተዋል ፤ እስታቲካዊ ፐርሰንቱ በመላዉ የአሜሪካ ሕዝብ በተዘረጋ ጊዜ በዮናይትድ ስቴት ከ64,000,000 የሚበልጥ አምላክ የለሾች ሊገኙ እንደሚችሉ ነው ፡፡ ፔዉ የጥናት ማዕከል አምላክ የለሾች ከ1980 በኋላ የተወለዱ ወጣት ወንዶች (68 ፐርሰንት)፣ ነጮች (78 ፐርሰንት) እና በጣም የተማሩ (43 ፐርሰንት የኮሊጅ ድግሪ ያላቸዉ) እንደሆኑ አግኝቷል ፡፡ የቅርብ ጥናቶች “ ምንም ያልሆኑ ሰዎች “ ከ36.6 ወደ 55.8 ሚሊዮን እንደጨመሩ አግኝተዋል ፡፡

የፐተዉ የጥናት ማዕከል የሆነዉ ማይክል ሊፓክ በአሜሪካ ስለ አምላክ የለሽነት አስር እዉነቶችን ያሳያል፡

  1. የአሜሪካ አምላክ የለሽ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ቅርብ አመታት ዉስጥ እጥፍ ሆኗል ፡፡
  2. አሜሪካዊያን አምላክ የለሾች/አምላክን የማያምኑት ወንዶችና “ ከጠቅላላዉ ህዝብ ቁጥር ወጣቶች “ እንደሚሆኑ ፡፡
  3. የአሜሪካ አምላክ የለሾሽ/አምላክን የማያምኑት ከድሞክራሲይና “ ከፖለቲካ ነፃነት “ ጋር የሚገናኙ ናቸዉ/ይሆናሉ ፡፡
  4. ከአሜሪካ አምላክን ከማያምኑት/አምላክ ከሌለሾች ዉስጥ ስምንት ፐርሰንቱ በእግዚአብሄር ወይም “ በአለማቀፋዉ መንፈስ “ ያምናሉ ፡፡
  5. ከአስሩ አምላክን ከማያምኑት ዉስጥ ለዘጠኙ ኃይማኖት የማያስፈልግ ነው ፡፡
  6. ጥቂት የአሜሪካ አምላክ የለሾች (9ፐርሰንቶቹ) ደከም ባለ መልኩ ስለ አምላክን አለማመን አመለካከታቸዉ ሲያወሩ 65 ፐርሰንቶቹ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ወይም በፍፁም አያወሩም ፡፡
  7. ጥያቄዎችን ለመመለስ ወይም ስርዓት የሆኑ ነገሮችን ለማዉሳት ወደ ኃይማኖት አይመለከቱም ፡፡
  8. ከአምላክ የለሾች የሚበልጡ ዋና ከሆኑ ኃይማኖቶች ቡድኖች ከአሜሪካኖች የሚመስል ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡
  9. ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አሜሪካኖች አንድ አምላክ የለሽ/አምላክን የማያምን ፕሬዜዳንት እንዲሆን አይደግፉም ፡፡
  10. ከግማሽ በላይ አሜሪካኖች እግዚአብሄርን ሳይታመን ፀባይተኛ መሆን ቀላል ነዉ ይላሉ ፡፡

በእነዚህ ቁጥሮች ልባችን ይሰበራሉ ፤ ይህ እንዴት ቀላል ነው ? ምክንያቱ ስለ ኢየሱስ ስለማናወራ ነው ? ምክንያቱ እነዚህ አምላክን የማያምኑት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ ስለ ምንጠብቃቸዉ ነው ? ምክንያቱ ወደ እያ እንደሚመጡ ስለምንጠብቅ ነው ? ምንም ይሁን ምክንያቱ አምላክን አናምንም ብለዉ የተናገሩትን /አምላክ የለሾች አንይዛቸዉም ፤ እንዲሁም አንዳንድ ቦታዎች በመንገድም ላይ እነዚህ ግለሰቦች በቤተ ክርስቲያን በኩል ይጎዳሉ ፡፡ ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር መንግስት እንዲገቡ በፍፁም መከራከር አንችልም ፤ ኢየሱስም በመምጣት ይህን አገኘ ምክንያቱም ይህን ማድረግ እንደማንችል ያዉቃል ፡፡ ሁላችንም ኃጢዓተኞች ነን፣ ኃጢዓትም ወደ ሞት ይመራል (ሮሜ 6፡ 23) ፡፡ እግዚአብሄር በጣም ስለሚወደን ልጁ በመሞት ያን ኃጢዓት ከእኛ እንዲወስድልን ላከው፡፡ መኖሩን እንደ መካድ በእግዚአብሄር ለማመን ብዙ እምነት ይወስዳል !

መዝሙር (10፡ 12-18)፡ በእግዚአብሄር የማናምን ከሆነ ነገሮች ለእኛ ተሸለዉ አናገኛቸዉም (ቁጥር 15) ፤ ነገር ግን “ እግዚአብሄር ለዘላለም ይነግሳል “ (ቁጥር 16) ፡፡

መደምደሚያ

የቅርብ እግዚአብሄርን የማያምነዉ እና ፀሀፊዉ ሲ.ኤስ. ሌዊስ፡ “ ሰዎች ብዙ ጊዜ ስለ እርሱ የሚናገሩትን ሞኝነት ነገሮችን እንዳይናገሩ ለመከላከል እሞክራለሁ፡ ኢየሱስን እንደ ታላቅ የባህሪይ አስተማሪ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ነገር ግን እግዚአብሄር ለመሆን የእርሱን ጥያቄ አልቀበልም ይላል ፡፡ ማለት የሌለብን ነገር አንዱ ያ ነው ፡፡ ዝም ብሎ የነበረ አንድ ሰዉ ኢየሱስ ስላላቸዉ ዝርዝር ነገሮች ታላቅ አስተማሪ አይሆንም ፤ የተቀቀለ እንቁላል ነዉ ከሚል ሰዉ ደረጃ ጋር የሚሆን እብድ ወይም ደግሞ የገሀነም አጋንንት ይሆናል ፡፡ ምርጫ ማድረግ አለባችሁ ፤ ይህ ሰዉ ሰዉ ነበር የእግዚአብሄርስ ልጅ ነው ፤ ወይስ ሌላ እብድ ሰዉ ወይስ አስከፊ የሆነ ነገር ነው ፡፡ ስለ መዋረዱ ልትጮኹበት ትችላላችሁ፣ ልትተፉበትና እንደ ሰይጣን ልትገድሉት ትችላላችሁ ወይም ደግሞ በእግሮቹ ላይ በመዉደቅ ጌታሆይ እና እግዚአብሄር ሆይ ብላችሁ ልትጠሩት ትችላላችሁ ፤ ነገር ግን ታላቅ የሰዉ መምህር ስለመሆኑ ትርጉም በማይሰጠው በማንኛዉም የንቀት ሁኔታ መምጣት የለብንም ፡፡ ያን ለእኛ እንዲከፈት አልተወዉም ፤ ያልተገባዉ አደረገ “ በማለት ፅፏል ፡፡

ኢየሱስን አንድ እድል ትሰጡታላችሁ ? ይህ እዉነት እንደሆነ እንዲያሳያችሁ በመጠየቅ ዛሬ ራሳችሁን ዝቅ ታደርጋላችሁ ? ይህን የምታደርጉ ከሆነ እግዚአብሄር በህይወታችን ይገለጣል ፡፡ ለእናንተ በመሞት ኢየሱስ በጣም ይወዳችኋል ! “ ጌታ ሆይ አንተን ማየት ያልቻልኩ ትዕቢተኛ ነበርኩ ፤ አንተ እዉነት ነህን ? “ በማለት የእግዚአብሄር ምህረት ጠይቁ ፡፡ በምላሹ እግዚአብሄር እንደሚገለጥላችሁ አረጋግጥላችኋለሁ ፤ በኢየሱስ ስትደገፉ ሁሉም መልስ ይኖራችኋል ማለት አይደለም ነገር ግን የምታገኙበት/የምትፀኑበት የሆነ ነገር አላችሁ ማለት ነው ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 654.

  2. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 604.

  3. Nelson’s Commentary, p. 654.

  4. MacArthur, p. 604.

  5. Nelson’s Commentary, p. 654.

  6. “How many American atheists are there really?”, May 17, 2017; available at https://www.vox.com/science-and-health/2017/4/13/15258496/american-atheists-how-many.

  7. Michael Lipka, “10 facts about atheists,” June 1, 2016; available at http://www.pewresearch.org/fact-tank/2016/06/01/10-facts-about-atheists/.

  8. Lipka; available at http://www.pewresearch.org/fact-tank/2016/06/01/10-facts-about-atheists/.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር ክፉዎችን እንዴት እንደሚያደርጋቸዉ የመዝሙረኞቹ ስሜት ምንድን ነበሩ ? አንዳንድ ጊዜ በተመሳሳይ መንገድ ይሰማችኋል ? በመፅሀፍ የእግዚአብሄርን አለመስራት የሚዋሹትን ለመዋጋት የት ልትሄዱ ትችላላችሁ ?
  2. “ እግዚአብሄር ረስቶናል “ በሚሉ አማኞች ስሜትና እግዚአብሄር ረስቶናል በሚል የግብዝነት ሀሳብ ምቾትን በሚወስዱ ኃጢዓተኞች መካከል ልዩነት ምንድን ነው (መዝ 10፡ 11) ?
  3. “ እንደ ወፍ ወደ ተራሮች እንዲያመልጥ “ (መዝ 11፡ 1) በነገሩት ጊዜ የዳዊት ወዳጆች ምን እያሉ ነበር ? ለዚያ የዳዊት ምላሽ ምን ነበር ?
  4. ዳዊት በእግዚአብሄር ሙሉ እምነት ነበረው (መዝሙር 11-12) ፤ እግዚአብሄር በሁኔታዎቻችሁ /በችግሮቻችሁ በሙሉ መቆጣጠር ላይ እንደሆነ እንዴት ታውቃላችሁ ? (ዘጸ 2፡ 23-25, 3፡ 6-15, ማቴ 19፡ 26)
  5. የሰዉን የፌዝ ቃል ከእግዚአብሄር ቃልና ተስፋ አነፃፅሩ (መዝሙር 12, 2ቆሮ 1፡ 20) ፤ መጠራጠር የጀመራችሁባቸዉ ነገር ግን እግዚአብሄር የታመነ እንደሆነ ያረጋገጠላችሁ ጥቂት ተስፋዎች ምንድን ናቸዉ?
  6. በመዝሙር (10-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 12:7–8

“You, LORD, will guard us; You will protect us from this generation forever. The wicked wander everywhere, and what is worthless is exalted by the human race.”

እግዚአብሔር ይጠብቅሀል ይከልልሀልም ፡፡ ክፉ ሰዎች በየስፍራው በሞሉበት ዓለም ሳይቀር ፡- በራሳቸው በሚመኩ ሰዎች ፣ በስስታሞች ፣ እግዚአብሔርን በሚንቁ እንድሁም እግዚአብሔር እንደሌለ በሚያምኑ ሰዎች መኃል ሳይቀር እግዚአብሔር ይጠብቅሀል ይከልልህማል ፡፡ በዚህ በወደቀ አለም ውስጥ እግዚአብሔር ከባድ ነገሮች እንድሆኑ ያደርጋል እናም አንተ ለምን እንደሆነ ላትገነዘብ ትችላለህ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጥበቃው በፈተና ውስጥ ሳለህ በሰላም በብርታት መልክ ይመጣል ፡፡ እንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ጥበቃ ነው ብለህ የምታስበው አይነት አይደለም ፡፡ የመኪና አደጋ ታስተናግዳለህ ፣ የቤት ቃጠሎ ፣ መጥፎ ቃል ልትሰማ ትችላለህ ወይም ህመም ፡፡ ጠባቂ እንዳለህ አይሰማህም ፡፡ እግዚአብሔር በመካከልህ እንዳለ እመን ፡፡ አንተ ያላየኸውን የሆነ ነገር እርሱ ያያል ፤ በትልቁ በሰፊው ምስል ላይ እየሰራ ነው ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፡፡

በኢየሱስ በማመን ፣ ተስፋዎቹን ታመንና ተደገፍ ፡፡ ራስህን በሚያስፈራ ሁኔታ ውስጥ ስታገኘው ፣ ጸልይ እናም እግዚአብሔር መሸሸጊያህ ፤ የመዳን ቀንድህ ፣ መደገፊያህ ፣ መኖሪያህ እና አዳኝህ እንደሆነ እመን ፡፡ ወደ እርሱ ስትጣራ ፣ ትድናለህ ፡፡ ዛሬ የገጠመህ የትኛውም ፈተና ይሁን እግዚአብሔር እንደሚጠብቅህና እንደሚከልልህ በማወቅ እረፍ ፡፡

“አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን ። በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ ። “ - መዝሙር 12፡7-8

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ሳሙኤል 22:3-4 — “እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኃኒቴ ሆይ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ ። “
  • መዝሙር 10:3–4 — “ ኃጢአተኛ በነፍሱ ፈቃድ ይወደሳልና፥ ዓመፀኛም ይባርካል ። ኃጢአተኛ እግዚአብሔርን አበሳጨው፥ እንደ ቍጣውም ብዛት አይመራመረውም፤ በእርሱ ፊት እግዚአብሔር የለም ። “
  • 2ኛ ተሰሎንቄ 3:3 — “ ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው ። “