God Cares for Us
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 7-9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ የሚያዝናና አይነት ነው - ኢዮብ ላይ አይደለንም ! ስለመሲሁ የተሻለ መረዳት ለማግኘት የመዝሙርን መፅሀፍ ሙሉ አገባብ ላይ ለመመልከት እየሞከርን ነው ፡፡ በመዝሙር ቢያንስ ሰባት ፀሀፊዎች አሉ ፤ ከጸሀፊዎቹ ጥቂቶቹ ዳዊትን፣ ሙሴን፣ ሰለሞንን እና የቆሬን ልጆች ያካትታል ፡፡ ቢያንስ 50 መዝሙሮች ጸሀፊያቸዉ ያልታወቁ ናቸው ፡፡ የመዝሙር አንዱ አላማ በህይወት በተለያዩ ክስተቶች ጊዜ የተዘመሩ ነበሩ - የምስጋና መዝሙሮች፣ ወደ ላይ የመዉጣት/የከፍታ፣ የኃዘን፣ የደስታና የፍቅር መዝሙሮች ፡፡ ለመዘምራን አለቃ ከዳዊት አቅጣጫ በመስጠት የሚጀምረዉን ምዕራፍ 8 እንመለከታለን ፡፡ መዝሙሩ እንደጊታር ልክ እንደ በገና በተገለፀ በጊታዝ የሚዘመር ነበር፡፡
ስለ መዝሙር 8 ማብራሪያ ፀሀፊዉ ጀምስ ጆንስቶን “ አምላክ/እግዚአብሄር ታላቅ ስራዉን ለመስራት ደካማ ሰዎችን በመጠቀምበዚህ አለም ላይ ግርማዊነቱን እንደሚገልጥ ፤ እግዚአብሄር ግርማውንበልጆች ድካም በኩል በመጠቀም ጠላቶቹን በመከላከል እንደሚገልጥ “ ፅፏል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (8፡ 1-2)፡ ቁጥር 1-2 ስለ ሰዉ ልጅ የእግዚአብሄር አፈጣጠር ላይ ያተኩራል ፡፡ ቁጥር 1 እግዚአብሄርን በሁለት ርዕሶች ይጠቅሰዋል - “ ያህዌ “ እና “ ጌታችን “ በሚል ነው ፤ “ ያህዌ “ የሚለዉ “ የእስራኤልን ኪዳን ጠባቂ አምላክ “ የሚለዉን ሲመለክት “ ጌታችን “ የሚለዉ ደግሞ አዶናይ ከሚለዉ ዕብራዊ ስም የተመሰረተ ሲሆን “ ህዝቡን ጨምሮ በፍጥረት ላይ ሁሉ ሉዓላዊነቱን “ ያመለክታል ፡፡ ዳዊት ጉዳዩን እየሰራ/እየገነባ ነበር ፤ ዳዊት ጌታን እያመሰገነ ነበር ፡፡
ኢየሱስም በአዲስ ኪዳንእግዚአብሄር በልጆች በኩል ስለመስራቱ አዉርቷል (ማቴ 21፡ 16) ፡፡ ኮንስታብል “ የሰዉ ልጅ ደካሞች የፈጠራቸዉን እንደሚያመሰግኑ !“ ፅፏል ፡፡ እግዚአብሄር ጠላቶቹን ዝም ለማሰኘት ልጆችን ሊጠቀም ይችላል ! ዋይርስቤ የልጆችን ወይም በእግዚአብሄር ጥቅም ላይ ስለሚዉሉት ምሳሌን በመስጠት የሚፅፋቸው “ የህፃኑ ሙሴ ጩኸት በመጨረሻም ግብፅን ወደ ጉልበቷ አመጣት፣ የሳሙኤል መወለድ እስራኤልን ለማዳንና ዳዊትን ወደ ዙፋን ለማምጣት እግዚአብሄር ተጠቅሞበት ነበር ፤ ዳዊት ራሱ ጎልያድን ዝም ባሰኘዉና ባሸነፈዉ ጊዜ ልጅ ነበር (1ሳሙ 17፡ 33, 42-43) ፤ እግዚአብሄር እንዲያከብሩት ደካሞችንና ረዳት የሌላቸዉን በመጠቀም ጠላቶቹን እንዲያሸንፍ እንዲያደርጉት “ ፅፏል ፡፡
መዝሙር (8፡ 3-4)፡ ቁጥር 3-4 እግዚአብሄር እንዴት ለእኛ እንደሚጠነቀቅልን ያተኩራል ፤ “ ሙሉ ፍጥረት/ጠፍር በመለኮታዊ ፈጣሪ እይታ ፊት አነስተኛ/ያነሰ(በጣም ትንሽ) ከሆነ የሰዉ ልጅ አስፈላጊነት ምን ያክል ያነሰ ነው ! “ የጠፈር ስፋት ምንም ያክል ቢሆን እግዚአብሄር ስለ ሰዉ ልጅ ይጠነቀቃል ፤ ፈጠረንም ፡፡
መዝሙር (8፡ 5-8)፡ ቁጥር 5-8 እግዚአብሄር እንዴት በራሱ መልክ እንዳከበረን ያተኩራል ፡፡ እግዚአብሄር በእኛ እንደሚጠቀም ለማሰብ እብደት ነው፣ አይደለምን ? ስራዉን እንድንሰራ በክብርና በምስጋና ዘዉድ ያከብረናል (ኢዮ 7፡ 17, 25፡ 6, መዝ 144፡ 3-4) ፡፡ ከነድካማችን እግዚአብሄር ያስብልናል፣ ይጠቀምብናል ይወደናልም ፡፡
ሮን ፎረስት በመፅኀፍ ዉስጥ እግዚአብሄር የተጠቀመባቸው ሰዎች የተሰበሩና በጥቂት ጥቅም የሌላቸውን ነበሩ ፡፡ ፎረስት “ በመፅኀፍ ቅዱስ ላይ ስለ ታላቅ ህይወት/ኑሮ እናወራለን - ከእነርሱም ዉስጥ ብዙዎች አሉ - ነገር ግን የሚያስደንቀኝ ነገር ከባድ በሆነ በቤተሰብ ጉዳይ በተጎዶ ሰዎች ታላቅ ህይወቶች እንዴት በትክክል እየኖሩት እንደ ሆነ “ ፅፏል ፡፡ ፎረስት አጠናቸዉ ስሞች ላይ እንድንመለከት እፈልጋለሁ ፡፡
- አዳም (ዘፍ 3፡ 12)
- ሔዋን (ዘፍ 3፡ 6)
- ቃየን (ዘፍ 4፡ 8)
- ኖኅ (ዘፍ 9፡ 20-21)
- አብርሃም (ዘፍጥረት 12, 20)
- ሳራ (ዘፍጥረት 16)
- ሎጥ (ዘፍጥረት 18-20)
- ኢዮብ (ኢዮ 2፡ 9)
- ይስሐቅ (ዘፍጥረት 26)
- ርብቃ (ዘፍጥረት 27)
- ያዕቆብ (ዘፍጥረት 25, 27, 30)
- ራሄል (ዘፍ 31፡ 19)
- ሮቤል (ዘፍ 35፡ 21)
- ሙሴ (ዘጸዓት 2, 32፡ 19, ዘኁ 20፡ 11)
- አሮን (ዘጸዓት 32)
- ማሪያም (ዘኁልቁ 12)
- ሳምሶን (መሳፍንት 16)
- ኤሊ (1ሳሙኤል 2, 4)
- ሳዖል (1ሳሙኤል 16, 18, 19, 31)
- ዳዊት (2ሳሙኤል 11)
- ሰለሞን (1 ነገስት 11)
እነዚህ እግዚአብሄር ልዩነት ለማድረግ የተጠቀመባቸዉ ሰዎች ነበሩ ! በመፅሀፍ የተማርናቸዉን ሰዎች ከፍ እናደርጋቸዋለን ነገር ግን ልክ እንደኛ ተሳስተዉ እንደ ነበር ለማስተዋል እንወድቃለን/እንቸገራለን ፡፡ ይህን ዝርዝር ለምን እያጠናነዉ ነው ? ምክንያቱም ይህ ዳዊት እያወራዉ የነበረዉ ነገር ስለ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እነዚህን ሁሉንም ሰዎች ድካማቸዉ እያለ ተጠቅሞባቸዋል ምክንያቱም እግዚአብሄር በምድሩ ላይ እንዲሆኑ ስለፈለገ ፤ እግዚአብሄር ድካም እያለብን ይጠቀምብናል ፡፡
ኮንስታብል “ እግዚአብሄር ሰዉን ማንም ፍጥረት በማይሸከመው በራሱ መልክ ከራሱ ትንሽ አሳንሶ ሰራው …… እግዚአብሄር ሰዉን የእርሱ ወኪል በመሆን ፍጥረት ሁሉ ላይ እንዲያስተዳድር በክብርና በግርማ አከበረዉ ….. የመጨረሻዉ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር በተመለሰ ጊዜና ሁሉንም ፍጥረት በቁጥጥሩ ስር ሲያመጣቸው የሰዉ ልጅ ፍፃሜን እንደሚፈፅመው “ ፅፏል (1ቆሮ 15፡ 27-28) ፡፡ እስካሁንም ይህ ሀሳባችን መሆን ይገባዋል፡ የክርስቶስ ብርሃን በእኛ ዉስጥ እንዲበራ የምንፈቅድ የተሰበርን ማድጋዎች እንሆናለን ፡፡
መዝሙር (8፡ 9)፡ የተሰበረ መተላለፊያ ብንሆንም እንኳን ክርስቶስ በእኛ እየሰራ ከሆነ ሁሉም ነገር ቀላል/የሚቻል ነው ፡፡ ኮንስታብል “ ሰዉ ብዙ አይነት እንስሳቶችን ቢያለምድ እና ቤት ዉስጥ ቢያስለምዳቸዉም ከመለኮታዊ እርዳታ ዉጪ ራሱን ለመቆጣጠርአስቸጋሪ/የማይቻል ሆኖ እንደሚያገኘው “ አመልክቷል ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ የስላሴን መለኮት ስራ በማጠቃለል ታላቅ ስራን ይሰራል፡
“ እግዚአብሄር አብ ነገስታት እንድንሆን ፈጠረን ነገር ግን የመጀመሪያዎቹ ቤተሰቦቻችን/አባቶቻችን አለመታዘዝ ዘዉዳችንን /ክብራችንን አሳጣን “ ፡፡
“ እግዚአብሄር ወልድ ወደ ምድር በመምጣት ነገስታቶች እንድንሆን ተቤዠን (ራዕ 1፡ 5-6) “ ፡፡
“ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በህይወት ላይ እንድንገዛ ያግዘናል (ሮሜ 5፡ 17) “ ፡፡
4 Constable, p 59.
6 From https://eternalfingerprints.wordpress.com/tag/sovereignty/.
8 Forseth.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 603.
James A. Johnston, Psalms 1-41, v. 1 (Wheaton: Crossway, 2015), p. 95.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Psalms, p. 58; available at https://planobiblechapel.org/constable-notes/pdf/psalms.pdf.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2004), p. 103.
Ron Forseth, “20+ Messed Up Bible Heroes And What We Can Learn From Them” Oct 14, 2019, https://www.sermoncentral.com/pastors-preaching-articles/ron-forseth-20-messed-up-bible-heroes-and-what-we-can-learn-from-them-1613.
Constable, p. 60.
Constable, p. 61.
Wiersbie, p. 104.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር በልባችን እና በኃሳባችን ዉስጥ በጥልቀት መመልከቱ ምቾትን ይሰጣችኋል ? መቼ ነዉ ምቾት የሚሆነዉ የማይሆነዉስ ?
-
እግዚአብሄር አለምን መዉደድና ክፉዎችን መጥላት ሁለቱንም እንዴት ይችላል ? (መዝ 5፡5, 7፡ 11, ዮሐ 3፡ 16 )
-
በመዝሙር 8 ዘማሪዉ በግርማዊዉ በእግዚአብሄር ስም በመጀመር ይጨርሳል ፤ ይህ ለምን አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኘዉ ምን ታስባላችሁ ? ለራሱ ለእግዚአብሄር የስም አስፈላጊነት ምንድን ነው ? (ዘጸ 3፡ 14-15)
-
በጉታ ደስታና መደሰት እንዲኖራችሁ እንዴት መቀጠል ትችላላችሁ ? (መዝ 19፡ 8, ዮሐ 15፡ 9-11, ፊል 4፡ 4-8)
-
በመዝ (9፡ 17) ሰዎች እግዚአብሄርን የማይቀበሉበት ጥቂት ምክንያቶች ምንድን ናቸው ? ለዘላለም እግዚአብሄር የማይተዋቸዉ እነማን ናቸው?
-
በመዝሙር (7-9) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 8:4–6
“What is man that You remember him, the son of man that You look after him? You made him little less than God and crowned him with glory and honor. You made him lord over the works of Your hands; You put everything under his feet.”
ዛሬ ዛሬ ሰዎች ሁሉንም አይነት ስነ ስርዓቶች ያዘጋጃሉ እናም ለእያንዳንዱ ነገር የተለየ ዝግጅት አላቸው ፤ ልክ በእግር ኳስ ጨዋታ ጎል ማግባት ፣ በስራ ዕድገት ማግኘት ፣ ጥርስ መንቀል ወይም ደግሞ የሆነ አመታዊ ክብረ በዓል ላይ ፡፡ ዛሬ የእግዚአብሔርን እጆች ስራ አድንቅ አክብር ! እግዚአብሔር አንተን ብቻ አይደለም የፈጠረው ነገር ግን ሰማይን ፣ ጨረቃንና ክዋክብትንም ጭምር እንጅ ፡፡ እርሱ በጎችን ፣ በሬዎችን ፣ የሰማይ ወፎችን ደግሞም እንድሁ የውቅያኖስ አሶችን ፈጥሯል ፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጠረው በእርሱ እጅ ነው ፡፡ እናም ይህን ሁሉ እንድገዛ ሰውን ፈጠረ ፡፡ ሁሉንም ነገር ከእግሮችህ ስር አስቀመጠው ፣ ድንቅ ስራውን ሁሉ ፡፡ እግዚአብሔር አንተን የሚገልጽህ ልክ እንድትሰራው የጠራህን ስራ ትሰራ ዘንድ የእርሱን ኃይል የያዘ የሸክላ ዕቃ አድርጎ ነው ፡፡
ስለዚህ እንደተሸነፍክ ሲሰማህ ፣ እንደወደክ ሲሰማህ ፣ እንደተሳሳትክ እንደተበላሸብህ ሲሰማህ እናም ደግሞ ልክ እንዳልሆንክ ሲሰማህ ይህ የመነሳት ጊዜ ነው ፡፡ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ፡፡ አንተ የእጁ ስራ ነህ ፣ እርሱም ያስብልሀል ፡፡ መቀጠል ትችላልህ ምክንያቱም የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው የኃያሉ እግዚአብሔር ኃይል በህይወትህ በስራ ላይ ስለሆነ ፡፡ በምድር ሁሉ ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን ፡፡ ዛሬ ደስ ይበልህ ደግሞም የተለየ ግብዣ ይኑርህ ምክንያቱም እግዚአብሔር ታላቅ ስራዎችን ሰርቷልና እንድሁም ታመሰግን ዘንድ ፣ ትመካ እና ስለ ስሙም ትዘምር ዘንድ ብዙ ምክንያትን ስለሰጠህ !
“ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው ? ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፤ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው ። በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት ፡፡ “ - መዝሙር 8፡4-6
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 8:9 — “አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ ። “
- መዝሙር 9:1–2 — “አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ ። በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ ። “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 4:7-9 — “ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን ፤ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም ፤ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።