Praying in the Morning
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 4-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ በመዝሙር በሁለተኛ ክፍል ጥናታችን በመዝሙር (4-6) ላይ ነን ፤ ለመዝሙር ሀረጋችን/ቃላችን የክብር ንጉስ ነው ፡፡ ዛሬ በአንድ የለቅሶ/የኃዘን መዝሙር ላይ እንመለከታለን ስለዚህም ስሜት በቦታዉ ላይ ይሆናል ፡፡ ማክአርቱር በኃዘን መዝሙር ላይ ሁለት ባህሪዎችን ያስቀምጣል፡ “ 1) የንፁህነት መግለጫ እና 2) ስለ ጥበቃ መፀለይና ልበሙሉነት “ ፡፡ የዳዊት ፀሎት ጠላቶቹን እንዲያሸንፍ ለእርዳት ለእግዚአብሄር ነበር ፡፡
ዳዊት ገጥሞት የነበረዉ ትክክለኛዉ ነገር የሚታወቅ አልነበረም ነገር ግን ይህ መዝሙር ዳዊት ከኢየሩሳሌም ከመሸሹ በፊት የተፃፈ እንደነበር የሆነ ነው ፤ በዚያን ጊዜ ዳዊት በፀሎት ወደ አምላኩ ተመለሰ ፡፡ ዋይርስቤ “ ከእግዚአብሄር ጋር የኃዘን ህብረት ከማድረጊያ ጊዜያችን ምንም ያለመመቸት መጠን ወይም ችግር እንደ ማይከለክለን “ አመልክቷል ፡፡ በመዝሙሩ ርዕስ ለመዘምራን ቡድን አለቃ እንደ ተጨማሪ ዋሽንት እንዲጠቀም አቅጣጫ ይሰጣል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (5፡ 1-3)፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ወደ ቃሉ፣ ወደ ልመናዉን ወደ ጩኸቱ እንዲያደምጥ ይጠይቀዋል (ቁጥር 1-2) ፡፡ ማክአርቱር “ ዳዊት በምድር ላይ የተቀባ መንፈሳዊ ንጉስ ነዉ ነገር ግን የሁሉም እስራኤልና የመላዉ አለም የመጨረሻ/ዋና ንጉስ እንደሆነ እንደሚያስተዉል “ ያመለክታል ፡፡ ቁጥር 3 ለፀሎት ጭብጥ ጥቅስ ነው፡ “ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እጠብቃለሁም “ ፡፡ ጥቂቶችይህን “ ሁሉንም የቀኑን እንቅስቃሴ ለእግዚአብሄር ክብር በመስጠት አንድን ግለሰብ ለመርዳት “ የተፈጠረ መሆኑን ለማሳየት እንደ ማለዳ መዝሙር ይጠቅሱታል ፡፡ ዳዊት በሁሉም ማለዳ ከእግዚአብሄር ጋር ቀጠሮ ነበረው ፡፡ በሁሉም ጣልቃ ገብነት ጊዜያት ላይ በመጠንቀቅ በቅደም ተከተልና በስርዓት/በዘዴ የፀሎት ጊዜን ቀረበ ፡፡ በቁጥር 3 “ ቀጥታ “ ብሎ የተተረጎመዉ ቃል በመሰዊያ ላይ በቅደም ተከተሉ የእንስሳት መስዋዕት ቁርጥራጭ የሚቀመጥበትን ለመግለፅ የሚጠቅም ነበር (ዘሌ 1፡ 8) ፤ በተጨማሪም በመሰዊያዉ ላይ የእንጨቱን አደራደር (ዘፍ 22፡ 9)፣ በታቦቱ ማደሪያ ዉስጥ በገበታዉ ላይ የገብስ እንጀራዉን አቀማመጥን(ዘሌ 24፡ 8) እና በእንግዶች ፊት የምግብን አቀማመጥ ይገልፃል (መዝ 23፡ 5) ፡፡ ዳዊት በፀሎቱ ግድየለሽ አልነበረም ፤ ሁሉም ነገር በስርዓት የተደረደረ ነበረው ፤ ለዉትድርና አስተሳሰብም ተመሳሳይ ቃል አለው፡ አንድ ወታደር ትዕዛዞችን ለመቀበል ከአዛዡ ፊት ራሱን ያቀርባል (መዝ 55፡ 18, 59፡ 17) ፡፡ ዳዊት በፀሎቱ በጣም የተለዬ ስለ ነበር በስርዓት በመሆን፣ በስልት እና የተለየን/አትኩሮት ሰጪዎች በመሆን የዳዊትን አቀራረብ በመጠቀም በተስፈኝነት የእግዚአብሄርን ምላሽ እንደምንጠብቅ አምናለሁ ፡፡ በደንብ የፀሎትን ኃይል ሞደል ካደረግን እግዚአብሄር ብዙ ክብርን ይቀበላል ፡፡
መዝሙር (5፡ 4-6)፡ ዳዊት በፀሎት ጌታን ተመለከተ ፡፡ ክፉ ሊቆም የማይችልበት እና በደልን በማይወድደዉ በእግዚአብሄር ርህራሄ ላይ አተኮረ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ዳዊት እንዲሰራዉ እግዚአብሄር የሚፈልገዉን ጉዳይ/ነገር እየገነባ ነበር ፡፡ “ ጉረኛ “ የሚለዉ ቃል “ የእግዚአብሄርን ምስጋና/አድናቆት ለመግለፅ “ የሚጠቅም ነበር ፤ ራስን በሚሞገስበት ጊዜ ጉራ “ የእዉነተኛ ሙገሳ የሰዉ የመጣመም መጠማዘዝ “ ይሆናል ፡፡ ዋይርስቤ እግዚአብሄርን ስንፈራው (መዝ 147፡ 11)፣ በአክብሮት ስናደንቀዉ/ስናመሰግነው (መዝ 69፡ 31)፣ እምነት ሲኖረን (ዕብ 11፡ 6) እና ራሳችንን በሚገባ ከሚደሰትበት ከልጁ ጋር ስናመሳስል (ማቴ 3፡ 17) እናስደስተዋለን ፡፡
መዝሙር (5፡ 7-12)፡ ዳዊት በእግዚአብሄር ቤት በቤተ መቅደሱ ዉስጥ እንደ ገባ ይናገራል በዚህም በመደነቅና በአምልኮ በእግዚአብሄር ፊት ይሰግዳል (ቁጥር 7) ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን እንዲመራዉ - በእግዚአብሄር መንገድ እንዲሄድ እንዲጠብቀዉ ይጠይቀዋል (ቁጥር 8) ፡፡ መዝ (119፡ 1-5) በእግዚአብሄር ፊት በትክክል ስለ መጓዝ ምሳሌ ይሰጣል ፡፡ ከዚያም በቁጥር 9 ዳዊት ንግግራቸዉ የማይረባ ስለነበረዉ፣ ድርጊታቸዉ አጥፊ ስለነበረው እና አጭበርባሪዎች ስለ ነበሩት ጠላቶቹ ፍትህን ይጠይቃል (ሮሜ 3፡ 10-18) ፤ ዳዊትም በእግዚአብሄር ላይ ስላመፁ እንዲሰብራቸዉ እግዚአብሄርን ይጠይቃል (ቁጥር 10) ፡፡ ማክአርቱር “ የመዝሙረኛዉ ፀሎቶች ተገልጥ በነበረዉ በእግዚአብሄር ስርዓት መሰረት የክፉዎች ማብቂያ እንዲሆን እንደሆነ “ ይናገራል ፤ እነዚህ ጠላቶች በእግዚአብሄር ላይ እና በቀባዉ ላይ በማመፅ ጥበቃዉ ተስፋ ተገብቶላቸዉ ለነበሩት የእግዚአብሄር ምርጫ ህዝቦች ለአይሁዶች ጠላት ሆነዉ ነበር ፡፡
ዳዊት እግዚአብሄርን በእርሱ መፅናናትን የሚያገኙትን በእርሱ ለዘላለም እንዲያስደስታቸው እና ስለ እግዚአብሄር መመካት የሚችሉ እንዲሆኑ እንዲፈቅድላቸዉ ይጠይቃል (ቁጥር 11) ፤ በመጨረሻም ዳዊት እግዚአብሄር ፃድቃንን እንደሚባርክና ፃድቃንን በሞከስ እንደ ጋሻ እንደሚከብባቸዉ ይናገራል (ቁጥር 12) ፡፡
መደምደሚያ
የመጨረሻ አንድ ክፍል ያለኝ ቢሆን መዝ (5፡ 12) “ አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና ፤ አቤቱ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸኝ “ የሚለዉ እንዳያመልጣችሁ እላለሁ ፤ ይህ በዋናነት/በመጨረሻ ወደ ጻድቁ ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 600.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 96.
MacArthur, p. 601.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 651.
Wiersbe, p. 96.
Nelson’s Commentary, p. 651.
Nelson’s Commentary, p. 651.
Wiersbe, p. 97.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 49; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.
MacArthur, p. 601.
ጥያቄዎች
-
በመዝ (4፡ 5) የተጠቀሰዉ የፅድቅ መስዋዕት ምን ይመስላል ? (መዝ 51፡ 17, 141፡ 2, ሚክ 6፡ 8, ሮሜ 6፡ 13, 12፡ 1, ዕብ 13፡ 15-16)
-
መዝ (4፡ 6), ዮሐ (1፡ 9) እና 8፡ 12 አንብቡ ፤ ዳዊት እንዴት ወደ መሲሁ አመለከተ ? ወደ መሲሁ ነበር ?
-
በመዝ (5፡ 4) የዳዊትን ንግግር በዘፍ (3፡ 4-5) ስለ እግዚአብሄር ከእባቡ ንግግር ጋር አነፃፅሩ ፤ ስለ እግዚአብሄር ያለን መረዳት ለምን እንደ ዳዊት አመለካከት መሆን አለበት ?
-
በመዝሙር 6 የተገለፀው ሀዘንና አመፅ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? እነዚህንቁጥሮች ማንበብ እንዴት ያበረታታችኋል ተስፋስ ይሰጣችኋል ?
-
በመዝ (6፡ 9) ዳዊት ልብ የሚሞላ ንግግርን አደረገ ፤ እግዚአብሄር ፀሎቱን እንደሚሰማዉና እንደሚመልስለት ለምን እርግጠኛ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? እንዲህ አይነት ማረጋገጫ ሌላ የት ላይ ታያላችሁ (ዮሐ 11፡ 41-42) ? ይን የሚመስል በራስ መተማመን አላችሁ ?
-
በመዝሙር (4-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 5:3
“At daybreak, LORD, You hear my voice; at daybreak I plead my case to You and watch expectantly.”
ልክ ጠዋት ስትነሳ ቀድመህ የምታደርገው ምንድን ነው ? ስልክህን ማየት ? ቡና ማፍላት ? እንክብካቤህን ለሚፈልጉ ልጆችን እንክብካቤን መስጠት ? ዛሬ በጸሎት ጀምር ፡፡ ቡናው እየፈላ ሳለ ፤ ፌስቡክ ወይም ኢንስታግራም ከመክፈትህ በፊት ፣ ኢሜይልህን ቸክ ከማድረግህ በፊት ወይም ደግሞ ከልጆችህ ጋር የጠዋት አሸንጉሊት ፊልም በማየት ላይ ሳለህ ፣ ቆም በልና ጸልይ ፡፡ የእግዚአብሔርን ስም ተጣራ ፡፡ ቀንህን ስትጀምር ድምጽህን እንድሰማ አድርግ ፡፡ ማመስገን የምትፈልጋቸውን ጥቂት ባህርያቱን አስብና አመስግነው ፡፡ ለቀኑ በልብህ ያለውን አካፍለው እንድረዳህም ወደ እርሱ ጸልይ ፡፡
እርሱ ጸሎትህን ይሰማል ስሙንም በተጣራህ ጊዜ ሊመልስልህ ቃል ገብቷል ፡፡ አንተም እንደሚሰማህ ስላወክ ፣ እንድመልስልህ ጠብቀው ፡፡ ምናልባት እርሱ አይሆንም ፣ ይቻላል ወይም አሁን ጊዜው አይደለም ብሎ ይሆናል የሚመልስልህ ነገር ግን እርሱ ይመልስልሀል ፤ መንገድህን ያቀናል በጉዞህም ማስተዋልን ይሰጥሀል ፡፡ አስታውስ ፣ ተነስና መልስን በመጠበቅ ጸልይ !
“በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም ። “
- መዝሙር 5፡3
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 6:9 — “ እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ ። “
ኤርምያስ 29:12 —“ እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ ። “
1ኛ የዮሐንስ 5:14 — “በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።