Introducing the Psalms
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ በመዝሙር የመጀመሪያ ጥናታችንና እስካሁን 393ተኛ ጥናታችን ነው ፡፡ መዝሙርን በማስተማሬ በትንሹ ተጨንቄአለሁ ስሜቴን ለመግለፅ ፈርቼ ሳይሆን መዝሙረኞቹ በእነዚህ መዝሙሮች ላይ በመስፍራዉ/በመስመሩ ላይ ልባቸዉን ለማስቀመጥ ፍቃደኞች ስለነበሩ እንጂ ፡፡ ለሁላችንም ትግሉ/ፈተናው በእግዚአብሄር ፊት ደካማ ለመሆን የመዝሙር ጥናታችን ችሎታችንን/አቅማችንን እንዲዘረጋ መፍቀድ ነው ፡፡ የመዝሙር መፅሀፍ መጀመሪያ ምስጋና ተብሎ የሚጠራ የምስጋና መፅሀፍ ነበር ፤ በቀድሞዉ በብሉይ ኪዳን መፈጠር እያንዳንዱ መዝሙር በሙዚቃ መሳሪያ የተዘመሩ እንደሆኑ መፈጠራቸዉን ለማመልከት “ መጎተት ወይም በክሮች መምታት/መጫወት “ የሚል ትርጉም ወዳለዉ የክሪክ ቃል ስሙ መዝሙር ተብሎ ተቀየረ ፡፡ አብዛኛዉ መዝሙር “ ብዙ አይነት መረጃዎችን የሚያደርሱ ልክ እንደ የፁሁፎችን አዉድ፣ የመቀደስ/የመሰጠት መረጃን፣ የታሪካዉ ክስተቶችን፣ ለአምልኮ መሪ የቤተ ክርስቲያን ተግባራትን፣ የአምልኮ ስነ ስርዓት ትዕዛዝ እና በታላቅ ጥንታዊነታቸዉ እርግጠኞች የማንሆንባቸዉ ሌሎች ስልታዊ ትዕዛዞችን መረጃ የሚሰጡ “ ርዕስና ንዑስ ርዕስ አላቸው ፡፡
150 እያንዳንዳቸዉ መዝሙሮች የተለያዩ ፀኃፊዎች አሉዓቸው ፤ ንጉስ ዳዊት 73 ፅፏል፣ የቆሬ ልጆች አስር ፅፈዋል፣ አሳፍ 12 ፅፏል፣ ሰለሞን ሁለት ሲፅፍ ሙሴ፣ ሄማን እና ናታን እያንዳንዳቸዉ አንድ አንድ ፅፈዋል ፡፡ ሀምሳ መዝሙሮች ፀኀፊያቸዉ የማይታወቅ ቢሆኑም ብዙ ምሁራን ከእነዚህ ዉስጥ ጥቂቶቹን ነቢዩ ዕዝራ እንደፃፋቸዉ ይናገራሉ ፡፡ መዝሙር 900 እና ከዚያ በላይ ጊዜ የሚሸፍን ሲሆንመዝሙር 90 ሙሴ በፃፈ ጊዜ በመጀመር ምርኮ ካበቃ በኋላ መዝሙር 126 በተፃፈ ጊዜ አብቅቷል ፡፡ ማክአርቱር ለመዝሙር ሁለት እጥፍ መነሻዎችን ይገልፃል፡ “ 1) የእግዚአብሄር ድርጊት በፍጥረትና በታሪክ እና 2) የእስራኤል ታሪክ “ ፤ ማክአርቱር በተጨማሪም በመዝሙር ዉስጥ የሚገኙ ሁለት ተቃራኒ ልኬቶች/ስፋቶችን ይገልፃል፡ “ የአግድም/ግድም ወይም ጊዚያዊ እዉነት እና 2) ከላይ ወደ ታች ወይም የተሸለ/የመጠቀ እዉነት “ ፤ በአጭሩ ትርጉሙ የሰዉ ልጅ ልምምድ እንደ አግድም የሚታይ እና ከእግዚአብሄር ጋር ያለ ልምምድ ደግሞ እንደ ተሻለ /ከላይ ወደታች የሆነ እንደሆነ ያስቀምጣል ፡፡
የመዝሙር ስብስብ እንዴት እንደሚኖር የጥበብ መዝሙርን፣ ስለ ህይወት ችግር የኃዘን መዝሙርን፣ የትዕግስት መዝሙርን፣ የንግስና መዝሙርን፣ የምስጋና መዝሙርን እና የመሲሀዊ መዝሙርን ያካተተ የተለያየ ይዘቶች አሉት ፤ በተጨማሪም ስብስቡ ወደ አምስት መፅኀፍት ተከፍሏል ፡፡ እያንዳንዱም ክፍል አምላክን በሚያመሰግን አንድ ጥቅስ ወይም ጥቅሶች ያበቃል፡ 1) መዝሙር 1-41፣ 2) መዝሙር 42-72፣ 3) መዝሙር 73-89፣ 4) መዝሙር 90-106 እና 5) መዝሙር 107-150) ፡፡
መዝሙር 2 አንዱ መሲሀዊ መዝሙር ነው፣ ስንቀጥል ብዙ መሲሀዊና ትንቢታዊ መዝሙሮችን እናጠናለን ፡፡ ለመዝሙር መፅኀፍ ሀረጋችን የክብር ንጉስ የሚል ሲሆን ይህ የምንጀምርበትና እንዴት እንደሚሄድ የምናይበት ነው ፡፡ ስንቀጥል/ስናጠናትንቢታዊ መዝሙሮች በጊዜዉ ለህዝቡ መልዕክቶች እንደነበራቸው እንዲሁም ወደ ፊት ስለ መጣዉ መሲህ መልዕክት እንዳላቸዉ አስታዉሉ/እንዳትረሱ ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (2፡ 1-6)፡ ይህ መዝሙር በእግዚአብሄር ላይ ስለ ሰዉ አመፅ ነው (ቁጥር 1) ፡፡ የምድር ነገስታቶችና ገዢዎች/አስተዳዳሪዎች በአንድ ላይ በእግዚአብሄር ላይ እና በቀባው በልጁ በመሲሁ ላይ በአመፅ መጥተዉ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ በአመፅ ሕዝቡ እግዚአብሄር መልሶ እንደያዛቸዉ ከተሰማቸዉ ገደብ/ክልከላዎች ነፃ መሆን ይፈልጋሉ (ቁጥር 3) ፤ ክልከላዎቹን እግዚአብሄር ሊይዛቸዉ እየተጠቀመባቸዉ የነበሩ እንደ “ ማሰሪያ ቀንበሮች “ አዩአቸዉ (ኤር 5፡ 5, ሆሴ 11፡ 4) ፡፡ እግዚአብሄርም ለአመፃቸው በፌዝ ሳቅ በመመለስ “ ፍፁም ከሆነዉ ቁጣው “ ተናገራቸው (ቁጥር 4-5) ፤ እግዚአብሄር ቀድሞ ንጉሱን ልጂን በፂዎን እንደቀደሰው፣ ለአለም ትዕዛዙን የሚያቀርብበት ቅዱሱን ተራራዉን እንደቀደሰዉ ገለፀላቸው (ቁጥር 6-7) ፡፡ ይህ “ በቀድሞ ዘላለም ዝምድና ትዕዛዝ በሆነዉ በስላሴ የአባትና/የልጅ ግንኙነት ለማሳየት በብሉይ ኪዳን የሚጠቀሰዉ ብቸኛዉ እና በአዲስ ኪዳን ዋና አካል የሆነዉን እንደ ሰዉ ስጋ መልበሱን ያሳዬ እንደሆነ “ አስተዉሉ ፡፡ እግዚአብሄር አሕዛቦች የተቀባዉ ርስት እንደሚሆኑ ተስፋን ሰጥቷል (ቁጥር 8) ፡፡
መዝሙር (2፡ 9-12)፡ አመፁ በብረት ዘንግ የተሰበረ ስለሚሆን የአለም ነገስታት ያዳምጣሉ ትዕዛዝም ይቀበላሉ (ቁጥር 9-10) ፤ እግዚአብሄር ለአመፆኞቹ ለንስሀ እድል ስለሰጣቸው በደስታና በአድናቆት ያገለግሉታል (ቁጥር 11) ፡፡ አመፀኛ ሰዎች ሁለት ምርጫዎች ተሰጥተዋቸዉ ነበር፡ “ የእግዚአብሄር የተቀባዉን በመዉደድ ወይም በማክበር ታላቅ በረከቱን ሊደርሱበት ይችላሉ ወይም ደግሞ ለመታዘዝ እምቢ በማለት የእግዚአብሄርን ቁጣ በራሳቸዉ ላይ ያመጣሉ “ ፡፡
መደምደሚያ
መዝሙር 2 በተመሳሳይ ለእኛም ነው ፤ በብዙ አመፀኞች ነን ፤ ለመስራት አንድ ምርጫ አለን ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ በኩል የተዋጀን በመሆን በኑሮአችን የእግዚአብሄር ታላቅ በረከት እንዲያገኘን የፈቀድን ለመሆን መምረጥ እንችላለን ፤ ወይም ደግሞ አመፀኛ ሆኖ መቀመጥን በመምረጥ ራሳችንን ለእግዚአብሄር ለማስገዛት እምቢ በማለት የእግዚአብሄርን ቁጣ በራሳችን ላይ እናመጣለን ፡፡ ምርጫዉ የእኛና በግል መደረግ ያለበት ነው ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 596.
MacArthur, p. 595.
MacArthur, p. 595-596.
MacArthur, p. 596.
MacArthur, p. 596-598.
MacArthur, p. 598.
MacArthur, p. 598.
MacArthur, p. 599.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 649.
ጥያቄዎች
-
የመዝሙር 1 ፀሀፊ መጓዝ፣ መነሳት እና መቀመጥ የሚሉትን ቃላቶች ተጠቅሟል ፤ ይህን በርካታ ቃላትን ለምን እንደተጠቀመ ምን ታስባላችሁ ? “ በክፉዎች ምክር መሄድ “ ምን ማለት ነው ? “ በኃጢዓተኛ መንገድ መቆም “ ማለትስ ?
-
መዝ (1፡ 3) በእግዚአብሄር ህግ ደስ የሚለዉን ሰዉ ለመግለፅ ዘይቤዎችን ይጠቀማል ፤ በዚህ መግለጫ ዉስጥ ራሳችሁን ታዩታላችሁ ? ለምን ወይም ለምን አታዩትም ? በዉሃ ወንዝ የሚያድግ አንድ ዛፍ አስፈላጊነቱ ምንድን ነው ?
-
በመዝ (1፡ 6) ቃሉን ስናነበው “ የክፉዎች መንገድ ትጠፋለች “ ይህ ምን እንድናደርግ ያነሳሳናል ?
-
በመዝ (2፡ 9) ፀሀፊዉ “ በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ “ ይላል ፤ አንድ ቤተሰብ ሆናችሁ ከልጆቻችሁ ጋር “ በብረት በትር መተዳደር “ አስፈልጓችሁ ያውቃል ? ይህን ቁጥር ቤተሰብን በመዉደድ እይታ ግለፁት
-
መዝሙር 2 ማን ያመለክታል ? በዚህ ምዕራፍ የትኛዉ ቁጥር ታላቅ እርካታ አመጣላችሁ ? ለምን ?
-
በመዝሙር 3 ዳዊት እንደገለፀው የእግዚአብሄርን ጥበቃና ከለላ ገጥሟችኋል ? አዎ ከሆነ በምን መንገድ ?
-
በመዝሙር (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 1:1-2
“How happy is the man who does not follow the advice of the wicked or take the path of sinners or join a group of mockers! Instead, his delight is in the Lord’s instruction and he meditates on it day and night.”
የመዝሙር መጽሀፍ የሚጀምረው ምርጫን በማቅረብ ነው ፡- የክፉዎችን ምክር መከተል ፣ በኃጢአተኞች መንገድ መሄድ ፣ በወዘኞች ወንበር መቀመጥ ወይም በእግዚአብሔር ህግ ደስ መሰኘትና ህጉንም በቀንና በለሊት ማሰብ ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛውን ምርጫ የምትመርጥ ከሆነ ደስተኛ እንደምትሆን ይናገራል ! ደስታ ደስ የመሰኘትንና የመርካትን ስሜት ይገልጻል ፡፡ እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር የሚሸሸጉ ደስተኞች ናቸው ፡፡ ምንም እንኳ ደስታ በዙሪያ ባለ ነገር ወይም በፈተና ላይ ባይመሰረትም ፣ አንተ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ በእግዚአብሔር ደስታን ታገኛለህ ፣ በፈተና ውስጥ እንኳ ቢሆን ፡፡ እንደዚህ የምታደርገው ቀንህን ስታሳልፍ አይኖችህን በራስህ ላይ ሳይሆን በክርስቶስ ላይ በማድረግ ነው ፡፡
ስለዚህ ዛሬ የሆነ ነገር ሞክር ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለመግለጥና ቀኑን ሙሉ የምታስበው የመጽሀፍ ክፍል እንድሰጥህ እግዚአብሔርን መጠየቅ ምረጥ ፡፡ በደንብ አስበህ የሚያንጹ ግጥሞች ያሏቸውን መዝሙሮች አድምጥ ፡፡ ራሳቸውን በኢየሱስ ደስ ከሚያሰኙ ሰዎች ጋር ጊዜን አሳልፍ ፡፡ እናም በቀንህ መጨረሻ ቀኑን ሙሉ የእርሱን ቃልና እውነት ማሰብህ በቀንህ ላይ የሳደረውን መልካም ተጽዕኖ ያሳይህ ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ እንደ ደቀ መዝሙር ከጌታ ጋር አብሮ ለመቆየት ፣ ይህንን ለብዙ ተከታታይ ቀናት አድርገው እናም ይህ ህይወትህን ሊለውጠው ይችላል ፡፡
“ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል ። “
- መዝሙር 1፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 2:12 — “ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው ። “
መክብብ 2:26 — “እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው ። “
ያዕቆብ 1:2 — “ወንድሞቼ ሆይ ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ፡፡
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።