Wisdom Books Job

Knowing God Better

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 41-42 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 393 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ ትምህርት ከኢዮብ መፅሀፍ ይህ የመጨረሻዉ ስለሆነ በጣም ተነቃቅቻለሁ ፡፡ የኢዮብ መፅሀፍ ጠንካራ ሊሆን ይችላል ፡፡ ኢዮብ ቀላላ የሚመስለ ዘሌዋዉያንን ሊሰራ ይችላል ፡፡ በምዕራፍ (38-41) እግዚአብሄር በመናገር ኢዮብን ለእርሱ (ለወዳጆቹ) ቅሬታና መነጫነጭ በቂ እንደ ነበር ይነግረዋል ፤ ኢዮብ የእግዚአብሄር ምላሽ በመስማት መደበቅ እንዲፈልግ አደረገው ፡፡ ኢዮብ 42 ለእግዚአብሄር ቃል የኢዮብን ምላሽ ይሰጣል ፡፡ መነጫነጩና ቅሬታዉ እያለ ኢዮብ ይህን በማስወጣት አይኖቹን በጌታ ላይ አደረገ ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (42፡ 1-6)፡ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ቁጥሮች ኢዮብ በራሱ ላይ ፍርድን ያሳልፋል ፡፡ ማክአርቱር “ ኢዮብ አሁንም በጥልቀት ለምን መከራ እንደደረሰበት አያዉቅም ነገር ግን ቅሬታ ማቅረቡን፣ መጠየቁን እና የእግዚአብሄር ጥበብንና ፍትህን መታገሉን እንዳቆመ “ ይናገራል ፡፡ ኢዮብ ማንም የእግዚአብሄር እቅድ ሊያሰናክል እንደማይችል በማወቅ ስለማያዉቀዉ ነገር ያወራ እንደ ነበር በማወቅ ተደነቀ (ቁጥር 1-3) (ኢዮ 38፡ 2-3) ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄር ትዕቢቱን እንደገሰፀዉ አስተዋለ (ቁጥር 4) በተጨማሪም “ የእግዚአብሄርን የዳኝነት ስልጣን ከራሱ ከከሳሹ ከኢዮብ መልሶችን እንደሚፈልግ “ ተረዳ ፤ ኢዮብ በስህተት ላይ እንደ ነበር ተገነዘበ ፡፡ ማክአርቱር “ በመጨረሻም ኢዮብ እግዚአብሄር ማን እንደሆነ በእምነት አይቼ ተረዳሁ አለ ፤ የእግዚአብሄርን ታላቅነቱን፣ ግርማዊነቱን፣ ሉዓላዊነቱን እና ጥገኛ አለመሆንን በዚያ ክስተት እንዳደረገዉ በፍፁም እንዳልያዘው “ ይናገራል ፡፡ በቁጥር 6 ኢዮብ በእግዚአብሄር ፊት ስለጥፋቱ ንስሃ ይገባል ፤ ኢዮብ ፊቱን በአመድ በመሸፈን የተሰበረ እንደሆነና ንስሀ የገባ እንደሆነ አሳዬ ፡፡ ቻርለስ ሱፐርገን “ የንስህ በር ወደ ደስታ አዳራሽ እንደሚያስገባ “ ተናግሯል ፡፡ ኢዮብ ንስሃ በሚገባ ጊዜ አሁንም ሁሉንም ነገር አጥቶ ነበርም እንደ ቆሰለም ነበር ፡፡ የተለወጠዉ ብቸኛዉ ነገር የኢዮብ ልብ ነበር ፡፡ ሰይጣን በኢዮብ ላይ ባመጣዉ ክስና በእግዚአብሄር ላይ ያላቸዉን ትክክለኛ እምነት ማጥፋት እንደሚችል እንዲያምኑ ማቅረቡ ስህተት እንደነበር የተረጋገጠ ነበር ፡፡

ኢዮብ (42፡ 7-9)፡ ይህ የእግዚአብሄርን ንግግር ሌላ ክፍል ይጀምራል ፡፡ እግዚአብሄር ኤልፉዝንና ሌሎች ወዳጆቹንኢዮብ አድርጎት ያልነበረዉን ስለ እርስ በስትክክል ስላልተናገሩ ተቆጣቸው (ቁጥር 7) ፡፡ ማክአርቱር እግዚአብሄር “ ስለ ተሳሳተ ዉክልናቸዉና ትዕቢታቸዉ ገሰፃቸዉ ፤ ይህ የተናገሩት ሁሉም ነገር ስህተት ነበር ማለት አልነበረም ነገር ግን ስለ ገፀ ባህሪዉና ስለ እግዚአብሄር ስራ የተሳሳቱ ንግግሮችን አድርገው እና በኢዮብ ላይ የተሳሳቱ ማስረጃዎችን አንስተዉ እንደ ነበር “ ያመለክታል ፡፡ እግዚአብሄርም በኢዮብ በኩል ሰባት በሬዎችንና ሰባት አዉራ በጎችን በመሰዋት ምህረትን እንዲፈልጉ እድልን ሰጣቸው (ቁጥር 8) ፤ ይህ ኤሊሁን አያካትትም ፡፡ እንደ ተነገሩት አደረጉ ኢዮብም ስለ እነርሱ ፀለየላቸው (ቁጥር 9) ፤ “ እግዚአብሄርም የኢዮብን ፀሎት ተቀበለ “ (ቁጥር 9) ፡፡ ኢዮብ በወዳጆቹና በእግዚአብሄር መካከል እንደ መካከለኛ አገለገለ ይህም ምን እንድንሰራ ወንጌል እኛን የጠራበት አስደናቂ ምሳሌ ነው ፡፡ ይህ እግዚአብሄር ማን እንደሆነ በወዳጆቹ አስተምሮ ላይ አስገራሚ ለዉጥን ያሳያል ፤ እግዚአብሄር ከርህራሄዉና ከምህረቱ የተነሳ ታደጋቸዉ/አደሳቸው ፡፡

ኢዮብ (42፡ 10-17)፡ ከዚያም ጌታ ኢዮብ አንድ ጊዜ የነበረዉን ሁሉንም ነገር እጥፍ በማድረግ ብልፅግናዉን መለሰለት (ቁጥር 10) ፡፡ ከኢዮብ መታደስ በኋላ ወደ ቤቱ ከመመለሱ በፊት ትተዉት የነበሩት ሁሉም ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ እንደ “ ማደሻ እርዳታ “ በማፅናኛ፣ በገንዘብና በወርቅ ጠየቁት (ቁጥር 8) ፡፡ እግዚአብሄር ኢዮብ በ14,000 በጎች፣ በ6,000 ግመሎች፣ 1,000 ጥማድ በሬዎችና በ1,000 ሴት አህዮች ባረከዉ (ቁጥር 12) ፤ እነዚህ እያንዳንዳቸዉ ቁጥሮች ኢዮብ መጀመሪያ የነበረዉ እጥፍ እንደሆኑ ያሳያሉ ፡፡ ኢዮብ መጀመሪያ እንደ ነበረዉ ተመሳሳይ የልጆች ቁጥር ተሰጠዉ (ቁጥር 13) ፡፡ ለሴት ልጆቹ የሰጠዉ ስም በረከቱን እንዴት ምላሽ እንደሰጠበት ያሳያል ፤ ይሚማ “ የቀን ብርሃን “ ማለት ነዉ፣ ቃስያ “ ጣፋጭ ሽታ “ ማለት ሲሆን እንዲሁም ደግሞ “ አማልቶያስ ቂራስ “ ሴቶች የአይን ቆባቸዉን ሊስሉበት የሚጠቀሙበትን የሚያምር ቀለም ይገልፃል “ (ቁጥር 14) ፡፡ ኢዮብ በአይሁድ ህግ ብቻ ዉርስ የሚቀበሉ ወንድሞች በማይኖሩ ጊዜ በሚሆነዉ ብቻ ወንድሞቻቸዉ በሚቀበሉት ዉርስ ለሴት ልጆቹ በሰጣቸዉ ስጦታዎች በጣም የተደሰተ ነበር (ቁጥር 15) ፡፡

ኢዮብ መጀመሪያ በብሽ ሲመታ ሰባ አመቱ ነበር፣ ከታደሰ/ከዳነ በኋላ ሌላ 140 አመታትን ኖረ (ቁጥር 27) ፤ ማክአርቱር “ ኢዮብ በብልፅግና እንደሞተና ቀናቶቹም እንደ በረከት እንደተቆጠሩ “ ይገልፃል (ቁጥር 17) ፡፡

መደምደሚያ

ማክአርቱር እንደ አንድ ባል የኢዮብን እነዚህን ባህሪያት ያስቀምጣቸዋል፡

  1. ኢዮብ ለሚስቱ የእግዚአብሄር መንገድን ለማሳየት ምሳሌ ሆናት (ኢዮ 1፡ 1) ፡፡
  2. ኢዮብ በቤቱ መንፈሳዊ መሪ ነበር (ኢዮ 1፡ 5) ፡፡
  3. በእነርሱ ላይ ስለወደቀዉ ጥፋት ኢዮብ የሚስቱን የተሳሳተ ምላሽ በፍቅር አስተካከለ/አረማት(ኢዮ 2፡ 10)፡፡
  4. ኢዮብ በእግዚአብሄር በፅድቅ በመከራ እንዴት መታመን እንዳለበት የሚስቱ ምሳሌ ነበር (ኢዮ 2፡ 10) ፡፡
  5. ኢዮብ የሚስቱን የተሳሳተ ምላሽ ላይ አልፀናም/አልተያዘም - ቆይቶም እንደገና ሌላ አዲስ ቤተሰብ ተጀመረ (42፡ 13-14) ፡፡

ኢዮብ የቤተሰቡን ተግባር እንደ መንፈሳዊ መሪ ወሰደ ፡፡ ይህን መስራት የሚችል ማንም በሌለ ጊዜ ለተግባሩ ቀጠለ/ተጓዘ ፡፡ ኢዮብ በመከራ ጊዜ በእግዚአብሄር መታመን ማለት ምን እንደሆነ ምሳሌ ሆኗል ፤ በኢዮብ መፅሀፍ መጨረሻ ላይ በማሳያነት ዋይርስቤ፡ “ ይህ ምዕራፍ በእኛ ላይ ምንም ነገር ቢሆን ችግር እንደሌለዉ እግዚአብሄርም ሁል ጊዜ የመጨረሻ ምዕራፋን እንደሚፅፈዉ ያረጋግጣል ፤ ስለዚህ መፍራት የለብንም ፡፡ ያለንበት ሁኔታዎቻችን ምንም ያክል የሚያሙ ቢሆንም ችግር የለዉም ልክ የሆነዉን እንደሚሰራዉ እግዚአብሄርን መታመን እንደምንችል “ ፅፏል ፡፡

ዋይርስቤ በዚህ ጉዞ ኢዮብ የተቀበለዉ ታላቅ በረከት “ እግዚአብሄርን በተሻለ ማወቅና በጥልቅ መንገድ ስራዉን ማስተዋል “ እንደነበር ይናገራል ፡፡ ኮንስታበል ከኢዮብ መፅኀፍ የምንወስደዉ “ ጌታ የሚያዉቀዉ ነገር ለምን እንደሆነ ማወቅ እንደማያስፈልገን ነዉ “ የሚናገረው ፤ ይህ ሁሉ እያለ ኢዮብ ተስፋ ነበረው ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 593.

  2. MacArthur, p. 593.

  3. MacArthur, p. 593.

  4. MacArthur, p. 593.

  5. Charles Spurgeon; quoted in William W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 81.

  6. MacArthur, p. 593.

  7. MacArthur, p. 593.

  8. William W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 82.

  9. MacArthur, p. 594.

  10. Wiersbe, p. 82.

  11. MacArthur, p. 594.

  12. MacArthur, p. 594.

  13. Wiersbe, p. 82.

  14. Wiersbe, p. 82.

  15. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Job (Sonic Light, http://planobiblechapel.org/soniclight/, 2017), p. 148.

ጥያቄዎች

  1. በኢዮብ 41 እግዚአብሄር ኢዮብን ስለ ትልቁ እንስሳ አወራው ፤ ከተሰጠዉ መግለጫ አንፃር ይህ ሰይጣንን የሚገልፅ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም?
  2. ኢዮ (41፡ 34/ምናልባት 26 ይሆናል) ሰይጣን እንደሚሆን የዚህን ምዕራፍ ሀሳብ ይደግፋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ትዕቢት ኃጢዓትና የብዙዎች መዉደቂያ ነው ሌላ መፅሀፍት የት ላይ ትዕቢት ጉዳይ ይሆናል? (ዘፍ 3፡ 4-6, ምሳ 6፡ 16-17, ሕዝ 28፡ 17)
  3. እግዚአብሄር በኢዮብ ፀሎት በኩል ለእነርሱ ለኢዮብ ወዳጆች ምህረቱን አሳዬ ፤ በዚያ ቀን ወዳጆቹ ዋጋ ያለዉ ነገር ተምረዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ስለ ጌታ የተሳሳተ ነገር ተናግራችሁ ተመልሳችሁ በመሄድ ይቅርታ ብላችሁ ታዉቁ ነበር ?
  4. በግል አስተያየታችሁ ኢዮ (42፡ 12-17) ለማደስ እግዚአብሄር በኢዩ (2፡ 25-27) የሰጠዉ ዉጤት ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም ?
  5. በኢዮብ 41-42 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 42:6, 10

“Therefore, I take back my words and repent in dust and ashes. After Job had prayed for his friends, the LORD restored his prosperity and doubled his previous possessions.”

እግዚአብሔር በፍጥረቱ ላይ ስላለው ኃይሉና ግርማዊነቱ ከተናገረ በኋላ ይመልስ ዘንድ ለኢዮብ እድልን ሰጠው ፡፡ በመጨረሻም ኢዮብ ሙሉ በሙሉ ራሱን ዝቅ አደረገ ፤ የእግዚአብሔርንም ታላቅነት አወደሰ እናም “ እግዚአብሔር ሁሉንም ማድረግ ይችላል አሳቡም አይከለከልም “ ብሎ ተናገረ ፡፡ ኢዮብ ስለልተረዳቸው ነገሮች እንደተናገረ በተገነዘበ ጊዜ ኢዮብ ስለተናገራቸው የትዕቢት ቃላት ንስሀ ገባ ፡፡ እግዚአብሔር ኢዮብ ስለ እራሱ የጸለየውን የንስሀ ጸሎት በኋላም እንድሁ ሰለ ጓደኞቹ ያደረገውን ጸሎት ተቀበለ ፡፡ ኢዮብ ከጸለየ በኋላ ፣ እግዚአብሔር ሀብቱን መለሰ እንድሁም ከወንድሞቹና ከእህቶቹ ጋር የነበረውን ግንኙነት መለሰ እንድሁም ቀድሞ የነበረውን ሁሉ መለሰ ፡፡ እግዚአብሔርም የኢዮብን ሁለንተናዊ ህይወት ቀድሞ ከነበረው አብልጦ ባረከ ፡፡

ንስሀ መግባት እና መልሶ ማግኘት ፡፡ ምናልባት ለአባት እድሜ ልክን ሊፈጅ ይችላል ኃጢአትን ወደ ልጅ ሳይተላለፍ ንስሀ ለመግባት ነገር ግን ንስሀ ሲገባ እግዚአብሔር ምርኮን እንደሚመልስ ተናግሯል ፡፡ ባልና ሚስት ባለመግባባት ምክንያት ተኩዋርፈው ሳምንት ሙሉ ሊያሳልፉ ይችላል ፡፡ ነገር ግን ልክ በእግዚአብሔር ፊት ንስሀ ሲገቡ ፣ አንድ በአንድ ምርኳቸው መመለስ ይጀምራል ፡፡ ንስሀ የተዋረደ ዝቅ ያለ ልብን ያሳያል ፡፡ ራስህን ዝቅ አድርግ ፤ ለእግዚአብሔር እና ለሌሎችም ተናዘዝ እናም ከዚያ ወደ ቀድሞ ቦታህ ትመለሰላህ ፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ደግሞ ደጋግሞ ተናግሯል ፡፡ ምን እየጠበክ ነው ? ንስሀ የሚያስፈልገውን የህይወት ክፍልህን እንድያሳይህ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ የሆነ የህይወት ክፍልንም ካሳያህ ፣ በተሰበረና በተዋረደ ልብ ንስሀ ግባ ፤ እግዚአብሔር ምህረት እንድያደርግልህ ለምን ከዚያ አንተም እንደገና ትመለሳለህ ! አሁን እግዚአብሔርን ለመፈለግና ንስሀ ለመግባት ጊዜ ውሰድ ፡፡ ምህረቱ በየማለዳው አድስ ነው ደግሞም እርሱ ፈውስንና መመለስን ተናግሯል ፡፡

“ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ።

ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔርም ምርኮውን መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ቀድሞ
በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው ። “

  • ኢዮብ 42፡6 ፤ 42፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

2ኛ ዜና 7:14 — “በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ። “

ሆሴዕ 6:1 — “ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል ። “

1ኛ የጴጥሮስ5:10 — “በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል ። “