Behemoth
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 39-40 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በትናትናዉ ትምህርት በመጨረሻም ኢዮብ የሚፈልገዉን አገኘ፣ ከእግዚአብሄር ጋር የፈለገዉን ቃለ ምልልስን ፡፡ ኢዮብ ከእግዚአብሄር ጋር ለመነጋገር ሲጠይቅ ነበር ምክንያቱም ያለፍትህ መከራ እየደረሰበት እንደ ነበር ተሰምቶት ስለነበር ፡፡ ኢዮብ ወዳጆቹ የደረሰበት ያለዉ ነገር ሁሉ ኃጢዓተኛ ስለሆነ እንደሚገባው ሙጭጭ ማለታቸዉን ቻለ፡፡ ኢዮብ ንፁህነቱን ጠበቀ ነገር ግን የሆነ ያክል የራስ ፅድቅ ሊሰማዉ ጀመረ ፡፡ ኤሊሁ በሁኔታዉ ላይ በመምጣት ኢዮብ ከራሱ ፅድቅ እንዲወጣና በራሱ ፅድቅ ሙጭጭ ከማለት ይልቅ እግዚአብሄርን ማመስገን እንዲጀምር ገሰፀው ፡፡ እግዚአብሄር ከምዕራፍ 38- 40 ድረስ 77 ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለኢዮብ መለሰለት ፡፡ በምዕራፍ 39 እንዴት እግዚአብሄር ኢዮብን ስለተለያዩ እንስሳቶች ሲጠይቀዉ እናነባለን ፤ በምዕራፍ 40 እግዚአብሄር ስለሁሉም የተለያዩ እንስሳቶች ይጠይቀዋል ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (40፡ 1-2)፡ እግዚአብሄር የመጀመሪያ ንግግሩን ለኢዮብ ያጠቃልለዋል ፡፡ ኮንስታብል “ የእግዚአብሄር የመጀመሪያ ንግግር ኢዮብን በመሞገት ጀመረም ጨረሰም ፤ ኢዮብ እንደ እግዚአብሄር ሀሳብ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሄር መከራ እንዲደርስበት በመፍቀዱ ጥፋት አግኝቶበት ነበር ፤ ስለ ፍትሀዊ አለመሆኑ እግዚአብሄርን ፊት ለፊት በፍርድ በማግኘት ምላሹን ለመስማት እንደሚፈልግ ተናግሯል (ኢዮ 13፡ 3, 15) ፡፡ አሁን እግዚአብሄር ኢዮብን እግዚአብሄር ጥበቡንና ኃይሉን ካሳሰበዉ በኋላ ከእርሱ ጋር መከራከር ይፈልግ እንደሆን እንደ ጠየቀው “ ይፅፋል ፡፡
ኢዮብ (40፡ 3-5)፡ በሙከራዊ መጀመሪያ ላይ ኢዮብ ራሱን ከእግዚአብሄር መከላከል እንደማይችል አስተዋለ ፡፡ እግዚአብሄርን ለመድረስ / ለመናገረ ያመነታ ነበር ፤ “ ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ ? “ (ኢዮ 9፡ 14) ፡፡ ኢዮብ ቀስ በቀስልበ ሙሉ በመሆን ከእግዚአብሄር ጋር ተመልካቾችን/አድማጮችን ፈለገ፡ “ ከዚያም በኋላ ጥራኝ እኔም እመልስልሃለሁ ፡፡ ወይም እኔ ልናገር አንተም መልስልኝ “ (ኢዮ 13፡ 22) ፡፡ ኢዮብ ለእግዚአብሄር መመለስ እንደማይችል ከማወቅ ወደ ከእግዚአብሄር ጋር አድማጭ በመፈለግ በጣም ግትር/ትዕቢተኛ በመሆን ንጉስ/ልዑል ብሎ ወደ መጥራት ዞረ፡ “ የእርምጃዬን ቁጥር አስታዉቀዉ እንደ አለቃም ሆኜ አቀርብለት ነበር “ (ኢዮ 31፡ 37) ፤ ኢዮብ ትዕቢተኛ ሆነ ፡፡
መጀመሪያ ላይ ኢዮብ ወዳጆቹን በመከራዉ ስፍራ ላይ አፋቸዉን እንዲዘጉ ነገራቸው (ኢዮ 21፡ 5)፣ አሁን ኢዮብ በራሱ ላይ በእግዚአብሄር ምርመራ የራሱን አፍ ዘጋ/ዝም አለ ፡፡ ዋይርስቤ የኢዮብን ምላሽ “ የማልበቃ/የማረባና ያልተገባኝ ነኝ ፤ ከእግዚአብሄር ጋር ለመከራከር መብት የለኝም “ በማለት ያጠቃልለዋል ፡፡
ኢዮብ (40፡ 6-8)፡ እነዚህ ቁጥሮች በእግዚአብሄር ሁለተኛ ንግግር ይጀምራሉ ፡፡ እግዚአብሄር ከአዉሎ ንፋስ ዉስጥ ለኢዮብ መመለሱን በመቀጠል ጥያቄዉን እንዲመልስለት ይሞግተዋል ፡፡
ኢዮብ (40፡ 9-14)፡ ዋይርስቤ እግዚአብሄር ኢዮብን በመሰረታዊነት የሚጠይቀዉ “ ኃጢዓተኞችን ለመዳኘት የሚወሰድ/የሚደረግ ጥንካሬና ቅዱስ ቁጣ አለህ ? “ የሚል እንደ ነበር ይፅፋል ፡፡ እግዚአብሄር ኢዮብን ልክ እንደ አንድ ዳኛ እንዲለብስ እና በትክክል በክፉዎች ላይ ፍርድንና ፍትህን እንዲፈፅም ሞገተዉ ፤ ኢዮብ እነዚህን ተግባራት ማድረግ የሚችል ከነበር እግዚአብሄር “ ቀኝ እጁ ታድነዉ ዘንድ እንድትችል እግዚአብሄር ይመሰክርለታል “ (ቁጥር 14) ፡፡
ኢዮብ (40፡ 15-24)፡ እግዚአብሄር “ ጉማሬ “ ይጠቅሳል (ቁጥር 15) ፡፡ ጉማሬ ማለት አዉሬ ማለት ነዉ ነገር ግን ዋይርስቤ ቃሉ ከአዉሬ የበለጠ ማለት እንደሆነ ያመለክታል ፡፡ አንዳንዶች ጉማሬ የጥቂት ዳይኖሰሮችን አይነት እንደሆነ ያምናሉ ፡፡ እግዚአብሄር የጉማሬ ብዙ ጥራቶቹን ይዘረዝራል፡
- ሳር ይበላል (ቁጥር 15) ፡፡
- ጠንካራና ኃይለኛ ነበር (ቁጥር 16) ፡፡
- ኃይለኛ ሰዉነት ነበረው (ቁጥር 16) ፡፡
- ጠንካራ ጡንቻዎች ነበሩት (ቁጥር 16) ፡፡
- እንደ ብረት ዱላ/ዘንጎች የሆኑ አጥንቶች ነበሩት (ቁጥር 18) ፡፡
- በወንዝ ይዝናናል (ቁጥር 21)
- በዉሃ ስር ተደብቋል (ቁጥር 21) ፡፡
- ወንዝን አይፈራም ነበር (ቁጥር 23) ፡፡
- ጠንካራ የፅድ ጭራዎች ነበሩት (ቁጥር 17) ፡፡
- ማንም ሊይዘዉ አልቻለም (ቁጥር 24) ፡፡
ብዙ አማራጮች ከዚህ ገለፃ ጋር ሊጣጣሙ ይችላሉ፡
ዝሆን - አንዱ ትልቅ ችግር ፤ ጉማሬን የሚገልጣ አንዱ ቃል እንደ ጠንካራ ፅድ ጭራ እንዳለዉ ሲሆን ዝሆን ደግሞ አጭር ጭራ አለው ፡፡
የዉሃ ጎሽ - አንዱ ትልቅ ችግር ፤ የዉሃ ጎሾች አንድም ረጅም ጭራ የላቸዉም ፡፡
ጉማሬ - ብዙ ሀተታ ሰጪዎችኢዮብ አንድ ጉማሬን እንደገለፀ ያስባሉ ነገር ግን “ የፅድ ጭራ “ የሚለዉ ገለፃ ለጉማሬም አይሰራም ፡፡
በዘፍጥረት መልሶች “ ጉማሬ “ ጥቂት የዳይኖሰር አይነት እንደ ነበር አቅርቧል ፡፡ እግዚአብሄር ኢዮብን ጉማሬን ከኢዮብ ጋር እንደፈጠረዉ አስታወሰው ፡፡ ዋይርስቤ ኢዮብ “ ብዙ አይነት የተለያዩ ምግቦች ካልበላ “ ጉማሬን “ ለመዋጋት የማይችልና ደካማ “ እንደ ነበር ይፅፏል ፡፡ ጉማሬ “ እርሱ የእግዚአብሄር ፍጥረት አዉራ ነው ፤ ሰሪዉም ሰይፉን ሰጠው “ (ቁጥር 19) ፡፡
መደምደሚያ
ይህ እንስሳ (ጉማሬ) እግዚአብሄር ብቻ ሊቆጣጠረዉ የሚችል በጣም ታላቅ እንስሳ ነበር ፡፡ ኢዮብ ስለ ሁሉም መደንፋቱ/ትዕቢቱ እግዚአብሄር የፈጠረዉን እንስሳት ለማቆም/ለመቆጣጠር የማይችል ኃይል የሌለዉ ሆኖ ቆመ ፡፡
Dr. Tom Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Job, p. 129; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.
Warren W. Wiersbe, Bible Exposition Commentary: Old Testament Wisdom and Poetry (Nashville: David Cook, 2004), p. 80.
Wiersbe, p. 80.
Wiersbe, p. 80.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 592.
MacArthur, p. 592.
B. Coureyer, “Qui est Behemoth?” Revue Biblique, v. 82 (1975):418-43; cited in Constable, p. 134.
MacArthur, p. 592.
Allan Steel, “Could Behemoth Have Been A Dinosaur,” Available at AnswersinGenesis.org., at https://answersingenesis.org/dinosaurs/could-Behemoth-have-been-a-dinosaur/;
Wiersbe, p. 80.
ጥያቄዎች
-
በምዕራፍ 39 እግዚአብሄር ኢዮብን ከጠየቀዉ በኋላችግር ፈላጊ ብሎ ጠራው (ኢዮ40፡ 2) ፤ ኢዮብ እንዴት ምላሽ ሰጠ ?
-
እግዚአብሄር “ እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ “ አለው ፤ ምን ማለቱ ነበር ?
-
እግዚአብሄር ኢዮብን ከማዕበል ዉስጥ ወጥቶ ማዉራትን ለምን እንደመረጠ ምን ታስባላችሁ ? በመፅኀፍት እግዚአብሄር ለሰዎች የተናገረባቸው ሌሎች መንገዶች ምንድን ናቸው ? ለእናንተ እንዴት ተናግሯችኋል ?
-
እግዚአብሄር ኢዮብን “ ራስህን ለማንፃት ጥፋተኝነቴን ትናገራለህን “ በማለት ጠየቀው ? በቀደሙት ምዕራፎች ኢዮብ ያን እንዳደረገዉ አስተዉላችሁታል ? ሌሎች ተመሳሳይ ነገር ሲያደርጉ ሰምታችሁ ታዉቃላችሁ ? ለእነርሱ እንዴት ምላሽ ሰጣችኋቸዉ ?
-
ኢዮብ ራሱን ማዳን እንደሚችል እዉቅና መስጠት እንዲችል እግዚአብሄር ለእርሱ ለማድረግ ኢዮብን በምን ሞገተው (ኢዮ 40፡ 10-14) ? መፅኀፍ ራሳቸዉን ስለሚያድኑ ምን ያስተምረናል ?
-
በኢዮብ (39-40) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ ያስረዳችኋል (ያስተምራችኋል) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 40:8–9
“Would you really challenge My justice? Would you declare Me guilty to justify yourself? Do you have an arm like God’s? Can you thunder with a voice like His?”
እግዚአብሔር ለኢዮብ እንድመልስ እድልን ሰጠው ፡፡ ኢዮብም እጆቹን በአፉ ላይ ከመጫን በቀር የሚመልሰው ምንም ቃል እንደሌለው አመነ ፡፡ እግዚአብሔርም ኢዮብን እንዴት የእርሱን ፍርድ ይቃወም ዘንድ እንደሚችል መጠየቁን ቀጠለ ፡፡ እግዚአብሔር ልቡን አይቶ ስለነበር ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት እንደገና ይመለስ ዘንድ ፣ ኢዮብ መስተካከል ያለበት የአመለካከት ችግር ማዳበሩን አውቆ ነበር ፡፡ እግዚአብሔርም ስለ ቤሄሞት እና በቃ ዳይኖሰርን የሚመስሉ ፍጥረታትን ወደ መግለጽ አመራ እናም እነዚህን አደገኛ የሆኑ አውሬ ፍጥረታት ከራሱ አርቆ መያዝ የሚችል መኖሩን ጠየቀ ፡፡ እናም ኢዮብ እነዚህን አውሬዎች መያዝ ካልቻለ እና ታድያ እንዴት ነው ራሱን በእግዚአብሔር ፊት ማጽደቅ የሚችለው ?
እግዚአብሔር ሀላፊነትን መወጣት ይችላል ፣ ስለዚህ ከህይወትህ ገደብን ቁጥጥርን አስወግድ እና የእግዚአብሔር ፍቃድ በህይወትህ እንድፈጸም ፍቀድ ፡፡ እና እንዴት ነው ታድያ ያ እንድሆን የምታደርገው ? ቆም በል ፡፡ ጸልይ ፡፡ ነገሮች እንድሆኑ አትገፋፋ አትጫን ፡፡ በእግዚአብሔር ሰላም ይኑርህ ፡፡ እግዚአብሔር በልብህ ሸክምን ካስቀመጠ እና ለሆነ አዲስ ነገር በር ከከፈተልህ ምንም የማይመስል ነገር ቢሆን እንኳ ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ በዚያ በር ተራመድ ፡፡ እግዚአብሔር በዚያ ውስጥ እንዳለ ካወቅህ ፣ በቃ ለእርሱ እግዚአብሔር ሆኖ እንድሰራ እንድመራ ፍቀድለት ፡፡ እግዚአብሔር በሺዎች ከፍታ ላይ መንጋውን ይጠብቃል ፡፡ ለምትወደው ሰው ወደ እግዚአብሔር እንድመለስ እየጸለይክ ከሆነ ፣ እግዚአብሔርን ጠብቅ ፡፡ እግዚአብሔር የንጉሥን ልብ መመለስ ከቻለ ፣ ስለዚህ እርሱ ደግሞ አንድ የኮበለለን ልጅ ልብ መመለስ ይችላል ፡፡ አሁንም በድጋሜ እግዚአብሔር ለመታመን ኃላፊነትን ለመቀበል ይችላል ፡፡ በእግዚአብሔር ታመን ፡፡ እግዚአብሔርንም እሻ ፤ እናም ሂድና ተከተለው ፡፡ እርሱ በዙፋኑ በስልጣን ላይ ነው ፡፡
“በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን ? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ትፈርዳለህን ? እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን ? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጕዳለህን ? “
- ኢዮብ 40፡8-9
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 50:10 — “ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና ። “
ምሳሌ 21:1 — “ የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል ። “
ራእይ 1:17 — “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ፣ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።