Wisdom Books Job

Fear Before God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 38 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 391 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በትናትናዉ ትምህርት የኤሊሁን ንግግር ደምድመናል (ምዕራፍ 32-37) ፤ የኤሊሁ ማዕከላዊ ተግባር ኢዮብ እግዚአብሄር እንዳልነበርና እንደሆነ የሚያደርገዉን ነገር እንዲያቆም ለማሳሰብ ነበር ፡፡ ዶር. ቢኒያም ዎት እግዚአብሄር ማን እንደ ነበር የግል አስተያየቱን አንድ ጊዜ ጠይቋል ፤ የምላሹን ጥቂት ንግግሮች ከሰጠ በኋላ ዶር. ዎት “ ይህ በእዉነት ለመጠየቅ ጥያቄ እንዳልሆነ ፤ ለመጠየቅ ጥያቄው፣ የእኔ የእግዚአብሄር የግል አስተያዬት ምንድን ነዉ ? እንደሆነ “ አስተዋለው ፡፡ ይህ በአመለካከት በኢዮብ 38 የሆነዉን የሚከፍት ነው ፡፡ አሁን በሆነዉ ነገር ላይ የእግዚአብሄርን አስተያዬት እናገኛለን ፡፡ ማክአርቱር የእግዚአብሄርን ምላሽ ለኢዮብ እንደ “ ምርመራ “ በማስረዳት “ እግዚአብሄር ከኢዮብ ጋር ፍርድ እንደ ነበረዉ “ ይፅፋል ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (38፡ 1-3)፡ እግዚአብሄር ኢዮብን “ ከአዉሎ ንፋስ ዉስጥ “ ይመልስለታል ፤ ከአዉሎ ንፋስ ዉስጥ እግዚአብሄር ኢዮብን ሲመልስለት ሌሎች ደግሞ እግዚአብሄርን በሚያስደንቅ መንገድ ያገኙታል፡

  • ነጎድጓድ - “ እንዲህም ሆነ ፤ በሶስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጎድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራዉ ላይ ሆነ ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ ፡፡ ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሄር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸው ፤ ከተራራዉም እግርጌ ቆሙ ፡፡ እግዚአብሄርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር ፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር ፡፡ የቀንደ መለከቱም ድምጽ እጅግ በበረታና በጸና ጊዜ ሙሴ ተናገረ እግዚአብሄርም ሙሴን ወደ ተራራው ራስ ጠራዉ ፤ ሙሴም ወጣ “ (ዘጸ 19፡ 16-19) ፡፡
  • ዝግ ያለ ሹክሹክታ - “ እርሱም ፡፡ ዉጣ በተራራዉም ላይ በእግዚአብሄር ፊት ቁም አለ ፡፡ እነሆም እግዚአብሄር አለፈ በእግዚአብሄርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ ዓለቶቹንም ሰባበረ እግዚአብሄር ግን በነፋሱ ዉስጥ አልነበረም ፡፡ ከነፋሱምበኋላ የምድር መናወጥ ሆነ እግዚአብሄር ግን በምድር መናወጥ ዉስጥ አልነበረም ፡፡ ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ እግዚአብሄር ግን በእሳቱ ዉስጥ አልነበረም ፡፡ ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ ፡፡ ኤልያስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፈነ ወጥቶም በዋሻው ደጃፍ ቆመ “ (1ነገ 19፡ 11-13) ፡፡
  • ማዕበል - ሕዝ (1፡ 4) ፡፡

ዋይርስቤ የእግዚአብሄር ጥያቄ ስለ ኢዮብ “ በተፈጥሮ በስራዉ ላይ ያማካለ እና ከጥያቄዎቹ ጋር ወደ ሚገናኙ በመለኮታዊ ማብራሪያ የተበተኑ ሰባ ሰባት ጥያቄዎችን እንደያዘ ፤ የዚህ ምርመራ አጠቃላይ አላማው ኢዮብ እንደ እኩልና ጉዳዉን እንደ ሚከላከል ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናገኘት ብቁ እና የሚችል እንዳልነበር እንዲያስተዉል እንደ ነበር “ ይፅፏል ፡፡ ኢዮብ ስለዚህ ነገር “ ከዚያም በኋላ ጥራኝ እኔም እመልስልሃለሁ ፡፡ ወይም እኔ ልናገር አንተም መልስልኝ “ (ኢዮ 13፡ 22) ፡፡

ዋይርስቤ የእግዚአብሄርን ጥያቄዎች በቀጣዮቹ ጥቂት ምዕራፎች ወደ ሰዎስት ክፍል ይመድባቸዋል፡

“ ፍጥረቴን መግለፅ ትችላለህ ? “ (ኢዮ 38፡ 1-38) ፡፡

“ ፍጥረቴን ማዬት ትችላላችሁ ? “ (ኢዮ 38፡ 39 – 39፡ 30) ፡፡

የኢዮብ የመጀመሪያ ምላሽ (ኢዮ 40፡ 1-5) ፡፡

“ ፍጥረቴን በቁጥጥር ስር ማድረግ/ዝም ማሰኘት ትችላለህ ? “ (ኢዮ 40፡ 6 – 41፡ 34) ፡፡

የኢዮብ ሁለተኛዉ ምላሽ (ኢዮ 42፡ 1-6) ፡፡

ኢዮብ ከእግዚአብሄር ጋር አንድ አድማጭ ፈለገ ፤ አሁን ነበረው፣ እግዚአብሄርም ምንም ነገር መልሶ አልያዘም ፡፡ በቁጥር 2 ለኢዮብ ከእግዚአብሄር ከመጀመሪያ ጥያቄ በኋላ ኢዮብ በፍርድ ከእግዚአብሄር ጋር ለመሆን የጠየቀበትን ቀን መፀፀቱን ይመስላል ፡፡

ኢዮብ (38፡ 4-7)፡ዋይርስቤ እግዚአብሄር “ በምድር አፈጣጠር “ የጥያቄዎቹን መስመር እንደ ጀመረ ይመለከታል፡፡ እግዚአብሄር “ ራሱን ሳይቱን ከሚያጠናው፣ ልኬቶቹን ከሚያሰምረው፣ መሰረቶቹን ከሚተክለው፣ የማዕዘን ድንጋዮቹን ከሚያስቀምጠውና መዋቅሮቹን ከሚያቆመዉ አንድ ግንበኛ ጋር አወዳደረ “ ፡፡

ኢዮብ (38፡ 8-11)፡ እግዚአብሄር ባህርን የሚመለከት ኢዮብ አለው ፤ እግዚአብሄር ባህሮችን በአንድ ላይ ይሸርባል ከዚያም “ ከማህፀን እንደሚወጣ ህፃን ወደፊት ይጥሳል/ይወጣል “ ፡፡

ኢዮብ (38፡ 12-15)፡ እዚህ እግዚአብሄር ፀሀይን የሚመለከት ኢዮብ አለው ፤ “ ኢዮብ እስካሁን ፀሀይ በመዉጣት ጨለማን እንደሚበትን ተነግሮት ነበር ? “ እግዚአብሄር ብርሃንን የምድርን አቀማመጥ ዝርዝር እንዲገልጥና ክፉ ስራን እንዲገልጥ በአለም ሁሉ ላይ እንዲዘረጋ አዝዟል ፡፡

ኢዮብ (38፡ 16-24)፡ አስራ አንዱ ጥያቄዎች የፍጥረትን በጣም ሰፊ ወርድን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ የሰዉ ልጅ እስካሁን ወደ ታች ወደ ዉቅያኖሶች ጥልቀት 35, 810 ጫማ (6.78 ማይል) እና 4.4 ቢሊዮን ማይል ወደ ህዋ በመድረስ ተጉዟል ፤ እግዚአብሄር በቅርበት የፍጥረትን እያንዳንዷን ስፋት ያውቃል ምክንያቱም ስለሰራው ፡፡

ኢዮብ (38፡ 25-30)፡ እግዚአብሄር ኢዮብን ስለ ዝናብ (ቁጥር 25-28), ስለ በረዶ እና ስለ ዉርጭ ይጠይቀዋል ፡፡

ኢዮብ (38፡ 31-33)፡ እግዚአብሄር ኢዮብን ስለ ከዋክብቶችና ስለ ክዋክብት ስብስብ ይጠይቀዋል ፡፡ ክርስቶፈር አሽ፡ “ የአለም ሰማያዊ መንግስት በእግዚአብሄር ቁጥጥር ስር እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡

ኢዮብ (38፡ 34-38)፡ እግዚአብሄር የኢዮብ ትኩረት ዳመናት ላይ እንዲሆን ይጠራዋል ፡፡

ኢዮብ (38፡ 39-41)፡ እነዚህ ቁጥሮች ወደ ምዕራፍ 39 የሚቀጥሉትን የስድስቱን አዉሬዎችና የአምስቱን ወፎች መግለጫዎች ይጀምራል ፡፡

መደምደሚያ

ይህ እግዚአብሄር ለኢዮብ የመለሰበትና የኢዮብን ኩራት/ትዕቢት የተናገረበት የመጀመሪያዉ ጊዜ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር የኢዮብን ሀቀኝነት ወይም ቅንነት አልጠየቀም፣ በአለም ላይ የእግዚአብሄርን መንገድ ለመግለፅ የኢዮብን ችሎታ ብቻ ጠየቀው ፤ ኢዮብ ስለ እግዚአብሄር እዉነት ተናግሮ ነበር (ኢዮ 42፡ 7) ነገር ግን ንግግሩ ትህትና እንዳልነበረው “ ያስቀምጣል ፡፡

  1. Benjamin Jowett; quoted in Christopher Ash, Job: The Wisdom of the Cross (Wheaton: Crossway, 2014), p. 374.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Nelson, 2005), p. 591.

  3. Warren Wiersbe, Bible Exposition Commentary: Old Testament Wisdom and Poetry (Nashville: David Cook, 2004), p. 76.

  4. Wiersbe, p. 76.

  5. Wiersbe, p. 76.

  6. Wiersbe, p. 77.

  7. Wiersbe, p. 77.

  8. Wiersbe, p. 77.

  9. Wiersbe, p. 77-78.

  10. Wiersbe, p. 78.

  11. Wiersbe, p. 78.

  12. Ash, C. (2014). Job: The Wisdom of the Cross. (R. K. Hughes, Ed.). Wheaton, IL: Crossway., p. 387.

  13. Wiersbe, p. 78.

  14. Wiersbe, p. 77.

ጥያቄዎች

  1. መከራዉን ለመግለፅ በኢዮብ ሙከራ ዉስጥ ጌታ የጠቀሰው የኢዮብ ትልቅ ስህተት ምን ነበር (ኢዮብ 19፡ 6) ?
  2. እግዚአብሄር ለወዳጆቹ ሳይሆን ለኢዮብ በቀጥታ ለምን እንደ ተናገረዉ ምን ታስባላችሁ (ኢዮ 7፡ 6-21, 30፡ 20) ? ወደ እግዚአብሄር መጮኽ ለምን የሚጠቅም ነው ?
  3. ከእግዚአብሄር ከተጠየቀ በኋላ ኢዮብ ጥያቄዉ እንደተሰማ እንዴት ተሰምቶት እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ? እግዚአብሄርን ስለ ምን ጠይቃችሁታል ?
  4. እግዚአብሄር ኢዮብን ስለማንኛዉ የፍጥረት አካል ጠየቀው ?
  5. በመፅሀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ የእግዚአብሄር መገኘት በአዉሎ ንፋስ ዉስጥ የታወቀ ተደረገ ? (2ነገ 2፡ 1-11, መዝ 77፡ 18, ኢሳ 66፡ 15, ሕዝ 1፡ 4)
  6. በኢዮብ 38 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 38:2–4

“Who is this who obscures My counsel with ignorant words? Get ready to answer Me like a man; when I question you, you will inform Me. Where were you when I established the earth? Tell Me, if you have understanding.”

ኤሊሁ በትዕቢት የተሞላውን የኢዮብን ልብ ከገሰጸና እግዚአብሔርን የመፍራት ጥቅም ከተናገረ በኋላ ፤እግዚአብሔር ለኢዮብ በአውሎ ነፋስ መለሰ ፡፡ እግዚአብሔር ኢዮብን ስለ ፍጥረት የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ በዋነኝነትም ደግሞ ማድረግ ትችላለህን ፤ የኔን ፍጥረታት መቆጣጠር ትችላለህን ? እያለ በመጠየቅ እግዚአብሔር አሳቡን ለኢዮብ ተናገረው ፡፡ በርግጥ ኢዮብ በታማኝነት ተመላልሶ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በፍጥረቱ ሁሉ ያለውን የእግዚአብሔርን እጅ ኃይል በደንብ አድርጎ ያውቅ ነበርን ? ኢዮብ በመከራ ውስጥ ሆኖ እንኳ ጭምር እግዚአብሔርን ይሞግት ዘንድ ፈጽሞ ምክንያት አልነበረውም ፡፡

ምንም እንኳ መልካም ባህሪ በህይወትህም ደግሞ ስኬት ሊኖር ይችላል ነገር ግን እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው ፡፡ ከእግዚአብሔርም በቀር ሌላ የለም ፡፡ እርሱ መንገድህን የሚያጸና አለትና መሸሸገያህ ነው ፡፡ እርሱ የክዋክብቱን ቁጥር ይቆጥራል ለእያንዳንዳቸውም ስምን ይሰጣል ፡፡ እርሱ ታላቅ ነው ፤ በኃይሉም ከፍ ያለ ነው ፤ ለጥበቡም ቍጥር የለውም ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን ምን ያህል እንደማታውቀው እርሱም እንዴት ድንቅ አምላክ እንደሆነ ተገንዘብ ፡፡ ይህ እውነት በእግዚአብሔር ፊት ትሁት እንድትሆንና በእርሱ በመደገፍ እንድትቆም ያደርግሀል ፡፡ በችግር ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ እንኳ የአለሙን ሁሉ ፈጣሪ እንድሁም የአንተን ህይወት በእጁ የያዘውን እግዚአብሔርን አስታውስ ፡፡ እግዚአብሔርን ታውቀው ይሆናል ፣ ነገር ግን በደንብ አድርገህ እግዚአብሔርን ታውቀዋለህ ?

“ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው ? እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ ። ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር ። “

  • ኢዮብ 38፡2-4

ተጨማሪ ጥቅስ

2ኛ ሳሙኤል 22:32–33 — “ ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው ? ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቃና ፣ “

ኢዮብ 38:34–35 — “ ውኆች ብዛት ይሸፍንህ ዘንድ ቃልህን ወደ ደመናት ታነሣ ዘንድ ትችላለህን ? መብረቆች ሄደው፦ እነሆ፥ እዚህ አለን ይሉህ ዘንድ ልትልካቸው ትችላለህን ? “

መዝሙር147:4–5 — “ የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል ። ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም ። “