Wisdom Books Job

Fear Before God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 37 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 390 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የኢዮብ መፅሀፍ ለማጥናት አስቸጋሪ ነዉ ምክንያቱም ረጅምና ድግግሞሽ ስለሆነ ፡፡ የመፅኀፉ አብዝሀኛው የኢዮብ እያንዳንዳቸው ሰዎስቱ ወዳጆቹ ለእርስ ስላቀረቡለት ክርክር (በአጠቃላይ ዘጠኝ ክርክር) ነው ፡፡ ለኢያንዳንዱ ንግግር/ክርክር ኢዮብ ኃጢዓት አልሰራሁም በማለት መለሰ ፤ የኢዮብ ወዳጆች ሊረዱት ባይችሉም ኢዮብ ተስፋዉን ተስፋ በተገባዉ ተቤዢ ላይ አደረገ (ኢዮ 19፡ 25-26) ፡፡ ኢዮብ 31 መጨረሻ ላይ ኢዮብ ራሱ ላይ ማትኮር በመጀመር አይኖቹን ከጌታ ላይ አንስቶ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 32-37 አዲስ ገፀ ባህሪይ ኤሊሁ እግዚአብሄርን በመወከል ይገባል ፡፡ ኤሊሁ በኢዮብና በወዳጆቹ መካከል መካከለኛ ለመሆን መጣ ፡፡ ኤሊሁ ለእግዚአብሄር ተናጋሪ ሰዉ ይሆንለታል ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (37፡ 1-9)፡ ኤሊሁ በሚያደርገዉ ነገርና የእግዚአብሄርን ድምፅ በማመልከት ልቡ እንደተንቀጠቀጠች በመግለፅ ተናገረ (ቁጥር ቁጥር 1-3) ፡፡ ከእግዚአብሄር ቀጥታ የመጣዉን ቃል እንዲሰሙ አድማጮቹን ይጣራል ፡፡ ኤሊሁ ለኢዮብና ለወዳጆቹ ቀጥታ እንዲናገር ለእግዚአብሄር የሚያዘጋጀዉ እግዚአብሄር ማን እንደሆነ ነገርን በመመስረት እየጀመረ ነው፤ የእግዚአብሄር ድምፅ በግርማዊነቱ በሰማይ ላይ በማንጎዳጎድ የሰዉ ልጅ ሊረዳዉ የማይችለዉ ድርጊት ይወስዳል (ቁጥር 4-9) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የሁሉንም ሰዉ እጅ ለማስቆም እግዚአብሄር የክረምትን ጎርፍ/ነጎድጓድ ስለሚጠቀም ብዙዎች የእግዚአብሄርን ስራ ያስተዉሉታል እንጂ እንደማይሰራ “ ይናገራል፡፡ በተጨማሪም የኤሊሁ ንግግር “ በኃይለኛ ዘይቤ አነጋገር በሁሉም በእግዚአብሄር ኃይል አመስግኗል “ እንዲሁም “ እግዚአብሄር በረዶን እንደሚያደርገዉ ንፋስን በፉካ እንደሚጠብቅ ገልፆታል “ ፤ ለምሳሌ በቁጥር 9 ኤሊሁ እግዚአብሄር በረዶንና ዉሽንፍሩን/ንፋሱን አጠራቅሞ ያስቀመጠባቸዉን ፉካ ይጠቅሳል ፤ ያ አስደናቂ ስዕል ነው ?

ኢዮብ (37፡ 10-12)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ኤሊሁ በዉሃማ ስፍራዎች የሚያቀዘቅዘዉንና በረዶ መስራት የሚችለዉን የእግዚአብሄርን እስትንፋስ ይገልፃል ፡፡ የእግዚአብሄር እስትንፋስ ደመናዎችን ይደርባል/ይጭናል በደመና ዉስጥ ብርሃንን ይበትናል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በቁጥር 12 እግዚአብሄር “ በመሪ ላይ ለእጁ በመታዘዝ ለሚመልስለት ለደመናት ስርዓቱን በችሎታ የሚመራ እንደ ጥበበኛ ካፒቴን “ የሚያሳይ እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡

ኢዮብ (37፡ 13-17)፡ ደመናት ለእግዚአብሄር ትዕዛዝ እና ምሪት ምላሽ ይሰጣሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እግዚአብሄር ማዕበልን ለሰዎስት ምክንያቶች እንደሚያደርገዉ ይገልፃል፡ “ 1) የሰዎችን ክፉነት ለመቅጣት, 2) ለምድር ምግብነት እና 3) ለህዝቡ አስፈላጊ ነገሮች ለማቅረብ “ ፡፡ ለምሳሌ አንድ ገበሬ የፀሎት ሰዉ ለመሆን ያዘነብላል ምክንያቱም የምርቱ እና የመተዳደሪያው ስኬት የአየር ንብረቱ መሬቱን እንዴት እንደሚከባከብለት ላይ የተደገፈ ነው ፤ ስለሆነም “ እግዚአብሄር ምድር ላይ ለመፍረድና ለህዝቡን የበረከትን ዝናብ ለማምጣት ለሁለቱም ማዕበልን ይጠቀማል “ (ዘጸ 15፡ 7-10, ዘዳ 28፡ 21-24) ፡፡

ኢዮብ (37፡ 18-21)፡ “ የቀድሞ መስታወቶች ጠንካራና የማይሰበሩ ነበሩ ምክንያቱም ከሚያብረቀርቅ ነሀስ የተሰራ ስለነበር “ ፡፡ የአየር ፀባይን በምድር ላይ የማሰራጨት ሀይል ያለዉ እግዚአብሄር ብቻ ነው ፤ ኤሊሁም ለአድማጮቹ በእግዚአብሄር ፊት የሚሉትን ነገር ለመማር ፈቃደኞች መሆን እንዳለባቸዉ ይነግራቸዋል (ቁጥር 18-20) ፡፡ የእግዚአብሄር ኃይል በቀጥታ ፀኃይ ላይ መመልከት ከምንችለዉ እንኳን በጣም የበለጠ ነው - እግዚአብሄር የፈጠረዉን ነገር (ቁጥር 21) ፡፡ እግዚአብሄርን ፊት ለፊት መቅረብ ምን ያክል አስቸጋሪ ይሆናል ?

ኢዮብ (37፡ 22-24)፡ ቁጥር 22 እግዚአብሄር ከሰሜን እንደሚመጣ ይናገራል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ በቀድሞዉ ጊዜ ሰሜን የእግዚአብሄር የመቆያ ስፍራ እንደ አቅጣጫ የሚታይ እንደ ነበር “ (ኢሳ 14፡ 13) ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር በወርቅ ድምቀትና ግርማ ይገለጣል (ዘጸዓት 34) ፡፡ “ በመጨረሻም ኤሊሁ ሁሉም ሰዉ ስለ ሁሉን ቻይ ፈጣሪያቸው ሊኖራቸዉ የሚገባዉን አክብሮታዊ ዉዳሴና አስደናቂ አምልኮን ይናገራል “ ፤ እግዚአብሄር በመሆኑ ምክንያት ሰዉ ይፈራዋል (ቁጥር 24) (ኢዮ 23፡ 13-16, መዝ 19፡ 9, 33፡ 8, 34፡ 11, 86፡ 11, 111፡ 10, ምሳ 1፡ 7, 9፡ 10, መክ 12፡ 13, ኤር 5፡ 22) ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄርን መፍራት ድንጋጤ፣ ስጋት፣ አክብሮት፣ ዉፋሴና ክብር መኖር ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሄርን እንዴት ነዉ የምንፈራው (መዝ 34፡ 11፡ 86፡ 11፣ መክ 12፡ 13) ? ፍጥረቱን በመመልከት (በእርሱ መገላገል ላይ የተፈጥሮን ኃይል)፣ ቃሉን በማንበብና በእምነታችን በመፅናት በመቆየት አክብሮትና ዉዳሴ ለእግዚአብሄር ያስፈልገናል ፡፡

1ዮሐ (4፡ 18)፡ “ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አዉጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም ፍርሃት ቅጣት አለዉና ፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም “ ፡፡ የእግዚአብሄርን ፍርድ የምንፈራ አንሆንም ወይም እርሱን አንፈራም ምክንያቱም ኢየሱስ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ሲሞት ቅጣታችንን ስለ ወሰደው ፤ እግዚአብሄር በፍራት እንድንወቀስ አይፈልግም በእርሱ ጥበቃ በጣፋጭ ሰላም እንድንደሰት እንጂ ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 638.

  2. Nelson’s Commentary, p. 638.

  3. Nelson’s Commentary, p. 638.

  4. Nelson’s Commentary, p. 638-639.

  5. Nelson’s Commentary, p. 639.

  6. Nelson’s Commentary, p. 639.

  7. Nelson’s Commentary, p. 639.

  8. Nelson’s Commentary, p. 639.

ጥያቄዎች

  1. የማዕበሉ ድራማ እስካሁን እግዚአብሄርን ተመልክቶት ስለ ነበረው ኤሊሁን ምን ያሳስበዋል (ኢዮ 36፡ 32-33, 37፡ 1) ?
  2. እግዚአብሄር የክረምት ማዕበልን የተጠቀመበትን ምክንያት ኤሊሁ ምን አለ ? (ኢዮ 37፡ 7)
  3. ኤሊሁ ኢዮብ “ የእግዚአብሄርን አስደናቂ ተዓምራቶችን መመልከት እንዲያቆም “ ፈለገ ፤ ጥቂት ደቂቃ ዉሰዱና በዚያ በራሳችሁ ላይ አትኩሩ ፤ እግዚአብሄር ስለ እናንተና በእናንተ ዉስጥ ያደረገዉን ተመልከቱ ፡፡
  4. በቁጥር 24 በመጨረሻ ኤሊሁ ከእግዚአብሄር አንፃር እንዴት መሆን እንደሚገባን ምን ተናገረ ? (ኢዮ 28፡ 24-28, ማቴ 10፡ 28, 11፡ 25)
  5. በኢዮብ 37 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 37:24

“Therefore, men fear Him. He does not look favorable on any who are wise in heart.”

ለኢዮብ የኤሊሁ የመጨረሻ ንግግር ፤ ኤሊሁ በአየር ሁኔታውና በፍጥረቱ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ታላቅና ኃያል ስራ ጥልቅ በሆነ ስሜት ገለጸ ፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ህይወታችንን እንደሚቆጣጠር በግልጽ ለማስረዳት ኤሊሁ የራሱን ጉዳይ አቀረበ ፡፡ ይህንን በማድረግም ኤሊሁ ለኢዮብ ህይወት የተናገረው የመጨረሻ ነጥብ በንጹህ ልብ እግዚአብሔርን እንድፈራ ነበር ፡፡ ኤሊሁ እንዳለው እግዚአብሔር እራሳቸውን ከፍ ባለ ጥበብ በሚደግፉ ሰዎች ላይ ይበሳጫል ፡፡ የፍጥረት ሁሉ አምላክ እርሱ ጥበብን ሁሉ ይዟል ታድያ ለምንድን ነው ስለ ጥበብ የምትመካው ደግሞስ ከእግዚአብሔር ይልቅ እንደምታውቅ የምታስበው ፡፡

በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ትዕቢት በልብህ ውስጥ ሊገባ ይችላል ፡፡ የአንድን ነገር ውጤት ቀድመህ እንደምታውቅ ታስብ ይሆናል ወይም የሆነን ነገር መከሰት ምክንያት እንደምታውቅ ልታምን ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ እንዳለህ ታስብ ይሆናል ፡፡ አስታውስ እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉና የታምራት ሁሉ አምላክ እንደሆነ ፤ አዎን እርሱ ፈጥሮሀል ደግሞም ልብህን ያውቃል ፡፡ እርሱ ያለምንም ትዕቢት በሙሉ ልብህ እንድትፈራው ይፈልጋል ፡፡ በየትኛውም ፈተና እና መከራ ውስጥ ስታልፍ በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ አትኩር እርሱንም በደንብ እንድታውቀው ቃሉን አንብብ ፡፡ እነዚህን ሁለት ነገሮች ስታደርግ ከራስ ወዳድነት በራስ ከመመካት በንጹህ ልብ እግዚአብሔርን ወደ መፍራት እንድትመለስ ያግዙሀል ፡፡ ለባህር ዳርቻን ያበጀው ፣ ዝናብንም የሚሰጠው ያ እግዚአብሔር ራሱ የአንተንም ህይወት ይቆጣጠራል ፡፡ እርሱ ከችሎታ ያለፈ ነው ፡፡ መንገዱን ያስተምርህ ዘንድ ፍቀድለት ፡፡

“ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም ። - ኢዮብ 37፡24

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 19:9 — “የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው ። “
  • መዝሙር 86:11 — “አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል ። “
  • ኤርምያስ 5:22–24 — “በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም ። በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም ። በልባቸውም፦ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም ። “