Wisdom Books Job

The Mediator

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 389 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሪቫይቭ ት/ቤት አላማ ሁሉም መፅኀፍት እንዴት ወደ መሲሁ እንደሚያመለክቱ ማመልከት ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ያ ጥቆማ የክርስቶስ ጥላ ነው ፤ አንዳንድ ጊዜ የተያዉ ራሱ ክርስቶስን ሲሆን ፤ አንዳንድ ጊዜ የክርስቶስ አይነት ስዕል አይተናል ፡፡ ኢዮብ ስለ አንድ መካከለኛ ከፀለዬ በኋላ ኤሊሁ በሁኔታዉ ላይ መጣ ፡፡ ኤሊሁ በዛሬዉ ምዕራፍ ሁለት ንግግሮችን ይሰጣል በአጠቃላይ አምስተኛዉንና ስድስተኛዉን ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (36፡ 1-7)፡ ኤሊሁ እግዚአብሄር “ፍፁም እዉቀት “ እንዳለዉ በማሳመን ለጀመረዉ ሌላ ንግግር ስለ ትዕግስት ይጠይቃል (ቁጥር 4) ፡፡ ማክአርቱር ኤሊሁ “ እግዚአብሄር መከራ ቢልክም ልክ እንደሆነና ምህረት እንደሚያደርግ ደግሞ በማሰብ እንደጀመረ “ ይመለከተዋል ፡፡ ኤሊሁ ክፉዎች በእግዚአብሄር አይቀጡም የሚለዉን የኢዮብን ማረጋገጫ ይከራከራል/ይሞግታል ፡፡

ኢዮብ (36፡ 8-15)፡ማክአርቱር “ መዓት/መቅሰፍት “ የሚለዉን ቃል በቁጥር ዘጠኝ ከተጠቀመው “ መከራ “ ወይም “ ድህነት “ ከሚለዉ ቃል ስር ትርጉም መምጣቱን ይፅፋል ፡፡ “ በዚህ ቃል አንድ ሰዉ በትልቅ ሸክም ስር መደፋቱን የሚያሳይ ስዕል መሆኑን ነው ፤ መፅሀፍ እግዚአብሄር በሕዝቡ ላይ ህመም የሚያመጣዉን መቅሰፍት እንደሚያይ እና በጭንቀት ዉስጥ ያሉትን የጭንቀት ድምፅ እንደሚሰማ ያሳያል ፡፡ ጌታ ለመሸከም በቂ ስለሆነና በሚያስፈልገን ጊዜ ሊረዳን ስለሚወድ ሸክማችንን በእርሱ ላይ እንድናስቀምጠዉ ያሳስበናል ፤ በተጨማሪም ሁሉንም ክስተት ከተቆጣጠረ አሁን ከገጠመን ጊዜያዊ አስቸጋሪ ነገር መልካም ነገር እንደሚፈፅም ማረጋገጥ እንችላለን ፡፡ የኢዮብ ጠቅላላ ታሪክ ለዚህ እዉነት ጉልህ ምሳሌ ይሰጣል “ ፡፡

“ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት “ (1ጴጥ 5፡ 7) ፡፡

“ እግዚአብሄርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናዉቃለን “ (ሮሜ 8፡ 28) ፡፡

ኮንስታብል በኤሊሁ መሰረት ለእግዚአብሄር ትምህርት የሚሆኑ ሁለት ዉጤቶችን ይናገራል፡ “ መስማት (ቁጥር 11) እና አለመስማት (ቁጥር 12) እያንዳንዱም ዉጤት አለዉ “ ፤ የእግዚአብሄርን የክፉ ብስጭት ትምህርትን ለመስማት የማይፈልጉ የእግዚአብሄር ልብ የሌላቸዉ፣ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ለመመለስ እምቢ የሚሉ፣ የእፍረትን ህይወት የሚኖሩ በመጨረሻ ይሞታሉ (ቁጥር 13-14) ፡፡ የእግዚአብሄር ልብ ያላቸዉ የተቸገሩ ወደ እግዚአብሄር የሚመለሱ፣ ለእርሱ የሚታዘዙ፣ ከመከራቸዉ የሚማሩ በህይወት ይኖራሉ (ቁጥር 15) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለእርዳታ ወደ እርሱ ለመጮኽ በመተዉ የእግዚአብሄርን መልዕክት አለመግፋት “ በማለት ኃላፊነት ይሰጣል ፡፡

ኢዮብ (36፡ 16-21)፡ ዋይርስቤ ኤሊሁ ለኢዮብ የሰጠዉን ሰዎስት ማስጠንቀቂያ አጉልቶ ያሳያል፡

  1. ኢዮብ ከችግሩ ለመዉጣት መንገድን ለመግዛት ሞከረ (ቁጥር 18-19) - በመንገድ ግድግዳ ላይ ያለ መፅሄት አንድ ፀሀፊ “ ገንዘብ ከሰማይ በስተቀር ለሁሉም ስፍራ እንደ አለም አቀፍ ፓስፖርት የሚጠቅም እና ከደስታ በስተቀር እንደ አለም አቀፍ ሰጪ ሁሉንም ነገር የሚሰጥ እቃ/ነገር እንደሆነ “ ተናግሯል/ፅፏል ፡፡
  2. ኢዮብ የራሱን ህይወት በመዉሰድ ተመለከተ (ቁጥር 20)
  3. ኢዮብ ተስፋ በመቁረጥ ወደ ኃጢዓት ተመለሰ (ቁጥር 21) ፡፡

ኢዮብ (36፡ 22-33)፡ በመጨረሻ ንግግሩ ኤሊሁ ኢዮብን አዲስ ነገርን እንዲሞክር አሳሰበው ፤ የእግዚአብሄር ታላቅነትን በመሳል እግዚአብሄርን እንዲያመሰግን ኢዮብን አሳሰበው ፡፡

ኤሊሁ የክርስቶስ ስዕል ነበር ፤ በእግዚአብሄርና በኢዮብ መካከል እንደ መካከለኛ ይወክላል ፡፡ የኤሊሁ ስም ትርጉሙ “ የኔ አምላክ ነዉ “ ወይም “ እግዚአብሄር አምላክ “ ማለት ነው ፤ የአባቱ ስምም ባርክኤል ሲሆን ትርጉሙም “ እግዚአብሄር ይባርክ “ ወይም “ እግዚአብሄር ይባርክሀል “ ማለት ነው ፤ ስለዚህም ኤሊሁ “ የእግዚአብሄር ይባርክህ “ ልጅ “ የኔ አምላክ “ ነበር ፡፡

“ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያዉ ከዉኃ ወጣ ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ ፤ እነሆም ድምፅ ከሰማያት መጥቶ ፡፡ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደዉ ልጄ ይህ ነው አለ “ (ማቴ 3፡ 16-17) ፡፡

ኤሊሁ ኢየሱስ በጥምቀቱ ላይ በህዝብ ፊት በድንገት እንዴት መጀመሪያ መገለጡን እንዳደረዉ በተመሳሳይ በኢዮብ ታሪክ ላይ ድንገት ታዬ ፡፡

ኤሊሁ ቡዛዊዉ ነበር (ኢዮ 32፡ 2) ፤ ቡዛዊ ማለት “ የተናቀ “ ማለት ነው ፤ ስለዚህም ኤሊሁ “ የተናቀዉ “ ነገድ “ እግዚአብሄር የባረከዉ “ ልጅ “ የኔ አምላክ “ ማለት ነበር ፡፡

“ እርሱም መልሶ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናናል ፤ ስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል ? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም “ (ማር 9፡ 12) ፤ ሁሉም የኤሊሁ ስሞችና የመላዉ ቤተሰቡ ዉርስ ወደ መጣዉ መሲህ አመልክተዋል ፡፡

“ ሄሮድስም ከሰራዊቱ ጋር ናቀዉ ዘበተበትም የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው “ (ሉቃ 23፡ 11) ፡፡

ኤሊሁ በተጨማሪም “ ታላቅ “ ወይም “ የበለጠ “ ማለት ለሆን ከሚችለዉ ከራም ወገን ነበር (ኢዮ 32፡ 2) ፡፡

ኤሊሁ በኢዮብ ላይ የተበሳጨ በመሆን ንግግሩን ጀመረ “ ምክንያቱም ከእግዚአብሄር ይልቅ ራሱን ጻድቅ ስላደረገ “ (ኢዮ 32፡ 2) ፡፡ የራስ ፅድቅ ሁልጊዜ ኑሮአቸዉን ለማፅደቅ ይሞክራል ፤ ይህ አይሰራም ፡፡ የዚህን ሌላ ስዕል አንድ ህግ አዋቂ ኢየሱስን በጠየቀዉ ጊዜ በሉቃስ 10 ላይ በሚገኘዉ በደጉ ሳምራዊ ታሪክ ላይ ማየት እንችላለን ፤ “ እርሱ ግን ራሱን ሊያፀድቅ ወድዶ ኢየሱስን ፡፡ ባልንጀራዬስ ማን ነው ? አለው “ (ሉቃ 10፡ 29) ፤ ኢየሱስም በታላቅ ምሳሌ ሰዉዬዉን እንዴት በራስ ፅድቅ ህይወት መኖር እንደማይቻል ያሳየዋል ፡፡

መደምደሚያ

ኢዮብ አንድ መካከለኝ ጠየቀ በኤሊሁ አንድ አገኘ ፤ ኤሊሁ እንደ ክርስቶስ ስዕል ያገለግላል ፡፡ ክርስቶስ እንደ መካከለኛ ያገለግለናል ፤ ክርስቶስ እንደ ቤዛ ያገለግለናል ፡፡ ክርስቶስ የህይወት ብርሃን ሲሆን ከኢዮብ ሰዎስት ወዳጆች ይልቅ በተሻለ መልስ በኢዮብ ጨለማ መካከል ላይ ኤሊሁ ተገለጠ ፡፡ ኤሊሁ ኢዮብን ራሱን ማፅደቅ እንደማይችል ነገረው ፤ ያን ለማድረግ እግዚአብሄር ያስፈልገዋል ልክ እኛ በእግዚአብሄር ፊት ለመፅደቅ ክርስቶስ እንደሚያስፈልገን ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 590.

  2. MacArthur, p. 590.

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Job, p. 118; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  4. Constable, p. 118.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 638.

  6. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 74.

  7. The Wall Street Journal; cited in Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 74.

  8. Wiersbe, p. 74.

  9. Steve Kline, Living Room Theology, iTunes; available at https://itunes.apple.com/us/podcast/living-room-theology/id1195467009?mt=2.

  10. Constable, p. 107.

  11. “Elihu the Son of Barachel the Buzite,” www.thetrueman.org, November 11, 2018; available at http://www.thetrueman.org/elihu-the-buzite/.

  12. Mark Allen Powell, ed., HarperCollins Bible Dictionary, abridged (Atlanta: Society of Biblical Literature, 2009, “Ram”; available at www.Bibleodyssey.org.

ጥያቄዎች

  1. ኤሊሁ ስለ እግዚአብሄር የሚናገረዉ ብዙ አለኝ አለ (ኢዮ 36፡ 2) ፤ እግዚአብሄር ስለ እርሱ የሚናገርለት ያስፈልገዋል ወይስ ይፈልጋል ? በተጨማሪም ኤሊሁ “ ፍፁም እዉቀት ያለዉ ከእኔ ጋር አለ “ አለ (ኢዮ 36፡ 4) ፤ ኤሊሁ ፍፁም እንደ ነበር እየተናገረ ነበር ? ልክ እንደ ኤሊሁ የሚናጓችሁ በህይወታችሁ አሉአችሁ ?
  2. ኤሊሁ እግዚአብሄርን ብትታዘዝና ብታገለግለዉ ሁሉም ዘመንህ በብልፅግናና በደስታ ያልፋል አለው (ኢዮ 36፡ 11) ፤ ይህ ንግግር ትክክል ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልነበረም (ዮሐ 16፡ 33, ሐዋ 14፡ 22, 2ጢሞ 3፡ 12, ዕብ 12፡ 1-11, 1ጴጥ 4፡ 12-13) ?
  3. ኤሊ ኢዮብን ከእግዚአብሄር ከሆነዉ መከራ ይልቅ ታማኝ አለመሆንን መርጠሀል አለው (ኢዮ 36፡ 21) ፤ ያ እዉነት ነበር ? ለምን ወይስ ለምን እዉነት አልነበረም ? “ ስለ እግዚአብሄር በሚናገር “ ሰዉ የተፈረደባችሁ እንደሆናችሁ የተሰማችሁ ጊዜ አለ ? ለምን ወይስ ለምን አልተዳኛችሁም ?
  4. በኢዮብ 36 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 36:21

“Be careful that you do not turn to iniquity, for that is why you have been tested by affliction.”

ኤሊሁ ኢዮብን ለተጨማሪ ትንስ ጊዜ እንድታገሰው በመጠየቅ ስለ ኢዮብ ህይወት መናገሩን ቀጠለ ፡፡ በብዙ መንገድ ኤሊሁ የኢዮብን ክስ ወቀሳ በማስታረቅ መለሰ ፡፡ እውቀትን ከሩቅ ቦታ እንደተቀበለ ሰው ኤሊሁ ኢዮብ በመከራ ውስጥ ሳለ የተለያዩ እውነቶችን ለኢዮብ ህይወት ተናገረ ፡፡ ኤሊሁ ኢዮብ በመከራው ውስጥ ሁኖ ወደ ኃጢአት ፊቱን ከማዞር እንድጠነቀቅ አስጠነቀቀው ፡፡

ወደ ተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ በገባህ ጊዜ በህይወትህ ወደ ኃጢአት ፊትህን ለማዞር ይህ ጊዜው አይደለም ፡፡ በመከራህ ውስጥ የጌታ ፍቃድ እንድትጠራ ደግሞም በትዕግስት ፣ በፈተና እና በተስፋ እንድታድግ ነው ፡፡ በተስፋ ተስፋ አትቁረጥ እናም ኃጢአትን አትምረጥ ፡፡ ህይወት ሲከብድ ወደ አልኮል አትመለስ ከህመምህም ለመሸሽ መጠጣት አትጀምር ፡፡ ህይወት ሲከብድህ እቃ ለመግዛት በመሄድ ብድርን አታከማች ፡፡ በትዳርህ ውስጥ ህይወት ሲከብድብህ የፈረሰውን ለመሸፈን ወደ ሌላ ግንኙነት ዘወር አትበል ፡፡ ይልቁንም ወደ ጌታ ተመለስ ፡፡ በመከራ ውስጥ በተስፋ ጽና ፡፡ ሌላ ነገር ሳይሆን ክርስቶስ ልብህን ያረካል ፡፡ ምንም ነገር ፡፡ ሴት አይደለም ፣ ወንድ አይደለም ፣ መጠጥ አይደለም ፣ መግዛት አይደለም ምንም ነገር ፡፡ ነገር ግን የክርስቶስ ፍቅር እንጅ ፡፡ እስኪገለጥ ድረስ አይኖችህን በኢየሱስ ላይ አድርግ ፡፡ እርሱም ይገለጣል ምክንያቱም ታማኝ ነው ፡፡ ተስፋ እንዳትቆርጥ ፡፡

“ከመከራ ይልቅ ይህን መርጠሃልና ኃጢአትን እንዳትመለከት ተጠንቀቅ ። “ - ኢዮብ 36፡21

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙረ37:24 — “ ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም፥ እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና ። “
  • ሮሜ 5:3–5 — “ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን ፤ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም ። “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 4:1–2 — “ ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም ። ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን ። “