Crying Out
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 34-35 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የኢዮብ ሰዎስት ወዳጆች ከኢዮብ ጋር ከባድ የሆነ ጉዳይ ነበራቸው ፡፡ የኢዮብ የራሱ ኃጢዓት ለደረሰበት መከራ ምክንያት እንደሆነ የወዳጆቹ ተደጋጋሚ ክስ ቢኖርም ኢዮብ የህይወቱን ሁሉንም ስፍራ እንዲፈትኑ፣ ኃጢዓት እንዳላደረገ እንዲያዉቁ ወደ ራሱ ፅድቅ ለማመልከት ወዳጆቹን ጋበዛቸዉ (ኢዮብ 31) ፡፡ በኢዮብ 32 አንድ አዲስ ገፀ ባህሪይ ኤሊሁ የሚባል ብስጭቱን በኢዮብና በወዳጆቹ በሁለቱም ላይ ገለፀ ፡፡ ምዕራፍ 34 እና 35 የኤሊሁ ንግግር መቀጠል ናቸው ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (35፡ 1-2)፡ ኤሊሁ ኢዮብን የራሱን ፅድቅ በማወጅ/በመናገር የእግዚአብሄርን ፍርድ ትክክል ነዉ ወይም አደለም ብሎ በመጠየቁ ትክክል ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ ገጠመዉ/ጠየቀው ፡፡ በመሰረቱ የኤሊሁ ጥያቄ “ ወደ ሁሉን ቻይ ፊት በመምጣት እኔ ፃድቅ ነኝ የሚል ማነው ? “ የሚል ነበር ፤ ኤሊሁ ኢዮብ “ ስነ ምግባራዊ ስርዓቱ ከእግዚአብሄር ይበልጥ እንደ ነበር እየተገበረ “ እንደ ነበር አሰበ በተጨማሪም በመጀመሪያ ቦታ የእግዚአብሄርን ፅድቅ ለመጠየቅ የኢዮብን ህጋዊ/ተገቢ ሁኔታን ጠየቀ ፡፡
ኢዮብ (35፡ 3-7)፡ በቁጥር 3 ኤሊሁ የኢዮብን የቅሬታ የትኩረት ሀሳብ ያጠቃልላል ፤ ኃጢዓትን ማስወገድ ኢዮብን አይጠቅምም ፡፡ ኢዮብ በፍፁም እነዚህን ቃላቶች አላለም ነበር ነገር ግን በንግግሩ ዉስጥ የሀሳቡ ትርጓሜ/አተገባበር ነበሩ ፡፡ ኤሊሁ የኢዮብን የራስ/የግል ፅድቅ ተናገረ ፡፡ የNKJV(አዲሱ ንጉስ ጀምስ እትም) የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት “ እግዚአብሄር ለኢዮብ ለማንኛዉም ስራ ወይም ተግባር በምንም ኃላፊነት ስር አልነበረም ፤ ስለዚህም እግዚአብሄር በፍርድ ፊት ይቅረብ የሚለዉ ፍላጎት ለኢዮብ በእዉነቱ የሚፃረር/ተለዋዋጭ እንደ ነበር “ ይፅፋል ፡፡
ኢዮብ (35፡ 8-14)፡ ኤሊሁ ብዙ ጊዜ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሄር ሲጮሁ ይመለከታል ምክንያቱም ከእነርሱ በሚበልጡ ጥቂት ሰዎች ስለተጨነቁ (ቁጥር 9) ማለትም ኢዮብ በፀሎቱ አክብሮታዊ አልነበረም ፡፡ ማክአርቱር እግዚአብሄር የኢዮብን ፀሎት ያልሰማበትን ሰዎስት ምክንያቶች ያቀርባል፡ ኩራት/ትዕቢት (ቁጥር 10, 12)፣ የተሳሳተ ፍላጎት (ቁጥር 13) እና በመታመን ትዕግስትን ማጣት (ቁጥር 14) ፡፡ ኤሊሁ ማንም እግዚአብሄር የት እንዳለና ሰዎች ስለቀኑ ሲዘምሩ መቼ መልካም ነገሮችን እንደሚሰጥ ማንም እንደማይጠይቅ ያመለክታል ፡፡ ቻርለስ ሱፐርገን “ ፅሁፉን/ማስታወሻዉን በቀን ብርሃን ማንበብ በምንችል ጊዜ ለመዘመር ቀላል ነዉ ፤ ነገር ግን ለማንበብ የፀሀይ ብርሃን ጨረር በሌለበት ጊዜ መዘመር የሚችል ችሎታ ያለዉ ዘማሪ እንደሆነ “ ይፅፋል ፡፡
ኤሊሁ እግዚአብሄር በትዕቢት በተሞላ ጊዜና ከንፁህ ፍላጎት ሲወጣ የአንድን ሰዉ ፀሎት እንደማይመልስ ተከራከረ (ቁጥር 12-13) ፡፡ በኢዮብ በእግዚአብሄር ላይ ትዕግስት የተሞላ መታመን በማጣቱ ምክንያት እግዚአብሄር ኢዮብን ሊመልስለት የተገደደ አልነበረም ፡፡
ኢዮብ ወደ እግዚአብሄር በትህትና፣ በትክክለኛ ፍላጎትና በትዕግስት ቢጮኽ ይህ ለኢዮብ ምን ይመስላል ? በመሰረታዊ የህይወት መርህ ያለ ተቋም ወደ እግዚአብሄር መጮኽን ለመግለፅ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የተጠቀመባቸዉን ቃላትና ሀረጋት ዋና ሀሳብ ይሰጣል፡
- የጥልቅ ጭንቀት ጩኸት፡ “ ዛአቅ “ (በዕብራዊ) ፤ “ በግብፅምሳሉ የአባቶቻችንን መከራ አየህ በኤርትራ ባሕርም ሳሉ ጩኸታቸዉን ሰማህ ፤ እንደ ታበዩባቸዉም አዉቀህ ነበርና በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምልክትና ተአምራት አሳየህ ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስምህን አስጠራህ ፡፡ ከፊታቸዉም ባሕሩን ከፈልህ በባህሩም መካከል በደረቅ አለፉ ፤ ጠላቶቻቸዉን ግን ድንጋይ ለጥልቅ ዉኃ እንዲጣል በቀላይ ዉስጥ ጣልሃቸዉ “ (ነህ 9፡ 9-11) ፡፡ በጥልቅ ጭንቀታቸው እስራኤላዊያን ፊታቸዉን የሚያዞሩበት እግዚአብሄር እንጂ ሌላ ስፍራ አልነበራቸውም ፡፡
ለእርዳታ መጮኽ፡ “ ፀአቅ “ (በዕብራዊ) ፤ “ ሙሴም ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፤ እግዚአብሄርም እንጨትን አሳየው በዉኃዉም ላይ ጣለው ዉኃዉም ጣፈጠ “ (ዘጸ 15፡ 25) ፤ ሙሴ ለእስራኤላዊያን እንዲጠጡት ዉ ለማግኘት ወይም ለመፍጠር ማድረግ የሚችለዉ ምንም ነገር እንዳልነበር ያውቃል ፤ ተስፋ በመቁረጡም ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፡፡
በታላቅ ድምፅ መጥራት፡ “ ቋራ “ (በዕብራዊ)፡ “ ያቤጽም ፡፡ እባክህ መባረክን ባርከኝ አገሬንም አስፋው ፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን ፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ ፤ እግዚአብሄርም የለመነዉን ሰጠው “ (1ዜና 4፡ 10) ፡፡
በጦርነት ጩኸት መጮኽ፡ “ ሩዋ “ (በዕብራዊ) ፤ “ የይሁዳም ሰዎች ጮኹ ፤ የይሁዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እግዚአብሄር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት መታቸው “ (2ዜና 13፡ 15) ፤ ይህ ጩኸት እንደተሰበሰበ ቡድን በአንድ ላይ ተደረገ ፡፡
ስለ እርዳታ መጮኽ፡ “ ሻቫኽ “ (በዕብራዊ)፡ “ ለሚፈሩት ምኞታቸዉን ያደርጋል ልመናቸዉንም ይሰማል ያድናቸዋልም “ (መዝ 145፡ 19) ፡፡
የጥልቅ ጭንቀት ጩኸት፡ “ ፃአቃህ “ (በዕብራዊ)፡ “ ደማቸዉን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና “ (መዝ 9፡ 12) ፡፡
በመጮኽ፡ “ ክራዞ “ (በግሪክ) ፤ “ ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ ፡፡ ጌታ ሆይ አድነኝ ብሎ ጮኸ ፡፡ ወዲያዉም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘዉና ፡፡ አንተ እምነት የጎደለህ ስለምን ተጠራጠርህ ? አለው “ (ማቴ 14፡ 30-31) ፡፡
በጠንካራ ድምፅ መለመን፡ “ ብኦእ “ (በግሪክ) ፤ “ እርሱም ፡፡ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ እያለ ጮኸ ፡፡ በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሰፁት እርሱ ግን የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ ፡፡ ኢየሱስም ቆሞ ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ ፡፡ በቀረበም ጊዜ ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ? ብሎ ጠየቀው፡፡ እርሱም ጌታ ሆይ አይ ዘንድ ነዉ አለው ፡፡ ኢየሱስም እይ እምነትህ አድኖሃል አለው “ (ሉቃ 18፡ 38-42) ፡፡ ይህ ሰዉዬ የኢየሱስ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ለመወሰን አላፈረም/አልተሸማቀቀም ፤ በታላቅና በኃይለኛ ድምፅ ለእርዳታ ኢየሱስን ለመጠየቅ እንዳይከለክለዉ ለኩራቱ/ለትዕቢቱ አልፈቀደም ፡፡
የመሰረታዊ ህይወት መርህ ተቋም ወደ እግዚአብሄር የመጮኽ ባህሪያት ያስቀምጣል፡
እዉነተኛ ትህትና፡ “ ደማቸዉን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና “ (መዝ 9፡ 12) ፡፡
ያልተገደበ መሰጠት፡ “ በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር “ (መዝ 66፡ 18) ፡፡
ስለ ምህረት መለመን፡ “ ያልጠፋነው ከእግዚአብሄር ምሕረት የተነሳ ነው ፤ ርኅራሄው አያልቅምና ፤ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ፤ ታማኝነትህ ባዙ ነው “ (ሰቆ ኤር 3፡ 22-23) ፡፡
ግላዊ ረዳት አለማጣት፡ “ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ ፡፡ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል “ (ዮሐ 15፡ 5) ፡፡
በእግዚአብሄር ምንጭና ኃይል ያለ እምነት፡ “ ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው ጌታ ሆይ አድነን ጠፋን እያሉ አስነሱት ! “ (ማቴ 8፡ 25) ፡፡
ተስፋ መቁረጥ፡ “ በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሄርን ጠራሁት ወደ አምላኬም ጮኽሁ ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮዉ ገባ “ (መዝ 18፡ 6) ፡፡
መደምደሚያ
ኤሊሁ የኢዮብን ኩራት/ትዕቢት፣ የራስ ፅድቅ እና በእግዚአብሄር ላይ እምነት ማጣቱን ተናገረ ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አለመፀለያችንን እንዴት እርግጠኛ ያደርገናል ? ራሳችሁን ፈትኑ፡ በእግዚአብሄር ፊት በመምጣት ማንኛዉንም ነገር ለመጠየቅ መነሳሳታችሁ ምንድን ነው ? ወዳጆቻችሁን/ጎረቤቶቻችሁ እንዲያድናቸዉ ጌታን ጠይቃችሁታል ? ትዳራችሁ እንዲታደስ ማየት ትፈልጋላችሁ ? ልጆቻችሁ በጌታ ሲጓዙ ማየት ትፈልጋላችሁ ?
5 “What Does It Mean to Cry Out to God?”; available at https://iblp.org/questions/what-does-it-mean-cry-out-god.
6 “What Does It Mean to Cry Out to God?”; available at https://iblp.org/questions/what-does-it-mean-cry-out-god.
New King James Version Study Bible, (Nashville: Thomas Nelson, 2014). p. 824; available at https://books.google.com/books?id=h12HBAAAQBAJ&printsec=frontcover&source=gbs_at- b#v=onepage&q&f=false.
New King James Study Bible, p. 824.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 589.
Charles Spurgeon, “Songs in the Night” in The Complete Works of C. H. Spurgeon, v. 44 (Harrington, DE: Delmarva, 2013), available at https://play.google.com/books/reader?id=4bgyC- gAAQBAJ&printsec=frontcover&source=gbs_atb&pg=GBS.PT7.
ጥያቄዎች
-
ኤሊሁ “ ጥበበኞች “ እና እናንተ “ አዋቂዎች “ ብሎ ማንን ጠራ ? (ኢዮ 34፡ 2)
-
ኢዮብን 34 ካነበባችሁ በኋላ ኤሊሁ ለኢዮብ እዉነቱን ነግሮታል ወይስ ትዕቢተኛ ነበር ? ፍርዳችሁ ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ ምን አለ ?
-
በአጠቃላይ በኢዮብ ዉስጥ የኢዮብ ወዳጆች እዉነትን በፍቅር ተናግረዋል ? እርሱን ከማስለቀስ እና እንደ አንድ ሰዉ አስከፊ ችግር ዉስጥ እንደ ነበር ከመናገር ዉጪ ምንም አላደረጉምን ? መፅሀፍ ሌሎችን እንዴት መንከባከብ/መመለክት እንዳለብን ያስተምረናል ? (ማቴ 7፡ 1-6, ሮሜ 12፡ 10, ገላ 5፡ 14, ኤፌ 4፡ 32)
-
በኢዮብ (34-35) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 35:12
“There they cry out, but He does not answer, because of the pride of evil men.”
ኤሊሁ በልቡ ስለከበደው መልዕክት ለኢዮብ መናገሩን ቀጠለ ፡፡ ኤሊሁ የራሱን ምልከታ ተናገረ ፤ በኢዮብ መከራም ውስጥ እግዚአብሔር ዝም ያለበትን ምክንያት አስቀመጠ ፡፡ በኢዮብ ልብ ውስጥም ያየውን ትዕቢት ተቃወመ ፡፡ በኢዮብም ትዕቢት ምክንያት ኢዮብ በጮኸ ጊዜ እግዚአብሔር አንዳልመለሰለት ተናገረ ፡፡
ለራስህ እርዳታ እንደሚያስፈልግህ ታስብ ይሆናል ነገር ግን ከእግዚአብሔር ወይም ከሌሎች እርዳታን አትጠይቅም ፡፡ እርዳታን መጠየቅ ወይም ስለ እርዳታ መጮኽ ድክመትን ያሳያል ብለህ ታምን ይሆናል ወይም ደግሞ ለሆነ ሰው ሀላፊነትን አሳልፌ እስጣለሁ ብለህ ትፈራ ይሆናል ፡፡ ኩራትህን ከመተው ይልቅ ልክ ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ እንደያዝክ ማስመስልን ትመርጣለህ ፡፡ ነገር ግን ጌታ እርዳታን ከእርሱ እንድትጠይቅ ይፈልጋል ፡፡ እርሱ ቀድሞ እርዳታውን እንደምትፈልግ ያውቃል ፡፡ እርሱ እንድትጠይቀው የሚፈልግበት ምክንያት አንተ ራስህን አሳልፈህ መስጠት ወይም መማረክ የምትችለው እርዳታን በመጠየቅ ስለሆነ ነው ፡፡ በመጠየቅ ትሁት መሆንህን ፣ ረዳት የለሽ እንደሆንክ ፣ በእግዚአብሔር ኃይልና ሀብት ላይ እንድሁም ለአሸናፊነት በእግዚአብሔር ላይ ያለህን እምነት ታሳያለህ ፡፡ ለእርዳታ መጮኽ የተለመደ ነው ፡፡ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ለአንተ ነው ፡፡ ይረዳህ ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ልኳል ፡፡ አንተ ይረዳህ ዘንድ የክርስቶስ አካል አለህ ፡፡ ጌታ ስለ እርዳታ ስትጣራ ሊሰማህ ቃል ገብቷል ፡፡ ያድንሀል ደግሞም ከፈተናዎችህ ያስመልጥሀል ፡፡ ዛሬ ልብህን ክፈትና እርዳታን ለማግኘት ተጣራ ፡፡ ጌታ ከአንተ ጋር ነው በትህትናም ያደረከውን የእርዳታ ጥሪ ይመልሳል ፡፡
“በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ትዕቢት ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም ። - ኢዮብ 35፡12
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 34:17 — “ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው ። “
- መዝሙር145:19 — “ ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም ። “
- ዮሐንስ 15:5 — “ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።