Wisdom Books Job

Elihu's Angry Response

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 32-33 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 387 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ የኢዮብ ጥናታችን ከተለያዩ መፅኀፍት እንደሆነ ይሰማናል ፤ ኤልፉዝ ወይም በልዳዶስ ወይም ደግሞ ሶፋር የለም፡፡ በእርግጥ በምዕራፍ 32 ከአዲስ ገፀ ባህሪይ እንሰማለን -ኤሊሁ ከሚባል ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በሁለት ቀን ኤሊሁ ማን እንደ ነበር አንዳንድ አመለካከቶችን ከእናንተ ጋር እንካፈላለን ፡፡ ፓርሰን በአብዛኛዉ በኢዮብ መፅሀፍ እየተካሄደ የነበረዉ ክርክር ላይ ጣልቃ የገባ እንደሚመስል ይገልፃል ፡፡ ኤሊሁ ለመናገር የእግዚአብሄርን(የያህዌን) ስፍራ ላይ የተቀመጠ ነበር ፤ ኤሊሁም እንደ መካከለኛ እያገለገለ እንደነበር ተከሰተ/ተገለጠ (ኢዮብ 36) ፡፡ ኤሊሁ ስለ ራሱ ፅድቅ ንስሀ እንዲገባና በተፈጥሮ ማስረጃ ያለዉን የእግዚአብሄርን ስራ እንዲያስበልጥ ኢዮብን እንዲያበረታታው ስለ ኢዮብ ተጠራ ፡፡ በኢዮብ 37 ኤሊሁ ኢዮብን እግዚአብሄርን የመፍራት ጊዜ እንደ ነበር ነገረው፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (32፡ 1-5)፡ ቁጥር 1 የኢዮብ ወዳጆች ለኢዮብ ምላሽ መስጠት አቁመዉ ነበር ምክንያቱም ለእነርሱ በራሱ የፀደቀ ስለመሰላቸዉ ይላል ፤ ነገር ግን ኤሊሁ ተከሰተ/መጣ፣ በኢዮብም ተበሳጨ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ፋንታ ኢዮብ ራሱን አፅድቆ ስለ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ አራት ጊዜ ፅሁፉ ኤሊሁ ተበሳጭቶ እንደ ነበር ይናገራል - በኢዮብ (ቁጥር 2) እና በኢዮብ ወዳጆች ላይ (ቁጥር 3, 5) ፡፡

ኢዮብ (32፡ 6-22)፡ እነዚህ ቁጥሮች የኤሊሁን የመጀመሪያ ንግግር ይይዛሉ ፡፡ ኤሊሁ ወጣትና በብስለት ከኢዮብ ያነሰ እንደሆነ እዉቅና ሰጠ እናም በዚህ ምንም ነገር ባለማለት ተመልሶ በፍርት ዉስጥ ተይዞ ነበር ፡፡ ኤሊሁ በዚያ ለነበሩትና ከእርሱ ለሚበልጡት አክብሮቱን ገለፀ (ቁጥር 6-7) ፤ በቁጥር (8-10) ኤሊሁ እግዚአብሄር ቃሉን በመለኮታዊነት እንዳነሳሳዉ - ጥበቡም ማስተዋል ከሰጠው “ ሁሉን ከሚችል ከአምላክ እስትንፋስ “ እንደ መጣ እዉቅና ሰጠ ፡፡ ኤሊሁ ጥበብ ከሽማግሌዎች ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር ከመረጣቸዉም እንደሚመጣ አመለከተ ፤ በቁጥር 10 ኤሊሁ አድማጮቹን እንዲሰሙት ይነግራቸዋል - ለሚናገረዉ/ለቃሉ ትኩረት እንዲሰጡ ፤ ይህ ለእነርሱ ከአስሩ ተግሳፅ የመጀመሪያዉ ነበር ፡፡

ኤሊሁ ምንም እንኳን በቀደሙት ምዕራፎች ዉስጥ ባይጠቀስም የሁሉንም የአራቱን (የኢዮብን፣ የኤልፉዝን፣ የበልዳዶስንና የሶፋርን) ንግግር ሲያደምጥ ነበር ፡፡ ለነገራቸዉ የቀረበ ትኩረት የሰጠ ቢሆንም ማንም ኢዮብ ጥፋተኛ እንደ ነበር ሊያሳምነዉ አልቻለም ፡፡ ኤሊሁ ጥበቡ ከእግዚአብሄር እንደ መጣ አብራራ ፤ ኤሊሁ ቅድሞ ክርስቶስ ሊሆን ይችላል ? በሁለት ቀን ዉስጥ ወደዚህ እንመለሳለን ፡፡ የሰዎስቱን ወዳጆች ንግግር ኤሊሁ ይመዝናል (ቁጥር 11-13) ፡፡ በቁጥር (14- 22) ኤሊሁ ገለልተኛነቱን ያሳያል ፡፡ የኢዮብ ወዳጆቹ የተጨነቁና ንግግር የሌላቸዉ ነበሩ (ቁጥር 15) ፡፡ ኤሊሁ የእግዚአብሄርን መልዕክት ለመናገር ተጣደፈ (ቁጥር 16-19)፣ እንዲሁም ደግሞ እንደ ገና የሆነ ነገር የሚናገራቸዉን ሁሉንም ገለልተኛ እንደ ሆነ ቃል ገባላቸው (ቁጥር 20-21) ፡፡ ኤሊሁ ገለልተኛ ባይሆን ኖሮ እግዚአብሄር ለእርሱ ከመናገር ያስወግደዋል/ይከለክለዋል (ቁጥር 22) ፡፡

መደምደሚያ

ፓስተር ጃክ ዌልማን ክርስቲያኖች ዝም ማለት የማይችሉባቸዉን አራት ምክንያቶች ለይቷል፡

  1. ምክንያቱም ንግግር/ቃል አስፈላጊ ስለሆነ (ሮሜ 10፡ 14, 17) ፡፡ ክርስቶስን ለሌሎች ለማሳየት/ለመግለጥ በቂ በሚሆኑ ድርጊቶች ጥሪያችንን በድርጊታችን እና በተስፋችን በኩል ብቻ መኖር አንችልም ፤ ምክንያቱም ስለ እኛ ስላደረገልን ስለ ክርስቶስ “ በመስማት እምነት ስለሚመጣ “ (ሮሜ 10፡ 17) ቃላት/ንግግር አስፈላጊ ነው ፡፡

ምክንያቱም በክርስቶስ ወንጌል የምናፍር መሆን ስለማንችል (ሉቃ 9፡ 26, 12፡ 9፣ ሮሜ 1፡ 16) ፡፡ እምነታችንን ከሌሎች ጋር ለማካፈል የቀረን/የደከምን መሆን ብንችልም ጳዉሎስ “ በወንጌል አላፍርምና ፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሄር ኃይል ለማዳን ነዉና “ (ሮሜ 1፡ 16) በማለት ፅፏል ፡፡

ምክንያቱም መርዳት ባንችልም እንሰብካለን (ኤር 20፡ 9, ሐዋ 4፡ 20, 9፡ 15, 1ቆሮ 9፡ 16) ፡፡ ኤርምያስ ስለ እግዚአብሄር የማይናገር ከሆነ “ በአጥንቶቼ ዉስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ ፤ ደከመሁ መሸከመም አልቻልሁም “ (ኤር 20፡ 9) ፡፡ ኑሮአችንን ስለ እርሱ በመስመር ላይ ለማስቀመጥ ፈቃደኞች ካልሆንን ስለ እኛ ህይወቱን በመስመራችን ላይ ለማስቀመጥ ፍቃደኛ ይሆናል ?

በኢየሱስ ርህራሄ/ቸርነት ምክንያት (ማቴ 28፡ 18-20, ሮሜ 1፡ 14, ራዕ 20፡ 12-15) ፡፡ ኢየሱስ ለእኛ በመስቀል ላይ በቸርነት/በርህራሄ ሞተ - በጥልቅ ፍቅር ! ስለዚህ የማያዉቁትን ለማዳን ኢየሱስ ያደረገዉን ለመናገር/ለማጋራት የመገደድ ስሜት ሊሰማን ይገባል ፡፡ በብዙ ከኢዮብ ወዳጆች ጋር የምንመሳሰል ከሆነ ከሌሎች ጋር ስለ ክርስቶስ አንናገረም ፤ ነገር ግን ክርስቶስ ለእኛ ያደረገልንን ስንቀበል ስላደረገዉ ነገር ዝም ማለት አንችልም !

1 Gregory W. Parsons, “The Structure and Purpose of the Book of Job,” Bibliotheca Sacra 138:550 (April–June 1981), 141; quoted in Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job, p. 81; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

ጥያቄዎች

  1. በኢዮብ 32 ኤሊሁ የሚባል አንድ ሰዉ መናገር ጀመረ ፤ ይህ ሰዉ ከየት ነበር የመጣው ? ሊሆን የሚችለዉን ስዕሉን መቼ አስገባ ?
  2. በኢዮብ 32 ኤሊሁ ወዳጆቹ ኢዮብን ያደረገዉን ስህተት ሳያረጋግጡ በመፍረዳቸዉ ተበሳጭቶ ነበር ወይስ ለእርሱ ምንም መልስ ባለማግኘታቸዉ ፈርቶ ነበር ?
  3. በኢዮ (33፡ 9) ኤሊሁ ኃጢዓት ያልነበረበት እንደሆነ እየገለፀ ነበር ?
  4. ከእኛ እንደሚበልጥ እያወቅን በተለይም ሁሉም እዉነቶች ሳይኖሩን እግዚአብሄር ፍትሀዊ ባለመሆኑ የመክሰስ መብት አለን ? (ኢዮ 33፡ 12-14)
  5. በኢዮብ (32-33) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 32:19–20

“My heart is like unvented wine; it is about to burst like new wineskins. I must speak so that I can find relief; I must open my lips and respond.”

ኢዮብ ለሶስቱ ጓደኞቹ ከመለሰ በኋላ ለኢዮብ መልዕክትን ይዞ አንድ ሌላ ጓደኛ ብቅ አለ ፡፡ ኤሊሁ በኢዮብ ፣ በበልዳዶስ ፣ በኤልፋዝ እና በሶፋር መካከል የነበረውን ሙግት አድምጦ ነበርና የእግዚአብሔር ቃል በውስጡ ዝም ብሎ መቆየት እስከማይችል ድረስ ይናገር ዘንድ አስገደደው ፡፡

እግዚአብሔር ለሌላ ሰው መልእክትን ፣ ቃልን ወይም የሚያነቃቃ ቃልን ከሰጠህ መልእክቱን አውጥተህ ተናገር ፡፡ በየቀኑ ከእንቅልፍህ ስትነሳ በልብህ ተመሳሳይ ሰውና ተመሳሳይ መልእክት ወይም ደግሞ ስለዚያ ነገር ቀኑን ሙሉ ብዙ ጊዜ ስታብ ከዋልክ ያኔ ነው ነገሩን ልትናገረው ወይም ልታወራው እንደሚገባህ የምታውቀው ! ከዚያም ሰው ጋር የምታወራበትን አጋጣሚ እንድሰጥህ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፤ ጌታም ለቃልህ እርግጠኝነትን ግልፅኝነትን እንደሚሰጥ እመን ከዚያም ሂድና አድርገው ! በእርግጥ ይህ ድፍረትን ይጠይቃል ፤ አዎ ይህ ጀግንነትን ይጠይቃል ፡፡ ይህ እምነትን ይጠይቃል ፡፡ ግን ወዳጄ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሆናል ፡፡ ተናገር ፡፡ እግዚአብሔር አንተ የእርሱ አፍ ፣ እቃ እና የምስራቹን በድፍረትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የምትናገር አምባሳደሩ እንደሆንክ ይናገራል ፡፡ በል ዛሬ ተነስና በልብህ ያለውን መልዕክት በፍቅር አድርስ ፡፡

“በተሐ ጠጅ እንደ ተሞላና ሊቀደድ እንደ ቀረበ አቁማዳ፥ ሊፈነዳ እንደማይችል እንደ ወይን ጠጅ
አቁማዳ፥ እነሆ፥ አንጀቴ ሆነ ። ጥቂት እንድተነፍስ እናገራለሁ፤ ከንፈሬን ገልጬ እመልሳለሁ ። “

  • ኢዮብ 32፡19-20

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘጸአት 4:11–12 — “እግዚአብሔርም፦ የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን ? እንግዲህ አሁን ሂድ፥ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፥ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ አለው ። “

2ኛ ቆሮንቶስ 5:20 — “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ። “

2ኛ ጢሞቴዎስ 1:7–8 — “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና ። እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል ፡፡ “