The Case of Innocence
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለኢዮብ መፅሀፍ ሀረጋችን ተስፋ የተገባዉ ተቤዢ ነው፣ ይህም መጥፎ ነገር ቢያገኘንም ችግር እንደሌለዉናበጌታ ላይ በመጣበቅ መጠበቅ እንዳለብን ያሳስበናል ፡፡ ኢዮብ እርዳታዉ ከእግዚአብሄር እንደሚመጣ ጠበቀ ፡፡ ኢዮብ በህይወቱ ስህተት ሊሆኑ በሚችሉ በሁሉም ነገሮች ላይ ሄደ ፤ ይሁን እንጂ ኢዮ (19፡ 25-26) “ እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም ፤ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ በዚያን ጊዜ ከስጋዬ ተለይቼ እግዚአብሄርን እንዳይ አዉቃለሁ “ ይላል ፡፡ በምዕራፍ 31 ስለ ንፁኅነቱ የኢዮብን የመጨረሻ ንግግር እናገኛለን ፤ “ ራስን በመራገም ትክክል ባልሆነ አይነት ንስሀን አደረገ “ ፡፡ ኢዮብ “ እግዚአብሄር ዝም ማለቱ የንፁህነቱ ማረጋገጫ እንደሚሆን አሰበ ፤ ነገር ግን ጥፋተኛ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሄር ጣልቃ በመግባት በእርሱ ላይ ደርሶበት የነበረዉን ቅጣት እንደሚጥለዉ “ አሰበ ፡፡ ዋይርስቤ በኢዮብ ባህሪይ መሰረት ምዕራፉን ይከፋፍለዋል፡ ሰዉዬዉ ኢዮብ (ቁጥር 1-12)፣ አሰሪዉ ኢዮብ (ቁጥር 13-15)፣ ባልነጀራዉ ኢዮብ (ቁጥር 16-23, 29-32)፣ አመስጋኙ/አምላኪዉ ኢዮብ (ቁጥር 24-34) እና ባላደራው ኢዮብ (ቁጥር 38-40) ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (31፡ 1-12)፡ ሰዉዬዉ ኢዮብ፡ ኢዮብ ሰዉ እንደ ሆነ እዉቅና በመስጠት ለወሲብ ፍላጎትም እዉቅና ሰጠ ፤ ነገር ግን ራሱን “ ከምኞት ኃጢዓት “ ለመጠበቅ ከእግዚአብሄር ጋር ኪዳን ማድረጉን አብራራ ፡፡ ምኞት በህይወቱ ጉዳይ አልሆም/አይደለም ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ የኢዮብ መከራ የዉስጠኝ ህይወቱን የመጥረግ ስራን እንዲያደርግ ምክንያት ሆኖት እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ ያዕ (1፡ 13-15) ምኞት ወደ ኃጢዓት ለመሄድ የመጀመሪያዉ እርምጃ እንደሆነ እና ኃጢዓትም ባደገ ጊዜ ወደ ሞት ለመሄድ የመጀመሪያዉ ህይወት እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡ ኔልሰን በኢዮብ 31 የተገኙትን የምኞት እርምጃዎች በመዘርዘር ይቀጥላል፡
- ድንግሊቱን በመመልከት (ቁጥር 1) ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር ስለሚመለከት ከእርሱ የሚደበቀው ኃጢዓት እንደ ማይኖር አመለከተ (ቁጥር 2-4) ፡፡ ኢዮብበእዉነትና በሀቀኝነት ሄዶ እንደ ነበርለማየት እግዚአብሄር ድርጊቱን እንደሚመዝነዉ ተናገረ (ቁጥር 5-6) (ምሳ 11፡ 1, ማቴ 5፡ 28, ዕብ 4፡ 12-13) ፡፡ እንደ አማኝ አሁን ይህን ነገር ለኃጢዓት ምክንያት ከሚሆንብን በፊት ማንፃት ያስፈልገናል ፤ የንስሀም ድርጊት የሚመጣዉ እዚያ ጋር ነው - በዚህ ስፍራ ስለ መዉደቃችን መንገድ የእግዚአብሄርን ንስሀ መጠየቅ፡፡
አይንን ልብ እንዲከተለዉ መፍቀድ (ቁጥር 7) ፡፡ ይህ በሆነ ሰዉ ላይ በዝሙት/በምኞት ከመመልከት በማለፍ ያ ዝሙት/ምኞት ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚደረግ ልብ እንዲያስብ መፍቀድ ማለት ነው ፡፡ ወደ ፍች የሚመራዉ አንዱ ነገር ነው፣ በቤተ ክርስቲያንም እንኳን ጥሩ ነዉ ተብሎ የታዬ ነገርን በልብ እንዴት ለማድረግ ለማሰብ መፍቀድ አንዱ ነው ፡፡
በአንዲት ሴት የተሳበ በመሆን ከዚያም የራስ እንድትሆን በማሴር መፍቀድ (ቁጥር 9) ፡፡ ኢዮብ በዝሙት እንኳን ሄዶ እንደሆንና እንዲሆን ፈደቆ እንደሆነ (ምሳ 6፡ 27-29, ኤፌ 5፡ 3-7, ዕብ 13፡ 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ ለዉጥ/እድገት የተለመደ ወይም ተፈጥሮአዊ እንዳይደል ጠቁሟል ፡፡ የማይወገድ እንደሆነ እናስባለን ነገር ግን ያ እዉነት አይደለም ከባድ የሆነ የስብዕና ዉድቀት ነው ፡፡
ኢዮብ (31፡ 13-15)፡አሰሪዉ ኢዮብ፡ በራሱ ላይ ባለዉ ጥናቱ ኢዮብ ሌሎችን እንዴት እንደተመለከታቸዉ አገልጋዮችንም እንኳን ሳይቀር እንዴት እንደተንከባከባቸዉ ተመለከተ ፡፡ ኢዮብ አገልጋዮቹን ሴቶቹንም ወንዶቹንም ሁለቱንም እንዴት እንደተንከባከበ ራሱን ያለዉድቀት እንደ ተገኘና አንድ ቀን በእግዚአብሄር ፊት በመቆም እንዴት ተንከባክቧቸዉ እንደ ነበር ይዳኛል (ኤፌ 6፡ 9) ፡፡
ኢዮብ (31፡ 16-23, 29-32)፡ባልንጀራዉ ኢዮብ፡ ኢዮብ ሌሎችን ያልረዳበት ወይም አባት የሌላቸዉን ምግብ ያላካፈለበት ጊዜ እንዳልነበር አመለከተ ፡፡
ኢዮብ (31፡ 24-28)፡አምላኪዉ ኢዮብ፡ ኢዮብ እምነቱን በብልፅግናና በገንዘብ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሄር ላይ እንዳስቀመጠ አጋራ ፤ እግዚአብሄርን ብቻ እንጂ ሌላ ምንም ነገር - ጣዖቶችን፣ ጨረቃን ወይም ፀሀይን እንዳላመለከ ተናገረ ፡፡ ከነበር ቅጣቱ ይገባዋል ፤ የኢዮብ ግንዛቤ በአንዱ ህያዉ እግዚአብሄር ብዙ ጣዖቶችን፣ አማልዕክቶች እና የተፈጥሮ አካላት በሚመለከዉ የሁልጊዜ ልምድ አልነበረም ፡፡
ኢዮብ (31፡ 29-37)፡ ኢዮብ አድርጎት የነበረዉን ሁሉንም ነገር ለማመልከት ቀጠለ በዚህም በእግዚአብሄር ፊት ራሱን ፃድቅ ሆኖ ሊያገኘዉ ቻለ ፡፡ በቁጥር 35 ኢዮብ እግዚአብሄርን እንደ “ ባላንጣው “ ጠቅሶታል ፤ ጉዳዩን እንዲሰማለት እግዚአብሄርን ፈለገው ፡፡ ሁላችንም አንድ መካከለኛ ያስፈልገናል ፡፡ ዋይርስቤ “ ኢዮብ እግዚአብሄርን ሰዎስት ነገሮች እንዲሰጠዉ ጠየቀው፡ አንዴ እንዲሰማው፣ ለክሱ መልስ እንዲሰጠዉና ስለ ንፁኅነቱ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሰጠው “ እንደጠየቀ ያመለክታል ፡፡ ኢዮብ ንፁህ ሆኖ ለመገኘት ዝግጁ ስለ ነበር በእግዚአብሄር ተረጋገጠ ፡፡ በራስ በመተማመን ንፁህነቱን ለማረጋገጥ በእግዚአብሄር ፊት ትህትና ያጣበትን ለማሳየት ኢዮብ በጣም ሩቅ ሄደ/መረመረ ፡፡
ኢዮብ (31፡ 38-40)፡ባላደራዉ ኢዮብ፡ ኢዮብ ራሱን የመዘነበትን አንድ የመጨረሻ ስፍራ ጨመረ - እግዚአብሄር የሰጠዉን መሬት/ምድር እንዴት ተንከባክቦ እንደ ነበር ፡፡ እንደ ገና ኢዮብ ስለ ሰራበት ስለ እርሻዉ ወይም ስለ ጭሰኛዉ ከማንኛዉም ክፉ/መጥፎ ነገር ንፁሁ እንደ ነበር ገለፀ ፡፡
1 Michael Brennan Dick, “The Legal Metaphor in Job 31,” Catholic Biblical Quarterly 41 (1979): 42, 47; quoted in Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job, p. 77; avail- able at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.
መደምደሚያ
ኢዮብ ስለ መካከለኛ ጠየቀ በምዕራፍ 32 አንድ ይሰጠዋል ፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ መካከለኛ ከአንድ ወገን አይወግንም ፡፡ ኢየሱስ መካከለኛችን ነው፣ እናም በእርሱ ንግግር/ቋንቋ በእርሱ ፊት ጥፋተኝነታችንን ማሳወቅ አለብን ፡፡
Norman C. Habel, The Book of Job (New York: Cambridge University Press, 1975), p. 164; quoted in Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job, p. 77; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Job (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2004), pp. 63–64.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 635.
Nelson’s Commentary, p. 635.
Nelson’s Commentary, p. 635.
Nelson’s Commentary, p. 635.
Wiersbe, p. 63.
ጥያቄዎች
-
በኢዮ (31: 1) ኢዮብ እንዳደረገው ከአይናችሁ ጋር ኪዳን አድርጋችሁ ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ምን ነበር ረድቷችኋልስ ?
-
ልባችሁን ከመረመራችሁ በኋላ በተሰማዉ ነገር ወዲያዉኑ እግዚአብሄርን እንደ ጠየቀዉ ኢዮብን ትመስላላችሁ ? ወይስ በዚያ ፋንታ ስለ ምህረትና ስለ ይቅርታ ትጠይቃላችሁ ?
-
በቁጥር (26-27) ኢዮብ ስለ ምን ያወራል ? ጸሀይንና ጨረቃን ስለ ማምለክ ሊሆን ይችላል ? በራሳችሁ ህይወት የሐሰት ጣዖቶችን ስታመልኩ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ምንድን ናቸው ?
-
በኢዮብ 31 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 31:4
“Does He not see my ways and number all my steps?”
ኢዮብ ከሌሎች ጋር በነበረው ግንኙነት በቅንነትና በጽድቅ እንደተመላለሰ ያምን ነበር ፡፡ ኢዮብም በእግዚአብሔር ፊት ምንም መተላለፍ ያልፈጸመባቸውን እያንዳንዶቹን አጋጣሚዎች ተራ በተራ ዘረዘራቸው ፡፡ የኃጢአት ህይወትን ኑሮ ቢሆን ኖሮ እንድሁም በሴሰኝነት መንገድ ተመላልሶ ቢሆን ኖሮ ፤ ለድሆች ሳይሰጥ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ ወይም ልብስ ለሚፈልገው ሰው ሳያለብስ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ ፤ እምነቱን በወርቅ ላይ ጥሎ ደግሞም በሀብቱ ተደስቶ ቢሆን ኖሮ ፤ ምናልባትም ልቡ በሌላ መንገድ ኮብልሎ ሄዶ ቢሆን ኖሮ ኢዮብ ውጤቱን ለመቀበል ፈቃደኛ ይሆን ነበር ፡፡ ክሱን ለመቀበል ፈቃደኛ ይሆን ነበር ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሔር መንገዱን እንደሚያይ እርምጃውንም እንደሚቆጥር ተገነዘበ ፡፡ ኢዮብ በውሸት መንገድ ተመላልሶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥም እግዚአብሔር ያውቅ ነበር ፡፡
እያንዳንዱን የህይወትህን ክፍል በእግዚአብሔር ፊት መግለጥ ትችላለህ ? ልትደብቀው ወይም ልትሸፍነው የምትፈልገው አንድ ወይም ሁለት የህይወት ገጽ አለ ይሆን ? ነገሩ ወድህ ነው እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ያያል ፤ እርሱ ሁሉንም ያውቃል ፡፡ ከእግዚአብሔር ልትደብቀው የምትችለው ምንም ነገር የለም ስለዚህ አትልፋ ፡፡ ምንም እንኳ እግዚአብሔር ስለ ህይወትህ ሁሉንም ነገር ቢያውቅም ነገሩ ምንም ቢሆን እርሱ እንደሚወድህ በአምሮህ ልትረዳ እና በልብህ ልታምን ያስፈልግሀል ፡፡ መውደድ ብቻ አይደለም ነገር ግን የእርሱ ጸጋ ደግሞ ኃጢአትህን ፣ በደልህን እና ኃፍረትህን ይሸፍናል ፡፡ አንተ ነጻ እንድትሆን ክርስቶስ ሞቶልሀል ፡፡ የኃጢአትህን ሸክም መሸክም አይገባህም ፡፡ ተሰርቷል ፡፡ የእግዚብሔር ልጅ ሆይ ጌታ በነጻነት እንድትመላለስ ይፈልጋል ፡፡ የእግዚአብሔርን ጸጋና ምህረት ተቀበል እናም ሁሉንም የህይወትህን ገጾች ለእርሱ ግለጽለት ፡፡
“መንገዴን አያይምን ? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን ? “ - ኢዮብ 31፡4
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 5:21 — “ የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና ። “
- ሮሜ 6:22 — “አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው ። “
- ዕብራውያን 4:13 — “ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።