Wisdom Books Job

Stormy Skies

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 30 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 385 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኢዮብ በጥንካሬ በእምነቱ ፀና ፡፡ ይህ ምዕራፍ በጥልቅ እየተሰማዉ የነበረዉን ብዙ ነገር የሚገልፅበት ስለ ኢዮብ መጨረሻ ንግግር መካከል ሀሳብ ላይ ነው ፤ በዚህ ምክንያት የዛሬዉ ምዕራፍ ንግግር በጥቂቱ የሚያስጨንቅ ነው ፡፡ ኢዮብ በፊት ደርሶበት ስለ ነበረዉ መልካም ነገር ምላሽ ከሰጠ በኋላ የንግግሩን ይህን አካል “ አሁን ግን “ (ቁጥር 1) በሚል ቁልፍ ንግግር ጀመረ ፡፡ ኢዮብን የገጠመዉ ሁሉም ከዉጪ የሆኑት መቅሰፍቶች የአስተሳሰብ ሁኔታዎችን ማጥቃት ጀምረዉ ነበር ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (30፡ 1-15)፡ ኢዮብ ክብሩን በማጣቱ ላይ ያስገነዝባል ፤ በህይወቱ የተቀመጠበት ስፍራ የተከበረ ከሆነበት ስፍራ በአመድ ስፍራ ላይ እንደ ተቀመጠ አንድ ሰዉ ተቀይሮ ነበር ፡፡ ማክኔን “ ከራሱ ከክርስቶስ ዉጪ ከኢዮብ በላይ ከታላቅ ዝና መዉደቅ ማንም እንዳልገጠመዉ ፤ በምሳሌነትም ከከተማዋ ቅጥር ዉጪ በአፈርና በአመድ ዉስጥ ለመጣል (ኢዮ 30፡ 19) ከከተማዋ በር ምርጥ መቀመጫ ላይ (ኢዮ 29፡ 7) እና ከአለቃ ወንበር ላይ (ኢዮብ 29፡ 25) ወረደ ፡፡ በማወደስ በፊቱ በዝምታ ይወድቁ የነበሩት ጎበዛዝቶች (ኢዮ 29፡ 8-9) አሁን በተናቁ ሰዎች ስብስብ በመናቅ የተተኩ ነበሩ (ኢዮ 30፡ 1) ፡፡ ይልቁንም በእድሜ ትልቆች በማክበር ቆሙ፣ አለቆችም ዝም አሉ፣ ታላላቆችም በፊቱ ተንሾካሾኩ (ኢዮ 29፡ 8-10)፣ ኢዮብ ጀሌ ከሆነዉ ህዝብ የመዘለፍ ነገር የደረሰበት እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ በምዕራፍ 30 የተገለጣ የኢዮብ መከራ/ችግር በጌተሰማኒ አትክልት ስፍራ እስከ መስቀል ድረስ ባለዉ ጊዜ መካከለ ኢየሱስ ከገጠመዉ ጋር ይመሳሰላል ፡፡

ኢዮብ ቀድሞ ያከብሩት የነበሩትን ነገር ግን አሁን ይዘልፉት የነበሩትን እነዚህን ክብር የማያዉቁ ሰዎችን በጥልቅ ወደ መግለፅ ሄደ (ቁጥር 2-8) ፡፡ ቀድሞ ኢዮብየተጠቀመባቸዉ ጉልበት አልነበረዉም - ለራሳቸዉ ፍላጎት ማሟላት አይችሉም ነበር፣ ለምግባቸዉ ከቆሻሻ ቦታ ለቀሙ፣ እንደ ሌባ ይታዩ ነበር፣ ቋሚ ቤት የላቸዉም ነበር፣ ለራሳቸዉ ስም እያላቸዉ እንኳን ልክ እንደ አህዮች ይናገሩና ይተገብሩ ነበር እንዲሁም ማህበረሰቡን እንዲለቁ ተገደዱ ፡፡ እነዚህ በእዉነትም የኢዮብ ማህበረሰብ ቆሻሻዎች/አተላዎች ነበሩ እናም አሁን በእርሱ ላይ ተናገሩ ፡፡

እነዚህ ሰዎች ኢዮብን በሚያሳዩት አለማክበር አሁን በጣም ደፋር ነበሩ (ቁጥር 9-15) ፤ ስለ ኢዮብ የሚያስቀይም መዝሙር ዘመሩ ፤ ከእርሱ ርቀዉ በመቀመጥ እንደ እርኩስ ቆጠሩት/ተመለከቱት ፤ በፊቱም ላይ ተፉበት ፡፡

ሰዎቹ ኢዮብን ስለተመለከቱበት መንገድ ኢዮብ እግዚአብሄርን ከሰሰ/ጥያቄ አቀረበ፡ “ የቀስቴን አዉታር አላልቶብኛል አዋርዶኝማል ፤ እነርሱም በፊቴ ልጓማቸዉን ፈትተዋል “ (ቁጥር 11) ፡፡ ይህ አሳብ ለኢዮብ የሚያደክም ነበር ፤ ሁሉም ጥንካሬዉ ከእርሱ ተወሰደ ፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች እንዴት እርሱን የተመለከቱበትን መንገድ ለመግለፅ ኢዮብ እንደ ምርኮና ጦርነት ስዕል ተጠቅሞበታል (ቁጥር 12) ፡፡ በሁሉም ነገር ላይ ኢዮብ ሽብርን/ድንጋጤን አዬ ፤ በሀይለኛ ንፋስ እንደ ሚወሰድ ክብሩ ከእርሱ መወሰዱን አዬ (ቁጥር 15) ፡፡ “ በምት ጥላ መካከል ብሄድ “ (መዝሙር 23) ተብሎ መገለፀ በሚችለዉ በዚህ አይነቱ ችግር መካከል ላይ እያለ እንኳን እግዚአብሄር ከኢዮብ ጋር ነበር ፤ ነገር ግንመከራዉ/ችግሩ አላቆመለትም ነበር ፤ ዉርደቱም አልተፈፀመም/አላበቃም ፡፡

ኢዮብ (30፡ 16-19)፡ የአካላዊ መከራዉ/ስቃዩ በኢዮብ ላይ ሀዘንን አመጣ ፤ ኢዮብ በእያንዳንዷ ሁሉም ነገር ህመምን አዉቋል ፤ ምንጩ ሁሉ አልቆበታል ፤ በምሽትና በቀን የሚቆረጣጥም/ከባድ የሆነ ህመም ደርሶበታል ፡፡ ኢዮብ ልብሱ “ ከታላቁ ደዌ ኃይል የተነሳ ልብሴ ተበላሸች ፤ እንደ ቀሚስም ክሳድ አነቀችኝ “ በማለት ተናግሯል (ቁጥር 18) ፡፡ ኢዮብ በማታ ከትኩሳት የደረሰበትን መከራዎች እያመለከተ ሲሆን ነገር ግን ኢዮብ በመጨረሻም በግልፅ ስለ መከራዎቹ እግዚአብሄርን ተጠያቂ ለማድረግ ያዘጋጀው ነው ፡፡ በእነዚህ ቁጥሮች ኢዮብ የወደቀበትን ከፍታ ሲያስታዉስ በስድብና በእዉነት መካከል ተጓዘ ፡፡ ኢዮብ ወደ እርሱ ስለ እግዚአብሄር የሚያሳምነው ሀሳብ ምንም ገለፃ አልነበረዉም ፤ ኢዮብ እንዳልተቀየረ ተሰምቶት ስለ ነበር እግዚአብሄር ደግሞ እንደ ተቀየረ ተሰማው ፤ ኢዮብ በትክክል ጠላቱ ማን እንደ ነበር አላወቀም ፡፡

ኢዮብ (30፡ 20-23)፡ ኢዮብ እግዚአብሄር እርሱን እንዴት አድርጎት እንደ ነበር የተሰማውንለመግለፅ ብዙ ስዕሎችን አስቀመጠ ፡፡ ጩኸቱን ለመስማት እግዚአብሄር እንደተወዉና ቅሬታዉን ለማቅረብ መቆሙን እንደገፋዉ ተሰማው (ቁጥር 20) ፤ እግዚአብሄር በእርሱ ላይ እንደተነሳበትና ጠላቱ እንደሆነ ተሰማው (ቁጥር 21) ፤ እግዚአብሄር በንፋስ ላይ እንደ በተነዉ ተሰማው (ቁጥር 22) ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር ወደ ሞቱ እየመራዉ እንደ ነበር ተሰማው (ቁጥር 23) ፡፡

ኢዮብ (30፡ 24-31)፡ ኢዮብ የተሰማዉን በትክክል እየገለፀ የእግዚአብሄርን ርህራሄ/ቸርነት ጠየቀ ፡፡ ኢዮብ ሰዎች “ በአንድ በወደቀ ሰዉ ላይ…. ስለ ጭንቀቱ ሲሉ “ (ቁጥር 24) እንደ ማይፈርዱበት አመለከተ ፡፡ ልክ እንደ ኢዮብ አይነቶቹ ላይ እግዚአብሄር ምን ያክል ይራራላቸዋል ? ኢዮብ “ በችግር ጊዜ ወድቀዉ ለነበሩት “ እና ለድሆች (ቁጥር 25) ርህራሄን አሳይቶ እንደ ነበር ጠቆመ ፤ ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር አሁን ከላይ ወደታች እንደ ተገለባበጠ ተሰማዉ፡ “ በጎነትን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ ነገር መጣችብኝ “ (ቁጥር 26) ፡፡ ሆዱ በጣም ስለተመሰቃቀለ ማረፍ አልቻለም ፡፡ ቆዳው “ ጠቆረ ነገር ግን በፅሀይ አልነበረም “ (ቁጥር 28) ፤ ከከተማ ዉጪ ከዱር እንስሳት ጋር ኖረ (ቁጥር 29) ፤ አካላዊ ቁስል ወደ መባስ ቀጠለ (ቁጥር 30) ፡፡

የኢዮብ ዉርደት በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የሚበለጥ ነበር ፤ ኢሳያስ የክርስቶስን መከራ “ የተናቀ ከሰዉም የተጠላ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያዉቅ ነው ፤ ሰዉም ፊቱን እንደሚሰዉርበት የተናቀ ነው እኛም አላከበርነዉም “ (ኢሳ 53፡ 3) በማለት በዚህ መንገድ አሳይቷል ፡፡ ኢዮብ ጥበብ በተሞላበት መንገድ የእድሉ መገልበጥን በሚያዉቃቸዉ መሳሪያዎች ሀዘኑንና ለቅሶዉን በማዜም አጠቃለለ (ቁጥር 31) ፡፡

መደምደሚያ

ንፋስና የህይወት ጥፋቶች ሁሉንም ነገር መለወጥ ይችላሉ ፡፡ በህይወታችን ዉስጥ ይህን እንዲሰራዉ ለእግዚአብሄር የፀናን መሆን አለብን ፡፡ የኢዮብ መከራ/ስቃይ የክርስቶስ መከራ ጥላ በመሆን ያሳያል ነገር ግን እግዚአብሄር ከሁለቱም ስቃዮች/መከራዎች ይበልጥ ነበር ፡፡

“ ሞት ቢሆን ሕይወትም ቢሆን መላእክትም ቢሆኑ ግዛትም ቢሆን ያለዉም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሄር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ “ (ሮሜ 8፡ 38-39) ፡፡

  1. David L. McKenna, The Preacher’s Commentary: Job, v. 12 (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1986), n. pp.180, 208; available https://books.google.com/books?id=c0kc4XPPjHkC&p-g=PT1&dq=the+preacher%27s+commentary+job&hl=en&sa=X&ved=0ahUKEwjj9K7E_MTfAhVGLKwKHRBdDrQQ6AEILTAB#v=onepage&q&f=false on 1/1/19.

ጥያቄዎች

  1. ኢዮብ “ አክታቸዉንም በፊቴ መትፋትን አልተዉም “ አለ (ቁጥር 10) ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ ሌላ የት ላይ የሆነ ሰዉ በፊት ላይ እንደተፋ እናገኛለን (ማቴ 26፡ 67, ማር 14፡ 65) ? ምን እየተካሄደ ነበር ?
  2. ኢዮብ በወቅቱ በግልፅ በሚያስጨንቅ ሁኔታ ዉስጥ ነበር ፤ ኢዮብ “ ወደ አንተ ጮኽሁ አልመለስህልኝም ፤ ተነሳሁ አልተመለከትኸኝም “ አለ (ቁጥር 20) ፡፡ በህይወታችሁ በጥልቅ ጭንቀት ዉስጥ በነበራችሁ ጊዜ እግዚአብሄር ጀርባዉን እንዳዞረባችሁ የተሰማችሁ ጊዜ አለ ? አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር ለምን ጀርባዉንያዞረባችሁ ይመስላችኋል ?
  3. ኢዮብ ገጥሞት የነበረዉ አካላዊ ህመም በጣም ኃይለኛ ነበር (ቁጥር 16-18, 27-30) ፤ እግዚአብሄር በእርሱ ላይ ጀርባዉን አዞሮበት እንደነበር ኢዮብ እንዴት ሊያስብ ቻለ ?
  4. በኢዮብ 30 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 30:17–18

“Night pierces my bones, but my gnawing pains never rest. My clothing is distorted with great force; He chokes me by the neck of my garment.”

ኢዮብ በመከራው ጸና ፤ ነገር ግን አሁንም ስቃዩን ፣ ህመሙንና ከማህበረሰቡ የሚደርስበትን መሳለቂያነት ይገልጽ ነበር ፡፡ አካላዊ ህመሙም አላበቃም ነበር ቀንና ሌሊትም ይቆረጣጥመው ነበር ፡፡ ፤ ምንም እንኳ በሚሞትበት አልጋ ላይ እያጣጣረ ቢሆንም አሁንም ግን ኢዮብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደነበር እንድሁም እርሱ እንደሚመራው ያውቅ ነበር ፡፡ ኢዮብ በህያው ተቤዥ ተስፋን አገኘ ፡፡

ዛሬ ይህን መስማት ያስፈልግህ ይሆናል ብቻህን አይደለህም ፤ እንዴት አድርጎ የሆነ ሰው ከባድ ህመምን ቀንና ለሊት ሊቋቋም ይችላል ፡፡ ታመህ ይሆናል ቃላት እንኳ ሊገልጹት በማይሞክሩት አካላዊ ህመም ፡፡ ከሞትም ውጭ የሆነ መጨረሻ ላይታይህ ይችላል ፡፡ ቀኖቹ ከባድ ናቸው ለሊቶቹም ከቀኖቹ አይለዩም ፡፡ ልክ ኢዮብ ይህንን ህመም እንደሚያውቀው ሁሉ አዳኝህ ኢየሱስ ክርስቶስም እርሱም እንድሁ ይህንን ከባድ ስቃይ ተሰቃይቷል ፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ናቁትና አዋረዱት ፡፡ ሰዎች ጀርባቸውን ሰጥተውታል አቃለውታል ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በመከራ ውስጥ ሁኖ በተስፋ የሚያልፍበት ምንም ይሁን ነገር ግን ምንም ነገር ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየው እንደማይችል ተናገረ ፡፡ ስለዚህ ዛሬ በመከራ ውስጥ ሆነህ ብቻህን የሆንክ ቢመስልም ነገር ግን በልብህ ብቻህን እንዳልሆንክ ተገንዘብ ፡፡ ሌሎችም ይህን ህመም እየታመሙ ነው ፡፡ በዚህ ተስፋ ላይ ተጣበቅ ምንም ነገር ፈጽሞ ከክርስቶስ ሊለይህ እንደማይችል ፡፡ ውድ ጓደኛዬ በመከራ ውስጥ ሆነህ እግዚአብሔር ያይሀል ፡፡

“በሌሊት አጥንቴ በደዌ ተነደለች፥ ጅማቶቼም አያርፉም ። ከታላቁ ደዌ ኃይል የተነሣ ልብሴ ተበላሸች
እንደ ቀሚስ ክሳድ አነቀችኝ ። “

  • ኢዮብ 30፡17-18

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢዮብ19:25–26—“ እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም ፥ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ ። “

ኢሳይያስ 53:3 — “ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም ። “

ሮሜ 8:38–39 — “ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ ። “