The Mystery of Wisdom
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 28-29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዛሬዉ ምዕራፍ ኢዮብ በእርሱ ላይ ምን ሆኖበት እንደ ነበርና እንዴት ወዳጆቹ መልሰዉለት እንደ ነበር በሁለቱም መታገሉን ቀጠለ ፡፡ የኢዮብ ምላሽ ወዳጆቹ ብለዉት ለነበሩት ነገሮችና ስለ ህይወት ተፈጥሮና መከራ አጠቃላይ ህይወት ስለ ሁለቱም የተወሰነ ነበር ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (28፡ 1-11)፡ ኢዮብ ከምድር ዉድ የሆኑ ብረቶችን ብርን፣ መዳብን፣ ወርቅንና ብረትን በማካተት ከመሬት የሚገኙበትን ሂደት ገለጸ ፤ የሰዉ ልጅ ከምድር በታች ያሉትን የሚያስፈልጉትን እቃዎች/ነገሮች ለማዉጣት በእዉቀት እንደ በለፀገ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ በሂደቱ ሌሎች ፍጥረት ያልሄዱበትንና በፍፁም ያልታዩበትን ስፍራ ላይ ሄደም ተጓዘም ፡፡ የሰዉ ልጅ እዉቀት “ ከድንጋይ ዉስጥ መንዶልዶያ በመዉቀር “ (ቁጥር 10) እና “ ፈሳሹ እንዳይንጠባጠብ በመገደብ “ (ቁጥር 11) በጣም ያደገ ነው ፡፡
ኢዮብ (28፡ 12-19)፡ ብልህነታቸዉንና ችሎታቸዉን ያሳዩትን ብዙ የሰዉ ልጅ ቴክኖሎጂ መሻሻሎችን ከተመለከተ በኋላ ኢዮብ የሚጠቁም/የሚያመለክት ጥያቄ፡ “ ነገር ግን ጥበብ የምትገኘዉ ወዴት ነዉ ? “ (ቁጥር 12) በማለት ይጠይቃል ፤ ኢዮብ ጥበብ በዉቅያኖስ ወይም በባህር ዉስጥ ሊገኝ እንደማይችል አመለከተ ፡፡ ጥበብ በወርቅ ወይም በብር ሊገዛ አይችልም ፤ ጥበብ ከማንኛዉም ዉድ ድንጋይ፡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመርገድ፣ ከሰንፔር፣ ከዛጎል፣ ከእምነበረድ፣ ከሸክኒት ወይም ከዕንቁ በጣም የከበረ ነበር ፡፡
ኢዮብ (28፡ 20-28)፡ የብዙ አይነት የከበሩ እቃዎችን ምንጭና በከበሩ ድንጋዮች ላይ ያለዉን የጥበብን ዋጋ በደንብ በማብራራት ካመለከተ በኋላ ኢዮብ እንደ ገና “ እንግዲያስ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች፣ የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው ? “ (ቁጥር 20) በማለት ጠየቀ ፡፡ ኢዮብ ጥበብ “ ከሕያዋን ሁሉ ዓይን ተሰዉራለች “ (ቁጥር 21)፣ ጣፋትና ሞትም ስለ ጥበብ ምንጭ መስማታቸዉን ፃፈ ፡፡
ሰዉ የሚያዉቃቸዉን ሁሉንም ነገሮች በጥንቃቄ ከዘረዘረ በኋላ ከዉድ እቃዎች በላይ ጥበብ ምን ያክል ዋጋዉ እንደሚበልጠው እና የጥበብን መደበቅ አጉልቶ በማሳየት ኢዮብ “ እግዚአብሄር መንገድዋን ያስተዉላል እርሱም ስፍራዋን ያዉቃል “ (ቁጥር 23) በማለት ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄር አለምን በመፍጠር ልክ እንደ ንፋስ፣ እንደ ዝናብ እና እንደ ብርሃን አይነት ሂደቶቹን ገደብ ባደረገላቸዉ ጊዜ ጥበብን መሰረተ ፡፡ እግዚአብሄር ጥበብን ስለመሰረተ ኢዮብ “ እነሆ እግዚአብሄርን መፍራት ጥበብ ነዉ ፤ ከኃጢዓትም መራቅ ማስተዋል ነው “ (ቁጥር 28) በማለት አጠቃለለ ፡፡ የእግዚአብሄርን መንገድ ማወቅ እግዚአብሄርን ከመፍራት ጋር እኩልና ጥበብ የሚገኝበት ነበር ፡፡ አንድን ሰዉ ከክፉ ነገር እንዲመለስ የሚያደርጉትን ነገሮች ማስተዋል እግዚአብሄርን የመፍራት ምላሽ ነበር ፡፡
“ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ የፈቃዱን ምስጢር አስታዉቆናልና ፤ በዘመን ፍፃሜ ይደረግ ዘንድ ያለዉ አሳቡም በሰማይና በምድር ያለዉን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው “ (ኤፌ 1፡ 9-10) ፡፡ ኢዮብ, ኤልፉዝ, በልዳዶስ እና ሶፋር ሁሉም “ የፍቃዱ ሚስጥር “ ምን እንደ ነበር ለመሳል ሞከሩ ፡፡
“ አስቀድሜ በአጭሩ እንደ ፃፍሁ ይህን ምስጢር በመግለጥ አስታወቀኝ ፤ ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምስጢር እንዴት እንደማስተዉል ልትመለከቱ ትችላላችሁ ፤ ይህም አሕዛብ አብረዉ እንዲወርሱ በአንድ አካልም አብረዉ እንዲሆኑ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎች ትዉልዶች ዘንድ ለሰዉ ልጆች አልታወቀም “ (ኤፌ 3፡ 3-5) ፡፡ ኢዮብና ወዳጆቹ ሙሉ ባልሆነ መገለጥ ታገሉ ፤ በዚያን ጊዜ መጥቶ ስላልነበር ስለ ክርስቶስ ሙሉ እዉቀት አልነበራቸዉም ፡፡
“ ፍለጋ የሌለዉን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሄር ከዘላለም የተሰወረው የምስጢር ስርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ “ (ኤፌ 3፡ 8-9) ፡፡ ኢዮብ ስለ ተፈጠረዉ አለም በብዙ ተረድቷል ነገር ግን የእግዚአብሄርን ዉስብስብነት ለመረዳት ታገለ በተለይም ከመለኮታዊ ፍትህ አንፃር ፡፡
“ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለዉ ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ስቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ “ (ሮሜ 8፡ 18) ፤ ይህ ኢዮብ ያጣዉ አመለካከት ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በህይወቱ መከራ ቢደርስበትም የደረሰበትን መከራ ተራ የሚያደርግ ክብር የሚቀበልበት ቀን እንዳለ ተረድቷል ፡፡
“ እግዚአብሄርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናዉቃለን “ (ሮሜ 8፡ 28) ፤ ኢዮብና ወዳጆቹ በዚህ ተፈተኑ ምክንያቱም ይህ በጊዜዉ ስላልተገለጠ ፡፡ በሰዉ ምክንያት የኢዮብን ችግር በማሰላሰል/በማቅረብ መረዳታቸዉ ገደብ ላይ ደረሱ ፤ የእግዚአብሄርን መንግስትና በምድራዊ ሰዉነት ግንኙነቱን ለመረዳት በራሳቸዉ መንገድ ለማቅረብ አልቻሉም ፡፡
እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር አዲስ ያደርገዋል ፤ ተመልሶ በመምጣት ሁሉንም ነገር ይመልሰዋል ፡፡ ከእግዚአብሄር አመለካከት አንፃር ነገሮችን መመልከት ስንችል በትክክለኛው መንገድ እንመለከታቸዋለን ፡፡ ሁኔታዎቻችንን ከእግዚአብሄር እይታ አንፃር ስንመለከተው ብንሞት እንኳን እንደ ገና በክብር ከእርሱ ጋር እንደምንሆን እንረዳለን ፤ ሁኔታዎቻችንን ከእግዚአብሄር እይታ አንፃር ስንመለከተው ሁሉንም ነገር ለመልካም እንደሰራዉና የወደፊት ክብር ከአሁኑ ችግር በብዙ እንደሚበልጥ እንረዳለን ፡፡ ነገር ግን ኢዮብ ሙሉ ለሙሉ እነዚህን ሀሳቦች አልተረዳቸዉም ፡፡
ኢዮብ (29፡ 1-25)፡ ኢዮብ ነገሮች እንዲሆኑ ለተጠቀመበት መንገድ ሀዘኑን ይገልፃል ፤ በቀድሞ/በፊት የእግዚአብሄር ጓደኝነት ተሰምቶታል (ቁጥር 4-5)፣ አሁንም የራሱ ልጆች ነበሩት (ቁጥር 5)፣ የስልጣን ስፍራ ነበረው (ቁጥር 7)፣ ታላቅ ጥበብ እንዳለዉ ያስብ ነበር (ቁጥር 8-11) እና ስለ ፍትህ ድሆችንና የተጨቆኑትን ረዳ (ቁጥር 12-17) ፡፡ በስቃዩ መካከል ላይ ኢዮብ እግዚአብሄር በህይወቱ ስፍራ እንደ ነበረዉ ያውቃል ፡፡ የተንከራተተ መሰለ “ እግዚአብሄርን ማገልገለ በዚህ ልክ ለምን አስቸጋሪ ይሆናል ? “
መደምደሚያ
ለጌታ ለመኖርና እንደ ቃሉ ለመኖር ምርጫን ባደረግን ጊዜ ከአንዳንድ ነገሮች ተለይተናል ፤ ነገር ግን ያን ተመሳሳይ ምርጫ በእምነት ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸዉ ከሌሎች ጋር በመቀላቀል አዲስ ንብረት የሆነን ስፍራ እናገኛለን ፡፡
ጥያቄዎች
-
ኢዮብ ምዕራፍ 28 ስለ ምድራዊ ኃብት በማዉራትና እንዴት አንድ ሰዉ እንደሚያገኘዉ ለምን እንደ ጀመረ ምን ታስባላችሁ ? ከዉድ ብረት ወይም ጌጣ ጌጥ ምን እንደሚበልጥ ተናገረ ?
-
ሰዉ እንዴት ጥበብን ያገኛል (ምሳ 2፡ 6, ያዕ 1፡ 5) ? መፅሀፍ ቅዱስ ስለዚህ ምን ይላል ? (ኢዮ 12፡ 12, ምሳ 8፡ 11, ያዕ 3፡ 17)
-
በምዕራፍ 28 እግዚአብሄር ጥበብን እንዴት ገለፀዉ ? እግዚአብሄርን ስለ ጥበብ ጠይቃችሁት ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ሁኔታዉን እንዴት አገዛችሁ ?
-
ኢዮብ (29፡ 7-17) አንብቡ ፤ ይህ ፅሁፍ ስለ ኢዮብ ባህሪይ ምን ያስተምራችኋል ? በማህበረሰቡ ዉስጥ ስፍራዉንስ ? ኢዮብ የስልጣን ስፍራ መያዝ ቀላል ነው ?
-
ኢዮብ 29 ኢየሱስን እንደ ጌታና አዳኝ እንዴት ያመላክታል/ጥላ ይሆናል ? (ኢሳ 61፡ 2-3, ማቴ 5፡ 4, 11፡ 4-5)
-
በኢዮብ (28-29) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 28:12, 27–28
“Where then does wisdom come from, and where is understanding located . . . He considered wisdom and evaluated it; He established it and examined it. He said to mankind, ‘The fear of the Lord is this: wisdom. And to turn from evil is understanding.’”
ኢዮብ ይህን ጥያቄ ጠየቀ “ ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው ? “ በውቅያኖስ ጥልቀት አትገኝም ፡፡ በወርቅ ፣ በብር ፣ በውድ አልማዝ ፣ በሰንፔር ፣ በዛጎል ወይም ደግሞ በእምነ በረድ አትለወጥም ፡፡ ጥበብ አለም ከሚሰጠው ሀብት ሁሉ በላይ ናት ፡፡ ኢዮብ የጥበብ ምንጭ የሚገኘው ሁሉን በሚያይና በሚያውቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እንሆነ የውቅ ነበር ፡፡
ልክ እንደ ኢዮብ አንተም ራስህን ትጠይቅ ይሆናል ፡- ጥበብ ምንድን ነው ከየትስ ይመጣል ? የአግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ደግሞም ከኃጢአት መራቅ ማስተዋል እንደሆነ ይናገራል ፡፡ ከመፅሀፍት ውስጥ መፈለግ ትችላለህ ፣ ከድህረ ገጽ ወይም ደግሞ የአማካሪህንም ምክር ልትሻ ትችላለህ ነገር ግን ፍጹም ጥበብ የሚገኘው እግዚአብሔርን ከመፍራት ነው ፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት ማለት እርሱ ስለ ሚሰራው ስራ ስለ ችሎታው ሁሉ የሚታይ አክብሮትን መስጠት እንድሁም እርሱ የአለምን ሚስጥራት ሁሉ በአንድ አድርጎ እንደያዘ ማመን ነው ፡፡ በእግዚአብሔር መንገድ ስትሄድ ክፋትንና ተግዳሮትን ተቃወም ፤ በማስተዋልም ተገለጥ ፡፡ እግዚአብሔር ከአለም ነገሮች ሁሉ እንደሚበልጥ ማመን አለብህ ፡፡ ጥበብ ከየትኛውም ውድ ድንጋይ በላይ ዋጋ አላት ፡፡ ጥበብ ታላቅ ናት ነገር ግን የማትገኝ አይደለችም ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን ጥበብ ለምን እርሱም እንደሚሰጥህ ተናግሯል !
“ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው ? ………..በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም
አዘጋጃትም፥ ደግሞም መረመራት ። ሰውንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው ። “
- ኢዮብ 28 ፡12 ፤ 28፡27-28
ተጨማሪ ጥቅስ
ኤፌሶን 1:7–9 — “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን ። በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና ፡፡ “
ቆላስይስ 2:2–3 — “ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ ፤ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና ። “
ያዕቆብ 1:5 — “ ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።