Wisdom Books Job

Hold Fast

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 383 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኢዮብ ሁሉንም መከራ መቋቋም ይችል ነበር ምክንያቱም በህያዉ ተቤዢዉ/ነፃ አዉጪ ላይ ወደፊት ስለተመለከተ (ኢዮ 19፡ 2526) ፡፡ በመጨረሻ ላይ ይህ ተቤዢ/ነፃ አዉጪ እንድንቋቋመዉ ተስፋን የሰጠን እና ኃጢዓታችንንና ችግራችንን የወሰደዉ ኢየሱስ ነበር ፡፡ የኢዮብ ሰዎስቱ ወዳጆች ክፉ እንደ ነበር በተደጋጋሚ ነገሩት ፤ ኢዮብም ተስፋበተገባዉ ተቤዢ ላይ ፀና ፡፡ የዛሬዉ ምዕራፍ ኢዮብ የራሱን ፅድቅ ለመከላከል ወደ ጠቅላላ በመጓዝ ለበልዳዶስ የመጨረሻ ንግግር የኢዮብ ምላሽ በመስጠት የሚቀጥል ነው

ትምህርት

ኢዮብ (27፡ 1-6)፡ዋይርስቤ ኢዮብ “ ህያዉ እግዚአብሄርን “ በማለት ንግግር በጀመረ ጊዜ እንደ መሀላ እንደወሰደዉ ተመለከተዉ ፡፡ እስከዚህ ስፍራ ድረስ ኢዮብ ፅድቁን እየተናገረ ቢጠይቅም እንኳን እግዚአብሄር ኢዮብን አልመለሰለትም ነበር ፤ እግዚአብሄር ዝም ቢልም እንኳን ኢዮብ “ ከንፈሩ ኃጢዓትን እንዳትናገር “ እና እንዳይዋሽ የቆረጠ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ ኢዮብ ስለ መኃላዉ የተጠነቀቀ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ በዚያን ጊዜ በምስራቅ ህዝቦች መካከል መኃላ ማድረግ ከባድ ነገር እንደ ነበር ፤ ተናግራችሁት የነበረዉ እዉነት ካልሆነ እግዚአብሄር እንዲገድላችሁ መጋበዝ እንደ ነበር “ አመልክቷል ፡፡

ማክአርቱር “ እግዚአብሄር የኢዮብን ንፁህነት ለማወጅ እንዳልተናገረ “ ፅፏል፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ኢሳያስ የኢየሱስን አደራረግ እንዴት ገለፅጽ እንደነበረዉ፡ “ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ ስለ ሕዝቤ ኃጢዓት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትዉልዱ ማን አስተዋለ ? “ (ኢሳ 53፡ 8) ፡፡

በመኃላዉ ስር ኢዮብ የወዳጆቹን አመለካከት በፍፁም እንደማያረጋግጥ ማለ ፡፡ ኢዮብ ምንም ስህተት ነገር አድርጎ ስላልነበር የሚያስፈራዉ ምንም ነገር አልነበረም ፤ ኢዮብ “ ጽድቄን እይዛለሁ “ (ቁጥር 6) በማለት ወሰነ ፡፡ አዲሱ የአሜሪካ የመፅኀፍ ቅዱስን ስነ ስርዓት “ አጥብቆ መያዝን “ እንደ “ መፅናት “ ይተረጉመዋል፡

  1. በጌታ መፅናት ፡፡ በጌታ ከእምነት የመጀመሪያ ንስሀ ዉጪ የምንፀናበት መንም ነገር አይኖረንም ፡፡ የዕብራዊ ፀሀፊ አስጠነቀቀ፡ “ የተስፋን ቃል የሰጠዉ የታመነ ነዉና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ “ (ዕብ 10፡ 23) ፡፡ የእግዚአብሄር መታመን ማን እንደሆነ እንድንፀናበት ያነሳሳናል ፡፡

“ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው ፤ እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን “ (ዕብ 3፡ 6) ፤ በራስ መተማመናችን/ኩራታችን በቤታችን ላይ እንደ ባለቤት በሆነዉ ከኢየሱስ ሁኔታ ይመጣል ፡፡

“ ወንድሞች ሆይ ምናልባት ሕያዉ እግዚአብሄርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ ፤ ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢዓት መታለል እልከኛ እንዳይሆን ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ ፤ የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻዉ አጽንተን ብንጠብቅ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና “ (ዕብ 3፡ 12-14) ፡፡ ኢዮብ የእግዚአብሄርን ፅድቅ እየያዘ እንደ ነበርና ከዚያ ማንም እንደማያስቀረዉ ያውቃል ፡፡

“ እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለዉን ድፍረታችሁን አትጣሉ ፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋል “ (ዕብ 10፡ 35-36) ፡፡

እስከሞት ድረስ የታመነ መሆን ፡፡ አንዴ በመሰረታችን በክርስቶስ በሙሉ ስንተማመን በኑሮአችን ሁሉ የታመንን ሆነን ለመኖር ችሎታ አለን ፡፡

“ ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ ፡፡ እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው አስር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ ፡፡ እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ “ (ዕብ 2፡ 35-36) ፡፡

ጳዉሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንን “ ንቁ በኃይማኖት ቁሙ ጎልምሱ ጠንክሩ “ (1ቆሮ 16፡ 13) በማለት አስጠነቀቃቸው ፡፡

“ ይህም ተመስርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በኃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል ፡፡ ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለዉ ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው እኔም ጳዉሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ “ (ቆላ 1፡ 23) ፡፡

በጌታ አሸናፊ መሆን ፡፡ ኢዮብ እምነቱ በማን ላይ እንዳስቀመጠና ምንም ቢፈጠር በእግዚአብሄር ላይ የታመነ ለመሆን መወሰኑን ያውቃል፤ ሽልማቱ በዚህ ህይወትና በሚመጣዉ ዘላለም እንደ ነበር ተረድቷል፡፡

“ ድል ለነሳዉና እስከ መጨረሻም ስራዬን ለጠበቀዉ እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ስልጣንን እሰጠዋለሁ “ (ቁጥር 2፡ 26) ፡፡

“ እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሳሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ ድል ለነሳው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ “(ዕብ 3፡ 21) ፡፡

“ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ ሩጫዉን ጨርሼአለሁ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ “ (2ጢሞ 4፡ 7) ፡፡

“ እግዚአብሄር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ያደረጋችሁትን ስራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና ፡፡ በእምነትና በትዕግስትም የተስፋዉን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን “ (ዕብ 6፡ 10-12) ፡፡

ኢየሱስ የእምነታችን ፈፃሚና ባለቤት/ደራሲ ነው ፡፡ “ እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢዓት አስወግደን የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚዉን ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለዉን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ “ (ዕብ 12፡ 1) ፡፡

“ በእናንተ መልካምን ስራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና “ (ፊል 1፡ 6) ፤ ክርስቶስ በእናንተ የጀመረዉን ይፈፅመዋል ፤ መጽናት አለብን ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር መንገዳችን ቀላል እንደሚሆን ተስፋ አልገባልንም ፡፡ ፅድቁን, ተስፋዉንና እንደማይተወን ዘላለማዊ እዉቀትን አጥብቀን መያዝ አለብን ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004) p. 54.

  2. Wiersbe, p. 54.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 585.

  4. Michael Bradley, “Holding Fast to the Lord”; available at BibleKnowledge.com at https://www.bible-knowledge.com/holding-fast/.

ጥያቄዎች

  1. ኢዮብ (27፡ 4) እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? (ኢሳ 53፡ 7, 9, 1ጴጥ 2፡ 22)
  2. ኢዮ (27፡ 8) አንብቡ ፤ ይህ መልካም ዜናን ለምታዉቋቸዉ ወይም ለምታገኟቸዉ በተለይም እንደ “ ክፉ “ ወይም እንደ “ መልካም “ ለምትለዩአቸዉ እንድትነግሯቸዉ እንዴት ያበረታታችኋል ? መልሳችሁን ለመደገፍ ምን መፅሀፍትን ልትጠቀሙ ትችላላችሁ ?
  3. በኢዮ (27፡ 12) የኢዮብ አድማጭ ማን ነበር ? አይተዉት የነበረዉን ኢዮብ ምን እየጠየቀ ነበር ? እንዴት በሞኝነት እየተገበሩ ነበር ? አንዳንድ ጊዜ ከምታዉቁት ወይም ከምትናገሩት እዉነት በተቃራኒ እንዴት ታደርጋላችሁ ?
  4. በኢዮብ 27 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 27:5–6

“I will never affirm that you are right. I will maintain my integrity until I die. I will cling to my righteousness and never let it go. My conscience will not accuse me as long as I live!”

ኢዮብ በመከራ ውስጥ ቢቀጥልም ፣ ጓደኞቹ ብዙም ተስፋ የሚሆን ነገር አልነገሩትም ፡፡ ይሁን እንጅ ኢዮብ በታማኝነት እንድሁም ተስፋውን አጥብቆ በመያዝና በመጣበቅ ለእግዚአብሔር ያለውን ቁርጠኝነት አረጋገጠ ፡፡ ለጓደኞቹም “ ፈጽሞ ትክክል እንደሆናችሁ አልመሰክርም “ አላቸው ፡፡ ከዚያም ኢዮብ “ጽድቄን እይዛለሁ እርሱንም አልተውም “ በማለት ገለጸ ፡፡

መጣበቅ ማለት በቶሎ መያዝ ፣ መትጋት ፣ አለመተው እና እግዚአብሔር እንድትሰራው ባዘዘህ ስራ ላይ መጽናት ማለት ነው ፡፡ ለተረፉ ነገሮች እንድትጠቀመው የሚመከረውን የፕላስቲክ መሸፈኛ አስብ ፡፡ የዚህ ነገር ጥቅሙ ሁለት ነገሮች በሚፋተጉበት ጊዜ በአንድ ላይ ተጣብቀው እንድቀሩ ማድረግ ነው ፤ ብዙ ጊዜ የምግብ ሳህንን ይሸፍናል ፡፡ የፕላስቲክ መጠቅለያው ተግባር የሚያቆመው ከምግብ መያዣው ጎን ጋር መጣበቅ ሲያቆም ነው ፡፡ ፓስታ ሊያሟልጥ ወይም ሊንሸራተት ይችላል ፣ ስለዚህም ከጥቅም ውጭ ሊሆን ይችላል ፡፡ በተመሳሳይ በአንተ ላይ ያለው የእግዚአብሔር አሳብና እቅድ ይፈጸም ዘንድ ጌታን በቶሎ ልትይዝና በእርሱ ላይ ልትጣበቅ ይገባል ፡፡ በህይወትህ በአምነት በእርሱ ፍቅርና ጸጋ ላይ ስትጣበቅ ፣ አግዚአብሔር ብርታትን ይሰጥሀል ፡፡ በመንገድህ አባጣ ጎርባጣ ቢያጋጥምህ እንኳ ፣ ተስፋ እንዳትቆርጥ ፡፡ ይልቁንም በክርስቶስ ባለህ ተስፋ ላይ ተጣበቅ ፡፡ በእርሱ ላይ ስትጣበቅ ፣ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ለመፈጸም የታመነ ነው ፡፡

“እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስክሞት ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅም ። ጽድቄን እይዛለሁ እርሱንም አልተውም፤ ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱ ልቤ አይዘልፈኝም ። “

  • ኢዮብ 27፡5-6

ተጨማሪ ጥቅስ

ፊልጵስዩስ 1:6 — “በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና ፡፡ “

ዕብራውያን 10:23 — “የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ፡፡ “

ራእይ 2:10 — “ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና ። “