Wisdom Books Job

Relationship, Not Righteousness

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 25-26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 382 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እነዚህ ምዕራፎች በኢዮብ ላይ ሰዎስተኛ ዙር ንግግሮችን ያጠቃልላል ፤ በእያንዳንዱ ንግግር ዉስጥ እያንዳንዱ ሰዉ እይታዉን ገፍተዉ ነበር ማንም አንድ ኢንች አልተሰጠዉም ነበር ፡፡ በልዳዶስ ለመጨረሻ ጊዜ በምዕራፍ 25 ይናገራል ፤ የበልዳዶስ ስፍራ በሁሉም ንግግሮቹ የፀና/የሚመሳሰል ነው ፡፡ በመደጋገም ንስሀ በመግባት እንዲድን በኢዮብ ላይ ተናገረ ፤ በልዳዶስ ደጋግሞ ለሚለዉ ነገር ኢዮብ ንፁህ መሆኑን ያለማቋረጥ አቀረበ ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (25፡ 1-6)፡ የበልዳዶስ የመጨረሻ ምላሽ ለኢዮብ ስለ እግዚአብሄርና ስለ ኃጢዓት ልማዳዊ መረዳቱን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ ማክኔን “ ልማድ በህይወት ላይ ላለዉ ሁኔታ ፈጣን ለዉጥ መልስ እንደ ሌለዉ “ይናገራል ፡፡ በምዕራፍ 24 ኢዮብ ወዳጆቹን እዉነት ባልሆነዉ አለም ላይ ስላለፍ ፍትህ አልባነት ጥያቄዉን እንዲመልሱለት ሞገታቸው ፤ ለኢዮብ በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ የበልዳዶስ አስተያዬቶች አጭር መግለጫ፣ እግዚአብሄር ላይ ያተኮሩና የቀደመዉን መደምደሚያዎቹን ያጠቃለሉ ነበሩ ፡፡ በልዳዶስ ለኢዮብ ምልከታዎችና ጥያቄዎች እዉነተኛ መልስ አልነበረዉም ፡፡

የበልዳዶስ የመጨረሻ ምላሽ ለእግዚአብሄር ማመስገኛ መዝሙር ነው ፡፡ ስለ እግዚአብሄር አጉልቶ አሳይቷቸዉ የነበሩት ሁሉም አመለካከቶች እዉነት ነበሩ ነገር ግን እያንዳንዱ አመለካከት/ሀሳብ ያላለቀ ነበር ፤ በልዳዶስ የሚያመሰግነዉ እግዚአብሄር በአንድ ሳጥን ዉስጥ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ኃያል ነበር፣ እግዚአብሄር ፍፁም ነበር እንዲሁም ደግሞ እግዚአብሄር ንፁህ ነበር ፤ ነገር ግን በመስተጋብር ዉስጥ መገኘቱን ያቀረበዉን የኢዮብን አምላክ አይመስልም ፡፡

በልዳዶስ “ ከሴትስ የተወለደ ንጹህ ይሆን ዘንድ እንዴት ይቻለዋል “ (ቁጥር 4) ? በማለት ጠየቀ ፤ መልሱ በቀላሉ ንፁህ ሆነን መወለድ አንችልም ነበር ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ይህ ኢዮብ በሁሉም መንገድ ተመልሶ በምዕራፍ 14 የደረሰበት መደምደሚያ ነበር፡ “ ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል ? አንድ እንኳ የሚችል የለም ! “ (ኢዮ 14፡ 4) ፡፡ ኢያሳያስም በዚህ ጥያቄ ታገለ፡ “ ሁላችን እንደ ርኩስ ሰዉ ሆነናል ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነዉ ፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል “ (ኢሳ 64፡ 6) ፤ በተጨማሪም ኢሳያስ በሰዉና በእግዚአብሄር መካከል ያለዉን ልዩነት ያገናኘዉን አዳኝ አይቶታል፡ “ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ ፤ እግዚአብሄርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ “ (ኢሳ 53፡ 6) ፡፡

በልዳዶስ ሰዉ በእግዚአብሄር ፊት መቆም እንደማይችል በፅድቁ ምክንያት በእግዚአብሄር ፊት መቆም ከሚችለዉ ከኢዮብ ስፍራ በላይ ለነበረዉ እዉነት ቅርብ ነበር ፡፡ ኢዮብ በችግሩ መካከል ላይ እግዚአብሄርን እንደሚያገኘዉ ስለ እግዚአብሄር የተማረበት ተለዋዋጭ እምነት የነበረዉ ቢሆንም በልዳዶስ ሰዉን ለመያዝ በፍፁም ማግየት የማይችለዉ የማያሳልፈዉ የእግዚአብሄር የተወሰነ ስዕል የማይንቀሳቀስ ነበር ፡፡ ማክኔን “ ኢዮብ በራሱ ጽድቅ በመኩራቱ ችግር ቢሆንም ለመቀየር ክፍት እንደ ሆነ አሳዬ ፤ በልዳዶስና ኢዮብ በክርስቶስ መምጣት ላይ ህያዉ ከነበሩ ኢዮብ ጌታን እኔን ማረኝ እያለ ሲያለቅስ በልዳዶስ ከፈሪሳዊያን ወገን እንደሚወግን እንደምንጠብቅ “ ፅፏል፡፡

ምስጋናዉን ለመደምደም በልዳዶስ ሰዉን “ ከአንድ ትል “ እና “ ከአንድ የእበት ትል “ ጋር በማወዳደር በእግዚአብሄርና በሰዉ መካከል ንፅፅርን አስቀመጠ ፤ በችግር በማይናገርበት ጊዜ ወዳጆቹ በፊቱ ሲቀመጡ ለእርሱ የበልዳዶስ የመጨረሻ ቃሉ አንድ ትል ወይም የእበት ትል በማለት መጣራቱ ነበር ፡፡ ዳዊት ሰዉን ከእግዚአብሄር ጋር በማነፃጸር በተመሳሳይ መረዳት ታገለ፡ “ የጣቶችህን ስራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሰራሃቸዉን ታስበዉ ዘንድ ሰዉ ምንድር ነው ? ትጎበኘዉም ዘንድ የሰዉ ልጅ ምንድር ነው ? ከመለዓክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸዉ ፤ በክብርና በምስጋና ዘዉድ ከለልኸዉ “ (መዝ 8፡ 3-5) ፡፡ የዳዊት ጥያቄ ከበልዳዶስ ጋር ተመሳሳይ ነበር ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በተቃርኖ መደምደሚያ መጣ ፤ ዳዊት ሰዉን በእግዚአብሄር የክብር አምሳል የተፈጠረ እንደሆነ ሲያይ በልዳዶስ ሰዉ እንደ አንድ ትል እንደሆነ አመነ ፡፡

ኢዮብ (26፡ 1-4)፡ የኢዮብ ንግግር ለበልዳዶስ በመልሱ ተቀየረ ፤ ለእርሱ ቅር መሰኘትና ወደ እርሱ ከማድመጥ ይልቅ በእምነታቸዉ ለመጉራት በመምረጣቸው በወዳጆቹ ላይ በመፍራት ኢዮብ የተፌዘበት ሆነ ፡፡ በልዳዶስ በጥበቡ የታወቅ ወዳጁ ነበር በኢዮብ ላይ ግን ጥበቡ ወደቀ/አልሰራም ፡፡ ማክኔን ኢዮብ “ በእግዚአብሄር መንፈስ ከሚንፀባረቀዉ ይልቅ በክፉ መንፈስ በመነካት የተበከለ ሰዉ ራሱን የሚከላከልበት መንፈስ በመሆኑ ቅር መሰኘቱን” ተመለከተ ፡፡ ማክኔን የመጀመሪያዎቹን አራት ቁጥሮች ከተናገረ በኋላ ኢዮብ ወዳጆቹ ምላሽ እንዲሰጡ እድለ ለመስጠት ዝም እንዳለ ተንግሯል ፡፡ ሶፋር, በልዳዶስም ሆነ ኤልፉዝ ቀጥለዉ ለመናገር ምንም ነገር ስላልነበራቸዉ የኢዮብ ንግግር ቀጠለ ፡፡

ኢዮብ (26፡ 5-14)፡ ኢዮብ ሞት የሰዉ ልጅ ሁሉ የሚገጥመዉ እዉነት እንደ ነበር ነገር ግን የእግዚአብሄር ኃይል በሰማይና ምድር ላይ ከሞት ያለፈ ነገር እንደሆነ አመለከተ ፡፡ የሰዉ ልጅ በሞትም እንኳን ቢሆን ከእግዚአብሄር መደበቅ አይችልም ምክንያቱም እግዚአብሄር ስለሚዳኘን/ስለሚፈርድብን፡ “ ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው “ (ዕብ 9፡ 27) ፡፡

በዚህ ብርሃን/መገለጥ ኢዮብ እግዚአብሄርን በፍጥረት ላይ ስላለዉ ኃይል አመሰገነው ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄርን እንደ መለኮታዊ አርክቴክት ለመግለፅ የማያቋርጥ ቃላትን ተጠቀ ፤ እግዚአብሄር “ ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል “, “ ዉኆችን በደመናዎቹ ዉስጥ ያስራል “ (ቁጥር 8), “ የዙፋኑን ፊት ይከድናል “, “ በዉኆች ፊት ላይ ድንበር አደረገ “ (ቁጥር 10), “ የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ ከተግሳጹም የተነሳ ይደነግጣሉ “(ቁጥር 11), “ በኃይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል “ (ቁጥር 12) እንዲሁም “ በመንፈሱ ሰማያት ዉበትን አገኙ “ (ቁጥር 13) ፡፡ ስለ እግዚአብሄር ኃይል ማስረጃዎቹን ከገለፀ በኋላ ኢዮብ በእግዚአብሄር ፊት በትህትና በመደፋት ሰገደ፡ “ እነሆ ይህ የመንገዱ ዳርቻ ብቻ ነው ፤ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው ! የኃይሉንስ ነጎድጓድ ያስተዉል ዘንድ ማን ይችላል ? “ (ቁጥር 14)፡፡

መደምደሚያ

ኢዮብ በራሱ ፅድቅ መታገሉን ይቀጥላል ፤ እስካሁን ግን እንዴትና ለምን ሁሉም ነገር በእርሱ ላይ እንደሆኑበት አልተረዳም ፤ ነገር ግን በጥቂቱም በእግዚአብሄር ጋር በሚኖር ግንኙነት እንደ ነበር መረዳት ጀመረ ፡፡

  1. David L. McKenna, The Preacher’s Commentary: Job, v. 12 (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1986), n. pp.180-181; available https://books.google.com/books?id=c0kc4XPPjHkC&p-g=PT1&dq=the+preacher%27s+commentary+job&hl=en&sa=X&ved=0ahUKEwjj9K7E_MTfAhVGLKwKHRBdDrQQ6AEILTAB#v=onepage&q&f=false on 12/29/18.

  2. McKenna, n. pp.180-181.

  3. McKenna, n. pp.180-181.

  4. McKenna, n. pp.180-181.

  5. McKenna, n. pp.180-181.

ጥያቄዎች

  1. በልዳዶስ ሁለት ጥያቄዎችን ጠየቀ ፤ መጀመሪያው “ አንድ ሰዉ በእግዚአብሄር ፊት እንዴት ፃድቅ ሊሆን ይችላል ? “ ይህን ጥያቄ እንዴት ትመልሱታላችሁ (ሮሜ 3፡ 26, 10፡ 9-10፣ ፊል 3፡ 9, 1ዮሐ 2፡ 1) ? ሁለተኛው “ ከሴት የተወለደ እንዴት ንፁህ ሊሆን ይችላል ? “ እንዴት ትመልሱታላችሁ ? ይህ ተስፋ ወደ ተገባዉ ተቤዢ እንዴት ያመለክታል ?
  2. በልዳዶስ ሰዉን በምን ገመተዉ (ኢዮብ 25፡ 6) ? ይህ ከቀሪዉ መፅሀፍት ጋር ይገናኛል/ይጣጣማል ? ይህ የመሲሁ ጥላ/የመሲሁን ጥላ ያመለክታል ? (መዝ 22፡ 6)
  3. በምዕራፍ 26 ኢዮብ ለበልዳዶስ ምላሽ ሰጠ ፤ ምዕራፉ በአንድ ጥያቄ ደመደመ ፤ ይህን ጥያቄ በራሳችሁ ንግግር እንደ ገና ተናገሩ ፤ ይህ ለመመለስ ምን መፅሀፍት ትጠቀማላችሁ ?
  4. በኢዮብ (25-26) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 26:7–8

“He stretches the northern skies over empty space; He hangs the earth on nothing. He wraps up the waters in His clouds, yet the clouds do not burst beneath their weight.”

በልዳዶስ እንደገና ለኢዮብ ተናገረ ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮብን የሚበስብስ ትል የሆነ ሰው ብሎ ጠራው ፡፡ የበልዳዶስ ምክርና አስተያየት ኢዮብ ሊሰማው የሚፈልገው አይነት አልነበረም ፡፡ ኢዮብ ጠንከር አድርጎ ተከታታይ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለበልዳዶስ ምላሽ ሰጠ ፡፡ ኢዮብ ጠንከር ብሎ “ ከአንተ መስማት በቅቶኛል “ አለ ፡፡ እናም ከዚያ በራሱ ምሬትና ስቃይ ውስጥ ሆኖ ኢዮብ ትክክለኛ እንደሆነ በሚያውቀው ሰማይንና ምድርን እንድሁም ፍጥረታትን ሁሉ በፈጠረው በእግዚአብሔር ላይ አተኮረ ፡፡ “ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል……..በውኆችም ላይ አድማሱን ይዘረጋል ፡፡”

ዛሬ እግዚአብሔር ለቀንህ ያዘጋጀውን እቅድ ስትከተል ፣ ቀኑ በደስታና በሃሴት የተሞላ ወይም በጭንቀትና በግራ መጋባት የተሞላ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሰማይንና ምድርን ለሰራው አምላክ ምስጋናን አቅርብ ፡፡ እግዚአብሔርን ባህርን ስለሚከፍል ኃይሉ አመስግነው ፡፡ አመስግነው ሰማያትን ውበት ስለሚሰጥ እስትንፋሱ ፡፡ መስኮትህን ክፈት ፣ ወደ ውጭ ተራመድ ፣ ንጹህ አየር ተንፍስ ፣ የጸሀይ ብርሀን ፊትህ ላይ ያብራ ወይም ዝናብ ጸጉርህን ያርስ ፤እግዚአብሔርንም ስለ ድንቅና ኃያል ፍጥረቱ አመስግነው ፡፡ ሰማይንና ምድርን የሰራው አምላክ እርሱ ከአንተ ጋር ለመገናኘት ይናፍቃል ፡፡ የድንቅና የተአምራት አምላክ ይወድሀል ፡፡ በእርሱ ድንቅ ላይ ጸንተህ ቁም ፡፡

“ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል ። ውኆችን በደመናዎቹ ውስጥ ያስራል ፥ ደመናይቱም ከታች አልተቀደደችም ። “

  • ኢዮብ 26፡7-8

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 104:24–25 — “አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች ። ይህች ባሕር ታላቅና ሰፊ ናት፤ በዚያ ስፍራ ቍጥር የሌለው ተንቀሳቃሽ፥ ታላላቆችና ታናናሾች እንስሶች አሉ ። “

ዮሐንስ 1:3 — “ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም ። “

ሮሜ 1:20 — “ የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና ፡፡ “