Injustice Everyone
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በኢዮብ ህይወት በሁሉም መዘበራረቅ መካከል ላይ ተስፋ በተገባለት ተቤዢ ተስፋዉን አደረገ (ኢዮ 19፡ 25-26) ፡፡ የዛሬዉ ምዕራፍ የኢዮብ ምላሽ ለኤልፉዝ መቀጠል ነው፣ ነገር ግን በደንብ ሰፋ በማለት ለሆሉም ለሰዎስቱ ወዳጆቹ የሚመለከት ንግግር ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ከኢዮብ አስተሳሰብ/አንፃር በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ጥሩዉ የማጠቃለያዉ ይዘት “ እግዚአብሄር ግራ አጋባኝ “ የሚል ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (24፡ 1-11)፡ዋይርስቤ እነዚህ ጥቅሶችን ያልተቀጡ ሆነዉ ያለፉ ስለሚመስሉት ስለ እስራኤል ፍትህ አልባነት የኢዮብን ቅር መሰኘት እንደሚይዙ ይመለከታል ፤ በቅሬታዉ መጀመሪያ ላይ ኢዮብ ፍርድን የሚይዙ እና የህዝቡን ቅሬታ በመስማት ፍርድን የሚሰጡ የተወሰኑ ጊዜያት ለምን እግዚአብሄር እንደሌሉት ተደነቀ ፡፡
በቁጥር 2-8 ኢዮብ በገጠር አካባቢዎች ላይ የተፈፀሙ ሰዎስት አይነት ኃጢዓቶችን እግዚአብሄር ሳይቀጣ የተዋቸዉ የሚመስሉትን ይዘረዝራል፡
- የድንበር ምልክቶችን ያፈረሱ ክፉዎችን (ቁጥር 2) ፤ ይህ በቀድሞ እስራኤል መሬትን ከመስረቅ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በእስራኤል የዚህን ወንጀል ከባድነት ያመለክታል ፤ የድንበር ድንጋዮችን በማንቀሳቀስ ጥፋተኝነት የተገኘባቸው በመለኮታዊ እርግማን የተረገሙ እንደሆኑ ይቆጠራሉ፡
- “ አምላክህ እግዚአብሄር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር በምትወርሳት ርስትህ የቀደሙ ሰዎች የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል “ (ዘዳ 19፡ 14) ፡፡
- “ የባልንጀራዉን የድንበር ምልክት የሚገፋ ርጉም ይሁን “ (ዘዳ 27፡ 17) ፡፡
- “ አባቶችህ የሰሩትን የቀድሞዉን የድንበር ምልክት አታፍልስ “ (ምሳ 22፡ 28) ፡፡
ማክአርቱር የመሬት ምልክቶች “ ይዞታቸዉን ለመጨመር በተለይም ባሎቻቸዉ በሞቱቧቸዉ መበለቶች የተያዙትን ስፍራዎች “ ለመዉሰድ በተበላሹ የመሬት ባለቤቶች እንደሚቀሳቀሱ ያስታዉቃል ፡፡
ክፉዎች ደካሞችን አንገላቱ (ቁጥር 3-8) ፤ ክፉዎች በድሀ አደጎች የተያዙትን አህዮች ነዱ፣ የሌሎች የሆነዉነ እንስሳትም ወሰዱ ፤ ለራሳቸዉ ከሚገባቸዉ ሁኔታ ዉጪ ስለ ምግብ ፍለጋ በማስገደድ ያለ ልብስ ሰደዷቸው ፡፡ ማክአርቱር የአንድን ሰዉ የዉጨኛዉን ልብስ እንደ እዳ መያዣ መዉሰድ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ የተለመደ ተግባር እንደ ነበር አመልክቷል ፤ ይሁን እንጂ ህጉ “ ባለቤቱ ብርድና ህመም ሊያገኘዉ የሚችል ከሆነ በምሽት ላይ ልብሱን እንዲተዉ ያዛል “ ፡፡
“ ለባልንጀራህ ባበደርኸዉ ጊዜ መያዣዉን ልትወስድ ወደ ቤት አትግባ ፡፡ አንተ በዉጭ ቁም ያበደርኸዉም ሰው መያዣዉን ያውጣልህ ፡፡ ያም ሰዉ ድሃ ቢሆን መያዣዉን በአንተ ዘንድ አታሳድር ፡፡ ለብሶት እንዲተኛ እንዲባርክህም ፀሐይ ሳይገባ መያዣዉን ፈጽመህ መልስለት ፤ በአምላክህም በእግዚአብሄር ፊት ጽድቅ ይሆንልሃል “ (ዘዳ 24፡ 10-13) ፡፡
ከፉዎች በምድሪቱ ላይ ለምስቅልቅል ምክንያት ሆኑ (ቁጥር 9-11) ፡፡ ክፉዎች ልጆችን ለእዳ እንደ መያዣ ወሰዱ፣ ድሆች እራቁታቸዉን እንዲሄዱ ምክንያት ሆኑ በተጨማሪም የሰራተኞችን ደሞዝ አልከፈሉም ፡፡
ኢዮብ (24፡ 12-17)፡ ኢዮብ እግዚአብሄር ሳይቀጣ የተዋቸዉን ወንጀሎች በከተማዋ ዉስጥ መመልከቱን ቀጠለ ፡፡ ኢዮብ ለቅሬታዉ እንደ ኃጢዓት ግድያን፣ ስርቆትንና ምንዝርናን ዘረዘረ/ጠቀሰ ፡፡
ኢዮብ (24፡ 18-25)፡ዋይርስቤ በሀገሪቱ ከዚያም በከተሞቹ ስላልተጠቀሱ ኃጢዓቶች ከዘረዘረ በኋላ አሁን ኢዮብ በክፉዎች ላይ እርግማንን እንደ ተናገረ ተመለከተ ፡፡ በዚህ ክፍል የኢዮብ ቋንቋ ከወዳጆቹ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፤ በይበልጥ አመለካከታቸዉ ስህተት መሆነን ለማስረዳት ኢዮብ እንደ ወዳጆቹ ለመናገር ሞከረ ፡፡ በስቃዩ መካከል ላይ ኢዮብ የሌሎችን መከራ ማየት ችሎ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ ብዙ ጊዜ የግል ችግር ራስ ወዳድ እንደሚያደርገንና ለሌሎች ፍላጎት ያሳዉረናል ነገር ግን ኢዮብ እየጉዱት የነበሩትን እግዚአብሄር እንደሚረዳቸዉ እንደተመለከተ “ አመለከተ ፡፡ ኢዮብ ከግል እይታ አንፃር ሊያያቸዉ የተመለከተዉን የኢዮብ ወዳጆች የሌሎችን ችግር እንደ አጠረ ሀሳብ ተመለከቱት ፡፡ ኢዮብ የራሱ ችግር/ስቃይ ታላቅ ቢሆንም ራሱን የመፍትሄዉ አካል ለማድረግ ፈለገ ፡፡
መደምደሚያ
ሀምፕተን ኬኤችሌይ አራተኛ በመንገድ ዳር ላገኘዉ የተቸገረ ሰዉዬ ምላሽ ደጉ ሳምራዊዉ ያደረጋቸዉን ሰዎስት ድርጊቶች ያስታውቃል ፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ችግር ላይ ያሉትን ለመርዳት ስንመለከት ለእኛ አጋዦች ናቸው፡
ርህራሄ ነበረው ፡፡ እየተሰቃየ ወደ ነበረዉ ሰዉዬ ለመሄድ ሳምራዊ መነሳሳትን አደረገ ፡፡
አሰበለት/ተጠነቀቀለት ፡፡ ሳምራዊዉ ሊያነሳው ጊዜን ወሰደ ፡፡
ዋጋ አስከፈለው ፡፡ ሳምራዊዉ ሰዉዬዉን ለመንከባከብ የራሱን ገንዘብ ተጠቀመ ፤ ለሌላ ሰዉ ማሰቡን ለማሳየት ዋጋ ከፈለ ፡፡
እንደ ደጉ ሳምራዊ ካደረግን/ከሰራን የኢዮብ የቅሬታ ሀሳቦችን በማግኘት በሌሎች ሰዎች ችግር ላይ የመፍትሄዉ አካል መሆን እንችላለን ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 52.
Wiersbe, p. 52.
Wiersbe, p. 52.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 630.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 584.
MacArthur, p. 584.
Wiersbe, p. 52.
Wiersbe, p. 52.
Wiersbe, p. 52..
Hampton Keathley IV, “The Good Samaritan”; available at https://bible.org/seriespage/4-good-samaritan.
ጥያቄዎች
-
በምዕራፍ 24 ኢዮብ በቀድሞ እድሜ የነበሩት ክፉዎች ለምን እንዳልተቀጡ ጠየቀ ፤ ኢዮብ ያን ጥያቄ ቢጠይቃችሁ እንዴት ትመልሱለታላችሁ ?
-
ኢዮብ 24 በአሁኑ ጊዜ ያለዉን አለም ሊገልፅ ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይችልም ? በምን መንገድ ?
-
ኢዮብ ኃጢዓተኞች ስለ ህይወታቸዉ ምንም ማረጋገጫ እንደሌላቸዉ ተናገረ (ኢዮ 24፡ 22) ፤ ኢየሱስ ስለዚህ ማረጋገጫ ምን አለ ? (ሮሜ 5፡ 8, 10፡ 9-10)
-
በኢዮብ 24 በትምህርትና በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 24:21–23
“They prey on the childless woman who is unable to conceive, and do not deal kindly with the widow. Yet God drags away the mighty by His power; when He rises up, they have no assurance of life. He gives them a sense of security, so they can rely on it, but His eyes watch over their ways.”
ኢዮብ ለጓደኞቹ በመለሰ ጊዜ በዙሪያው ሆነው በመከራ ውስጥ ስላሉ ሌሎች ሰዎች ትኩረት አደረገ :- የሚፈጸመው በደል ፣ በከተማው ውስጥ ያለ ወንጀል በተጨማሪም በክፉዎች ላይ ስላለው እርግማን ፡፡ ኢዮብ በራሱ መከራ ላይ ብቻ ትኩረትን ከማድረግ ይልቅ በድሀ አደጎች ፣ በመበለቶች በተጨማሪም በሌሎች በተበደሉ እና እርዳታ የለሽ ሰዎች ምንያህል እርዳታ ፣ ተስፋ እና ፍቅር እንደሚፈልጉ አስተዋለ ፡፡
በራስህ መከራ ውስጥ ሆነህ ሳለ አይኖችህን ከራስህ ላይ አንሳና በዙሪያህ ያሉትን ሌሎችን ተመልከት ፡፡ ምናልባት ለህክምና በሆስፒታል ውስጥ ልትሆን ትችላለህ ወይም ለተፈጠረ አደጋ ለማመልከት በኢንሹራንስ መስሪያ ቤት ውስጥ ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን በዙሪያህ ያሉትን ለማየት ለአንድ ጊዜ አይንህን ክፈት ፡፡ እንደ ኢየሱስ ተከታይ የተጠራኸው እግዚአብሔርንና ሌሎችን እንድትወድ ነው ፤ ነገር ግን በህይወትህ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ሲሄዱ ብቻ አይደለም ፡፡ ማን ያውቃል ፤ ምናልባት በህመምና በማጣት ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር ለሌላ ሰው ተስፋ እንድታስገኝ ቢፈልግስ ፡፡ አይኖችህን ከራስህ ላይ ስታነሳና ለሌሎች ርህራሄና ፍቅርን ስታሳይ ፣ እግዚአብሔር ምን ሊሰራ እንደሚችል አታውቅም ፡፡ ድካም በሚሰማህ ጊዜ እንድሁም የምትሰጠው ምንም ነገር በእጅህ ላይ በሌለ ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ በቂ ነው ፣ እርሱም ደግሞ ብርታትን ይሰጥሀል ፡፡ በህመም ውስጥ እንኳ ሌሎችን መውደድ ፡፡ ምናልባት ይህ በመከራ ጊዜህ ውስጥ ለማለፍ የሚያስፈልግህ ነገር ሊሆን ይችላል ፡፡
“የማትወልደውን መካኒቱን ይበድላታል፤ ለመበለቲቱም በጎነት አያደርግም ። ነገር ግን በኃይሉ ኃያላንን ይስባል፤
እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም ። እግዚአብሔር በደኅና አኑሮአቸዋል፥ በዚያም ይታመናሉ፤ ዓይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው ። “
- ኢዮብ 24፡21-23
ተጨማሪ ጥቅስ
ኤፌሶን 5:2 — “ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ ። “
ፊልጵስዩስ 2:3–4 — “ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር ፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ ። “
1ኛ ዮሐንስ 4:19–21 — “ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን ። ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል ? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።