Wisdom Books Job

The Bottom Line

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 22-23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 380 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሁሉንም የማጣት፣ የህምና የችግር/የመከራ ሀሳቦችን አዉርተናል ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ሲገጥሙን በሁኔታዎቹ ዉስጥ ለማለፍ በዚያ ዉስጥ ምን አፅንቶ እንደሚያቆመን ለራሳችን መወሰን ያስፈልገናል ፤ በመንገዱም የትኛዉን እዉነት ማመን እንዳለብንም መወሰን ያስፈልገናል ፡፡ ኢዮብ ለእኛ የፍልስፍና ትምህርት ነገር ነው ፡፡ ፍልስፍና ከሁለት የግሪክ ቃል “ ፍቅር “ እና “ ጥበብ “ ከሚለዉ የመጣ ሲሆን “ ፍልስፍና “ ማለት “ የጥበብ ፍቅር “ ማለት ነው ፡፡

በዛሬዉ ምዕራፋችን ኤልፉዝ ለኢዮብ ሰዎስተኛ ምላሹን ሰጠ እንደ ገና ኢዮብምለኤልፉዝ መለሰለት ፡፡ ኤልፉዝ የታይታ ጀግንነት ነበረው ፤ እየተከናወነ ለነበረዉ ልብ ዉስጥ በመግባት አንዱ ለመሆን ፈለገ ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (22፡ 1-4)፡ ኤልፉዝ በተገቢዉ ሁኔታ “ ሁሉም ነገር ካለዉ ሰዉ ምን ታገኛለህን ? “ በማለት ጠየቀው ፡፡ በኤልፉዝ አይምሮ/ሀሳብ ዉስጥ እግዚአብሄር የማይተኛ፣ ሁሉን የሚያደርግ እና ሁሉን የሚችል ነበር ፤ ይህ ማለትም እርሱ ቀድሞ የሌለዉ ምንም ነገር የሰዉ ልጅ ሊሰጠዉ የሚችለዉ ነገር የለም ማለት ነዉ ፤ ይህ መንፈሳዊ ነገርን ሳይመለከት በአካላዊ ለሚጓዙ የሰብዓዊነትን ልብ የሚነካ/የሚያስለቅስ ነበር ፡፡ ኤልፉዝ በህይወቱ ፅድቁና ጥበቡ የተሸሉ መንገዶች እንደሆኑ ማሳመን ቢችልም ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ለእግዚአብሄር ምንም ነገር መጨመር አይችሉም ፡፡

ኢዮብ (22፡ 5-9)፡ ኤልፉዝ በኢዮብ ላይ ጠንካራ የሆነ ክስ አቀረበ ነገር ግን በተፈጥሮ አንድ የሆነ/ጠቅለል ያለ ይሰማቸዋል ፡፡ ኤልፉዝ ኢዮብ ኃጢዓት ያደረገባቸዉን አንዳንድ ሁኔታዎችን ለማሳየት ሞከረ ፡፡

ኢዮብ (22፡ 10-20)፡ ኤልፉዝ ኢዮብ እንደ ማንኛዉም ሌላ ሰዉ አይነት ስለነበር በአንዳንድ ጠቅላላ መንገዶች ኃጢዓት ሰርቶ እንደነበሩት “ ፈጣንም ስጋት “ በኢዮብ ላይ እንደመጣበት ተከራከረ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን የሚገጥሙን መልካም ነገሮች ከእግዚአብሄር ጠቅላላ ፀጋ ይመጣሉ/የሚመጡ ናቸው ፤ እነዚህ ነገሮች በተወሰዱ ጊዜ እግዚአብሄር እንዲወስዳቸዉ ምን ምክንያት እንዳደረግን በማሰብ ልንጨነቅ እንችላለን ፤ መጥፋታቸዉ “ ፈጣን ስጋት “ የሚመስል ያሰማሉ/እንዲሰማ ያደርጋሉ ፡፡

ኤልፉዝ ክፉዎች በጸሀይ ጊዜ ዘመን ሊኖራቸዉ እንደሚችል እዉቅና ሰጠ ነገር ግን እንደ ገና “ ጊዜያቸዉ ሳይደርስ ይነጠቃሉ “ (ቁጥር 16) በማለት እምነቱን አረጋገጠ ፡፡

ኢዮብ (22፡ 21-30)፡ ኤልፉዝ ኢዮብን “ ከእግዚአብሄር ጋር ተስማማ ሰላምም ይኑርህ “ (ቁጥር 21) በማለት አበረታታዉ ይህ ማለትም ኃጢዓቱን እና የእግዚአብሄር ፍትህ በእርሱ ላይ እየፈረደ እንደ ነበር እዉቅና እንዲሰጥ ነገረዉ ማለት ነው ፡፡ እንደ ኤልፉዝ ንግግር ኢዮብ በቀላሉ በዚህ መንገድ ራሱን ቢያዋርድ እግዚአብሄር እንደ ገና ያከብረዋል ፡፡

“ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ፤ ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ እግዚአብሄር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና “ (ዕብ 11፡ 6) ፤ እግዚአብሄርን ለማስደሰት የተናገራቸዉ ነገሮች እዉነት እንደሆኑና እርሱን በመታዘዝ ለሚሄዱት እንደሚሰጥ በነገሮች ማመን ያስፈልገናል ፡፡

“ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሄር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ ፤ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል ፤ በእግዚአብሄር ክብርም ተስፋ እንመካለን ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ነገር ግን መከራ ትዕግስትን እንዲያደርግ ትዕግስትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን ፤ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም “ (ሮሜ 5፡ 1-5) ፡፡ እግዚአብሄር በዝቅተኛ ስፍራ ላይም ሊገይ ይቸላል ፤ ዝቅ ባለ ስፍራ ላይ በሚገኝ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተስፋን እና ነገሮች እንዲመጡ ተግቶ መጠበቅን ሲሰጥ እርሱን መታመን እንማራለን ፡፡

ኢዮብ (23፡ 1-7)፡ ኢዮብ ተስፋን ተመለከተ ነገር ግን የት እንደሚመለስ አያዉቅም ፤ በእግዚአብሄር ፊት መቆም ፈለገ ነገር ግን ከዚህ በኋላ እግዚአብሄርን የት እንደሚያገኘዉ አያዉቅም ፤ ይህ እያለ ኢዮብ በእግዚአብሄር ፊት መቆም ከቻለ እግዚአብሄር ከወዳጆቹ በተለየ መልኩ እንደሚያየዉ አዉቋል ፡፡ እግዚአብሄር ኢዮብን ያጠነክረዋል ከኤልፉዝ፣ ከበልዳዶስና ከሶፋር በተለየ መልኩ ኢዮብ “ ከእግዚአብሄር ጋር መከራከር ይችላል “ (ቁጥር 7) ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄር ለሰብዓዊነት ሀሳቡን የሚያረጋግጥ አልነበረም ለሰብዓዊነት መልሱን መስጠት የሚፈልግ እንጂ፣ ይህም ስለሆነ ሰበዓዊነት በእርሱ ብርሃን መኖሩን መረዳት ይችላል ፡፡

ኢዮብ (23፡ 8-12)፡ ኢዮብ እምነቱን “ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ “ (ቁጥር 10) በማለት ተናገረ ፡፡ ኢዮብ መከራዉን/ችግሩን አልናቀም ፤ በመከራ ጊዜ እንዲያልፈበት ለእርሱ የሆነዉንም ፀረ- እግዚአብሄር እንደነበር አላመነም ፡፡ ኢዮብ በችግሩ ዉስጥ እግዚአብሄርን በደንብ የለመደዉ መረዳት ያለዉ መሰለ ፡፡

ኢዮብ (23፡ 13-17)፡ ኢዮብ እግዚአብሄርን አሁን በኢዮብ ሁኔታ ዉስጥ እየሰራበት የነበረዉን ማንኛዉንም ስራ ጨምሮ ሁል ጊዜ የፈለገዉን እንደሚያደርግ አመነ ፡፡ በዚህ ብርሃን ዉስጥ ኢዮብ “ በእርሱ መገኘት እንደደነገጠ “ በዚህም ምክንያት “ እንደ ፈራዉ “ ገለጸ (ቁጥር 15) ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄር ማን እንደ ነበር ያውቃል ነገር ግን ለእርሱ በእግዚአብሄር ኃይልና እቅድ በእይታዉ ስር እንደተሸጠ አረጋገጠ ፤ ኢዮብ እግዚአብሄር በኃይል ገደብ የለሽ እንደ ሆነ ያምናል ፤ ኢዮብ እግዚአብሄር ሁሉም ቦታ የሚገኝ እንደ ሆነ ያምናል ፤ ኢዮብ እግዚአብሄር ሁሉም ጥበብ እንዳለዉ አምኗል ፡፡ እነዚህን ሁሉንም ነገሮች በተመለከተ ጊዜ ለእግዚአብሄር ኃይላና ጥበብ ቅዱስ አምልኮ ወደ ሚደረግበት አስፈሪ/አስገራሚ ስፍራ መጣ ፡፡

መደምደሚያ

በህይወት ማንኛዉንም ቅጣት ወይም መከራ ለመቋቋም የሚያስችለንን እግዚአብሄር ማን እንደሆነ በሚገባ መረዳት ነው ፡፡ ልንረካበት/ልንደሰትበት የሚገባን አንዱ ስፍራ እግዚአብሄርን የምናዉቅበትና የሚያዉቀንን የምናውቅበት ነው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ኤልፉዝ እግዚአብሄርን ለመርዳት አንድ ሰዉ ይኖር ይሆን በማለት ጠየቀ (ኢዮ 22፡ 2) ፤ ምን ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር እርዳታችን ያስፈልገዋልን ?
  2. በሕይወታችሁ ለእናንተ “ ለእግዚአብሄር መገዛት “ ምን ይመስላል (ኢዮ 22፡ 21-22) ? ሌላ የት ላይ “ ለእግዚአብሄር እንድንታዘዝ “ ይነግረናል (ያዕ 4፡ 7-10) ? በእነዚህ ቁጥሮች መካከል ጥቂት ልዩነቶቻቸዉ ምንድን ናቸው ? ተመሳሳይነታቸው ?
  3. በኢዮ (23፡ 3) ኢዮብ “ እርሱን ወዴት እንዳገኘዉ ምነዉ ባወቅሁ “ አለ ፤ ኢዮብ እግዚአብሄር ጋር መድረስ እንዳልቻለ ተሰማው ፡፡ እግዚአብሄር ጋር መድረስ እንዳልቻላችሁ ተሰምቷችሁ ያዉቃል - ከእናንተ ሩቅ እንደ ነበር ? ወደ እግዚአብሄር እንዲስቧችሁ ያደረጋችኋቸዉ ጥቂት ነገሮች ምን ነበሩ ? መጽሀፍት ምን ይላል (ዘዳ 4፡ 29, ኤር 29፡ 13) ? ሊፈትነን ለአንድ ወቅት እግዚአብሄር የሚተዉን ጊዜያቶች አሉ ?
  4. በኢዮብ (22-23) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 23:9–10

“When He is at work to the north, I cannot see Him; when He turns south, I cannot find Him. Yet He knows the way I have taken; when He has tested me, I will emerge as pure gold.”

አሁንም እንደገና ኢዮብ ለእርሱ መከራ ምክንያት የሆነውን ነገር ከጠየቀው ከኤልፋዝ አደመጠ ፡፡ ኤልፋዝ ለኢዮብ መፍትሔን አቀረበ ፤ በዋነኝነትም :- “ ኢዮብ እንድህ እንድህ ካደረገ ብቻ ነው መከራው ሊያቆም የሚችለው ፡፡ “ በማለት ተናገረ ፡፡ ነገር ግን ኢዮብ ህይወት ልክ እንደ ቀመር እንደማይከውን ተረድቶ ነበር ፡፡ ኢዮብ የትም ቦታ በሰሜን ፣ በደቡብ ፣ በምስራቅ ወይም በምዕራብ እግዚአብሔርን ፈልጎ ማግኘት እንደማይችል አመነ ፤ ነገር ግን አሁንም ኢዮብ “ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል ፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ “ በማለት ኢዮብ እምነቱን ቀጠለ ፡፡ ኢዮብ ደንግጥኖ እግዚአብሔርን ፈርቶ እንደነበር ተናገረ ፤ ነገር ግን አሁንም ኢዮብ በተስፋው ላይ በመጣበቅ “ከጨለማው የተነሣ፥ ድቅድቁም ጨለማ ፊቴን ከመክደኑ የተነሣ አልደነገጥሁም “ አለ ፡፡

ምናልባት ዛሬ የኢዮብን በሚመስል ፈተና ውስጥ ልትሆን ትችላለህ ፡፡ በህይወትህም የትም ቦታ ላይ የእግዚአብሔርን እጅ ላታይ ትችላለህ ፣ አሁንም ግን እርሱ ከአንተ ጋር እንደሆነ ታውቃለህ ፡፡ ደንግጠህ ሊሆን ይችላል ፣ አሁንም ግን ታምናለህ አልጠፋህምም ፡፡ እምነት አለህ እናም ተስፋ ይህ በአስቸጋሪና በመከራ ቀናት ይሸከምሀል ፡፡ አስተውል በመከራ ውስጥ እግዚአብሔር በአንተ ውስጥ ትእግስትን ፣ መከራንና ተስፋን እንደሚያደርግ ፡፡ ዛሬ በጨለማው ውስጥ ስትራመድ እግዚአብሔር የምትሄድበትን መንገድ ያውቃል ፡፡ አልጠፋህም ፡፡ እንደ ንጹህ ወርቅ ሆነህ ትወጣለህ ፡፡ በእምነት ጽና በውስጥህም ወዳለው ተስፋ ተጣበቅ ፡፡

“ ወደሚሠራበት ወደ ግራ ብሄድ አልመለከተውም፤ በቀኜም ይሰወራል፥ አላየውምም፤ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ ። “

  • ኢዮብ 23፡9-10

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 48:10 — “እነሆ፥ አንጥሬሃለሁ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፤ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ ። “

ሮሜ 5:3–5 — “ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን ፤ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም ። “

ዕብራውያን 11:6 — “ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና ። “